በለዓም ~ Balaam: ም፣ አምልኮት ያለው፣ የሕዝብ ጌታ... ማለት ነው። የነቢይነት ስጦታ ያለው፥ የቢዖር ልጅ፥ ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለዓም እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ አለ እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፥ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል...” (ዘኊ 22:5)

በላሳን ~ Bilshan: ን፣ በተናጋሪ፣ አንደበተ ቱዕ... ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ በላሳን ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።” (ዕዝ 2:2)

በልቤ ሁሉ ~ Muth-labben: ሙተ ልብነ፣ የወዳጅ ሞት፣ ልባዊ ዘን... ማለት ነው።

Muth-labben - ‘ሞትእና ልብከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ነው። በዳዊት መዝሙር የተገለጸ ቃል፥ አቤቱ፥ ልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ...” (መዝ 9:1)

በልዳዶስ ~ Bildad: በደል፣ የጥል፣ የጭቅጭቅ፣ የጠብ ልጅማለት ነው። ዮብ ሦስት ወዳጆች ሁለተኛው፥ ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆችቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። (ኢዮ 2:11)

በሶድያ ~ Besodeiah: የሕያው ወዳጅለአምላክ የቀረበ ማለት ነው። የኢየሩሳሌምን ቅጥር ከጠገኑ፥ የሜሱላም አባት፥ የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና በሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን በር አደሱ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ (ነህ 3:6)

በሪዓ ~ Beriah: በረያሕ፣ የሕያው ልጅ፣ ወላጅ አልባ... ማለት ነው።

1. ከአሴር አራት ልጆች አንዱ፥ የሔብር አባታ፥ (ዘፍ 46:17) የአሴርም ልጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሪዓ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር፥ መልኪኤል።

2. የኤፍሬም ልጅ፥ (1 ዜና 7:20-23) ወደ ሚስቱም ገባ፥ አረገዘችም፥ ወንድ ልጅም ወለደች በቤቱም መከራ ሆኖአልና ስሙ በሪዓ ብሎ ጠራው።

3. ከኤሎን ሰዎች ጋር የጌትን ሰዎች ያሳደዱ፥ ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ (1 ዜና 8:13) “በሪዓ ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ

በራኪያ ~ Berachah: ቡሩክ፣ ቡሩክ አምላክ፣ አምላክ የባረከው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በራክዩ፣ በራክያ፣ ባርክኤል፣ ባሮክ]

“...የዓዝሞት ልጆች በራኪያ ዓናቶታዊው ኢዩ፥ (1 ዜና 12:3)

በራክዩ ~ Barachias, Berechiah: ቡሩክ ዋስ፣ ቡሩክ አምላክ፣ አምላክ የባረከው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በራኪያ፣ በራክያ፣ ባርክኤል፣ ባሮክ]

Barachias -‘በረከእና ዋስከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። Berechiah -‘በረከ እና ያሕ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       በራክዩ / Barachias: የዘካርያስ አባት፥ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ  ...” (ማቴ 2335)

        በራክዩ / Berechiah: የነቢዩ የዘካርያስ አባት፥ (ዘካ 1:1 7)

በራክያ ~ Berechiah, Berachiah: ቡሩክ ያሕ፣ ቡሩክ ሕያው፣ ቡሩክ አምላክ፣ አምላክ የባረከው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በራኪያ፣ በራክዩ፣ ባርክኤል፣ ባሮክ]

በረከ እና ያሕ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       በራክያ / Berechiah:

1. የዘሩባቤል ልጅ፥ በራክያ (1 ዜና 3:20)

2. ከሌዋውያን የሜራሪ ልጅ፥ በራክያ (1 ዜና 9:16)

3. ከዳዊት መዘምራን የአሳፍ አባት፥ በራክያ (1 ዜና 15:17)

4. የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ከተቀደሱ፥ በራክያ (1 ዜና 15:23)

5. ከኤፍሬም ልጆች አለቆች፥ በራክያ (2 ዜና 2812)

6. ኢየሩሳሌምን በማደስ ከተባበሩት የሜሱላም አባት፥ በራክያ (ነህ

3:4 30 6:18)

       በራክያ / Berachiah: ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ከነበሩ በየተራቸውም ያገለግሉ ከነበሩ አገልጋዮቹና ልጆቹ፥ (1 ዜና 6:39)

በር ~ Bar: በር፣ መግቢያ፣ ደጆች፣ መወርወሪያ፣ መዝጊያ፣ የቤት መቆለፊያ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

 የበር ይነቶች

. የቤት መቆለፊያ፥ የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። (ነህ 33)

. የባሕር በር፥ ሐኖንና የዛኖዋ ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ ደግሞም እስከ ጕድፍ መጣያው በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ። (ነህ 3:13)

. ድንበር፥ በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ (ኢሳ 45:2) የደማስቆንም መወርወሪያ እሰብራለሁ...” (አሞ 1:5)

. ምሽግ፥ በሬማት ዘገለዓድ የጌበር ልጅ ነበረ፥ ... መወረወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት (1 ነገ 4:13)

. በር የሚሰራው:

. ከብረት፥ “... ብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ (ኢሳ 45:2)

. ከነሀስ፥ “... የናሱ ደጆች ሰብሮአልና፥ የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጦአልና።” (ኢሳ 45:2)

. ከእንጨት (ነህ 3:13) (መዝ 107:16)

በርስያን ~ Barsabas: በርሳባ፣ ቤተ ሳባ፣ ሳባዊ፣ የሳባ ልጅ፣ የሰው ልጅ... ማለት ነው።

Barsabas- በር እና ሳባ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዮሴፍ ሌላ ስም፥ በይሁዳ ፈንታ ለመሾም ከማትያስ ጋር እጣ የተጣጣለ፥ ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍን ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።” (ሥራ 123)

2. የሐዋርያው ይሁዳ ሌላ ስም፥ “...እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳ ሲላስ ነበሩ። (ሥራ 15:22)

በርባን ~ Barabbas: በረ አባ፣ በረ አባስ፣ የአባስ ልጅ... ማለት ነው። ፍልስጥኤም ቅኝ ይገዛ የነበር፥ የሮማን መንግሥት በማሸበር የተከሰሰ፥ ሁሉም ደግመው። በርባን እንጂ ይህን አይደለም እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ” (ዮሐ 18:40)

በርተሎሜዎስ ~ Bartholomew: በርተ ለሚዎስ፣ በትረ ለሙዋሴ፣ ብትረ ሙሴ፣ የሙሴ ዱላ፣ ተአምር አድራጊ... ማለት ነው። [የተሎሜዎስ ልጅ ማለት ነው / መቅቃ]

ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ከሰጣቸው፥ በርተሎሜዎስ (ማቴ 10:3)

በርኒቄ ~ Bernice: ድል አቀዳጅ፣ የአሸናፊ ልጅማለት ነው። የሄሮድስ ትልቋ ሴት ልጅ፥ ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄ ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ። (ሥራ 25:13)

በርናባስ ~ Barnabasየመጽናናት ልጅ ማለት ነው። ሌዋዊው ዮሴፍ፥ ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው” (ሐዋ 4: 36)

በርያሱስ ~ Bar-jesus: በረ ያሱ፣ ልጅ እያሱ፣ ወልደ ኢየሱስ፣ ያዳኝ ልጅ፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው።

በር የሽ እና ዋስ’(ኢያሱ ኢየሱስ) ከሚሉ ስሞች የተመሠረተ ቃል ነው አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ የተቃወማቸው፥ በርያሱስ (ሥራ 136)

በቅዱስ ማደሪያው ~ Heaven: የሕያው ቦታ፣ የሕያው መኖሪያ፣ የዘላለማውያን ማረፊያ፣ የእግዚአብሐር መኖሪያ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች - ሰማይ፣መቅደሱ ከፍታ]

Heaven- የሚለው ስም የመጣው ሕያዋን ከሚለው ቃል ነው።

. ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ (መዝ 18:16) ሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፥ ...ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል (ኢሳ 24:18) ስለዚህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ። እግዚአብሔር በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያው ሆኖ ድምፁን ያሰማል... ይጮኻል። (ኤር 25:30)

. ሰማይ፥ እግዚአብሔር መቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና” (መዝ 102:19)

. ከመሬት በላይ ያለውን ሁሉ፥ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” (ዘፍ 11)

.ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል... በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል።” (ሕዝ 17:23)

.ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።” (ኢዮ 35:5 33:26)

. “... እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ።” (2 ቆሮ 12:2)

በቱል~Bethuel, Bethul: ቤቱል፣ ቤተ ኤል፣ የአምላክ ቤት፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤት]

Bethuel- ‘ቤተእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው የወጣ፣ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መከከል የነበረ የቦታ ስም፥ (ኢያ 194 5)

በናያስ ~ Benaiah: በነ ያሕ፣ ያምላክ ልጅ፣ የሕያው ልጅ፣ የእግአብሔር ቤተሰብ... ማለት ነው።

Benaiah- ቤን እና ያሕ (ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉ ስሞች የተመሠረተ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ፥ በናያስ (1 ዜና 275)

2. የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ከተቀደሱ፥ (1 ዜና 15:18 20)

3. በእግዚአብሔር ታቦ ፊት መለከት ይነፉ ከነበሩ፥ ከካህናቱ አንዱ፥ በናያስ (1 ዜና 15:24 16:6)

4. የይዒኤል ልጅ፥ በናያስ (2 ዜና 20:14)

5. በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ ሌዋዊ፥ (2 ዜና 31:13)

6. ከሲምዖን ወገን የሆነ፥ በናያስ (1 ዜና 4:36)

7. በዕዝራ ዘመን ከግዞት የተመለሱ፣ እንግዶች ሴቶችን ያገቡ፣ አራት ሰዎች አንዱ፥ (ዕዝ 10:25 30 35 43)

8. የፈላጥያ ልጅ፥ በናያስ (ሕዝ 11:1 13)

9. የዳዊት ልጆች አማካሪዎች የነበረ፥ የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ...” (መሣ 8:18) (መሣ 20:23)

በኖ ~ Beno: ቤኖ ቤን፣ ልጅ... ማለት ነው።

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደ ሰጣቸው ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚገቡ፥ የያዝያ ልጅ፥ “...የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ ከያዝያ ልጅ በኖ (1 ዜና 24:26 27)

በዓለ ኀምሳ ~ Pentecost: አምሳኛ ቀን ማለት ነው። በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ... (ሐዋ 2:1 20:16 1 ቆሮ 16:8)

በኣሊም ~ Baalim: ባላም፣ ባለ ጌታ፣ ባለአምላክ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣሊስ፣ በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል]

. የጣዖት ስም፥ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ” (መሣ 2:11)

. የእስራኤልም ልጆች በኣሊምንና አስታሮትን አራቁ፥ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ፥(1 ሳሙ 7:4)

በኣሊስ ~ Baalis: በለስ፣ ገድ፣ እድል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - በኣሊም፣ በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] በለስከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

የአሞን ልጆች ንጉሥ፥ በኣሊስ (ኤር 4014)

በኣላ ~ Baalah: ባለ፣ ባል፣ ጌታ፣ ባለቤት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - በኣሊም፣ በኣሊስ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታዎች:-

1. በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች፥ (ኢያ 15:29)

2. የይሁዳ ድንበር፥ በምዕራብ በኩል፥ (ኢያ 15:10)

3. የይሁዳ ድንበር፥ ወደ ሰሜን ወገን ያለ ተራራ፥ (ኢያ 15:11)

በኣል ~ Baal: ባል፣ ባለ፣ ጌታ፣ ባለቤት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቢኤል፣ በኣሊም፣ በኣሊስ፣ በኣላ፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርሚያስ ለእስራኤላውያን እንዲያሳስብ ካዘዘው ቃላት ውስጥ የተጠቀሰ የጣዖት ስም፥ እኔም ያላዘዝሁትን ... በኣል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በኣል የኮረብታውን መስገጃዎች …” (ኤር 19:5)

2. በትውልዶቻቸው አለቆች ከነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት የይዒኤል ልጅ፥ (1 ዜና 8:3031 9:36)

. የእስራኤል በኵር የሮቤል የልጅ ልጅ፥ (1 ዜና 55)

በዓል ~ Feast: ፌስታ፣ ደስታ፣ ድግስ፣ ግብዣ፣ በዓል... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ማዕድ፣ ሰርግ፣ ግብዣ]

. ምሶን ለወላጆቹ ክብር ያዘጋጀው ድግስ፥ አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ ጎበዞችም እንዲህ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ በዓል አደረገ። (መሣ 14:10)

. አብርሃም ላሴን ተቀብሎ ማዕድ አቀረበላቸው፥ (ዘፍ 193)

. የያቆብ አማት ልጁን ለመዳር ያደረገው ሰርግም፥ (ዘፍ 29:22)

. አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ያደረገው ድግስ፥ ሕፃኑም አደገ፥ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣ አደረገ። (ዘፍ 21:8) (ሉቃ 15:23)

በኣልሐና ~ Baal-hanan: በዓለ ሐና፣ የሐና በዓል፣ የሐና ጌታ፣ የክብር ጌታ፣ ክብረ በዓል... ማለት ነው።

ባል እና ሐና ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር ከነገሡ ነገሥታት አንዱ፥ የዓክቦር ልጅ፥ በኣልሐና (ዘፍ 363839)

2. የእስራኤል ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉት ሹማምት፥ በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ሹም የነበረ፥ (1 ዜና 27:28)

በኣልሜዎን ~ Baal-meon: የሜዎን ጌታ ማለት ነው። የሮቤል ከተማ፥ (ዘኊ 32:38) ቂርያታይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ሠሩ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው።

በኣል ሻሊሻ ~Baal-shalisha: በዓለ ሽላሼ፣ በዓለ ሥላሴ፣ የሥላሴ በዓል፣ ሦስትነት... ማለት ነው።

በዓል እና ሥላሴ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

ለኤልሳ ምግብና መጠጥ ያመጣ ሰው፥ የቦታ ስም፥ አንድ ሰውም በኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ...” (2 ነገ 442)

በኣል ብሪት ~ Baal-berith: ባለ በረት፣ ባለ በራት፣ ባለቃል ኪዳን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤልብሪት]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. እስራኤልን አርባ ዓመት ያስተዳደረ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በመተው በኣሊምን በመከተል ያመልኩት የነበረ የጣዖት ስም፥ “...በኣሊምንም ተከትለው አመነዘሩ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ።” (መሣ 833)

. በመጽሐፈ መሳፍንት በኣልብሪትን ኤልብሪት ይለዋል፥ በሴኬምም ግንብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ኤልብሪት ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ።” (መሣ 9:46)

በኣልታማር ~ Baal-tamar: ባለ ተምር፣ የተምር ባለቤት፣ ተምር ያለው፥ ምረኛ፣ ምር የሚፈጥር... ማለት ነው።

በዓል እና ታምር ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የእስራኤል ልጆች ከወንድሞቻቸው ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት የወጡበት የቦታ ስም፥ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከስፍራቸው ተነሥተው በኣልታማር ተሰለፉ ...” (መሣ 20:33)

በኣልአርሞን ~ Baal-hermon: የሄርሞን በዓል... ማለት ነው።

1. በኤፍሬማውያን የተያዘ፥ በአርሞን ተራራ አጠገብ የሚገኝ ከተማ፥ (1 ዜና 5:23) የምናሴ የነገድ እኵሌታ ልጆች በምድሪቱ ተቀመጡ። ከባሳንም ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔምና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በዙ።

2. የሌበናን ምሥራቃዊ ተራራ፥ (መሣ 3:3) አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ፥ ሲዶናውያንም፥ በኣልአርሞንዔም ተራራ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዊያውያን።

በኣልዛፎን ~ Baal-zephon: ሰሜና ባል፣ የሰሜን አምላክማለት ነው። ሰሜናዊ የግብፅ ከተማ፥ ተመልሰው በሚግዶልና በባሕር መካከል፥ በኣልዛፎን ፊት ለፊት ባለው በፊሀሒሮት ፊት እንዲሰፍሩ ለእስራኤል ልጆች …” (ዘጸ 14:2)

በዓልያ ~ Bealiah: ባለያ፣ ባለ ያሕ፣ ሕያው በዓል፣ ሕያው ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣሊም፣ በኣሊስ፣ በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል]

በዓለ እና ያሕ (ያሕዌ ህያዊ) ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ በዓልያ (1 ዜና 12:5)

በኣልጋድ ~ Baal-gad: ባለ ገድ፣ አምላክ የረዳው፣ እድል የቀናው፣ ባለ እድል፣ እድለኛ... ማለት ነው።

Baal-gad- በኣለእና ገድከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የቦታ ስም ነው። እግዚአብሔር ኢያሱን፥ በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ እነዚህን ከእስራኤል ልጆች ፊት አባርራቸዋለሁ እንዳዘዝሁህም ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ አካፍላቸው ብሎ ያዘዘው የቦታ ስም፥ (ኢያ 135 11:17 12:7-8)

በዓሎት ~ Bealoth: ማለት ነው። በይሁዳ በደቡብ በኩል፥ በምድሩ ዳርቻ የሚገኝ ከተማ፥ ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥” (ኢያ 15:24)

በዓሤያ ~ Baaseiah: የአምላክ ሥራማለት ነው። በሰሎሞን መገናኛ ድንኳን፥ እያዜሙ ያገለግሉ ከነበሩ፥ የአሳፍ ቅድመ አያት፥ (1 ዜና 6:40) የሳምዓ ልጅ፥ የሚካኤል ልጅ፥ በዓሤያ ልጅ፥

በዓና ~ Baanah: የጣር ልጅ፣ የመከራ ልጅማለት ነው።

1. የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ፥ ከሁለቱ የጭፍሮች አለቆች አንዱ፥ (2 ሳሙ

4:2) ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት የአንዱም ስም በዓና የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ ብኤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር።

2. ከንጉሥ ዳዊት ሠላሳ ክብር ዘበኞ የአንዱ የሔሌብ አባት፥ (2 ሳሙ 23:29 1 ዜና 11:30)

በዕራ ~ Baara: በራ፣ ነደደ፣ ብርሃን ሆነ፣ መብራት... ማለት ነው። በጌባ ከሚቀመጡ ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራ ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ። (1 ዜና 8:8)

በኩር ~ First-born: ብኵር፣ የመጀመሪያ ልጅ፣ በኵሬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኵሬ፣ ቢክሪ፣ ቢክሪ፣ ቤኬር፣ ብኵር፣ ብኮራት፣ ቦክሩ] በከረከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

[ከሰው ወይም ከከብት መጀመሪያ የሚወለድ / መቅቃ]

. የኃይሉ መጀመሪያ፥ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው (ዘዳ 2117)

. ሳው ፋንታ ያዕቆብ በኩር ተብሎ ተጠራ፥ “...ታላቁም ለታናሹ ይገዛል። (ዘፍ 25:23) ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። ... ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት (ዘፍ 25:31-34) “... በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ...” (ዕብ 12:16)

. የያቆብ ልጅ ሮቤል፥ ሮቤል፥ አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ...” (ዘፍ 49:3) የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች ...” (1 ዜና 5:1)

. ንጉሥ ዳዊት ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተናገረው ትንቢት በኩር ብሎ ጠርቶታል፥እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፥ ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።” (መዝ 89:27)

. እስራኤል የእግዚአብሔር የበኩር ልጅ ተብሎ ተጠራ፥ እስራኤል በኵር ልጄ ነው ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ እነሆ እኔ በኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ” (ዘጸ 4:23)

በጉዋይ ~ Bigvai: በጉያ፥ በሰውነት... ውስጥ ማለት ነው።

1. ከምርኮ ከተመለሱት፥ የበጉዋይ ልጆች ይገኙበታል፥(ዕዝ 2:14 ነህ7:19) የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት።

2. የቃል ኪዳን ውል ከተፈራረሙት፥ (ዕዝ 2:2 ነህ 7:7) ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ በጉዋይ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።

ቡል ~ Bul: ብል፣ አሮጌ፣ ያረጀ፣ ያፈጀ... ማለት ነው። ስምንተኛው የአይሁድ ወር፥ በአሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዓቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባትም ዓመት ውስጥ ሠራው።” (1 ነገ 6:38)

ቡቂ ~ Bukki: ማጥፋት፣ ማበላሸትማለት ነው።

1. የኦዚ አባት፥ (1 ዜና 6:5 6:551) አቢሱም ቡቂ ወለደ ቡቂም ኦዚን ወለደ

2. የከነዓናንን በነገድ እንዲያከፋፍሉ ከተመረጡ፥ ከዳን ልጆች ገድ፥ (ዘኊ 34:22) ከዳን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የዮግሊ ልጅ ቡቂ

ቡቅያ ~ Bukkiah: እግዚአብሔር የተወው፣ አምላክ የጣለውማለት ነው። የኤማን ልጅ፥ ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥” (1 ዜና 25:413)

ቡባስቱ ~ Pi-beseth: አፈ ሐሰት፣ ውሸታምማለት ነው። የጣዖት ስም፥ (ሕዝ 30:17) የሄልዮቱ ከተማና ቡባስቱ ጕልማሶች በሰይፍ ይወድቃሉ ሴቶችም ይማረካሉ

ቡናህ ~ Bunah: መረዳት ማለት ነው። የይረሕምኤል ልጅ፥ በኵሩ ራም፥ ቡናህ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ (1 ዜና 2:25)

ቡዝ ~ Buz, Buzi: የተነቀፈማለት ነው።

1. የሚልካ እና የናሆር ሁለተኛ ልጅ፥ (ዘፍ 22:21) “እነርሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወንድሙ ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፥

2. በነገደ ጋድ የትውልድ ሐረግ የተጠቀሰ፥ (1 ዜና 5:14)

      ቡዝ / Buzi: የሕዝቅኤል አባት፥ (ሕዝ 1:3) “ከወሩም በአምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፥

ቢልዓም ~ Bileam: ም፣ እንግዶች፣ ጤዎች፣ የሰው አገር ሰዎችማለት ነው። የምናሴ ነገድ፥ የምዕራብ አጋማሽ የሚሆን ከተማ፥ ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ቢልዓምንና መሰምርያዋን ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።” (1 ዜና 6:70)

ቢልጋ ~ Bilgah: በለጋ፣ በሕፃንነትማለት ነው።

1. በዳዊት ዘመን፥ የሃምኛው ተራ ሐላፊ፥ የቤተ መቅደሱ አገልጋይ ካህናት፥ አሥራ አምስተኛው ቢልጋ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር” (1 ዜና 24:14)

2. ከኢያሱና ከዘረባቢሎን ጋር ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የካህናት ወገኖች፥ መዓድያ፥ ቢልጋ ሸማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ” (ነህ 12:518)

ቢሽላም ~ Bishlam: በሸላም፣ በሰላም፣ በደና፣ በአማን... ማለት ነው። ሰላም ከሚለው ቃል፥ በሰላም የሚለው የቦታ ስም ተገኘ።

በአርጤክስስ መንግሥት፥ በመንግሥቱም በመጀመሪያ ዘመን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ላይ የክስ ነገር ከጻፉ መንግሥታት፥ ቢሽላም (ዕዝ 47- 24)

ቢታንያ ~ Bethany, Bithynia: ቤታኒያ፣ ሐና፣ የምሕረት ቤት፣ የይቅርታ ቤት፣ ባለጸጋ፣ የሐና አገር ሰው... ማለት ነው።

ቤት እና ሐና ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[የበለስ ቤት ማለት / መቅቃ]

በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ቦታዎች አሉ።

        ቢታንያ / Bethany: የለምጻሙ የስምዖን አገር፥ የማርያምና የእኅትዋ የማርታ መንደር፥ (ማር 111)

       ቢታንያ / Bithynia: በጴጥሮስ መልእክት የተጠቀሰ፥ (1ጴጥ 11) ሐዋርያው ጳውሎስ ባደረገው ጉዞ የጠቀሰው፥ (ሥራ 16:7)

ቢትሮን ~ Bithron: ክፍፍል፣ መለያየትማለት ነው። በዮርዳኖስ ሸለቆ፥ በወንዙ በስተምሥራቅ ያለ ቦታ፥ አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ዓረባ እያለፉ ሄዱ ቢትሮንንም ሁሉ ካለፉ በኋላ ወደ መሃናይም መጡ።” (2 ሳሙ 2:29)

ቢትያ ~Bithiah: ቢት ያሕ፣ ቤተ ሕያው፣ የአምላክ ቤት፣ የጌታ ቤተሰብ፣ የእግዚአብሔር ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤት፣ ቤትኤጼል፣ ቤትጹር]

ቤት እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የፈርዖን ልጅ፥ ቢትያ (1 ዜና 418)

ቢንዓ ~ Binea: የምንጭ ፏፏቴ ማለት ነው። የሳኦል ወገን፥ ሞጻም ቢንዓ ወለደ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል (1 ዜና 8:37 7:43)

ቢንዊ ~ Binnui: ልጅት፣ቤተዘመድ ማለት ነው።

1. የሌዋዊው የኖዓድያ አባት፥ ... የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና ቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።” (ዕዝ 8:33)

2. እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ ከፈሐት ሞዓብ ልጆችም፤ ዓድና፥ ክላል፥ በናያስ፥ መዕሤያ፥ ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊ፥ ምናሴ። (ዕዝ 10:30)

3. ሌላ እስራኤላዊ፥ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ መትናይ፥ የዕሡ፥ ባኒ፥ ቢንዊ ሰሜኢ፥” (ዕዝ 10:38)

4.ከግዞት ከተመለሱ የቢንዊ ልጆች ይገኙበታል፥ ቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት።” (ነህ 7:15)

5. ኢየሩሳሌምን በመጠገን ከተባበሩ፥ የኤንሐደድ ልጅ፥ ከእርሱም በኋላ የኤንሐደድ ልጅ ቢንዊ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ” (ነህ 3:2410:9)

ቢንዞሔት ~ Benzoheth: የመለየት ልጅማለት ነው። የይሁዳ ወገን የሆነ፥ የይሽዒ ልጅ፥ ሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ። (1 ዜና 4:20)

ቢኤል ~ Baal: ባል፣ ጌታ፣ ባለቤት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣላ፣ በኣሊም፣ በኣሊስ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።

. የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጅ፥ (1 ዜና 55)

. የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት፣ የይዒኤል ልጅ፥ (1 ዜና 8:3031 9:36)

ቢዖር ~ Beor: ሪ፣ የሚበራ፣ የሚነድ፣ የተቀጣጠለ ችቦ... ማለት ነው።

1. ከቀደሙት የኤዶም ነገሥታት የአንዱ፥ የቤላ አባት፥ በኤዶምም ቢዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት። (ዘፍ 36:32 1 ዜና 1:43

2. (ዘኊ 22:5 24:315 31:8 23:4፤ኢያ13:22 24:9 ሚካ 6:5)

ቢክሪ ~ Bichri: በኩሬ፣ በኩር፣ ፊተኛ፣ ቀዳሚ፣ የመጀመሪያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኩር፣ በኵሬ፣ ቤኬር፣ ብኵር፣ ብኮራት፣ ቦክሩ] በንጉሥ ዳዊት ያመጸ የሳቤዔ አባት፥ (2 ሳሙ 201)

ቢዝዮትያ ~ Bizjothjah: እግዚአብሔር የጠላውማለት ነው። ይሁዳ ደቡብ ግዛት ያለ ከተማ፥ ቤትጳሌጥ ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ” (ኢያ 15:28)

ቢድቃር ~ Bidkar: ‘ውርደት፣ ሽንፈት፣ ጸጸትማለት ነው። የኢዩ አለቃ፥ ኢዩም አለቃውን ቢድቃር እንዲህ አለው፦ አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ጣለው፥ አንተና እኔ ጎን ለጎን በፈረስ ተቀምጠን አባቱን ...” (2 ነገ 9:25)

ባላ ~ Bela: በላ፣ መብላት፣ መጉረስ፣ መዋጥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቤላ፣ ባላቅ፣ ቤላውያን]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዝተው ሲኖሩ፥ በአሥራ ሦስተኛውም ዓመት ዐመፁ፥ (ዘፍ 1428)

2. የብንያም ልጅ፥ (ዘፍ 46:21)

3. የዖዛዝ ልጅ፥ (1 ዜና 5:8)

ባላ ~ Bera, Bilhah: ድንጉጥ፣ አፋራምማለት ነው። የሰዶም ንጉሥ፥ ከሰዶም ንጉሥ ባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፥ ከሰቦይም ንጉሥ ከሰሜበር፥ ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ። (ዘፍ 14:2)

      ባላ / Bilhah:  የራሔል ሠራተኛ፥ የያቆብ የልጅ እናት፥ ላባም ለልጁ ለራሔል ባርያይቱን ባላ ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። (ዘፍ 29:29)

ባላቅ ~ Bela: ... (ክቡር ድንጋይ / አኪወ / )[ተዛማጅ ስሞች- ባላ፣ ቤላ፣ ቤላውያን]

የቢዖር ልጅ፥ በኤዶምም የቢዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት” (ዘፍ 36:32 33 1 ዜና 1:43)

ባላቅ ~ Balak: ቅ፣ ያለቀ፣ ባዶ የሆነ... ማለት ነው። የሴፎር ልጅ፥ የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ (ዘኊ 22:24)

ባሌ ~ Baali: ባሌ፣ ጌታዬ፣ ባለቤት፣ ገዥ፣ የትዳር ጓደኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] ስለ እስራኤል በተነገረ ትንቢት፥ በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ በኣሌ ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል እግዚአብሔር (ሆሴ 216-18)

ባል ~ Beulah: ባል፣ የትዳር ጓደኛ፣ ገዥ፣ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባዕላት፣ ቤላ፣ ቤል] [የሚስት ራስ / መቅቃ]

ስለእስራኤል የተነገረ፥ ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።” (ኢሳ 624)

ባልዳን ~ Baladan: ባለ ዳን፣ ባለ ዳኛ፣ ባለ ፍርድ፣ ጋዊ... ማለት ነው።

ባለእና ዳኛከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። የባቢሎን ንጉሥ የመሮዳክ አባት፥ (2 ነገ 20:12)

ባማ ~ Bamah: ታላቅ፣ የተከበረ ሥፍራማለት ነው። ራኤላውያን በጣዖት አምልኮ የሳቱበት ቦታ፥እኔም፦ እናንተ ወደ እርሱ የምትሄዱበት ከፍታ ምንድር ነው? አልኋቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠርቶአል” (ሕዝ 20:29)

ባሞት ~ Bamoth: ባመት፣ በመት፣ በማት፣ በብዛት ማለት ነው።

ከሚለው ቃል የተገኘ የቦታ ስም ነው።

የእስራኤልም ልጆች ከሰፈሩባቸው ቦታዎች፥ (ዘኁ 2119 20)

ባሞትበኣል ~ Bamoth-baal: በመ ባል፣ ዓመት በዓል፣ በዓል፣ ታላቅ በዓል፣ ከፍተኛ በዓል... ማለት ነው።

እና በዓል ከሚሉ ቃላት የተገኘ የቦታ ስም ነው።

ሙሴ ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስት ይሆናቸው ዘንድ የሰጣቸው ድንበር፥ ባሞትበኣል (ኢያ 137)

ባሳን ~ Bashan: በዛን፣ ፍሬያማ ሆንንማለት ነው። በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ፥ የጋድም ልጆች ባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ ...” (1 ዜና 5:11)

ባስልኤል ~ Bezaleel: ቤዛ` ኤል፣ ቤዛለኤል፣ በአምላክ ጥላ በጌታ ከለላ ... ማለት ነው።

ንዋዬ ቅዱሳትን ለሙሴ እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔር የመረጠው፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል (ዘጸ 31:2 35:30)

ባስማት ~ Bashemath: ` መት፣ በሺህ ሞት፣ የብዙዎች ሞት፣ እልቂት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ቤሴሞት]

ሺህእና ሞትከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የሰሎሞን ልጅ፥ የአኪማአስ ሚስት፥ ባስማት (1 ነገ 4:15)

2. የእስማኤል ልጅ የነባዮትን እኅት ቤሴሞት (ዘፍ 36፡፣3413)

ባሶራ ~ Bozrah: በዙር፣ በዜሮ፣ የታጠረ፣ የተከለለ፣ ምሽግ... ማለት ነው።

1. ኢዮባብ የነገሠበት፥ ጥንታዊ የኤዶማውያን ከተማ፥ (ዘፍ 36:33) “ባላቅም ሞተ፥ በስፍራውም ባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ

2. (ኤር 48:24) በቤትምዖን ላይ፥ በቂርዮት፥ በባሶራ፥ በሞዓብም ምድር ከተሞች ሁሉ ቅርብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥቶአል።

ባሬድ ~ Bered: በረድ፣ በረዶ፣ ብርድ፣ ቀዝቃዛ አገር... ማለት ነው።

1. በደቡብ ፍልስጥኤም ያለ ቦታ፥ የኤፍሬም ልጆች ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሽቱላ (ዘፍ 16:14)

2. የኤፍሬም ልጅ፥ የኤፍሬም ልጆች ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሽቱላ፥ (1 ዜና 7:20)

ባርቅ ~ Barak: ብራቅ፣ መብረቅ፣ ነጸብራቅ፣ ቅጽበታዊ ብርሃን፣ ብልጭታ... ማለት ነው።

Barak- በረቀ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። [መብረቅ ማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

        ባርቅ / Barak: ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ ያዘዘችው፥ (መሣ 4 6)

       ባርቅ / Bedan: እግዚአብሔርም ይሩበአልም፥ ባርቅንም፥ ዮፍታሔንም፥ ሳሙኤልንም ላከ...” (1 ሳሙ 211)

ባርክኤል ~ Barachel: በረከ ኤል፣ የጌታ ቡሩክ፣ አምላክ የባረከው፣ ለጌታ የሚታዘዝ፣ ትሑት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በራኪያ፣ በራክዩ፣ በራክያ፣ ባሮክ]

በረከእና ኤልከሚሉ ቃላት የተገኘ ነው።

ኢዮብ መከራ በደረሰበት ወቅት፣ ሊያጽናኑት ከመጡ፣ ቡዛዊው የኤሊሁ አባት፥ (ኢያ 3226)

ባርክኤል ~ Barachel: በረከ ኤል፣ ለአም መንበርከክ፣ ለጌታ መስገድ... ማለት ነው። ከኢዮብ ወዳጆች አንዱ፥ ቡዛዊው፥ የኤሊሁ አባት፥ (ኢዮ 32:26) “ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው ባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቍጣ ነደደ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።

ባርያሕ ~ Bariah: በረ ያሕ፣ የሕያው ልጅ፣ ወላጅ አልባ፥ ቅን አገልጋይ፣ የጌታ ወገን፣ የእግዚአብሔር እንግዳ... ማለት ነው።

በረ እና ያሕ’ (ያሕዌ ህያዊ) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የንጉሥ ዳዊት የልጅ፣ የሸማያ ልጅ፥ (1 ዜና 322)

ባሮክ ~ Baruch: ባሩክ፣ ቡሩክ፣ የተባረከ፣ ታዛዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በራኪያ፣ በራክዩ፣ ባርክኤል]

በረከከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። [ቡሩክ ማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዘባይ ልጅ፥ ባሮክ (ነህ 3:20)

2. የኔርያ ልጅ፥ ባሮክ (ኤር 32:12 36:4) (ኤር 32:12)

3. የቃልኪዳኑን ደብዳቤ ከፈረሙት ካህናት፥ ባሮክ (ነህ 10:6)

4. የኮልሖዜ ልጅ፥ ባሮክ (ነህ 11:5)

ባቢሎን ~ Babel, Babylon: መደባለቅ፣ መዘባረቅ፣ መደናገርማለት ነው። ከናምሮድ ዘመን ጀምሮ የተመሠረተ መንግሥት፥ የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።(ዘፍ 10:6-10)

    ባቢሎን / Babylon: የአምላክ ደጅ ማለት ነው። በዮሐንስ ወንጌል የተጠቀሰች ከተማ፥ ሌላም ሁለተኛ መልአክ። አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው። (ራእይ 14:8 17:18)

ባቱኤል ~ Bethuel, Pethuel: ቤቱ ኤል፣ ቤተ ኤል፣ የአምላክ ወገን፣ የጌታ ዘመድ፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤት]

ቤት እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

        ባቱኤል / Bethuel: የይስሐቅ ሚስት፣ የርብቃ አባት፣ ሚልካ ለናኮር የወለደችለት፥ (ዘፍ 222223)

        ባቱኤል / Pethuel: የነቢዩ ኢዩኤል አባት፥ (ኢዩ 1:1)

ባኒ ~ Bunni: ግንቤ፣ ሕንማለት ነው።

1. በነህምያ ዘመን የነበረ ሌዋዊ፥ ሌዋውያኑም ኢያሱና ባኒ ቀድምኤል፥ ሰበንያ፥ ቡኒ፥ ሰራብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ በደረጃዎች ላይ ቆመው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ ጮኹ።” (ነህ 9:4)

2. ቡኒ የተባለ ሌዋዊ፥ ከሌዋውያንም ቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሻማያ” (ነህ 11:15)

ባዕላት ~ Baalath: ባላት፣ በዓላት፣ ጌቶች፣ አማልክት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣሊም፣ በኣሊስ፣ በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባላ፣ ባሌ፣ ባል፣ ቤላ፣ ቤል]

በዓል ከሚለው ቃል የመጣ የቦታ ስም ነው።

ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው የርስታቸው ዳርቻ፥ ባዕላት (ኢያ 1944)

ባዕላትብኤር ~ Baalath-beer: የበዓላት በር፣ የቃል ኪዳን በዓላት... ማለት ነው፥ የስምዖን ልጆች ስት፥ እስከ ባዕላትብኤር እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።” (ኢያ 19:8)

ባኦስ ~ Baasha: ጀግና፣ ደፋር፣ ልበሙሉማለት ነው። የእስራኤል መንግሥት ከተከፈለ በኋላ፥ በሦስተኛ ተራ የነገሠ፥ በአሳና በእስራኤል ንጉሥ ባኦስ መካከል በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ። (1 ነገ 15 16 2 ዜና 16:1-6)

ባይት ~ Bajith: ቤይት፣ ቤት፣ ማደሪያ፣ መኖሪያ፣ ጎጆ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ቤቴል ቤት፣ ቤትኤጼል፣ ቤትጹር]

ቤተከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

ስለ ሞዓብ በተነገረ ሸክም የተጠቀሰ፥ ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም...” (ኢሳ 152)

ባዳድ ~ Bedad: አድ፣ በዓዳ፣ ገለልተኛ፣ ብቸኛ ማለት ነው። የኤዶም ንጉሥ የሃዳድ አባት፥ ሑሳምም ሞተ፥ በስፍራውም የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የመታ ባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ” (ዘፍ 36:35 1 ዜና 1:46)

ቤላ ~ Bela, Belah: በላ፣ አጠፋ፣ አወደመ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ባላ፣ ቤላ፣ ባላቅ፣ ቤላውያን]

በላከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ቤላ / Bela:

1. በሎጥ ዘመን የነበረ፥ የሰዶም ንጉሥ፥ “...ዞዓር ከተባለች ቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ” (ዘፍ 1428)

2. የብንያም ልጅ፥ ቤላ (ዘኁ 26:38)

3. የዖዛዝ ልጅ፥ (1 ዜና 5:8)

4. የቢዖር ልጅ፥ (ዘፍ 36:32 33 1 ዜና 1:43)

        ቤላ / Belah: የብንያም ልጅ ቤላ (ዘፍ 46:21)

ቤላውያን ~ Belaites: በላያት፣ በላተኛ፣ አጥፊዎች፥ ቤላያውያን፣ ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ባላ፣ ቤላ፣ ባላቅ]

በላ ከሚለው ቃል የመጣ የነገድ ስም ነው። ከብንያም ወገን የቤላ ልጅ፥ (ዘኁ 2638)

ቤል ~ Bel: ባለ፣ ባል፣ ጌታ፣ ገዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኣላ፣ በኣል፣ በዓል፣ በዓልያ፣ ቢኤል፣ ባሌ፣ ባል፣ ባዕላት፣ ቤላ]

[የባቢሎን ጣዖት ስም / መቅቃ]

የባቢሎናውያን ጣዖት ስም፥ ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ ...” (ኢሳ 461)

ቤልሆር ~ Belial: ምንቴ፣ ብኩን፣ ከንቱ፣ የማይጠቅምማለት ነው። የጣዖት ስም፥ ክርስቶስስ ቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?” (2 ቆሮ6:15)

ቤሳይ ~Besai: ቤሳ፣ ሰይፍ... ማለት ነው። ከባቢሎን ወደ ይሁዳ ከተመለሱ፥ ቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ ... (ዕዝ 2:50 ነህ 7:52)

ቤሳይ ~ Bezai: ገዥማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ሦስት (ዕዝ 2:17 ነህ 7:23 10:18)

ቤሴሞት ~ Bashemath: በሺህ ት፣ በሺህ ሞት፣ የብዙዎች ሞት፣ እልቂት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ባስማት]

ሺህ እና ሞት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. የኬጢያዊ የኤሎን ልጅ፣ የዔሳው ሚስት፥ (ዘፍ 26:34) (ዘፍ 36፡፣3413)

. የሰሎሞን ልጅ፥ ባስማት- (1 ነገ 4:15)

ቤሪ ~ Beera, Berites: በርዬ፣ በር፣ ደጅ፣ መግቢያ... ማለት ነው። (ውል፣ ስምምነት፣ ቃል ኪዳን ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

በርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።

       ቤሪ / Beera: ከአሴር፣ የጾፋ ልጅ፥ (1 ዜና 737)

       ቤሪ / Berites: የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ ኢዮአብን ሲሸሽ ያለፈበት የቦታ ስም፥ (2 ሳሙ 20:14)

ቤሪ ~ Beri: በሬ፣ መግቢያዬ... ማለት ነው። ከአሴር ነገድ፥ የጾፋ ልጅ፥ ሦጋል፥ ቤሪ ይምራ፥ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ፥ ይትራን፥ ብኤራ ነበሩ(1 ዜና 7:36)

ቤርሳቤህ ~ Bath-sheba, Bathsuha, Beersheba: ቤት ሸባ፣ ቤት ሳባ፣ ቤተሰብ፣ የሳባ ልጅ፣ የሰው ልጅ ማለት ነው። (ውል፣ ስምምነት፣ ቃል ኪዳን ተብሎም ይተረጎማል።)

Bath-sheba- ቤት እና ሳባ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። Beersheba - በርእና ሳባከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች እና አንድ ቦታ አሉ።

       ቤርሳቤህ / Bath-sheba: የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት፣ ዳዊት ከወሰዳትና ኦርዮን ካስገደለ በኋላ ሰሎሞንን ወለደች፥ ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ አንድ ሰውም ይህች የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን፣ አለ” (2 ሳሙ 113)

       ቤርሳቤህ / Bathshua: የዓሚኤል ልጅ፥ (1 ዜና 35)

       ቤርሳቤህ / Beersheba: አቢሜሌክና አብርሃም ቃል ኪዳን ያደረጉበት ቦታ፥ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና። ቤርሳቤህ ቃል ኪዳን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።” (ዘፍ 21:31-32) (ኢያ 1528)

ቤርዜሊ ~ Barzillai: ብሮንዝ፣ የብረት ይነት፥ ነው።

1. ዳዊት፥ ከወንድሙ ከአቤሰሎም ሸሽቶ በሄደ ጊዜ ተቀብሎ ያስተናገደው፥ ገለዓዳዊ ባለጸጋ፥ ዳዊትም ወደ መሃናይም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች አገር በረባት የነበረ የናዖስ ልጅ ኡኤስቢ፥ የሎዶባርም ሰው የዓሚኤል ልጅ ማኪር፥ የሮግሊምም ሰው ገለዓዳዊ ቤርዜሊ” (2 ሳሙ 17:27)

2. የሳኦል ልጅ የሜሮብ የባሏ አባት፥ ... ቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን የሳኦልን ልጅ የሜሮብን አምስቱን ልጆች ወሰደ፥” (2 ሳሙ21:8) 3. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ይገኙበታል፥ ከካህናቱም ልጆች የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች” (ዕዝ 2:61 ነህ 7:6364)

ቤርያ ~ Berea: በርያ፣ ቤት፣ ልጅ፣ ቤተሰብ... ማለት ነው። (ውል፣ ስምምነት፣ ቃል ኪዳን ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

ጳውሎስንና ሲላስ፥ በአቴንስ ተቃውሞ ሲበረታባቸው የሸሹበት ከተማ፥ (ሥራ 17 1013)

ቤሮታ ~ Berothah: በራት፣ በሮች፣ ቤቶች፣ መግቢያዎች... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርገው ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የሚከፍሉበት ድንበርን ለነቢዩ ሕዝቅኤል እንዳሳየው፥ ሐማት፥ ቤሮታ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር...” (ሕዝ 4715 16)

ቤሮታይ ~ Berothai: ቤሮታይ፣ በራት፣ በሮች፣ ቤቶች፣ መግቢያዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት] ንጉሥ ዳዊት ካሸነፋቸው የአሕዛብ ከተሞች፥ ንጉሡም ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከቤጣሕና ቤሮታይ እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ (2 ሳሙ 8:8)

ቤባይ ~ Bebai: ባብዬ፣ አባብዬ፣ አባታዊ... ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት (ነህ 6:28)

ቤተ ለባኦት ~ Bethlebaoth: ቤተ ልባት፣ የልባም ቤት፣ ልበ ሙሉ፣ የደፋር ወገን፣ የጀግኖች አገር... ማለት ነው።

ቤት እና ልብ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

ለስምዖን ልጆች ነገድ ርስት፥ ሐጸርሱሳ፥ ቤተ ለባኦት ሻሩሔን አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 196)

ቤተልሔም ~ Bethlehem: ቤተ ላህም፣ የላሕም ቤት፣ የላም ቤት፣ የከብቶች ማደሪያ ማለት ነው።

ቤተ እና ላም ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[የእንጀራ ቤት ማለት ነው / መቅቃ] በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታ እና ሰው።

. ያቆብ ከመስጴጦምያ በመጣ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ሲቀር በመንገድ ያለ ቦታ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት፥ ቀበርኋት...” (ዘፍ 487) “...አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም ቤተ ልሔም ይጠራ። (ሩት 4:11)

. ጌታ ኢየሱስ አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ ...” (ሚካ 5:2) (1 ሳሙ 17:12) ቤተልሔም ይሁዳ፥ (ሉቃ 2:4) የዛብሎን ልጆች ርስት፥ ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም አሥራ ሁለት …” (ኢያ 19:15)

. የካሌብ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፥ ቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ ...” (1ዜና 2:51)

ቤተ ሳይዳ ~ Bethesda: ቤተ ጻዳ፣ የጽዳት ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ መዋኛ፣ መጠመቂያ፣ መፈወሻ፣ የምሕረት ቤትማለት ነው። በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ የነበረች መጠመቂያ ስም፥ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ ...” (ዮሐ 5:2)

ቤተ ሳይዳ ~ Bethsaida: ቤትማለት ነው። የሐዋርያቱ፥ የእንድርያስ፣ የጴጥሮስና የፊሊጶስ አገር፥ እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው። ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...” (ዮሐ 12:21)

ቤተራባ ~ Bethabara : ቤተ በረ፣ ቤተ በር፣ ድንበር፣ ወሰን... ማለት ነው። Bethabara- ቤት እና በር ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

አይሁድ ዮሐንስን፥ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ?’ ብለው የጠየቁበት ቦታ፥ (ዮሐ 128)

ቤተ ፋጌ ~ Bethphage: ቤተ ፋጌ፣ የፋጌ ቤት፣ የሾላ ቤት፣ የበለስ ቤት... ማለት ነው።

ቤት እና ፋጌ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[የበለስ ቤት ማለት ነው / መቅቃ]

ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ባደረገው ጉዞ ካለፈባቸው ከተሞች፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ...” (ማቴ 21:1)

ቤተ ፌጎር ~ Beth-peor: የተከፈተ ቤት ጉድጓድ፣ ዋሻማለት ነው። በኢያሪኮ አንጻር፥ በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሆነ፥ የሞዓብያን ቦታ፥ ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትየሺሞት” (ኢያ 13:20 ዘዳ 3:29 4:46)

ቤቱኤል ~ Bethuel: ቤቱል፣ ቤቱ ኤል፣ የአምላክ ቤት፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት]

ቤተ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

. በይሁዳ በስተደቡብ የነበረ ከተማ፥ በቶላድ፥ ቤቱኤል በሔርማ፥ በጺቅላግ፥” (1 ዜና 4:30)

. በቱል- (ኢያ 194)

. ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር የወለደችለት ልጅ፥ ባቱኤል- (ዘፍ 22:23)

ቤቴል ~ Beth-el, Bethuel: ቤተ ኤል፣ ቤቴል፣ የአምላክ ቤት፣ የጸሎት ቤት ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤት፣ ቤትኤጼል፣ ቤትጹር]

ቤት እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። [የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታዎች:-

       ቤቴል / Beth-el:

1. አብርሃም ወደ አዜብ ባደረገው ጉዞ ያለፈበት የቦታ ስም፥ ከዚያም ቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴል ...” (ዘፍ 12:8)

2. ሎዛ ይባል የነበረ፥ በያቆብ ቤቴል ተብሎ የተሰየመ የቦታ ስም፥ ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።” (ዘፍ 2819)

        ቤቴል / Bethuel: ቤቴል ለነበሩ፥ በራሞት በደቡብ ለነበሩ” (1 ሳሙ30:27)

ቤት ~ Beth: ቤት፣ ማደሪያ፣ መኖሪያ፣ መጠለያ፥ ወገን፣ ልጅ፣ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤትኤጼል፣ ቤትጹር]

. መኖሪያ ንጻ፣ ጎጆ፥ እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። (ዘፍ 12 1)

. ወገን፣ ዘመድ፥ እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ ...” (ዘፍ 71)

ቤት ሳሚስ ~ En-shemesh: የፀሓይ ፏፏቴማለት ነው። በይሁዳና በብንያም ጉልህ ድንበር ላይ የሚገኝ ምንጭ፥ ... ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ (ኢያ 15:7 18:17)

ቤት ዲብላታይም ~ Beth-diblathaim: የደረቅ በለስ ቤትማለት ነው። የሞዓብውያን ከተማ፥ በዲቦን፥ በናባው፥ ቤት ዲብላታይም ላይ፥” (ኤር 48:22)

ቤትሀራም ~ Beth-aram: ታላቅ ቤት፣ ከፍታኛ ቤት... ማለት ነው። በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ ...” (ኢያ 13:27)

ቤትሐካሪም ~ Beth-haccerem: የቃርሚ ቤት፣ የወይን ማሳ ቤትማለት ነው። በይሁዳ ግዛት የሚገኝ ቦታ፥ ቤትሐካሪም ግዛት አለቃ የሬካብ ልጅ መልክያ የጕድፍ መጣያውን በር አደሰ ሠራው፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ...” (ነህ 3:14)

ቤትሖሮን ~ Beth-horon: መቃብር ቤትማለት ነው። በኤፍሬም ግዛት የነበሩ የሁለት ከተሞች ስም፥ ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ መወርወሪያም .... ላይኛውን ቤትሖሮን ታችኛውንም ቤትሖሮን ሠራ። (2 ዜና 8:5 1 ዜና 7:24)

ቤትዓረባ ~ Betharabah: ቤተ ረባ፣ ረብ ወገን፣ ረባዊ ማለት ነው።

ቤት እና ረብ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ቦታዎች አሉ።

1. የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት፥ በምድረ በዳ ቤትዓረባ ሚዲን፥ ስካካ፥” (ኢያ 15:61)

2. የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች፥ ቤትዓረባ ዘማራይም፥ ቤቴል፥” (ኢያ 18:22)

ቤትመዓካ ~ Bethmaachah: ቤተ መቅ፣ መቃብር ቤት፣ መቀመቅ፣ የሥቃይ ሥፍራ ማለት ነው።

ቤት እና መቅ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ኢዮአብ ያለፈበት አገር፥ (2 ሳሙ 2014)

ቤትሳሚስ ~ Beth-shemesh: ቤተ ሲመሽ፣ የፀሓይ ቤት የፀሓይ መግቢያ፣ መጥለቂያማለት ነው።

1. በዳን ነገድ የነበረ፥ የተቀደሰ ከተማ፥ዓይንንና መሰምርያዋን፥ ዮጣንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰምርያዋን ...” (ኢያ 21:16 1 ሳሙ 6:15)

2. በይሳኮር ደቡባዊ ድንበር የሚገኝ የከተማ ስም፥ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤትሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መውጫ ...” (ኢያ 19:22)

3. ከተቀጠሩ ፍታሌም ከተሞች አንዱ፥ቃዴስ፥ ኤድራይ፥ ዓይንሐጾር፥... ቤትዓናት፥ ቤትሳሚስ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 19:38)

ሄልዮቱተብሎም ይጠራል፥በግብፅም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብፅንም አማልክት ... ያቃጥላል። (ኤር 43:13)

ቤትራፋ ~ Bethrapha: ቤት ረፈ፣ የዕረፍት ቤት፣ የሰላም ቦታ... ማለት ነው። ቤት እና ረፍ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ነው።

ከይሁዳ ነገድ የሆነ የኤሽቶን ልጅ፥ (1 ዜና 412)

ቤትባራ ~ Beth-barah: ቤተ በር፣ ድንበር፣ የቤት ልጅ፣ ቤተኛ፣ ወዳጅ፣ የተቀደሰ ቤተሰብ... ማለት ነው።

ቤት እና በር ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

የእስራኤል ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን ሲያሳደዱ የያዙት ቦታ፥ (ይሁ 724)

ቤትአዌን ~ Beth-aven: ቤተ አቬን ወገን፣ የጣዖ ቦታ... ማለት ነው።

Beth-aven- ከቤቴል በምሥራቅ በኩል የሚገኝ ቦታ ስም፥ (ኢያ 7:2)

ቤትዓናት ~ Beth-anath: ቤተ አናት፣ ራስ፣ አለቃ፣ የበላይ አዛዥ... ማለት ነው። ቤት እና አናት ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ የቦታ ስም ነው።

ከንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ (ኢያ 19 38)

ቤትዓፍራ ~ Beth-le-Aphrah: ቤተ አፈር፣ ቤት ለአፈር፣ የአፈር ቤት፣ የጭቃ ቤት፣ ጉጆ ቤት... ማለት ነው።

ቤት እና አፈር ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የቦታ ስም ነው።

በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል፥ (ሚክ 110)

ቤትዔሜቅ ~ Bethemek: ቤተ መቅ፣ መቀመቅ፣ መቃብር ቤት፣ የመከራ ቦታ፣ የሥቃይ ቤት... ማለት ነው።

ቤት እና መቅ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ርስት፥ (ኢያ 1927)

ቤትኤጼል ~ Bethezel: ቤተ ኤል፣ የአምላክ ቤት፣ ቤተ እግዚአብሔር፣ ቤት ለእንግዳ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤት፣ ቤትጹር]

Bethezel- ቤት እና ኤል ከሚሉ ሦስ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ በመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል የተጠቀሰ ቦታ፥ (ሚክ 111)

ቤትካር ~ Beth-car: በረት፣ ጋጥ ማለት ነው። ራኤላውያን ከምጽጳ ፍልስጤማውያንን ያሳደዱበት ቦታ የእስራኤልምሰዎች...   

ፍልስጥኤማውያንንም አሳደዱ ቤትካር ታችም እስኪደርሱ ድረስ መቱአቸው። (1 ሳሙ 7:11)

ቤት የሺሞት ~ Beth-jeshimoth: ቤት የሺህ ሞት፣ የሺህ ሞት ቤት፣ ብዙ ሰዎች የሞቱበት ቤት፣ ብዙ ስዎች የተገደሉበት ቦታ... ማለት ነው።

ቤት ሺህ እና ሞት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

. የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ ያለበት ቦታ፥ (ዘኁ 3349)

. በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ ቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ረባ ባሕር እስከ ጨው... (ኢያ 12:3)

ቤትዳጎን ~ Beth-dagon: የእህል ማስቀመጫ ክፍል፣ ጎተራማለትነው።

1. በታችኛው የይሁዳ መስክ የሚገኝ ከተማ። ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ ስድስት ... (ኤያ 15:41)

2. በአሴር ደቡባዊ ምሥራቅ አዋሳኝ የሆነ፥ የከተማ ስም፥ ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ ... ወደ ካቡል ወጣ” (ኢያ 19:27)

ቤትጋሙል ~ Beth-gamul: የግመል ቤት ማለት ነው። በነቢዩ ኤር የተወገዘች የሞዓብያን ከተማ፥ በቂርያታይም፥ ቤትጋሙል” (ኤር 48:23)

ቤትጌልገላ ~ Bethgilgal: ቤተ ግልገል፣ የግልግል ቤት፣ የግልግል ቦታ፤ የዕረፍት ቤት፣ የነጻነት አገር... ማለት ነው።

ቤትእና ግልግልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን ከፈለጉባቸው ቦታዎች፥ (ነህ 1229)

ቤትጹር ~ Bethzur: ቤት ዙር፣ ቤተ ዘር፣ ወገን፣ ቤተ ዘመድ፣ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በቱል፣ ቤቱኤል፣ ቢትያ፣ ባቱኤል፣ ባይት፣ ቤቴል፣ ቤት፣ ቤትኤጼል]

. በይሁዳና በብንያም ያሉትንም ከተመሸጉ ከተሞች አንዱ፥ (2 ዜና

11:7)

. ሐልሑል፥ ቤትጹር ጌዶር፥ ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 1558)

ቤን ~ Ben: ቤን፣ ልጅ፣ ቤተኛ፣ ቤተሰብ... ማለት ነው።

ዳዊት በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆች የተናገረ፥ (1 ዜና 1518)

ቤንሐናን ~ Benhanan: ቤን ናን፣ ወገን፣ የሐና ልጅ፣ ትሑት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሐናን]

ቤን እና ሐና ከሚሉ ሁለት ስሞች የተመሠረተ ስም ነው። ከይሁዳ ወገን፣ የሺሞን ልጅ፥ (1 ዜና 420)

ቤንኃይል ~ Benhail: ቤን ኃይል፣ የኃያል ልጅ፣ ብርቱ ወገን፣ ጠንካራ ቤተሰብ... ማለት ነው።

ቤን እና ኃይል ከሚሉ ሁለት ስሞች የተመሠረተ ቃል ነው።

ኢዮሣፍጥ በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እንዲያስተምሩ ካዘዛቸው መሳፍንት፥ “...ያስተምሩ ዘንድ መሳፍንቱን፥ ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን...” (2 ዜና 177)

ቤንኦኒ ~ Benoni: የጸጸት ልጅ፣ የስቃይ ልጅ፣ የመከራ ልጅ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ብንያም]

ራሔልም ስትወልድ በምጥ ከመሞቷ በፊት ለብንያም የሰጠችው ስም፥ እርስዋም ስትሞት ነፍስዋ በምትወጣበት ጊዜ ስሙን ቤንኦኒ ብላ ጠራችው አባቱ ግን ብንያም አለው።” (ዘፍ 3518)

ቤኬር ~ Becher: ቤኪር፣ በከረ፣ ቀደመ፣ መጀመሪያ ተወለደ፣ አንደኛ ሆነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኩር፣ ቢክሪ ብኵር፣ በኵሬ፣ ቢክሪ፣ ብኮራት፣ ቦክሩ]

በከረከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የብንያም ልጅ፥ ቤኬር (ዘፍ 4621)

2. የኤፍሬም ልጅ፥ (ዘኁ 26:35)

ቤዜቅ ~ Bezek: ብራቅ፣ ነጸብራቅ... ማለት ነው።

1. በይሁዳ ነገድ ድርሻ፥ የአዶኒቤዜቅ መኖሪያ፥ አዶኒቤዜቅንም ቤዜቅ አገኙትና ተዋጉት ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንንም መቱአቸው።” (መሣ 1:5)

2. ሳኦል የእስራኤልንና የይሁዳን ሠራዊት የቆጠረበት ቦታ፥ ቤዜቅ ቈጠራቸው የእስራኤልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ ... ሺህ ነበሩ። (1 ሳሙ 11:8)

ቤጣሕ ~ Betah: ቤተህ፣ ቤት፣ ማደሪያ፣ ወገን፣ ቤተዘመድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቢትያ፣ ባይት፣ ቤት]

ቤተከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

ንጉሥ ዳዊትም ካስገበራቸው የአሕዛብ ከተሞች፥ ንጉሡም ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ቤጣሕ ከቤሮታይ እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ።” (2 ሳሙ 88)

ቤጤን ~ Beten: ከፍተኛ ማለት ነው። የአሴር ነገድ አዋሳኝ ከተማ፥ ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን አዚፍ” (ኢያ 19:25)

ቤጼር ~ Bezer: በዘር፣ በወገን፣ በዘመድ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ቦሶር]

ዘርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታዎች:-

. የአሴር ወገን፥ ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ ቤጼር ሆድ፥ ሳማ...” (1 ዜና 7:37)

. መሸሻ ከተሞች፥ ቦሶር- (ኢያ 208)

ብላስጦስ ~ Blastus: እምቡጥ፣ ውልድ፣ ውላጅ፣ ልጅማለት ነው። የሄሮስ አማካሪ (ቢትወደድ) ... የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስ እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና።” (ሐዋ 12:20)

ብልጣሶር ~ Belshazzar, Belteshazzar: ባለ ሺህ ዘር፣ ባለብዙ ዘር፣ ሀብታም፣ ኃያል... ማለት ነው።

Belshazzar- ባለ ሺህ እና ዘር ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የባቢሎን ንጉሥ፥ ንጉሡ ብልጣሶር ለሺህ መኳንንቶቹ ትልቅ ግብዣ አደረገ፥ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። (ዳን 5:1)

       ብልጣሶር ~ Belteshazzar: የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነፆር የጃንደረቦቹ አለቃ፥ ለዳንኤል የሰጠው ስም፥ የጃንደረቦቹም አለቃ ስም አወጣላቸው ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያንም ሲድራቅ፥ ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።” (ዳን 1:7)

ብራቂም ~ Bahurim: ዝቅተኛ ሥፍራማለት ነው። ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ፥ ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፥ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም ሂድ፥ ተመለስ አለው እርሱም ተመለሰ” (2 ሳሙ 3:16 19:16)

ብራያ ~ Beraiah: ባሪያ፣ በረ ያሕ፣ የሕያው ልጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብኤሮት] በር (ቤት ወገን) እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በኢየሩሳሌ ከተቀመጡ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች” (1 ዜና 8:21)

ብርሳ ~ Birsha: የእምነተ ቢስ ልጅ፣ ከሃዲ ማለት ነው። ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ብርሳ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፥ ከሰቦይም ንጉሥ ከሰሜበር፥ ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ።” (ዘፍ14:2)

ብኔብረቅ ~ Beneberak: ቤን በራቅ፣ የብራቅ ልጅ፣ የመብረቅ ልጅ፣ ወልደ ነጸብራቅ፣ ወልደ ነጎድጓድ... ማለት ነው።

ቤን እና ብራቅ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የዳን ልጆች ነገድ ርስት የወገኖቻቸው መጠሪያ፥ (ኢያ 1945)

ብኔያ ~ Ibneiah: ቤነ ያሕ፣ የሕያው ልጅ... ማለት ነው። የአምላክ ለት ማለት ነው። ተብሎም ይተረጎማል። የይሮሐም ልጅ ብኔያ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ የዪብንያ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም” (1 ዜና 9:8)

ብኔያዕቃን ~ Bene-jaakan: ዘን ልጅ፣ የብሶት ልጅ፣ የጸጸት ልጅማለት ነው። ራኤላውያን ወደ ተስፋ ምድር ባደረጉት ጉዞ ካረፋባቸው ቦታዎች፥ ከሞሴሮትም ተጕዘው ብኔያዕቃን ሰፈሩ።” (ዘኊ 33:3132)

ብንያም ~ Benjamin: ቤን ያሚን፣ ቤን አሚን፣ ምነት ልጅ፣ የተስፋ ልጅ... ማለት ነው።

ቤን እና ያምን ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [የስሙ ትርጉም የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አንዱ የሚጠራበት፣ የያቆብ ልጅ፥ “... ስሙን ቤንኦኒ ብላ ጠራችው አባቱ ግን ብንያም አለው። (ዘፍ 3518)

2. የጦር አዛዥ የነበረ፣ የቢልሐን ልጅ፥ (1 ዜና 7:10)

3. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስት ካገቡ፣ የካሪም ልጅ፥ (ዕዝ 10:32)

ብኤላሞን ~ Baal-hamon: የሐሞን በዓል፣ የሐሞን ጌታ፣ የብዙኃን ጌታ... ማለት ነው። የንጉሥ ሰሎሞን የወይን ቦታ፥ ለሰሎሞን ብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው ሰው ሁሉ ...” (መኃ 8:11)

ብዔል ዜቡል ~ Beelzebub, Baal-zebub: የዝንብ አምላክማለት ነው። ከሰይጣን መጠሪያ ስሞ አንዱ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!” (ማቴ 10:25 12:2427 ማር 3:22)

      ብዔልዜቡል / Baal-zebub: በአቃሮን የነበረ የፍልስጥኤማውያን አምላክ፥ አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዓይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ እርሱም፦ ሂዱ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡል ጠይቁ ብሎ መልእክተኞችን ላከ" (2 ነገ 1:2316)

ብዔልፌጎር~ Baal-peor: ባለ ክፍተት፣ ባለ ጉድ ለቁልፍማለት ነው። እስራኤልም ብዔልፌጎር ተከተለ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።” (ዘኊ 25:331:16 ኢያ22:17)

ብኤሪ ~ Beeri: በሬ፣ በር፣ ደጅ፣ መግቢያዬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዔ ሚስት፣ የዮዲት አባት፥ ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ ብኤሪ ልጅ ዮዲትን፥ ... ሚስቶች አድርጎ አገባ፥” (ዘፍ 2634)

2. የነቢዩ ሆሴዕ አባት፥ (ሆሴ 1:1)

ብኤር ~ Beer: በር፣ ደጅ፣ መግቢያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤሮት]

በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ቦታዎች አሉ።

1. የእስራኤልም ልጆች ከተጓዙባቸው፥ ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው።” (ዘኁ 2116-18)

2. ኢዮአታ ወንድሙን አቤሜሌክን ፈርቶ የሸሸበት፥ (መሣ 9:21)

ብኤርለሃይሮኢ ~ Beer-lahai-roi: ይስሐቅ ይኖርበት የነበረ ሥፍራ፥ ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና።” (ዘፍ 24:62 25:11)

ብኤርኢሊም ~ Beerelim: በረ አለም፣ የጀግኖች በርማለት ነው። በሞዓብ አዋሳኝነት የሚታ የቦታ ስም። ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።” (ኢሳ 15:8)

ብኤሮት ~ Beeroth: ቤሮት፣ በራት፣ በሮች፣ መግቢያዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በር፣ ቤሪ፣ ቤርያ፣ ቤሮታ፣ ቤሮታይ፣ ብኤሪ፣ ብራያ፣ ብኤር] የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ በወጡ ጊዜ ያለፋባቸው ቦታዎች፥ ኢያሱ በዚህ ከተማ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ገባ፥ ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት” (ኢያ 1825)

ብኮራት ~ Bechorath: በኩራት፣ ቀዳሚያት፣ ቀዳማውያን፣ መጀመሪያዎች፣ ፊተኞች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኩር፣ ቢክሪ ብኵር፣ በኵሬ፣ ቢክሪ፣ ቦክሩ]

በኩር ከሚለው ስም በኩራት (ለብዙ) የሚለው ስም ተገኘ።

የቂስ አያት፥የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ፥ ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ብንያማዊ ሰው ነበረ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ ብኮራት ልጅ፥ ... ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበረ።” (1 ሳሙ 91)

ብጦኒም ~ Betonim: ሆድ ማለት ነው። የነገደ ጋድ ልጆች ርስት የሆነ የቦታ ስም፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥ (ኢያ 13:26)

ቦሀን ~ Bohan: አሳሽ፣ ዳሳሽማለት ነው። የሮቤል ወገን፥ ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ” (ኢያ 15:6 18:17)

ቦሶር ~ Bezer: ዘር፣ በዘር፣ በወገን፣ በዘመድ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቤጼር]

ዘርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. ሙሴ ትናንት ከትናንት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይሸሽባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች ለየ፥ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለች፥ (ኢያ 20 8)

. ቤጼር- (1 ዜና 7:37)

ቦሦር ~ Besor: ብሥር፣ ብሥራት፣ የምሥራች፣ መልካም ዜና... ማለት ነው። የይሁዳ የታችኛው፥ ደቡባዊ ድንበር፥ ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፥ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም ... (1 ሳሙ 30:91021)

ቦአኔርጌስ ~ Boanerges: የነጎድጓድ ልጅ፣ ወልደ ነጎድጓድ... ማለት ነው። ለያቆብና ለዮሐንስ በጌታ የተሰጠ መጠሪያ፥ የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤” (ማር 3:17)

ቦዔዝ ~ Boaz: ንካሬ፣ ብርታትማለት ነው።

1. ባለጸጋው የቤተልሔም ሰው፥ የሩት ባል፥ ቦዔዝ ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ ... (ሩት 4:1-13)

2. ሰሎሞን በቤተ መቅደስ ካቆማቸው ሁለት አዕማድ አንዱ፥ በለዝ ተብሏል አዕማዱንም ... አቆማቸው የቀኙንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው የግራውንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።” (1 ነገ 7:21 2 ዜና 3:17)

ቦኪም ~ Bochim: በቂም፣ በለቅሶ፣ በሐዘን... ማለት ነው። ከጌልጌላ በላይ በዮርዳኖ በስተምዕራብ የሚገኝ ቦታ፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ከግብፅ አውጥቻችኋለሁ፥ ... (መሣ 2:16)

ቦክሩ ~ Bocheru: በኩሩ፣ በክሩ፣ በኩር፣ ቀዳሚው፣ ፊተኛው፣ የመጀመሪው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኩር፣ ቢክሪ ብኵር፣ በኵሬ፣ ቢክሪ]

በከረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። የኤሴል ልጅ፥ (1 ዜና 838)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ