ሰለሚኤል ~ Shelumiel: ሸላመ ኤል፣ ሰላመ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የጌታ ምሕረት... ማለት ነው።

ሰላመ እና ኤል ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ከእስራኤል ወደ ሰልፍ ከወጡ፥ (ዘኁ 1:6)

ሰለጰዓድ ~ Zelophehad: የፍራቻ ድባብማለት ነው። የምናሴ የልጅ ልጅ፣ ለኦፌር ልጅ፥ ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፥ ለኦፌር ልጅ፥ ሰለጰዓድ ግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ (ኢያ 17:3)

ሰሊሳ ~ Shelesh: ሽለሽ፣ ስለሽ፣ ስለሺህ፣ ስለ ብዙ፣ ኃያል... ማለት ነው።

Shelesh- ስለ እና ሺህ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ከአሴር ነገድ የሆነ፣ የጾፋ ልጅ፥ ሰሊሳ (1 ዜና 7:37)

ሰላሚኤል ~ Shemuel: ስማ ኤል፣ አምላክ ሰማ፣ ጌታ አዳመጠ፣ ልመናን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሙኤል፣ ሽሙኤል]

Shemuel -‘ሰማ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

. ከስምዖን ልጆች ነገድ የሆነ፣ የዓሚሁድ ልጅ፥ ከስምዖን ልጆች ነገድ የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል” (ዘኁ 34:20)

. የሕልቃና አባት፥ ሳሙኤል- (1 ዜና 6:3334)

. የቶላ ልጅ፥ ሽሙኤል- (1 ዜና 7:2)

ሰላትያል ~ Salathiel, Shealtiel: ለተ ኤል፣ ከአምላክ የተጠየቀ፣ የጌታ ለት፣ የስለት ልጅ... ማለት ነው።

Salathiel- ለት እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

       ሰላትያል / Salathiel: የምርኮኛው የኢኮንያን ልጅ ሰላትያል

(1 ዜና 3:17)

       ሰላትያል / Shealtiel: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የኢኮንያን ልጅ፥ (ማቴ 1:12) የኔሪ ልጅ፥ (ሉቃ 3:7)

ሰሌምያ ~ Shelemiah: ሰላመ ያሕ፣ የአምላክ ሰላም፣ የሕያው ሰላም፣ የአምላክ እርቅ፣ የአምላክ አንድነት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌሚ፣ ሴሌም፣ ሺሌም]

ሰላመ እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. “በምሥራቅም በኩል ዕጣ ሰሌምያ ወደቀ። ለልጁም ብልህ መካር ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። (1 ዜና 26:14)

2. ከግዞት ተመልሰው ኢየሩሳሌምን ካደሱ፣ የሐናንያ አባት፥ ሰሌምያ (ነህ 3:30)

3. በመጽሐፈ ዕዝራ የተጠቀሰው የባኒ ልጅ ሰሌምያ (ዕዝ 10:39) (ዕዝ 10:30)

4. በነህምያ ዘመን የነበረ ካህኑ ሰሌምያ (ነህ 13:13)

5. ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ ብሎ ወደ ኤርምያስ የላከው፥ ሰሌምያ (ኤር 37:3 38:1)

6. የዘበኞች አለቃ፥ የሐናንያ ልጅ፣ የየሪያ አባት፥ ሰሌምያ (ኤር 37:13)

7. የኵሲ ልጅ፥ ሰሌምያ (ኤር 36:14)

8. የዓብድኤል ልጅ፥ ሰሌምያ (ኤር 36:26)

ሰሌስ ~ Shelesh: ስለሽ፣ ስለሺህ፣ የሺህ ሰው ያሕል፣ ኃይለኛ... ማለት ነው።

Shelesh-‘ስለ እና ሺህ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የኤላም ልጅ፥ (1 ዜና 7:35)ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ ይትራን፥ ብኤራ ነበሩ።(1 ዜና 7:37)

ሰልሙና ~ Salmone: ሰላምነ፣ ሰላማዊ፣ ሰላማችን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰልማን፣ ሰሎሞን]

ሰላምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ጳውሎስና ሌሎች ወደ ሮም ሲሄዱ ያለፉበት የወደብ ስም፥ ሰልሙና (ሥራ 27:7)

ሰልማን ~ Shalman: ስለ አማን፣ ሰለሞን፣ ሰላማዊ፣ አማናዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰልሞን፣ ሰሎሞን]

ስለእና አማንከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በነቢዩ ሆሴዕ ትንቢት የተጠቀሰው፥ ሰልማን (ሆሴ 10:14)

ሰልሞን ~ Zalmon, Salma: ስለአማን፣ ሰላማዊ፣ ናነት፣ ርጋታ፣ ጸጥታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌሚ፣ ሴሌም፣ ሺሌም] ስለ እና አማን ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።

. የተራራ ስም፥ (መሣ 9:48)

. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የነአሶን ልጅ፥ (ማቴ 1:4 5) (ሩት 4:20)

       ሰልሞን / Salma: ሰላም፣ ጸጥታ ማለት ነው። የነአሶን ልጅ፥ የቦዔዝ አባት፥ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞን ወለደ፥” (ሩት 4:20 21 1 ዜና 2:1151 54 ማቴ 1:45 ሉቃ 3:32)

ሰልካ ~ Salcah: ስደትማለት ነው። ለምናሴ ነገድ የተሰጠ፥ የባሳን ከተማ፥ በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ሰልካ እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን” (ዘዳ 3:10 ኢያ 12:5 13:11)

ሰሎሚት ~ Shelomith, Shelomoth: ሰላሚት፣ ሰላማዊት፣ አማናዊት፣ ንነት... ማለት ነው።

ሰላምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሰሎሚት / Shelomith:

1. ከዳን ወገን የሆነች የደብራይ ልጅ፥ ሰሎሚት (ዘሌ 24:11)

2. የዘሩባቤል ልጅ፥ ሰሎሚት (1 ዜና 3:19)

3. የይስዓር ልጆች አለቃው፥ ሰሎሚት (1 ዜና 23:18)

4. በንጉሥ ዳዊት ዘመን ከሙሴ ልጅ ወገን፣ የአልዓዛር ልጅ፣ ሰሎሚት

(1 ዜና 26:25 26 28)

5. የለአዳን አባቶች ቤቶች አለቃ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ ሰሎሚት (1 ዜና

23:9)

6. ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን ከተመለሱ፥ የዮሲፍያ አባት፥ ሰሎሚት (ዕዝ 8:10)

       ሰሎሚት / Shelomoth: ይስዓራዊው፥ ሰሎሚት (1 ዜና 24:22)

ሰሎሜ ~ Salome: ሰላሜ፣ ሰላም፣ ንነት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎም፣ ሺሌም]

ሰላምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በሰንበት ወደ ጌታ መቃብር ከሄዱት፥ “…የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜ ነበሩ፥” (ማር 15:40)

ሰሎም ~ Shallum: ሰላም፣ ንነት፣ ስምምነት፣ እርቅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሺሌም]

ሰላምከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የንጉሥ ዳዊት ዘበኛ የነበረ፥ በረኞችም ሰሎም ዓቁብ፥ ጤልሞን ...” (1 ዜና 9:17)

2. በሰማርያ አንድ ወር የነገሠ፣ የኢያቤስ ልጅ ሰሎም (2 ነገ 15:10 13)

3. የይሁዳ ልጆች ወገን የሆነ፥ የሲስማይ ልጅ፥ ሰሎም (1 ዜና 2:40 41)

4. የንጉሡ የኢዮስያስ ልጅ፥ ሰሎም (1 ዜና 3:15 ኤር 22:11)

5. የስምዖን ልጅ፥ ሰሎም (1 ዜና 4:25)

6. ከካህናቱ አንዱ፥ የሳዶቅ ልጅ ሰሎም አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ ሳዶቅም ሰሎም ወለደ (1 ዜና 6:12 13) (ዕዝ 7:2)

7. የንፍታሌም ልጅ፥ ሰሎም (1 ዜና 7:13)

8. በንጉሥ ዳዊት ዘመን አገልጋይ የነበረ የቆሬ ልጅ፥ ሰሎም (1 ዜና

9:19 31)

9. ከኤፍሬም ልጆች አለቆች፥ ሰሎም (2 ዜና 28:12)

10. በባቢሎን የምርኮ ዘመን ከነበሩት፥ ከመዘምራን አንዱ ሰሎም (ዕዝ 10:24)

11. በባቢሎን የምርኮ ዘመን ከነበሩት፥ (ዕዝ 10:4142)

12. በኢየሩሳሌም እኩሌታ አለቃ የነበረ፥ የአሎኤስ ልጅ ሰሎም (ነህ

3:12)

13. የነቢዩ የኤርምያስ አጎት፥ የአናምኤል አባት ሰሎም (ኤር 32:7)

14. የበረኛው የመዕሤያ አባት፥ ሰሎም (ኤር 35:4)

ሰሎሞን ~ Solomon: ስለ አማን፣ ስላማን፣ ሰለሞን፣ ሰላማዊ፣ ሰላም፣ ንነት፣ ጸጥታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌም፣ ሺሌም] [ሰላማዊ ማለት ነው / መቅቃ]

ንጉሥ ዳዊት ከቤርሳቤህ የወለደው ሁለተኛ ልጅ፥ ንጉሥ ሰሎሞን “...ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው። ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው።” (2 ሳሙ 12:24 25)

ሰሙኤል ~ Shammua: ሰማ አምላክ፣ አዳመጠ፣ ታዘዘ... ማለት ነው። Shammua- ሰማከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

ኢያሪኮ እንዲሰልሉ በሙሴ ከተላኩት አንዱ፥ ከሮቤል ነገድ፥ (ዘኁ 13:4)

ሰሚራሞት ~ Shemiramoth: ስመ ራማት፣ ታላቅ ስም፣ ከፍተኛ ዝና... ማለት ነው። (ሺህ መሪ ተብሎም ይፈታል)

ስም ራማ እና መአት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. በንጉሡ በኢዮሳፍጥ ትእዛዝ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበሩት፥ (2 ዜና 17:8)

2. በሁለተኛው ተራ የዳዊት መዘምራን ከነበሩ፥ (1 ዜና 15:18 20)

ሰማሪት ~ Shimrith: ሺህ መሪት ማለት ነው። የሞዓባዊቱ የዮዛባት እናት፥ የተማማሉበትም የአሞናዊቱ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቱም ሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ።” (2 ዜና 24:26)

ሰማራያ ~ Shamariah, Shemariah: ሺህ መሪ ያሕ፣ የሽዎች መሪ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሳሜር፣ ሳምር፣ ሰማርያ]

ሺህ መሪ እና ያሕ’(ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሰማራያ / Shamariah: የሮብዓ ልጅ፥ ሰማራያ (1 ዜና 11:19)

       ሰማራያ / Shemariah:

1. በጺቅላግ ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡት፥ ሰማራያ (2 ዜና 12:5)

2. ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን ከተመለሱት፥ ሰማራያ (ዕዝ 10:`41)

3. የካሪም ልጅ፥ ሰማራያ ሸማያ፥ ስምዖን፥ ብንያም፥ መሉክ፥ ሰማራያ” (ዕዝ 10:32)

ሰማርያ ~ Samaria: መሰማሪያ፣ የመጠበቂያ ተራራማለት ነው። በኢየሩሳሌም በስተሰሜን የነበረ ከተማ፥ ከሳምርም በሁለት መክሊት ብር ሰማርያ ተራራ ገዛ ... በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው። (1 ነገ 16:24)

ሰማክያ ~ Semachiah: አምላክ የጠበቀውማለት ነው። የሸማያ ልጅ፥ (1 ዜና 26:7) ለሸማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም ኃያላን የነበሩ ኤልዛባድ፥ ኤልሁ፥ ሰማክያ

ሰማያስ ~ Ishmaiah: ሰማ ዋስ፣ ሰማ ያሕ፣ ሕያው አዳመጠ፣ አምላክ ሰማ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሙኤል፣ እስማኤል፣ ይሽማያ፣ ይሽማያ] Ishmaiah- ሰማእና ያሕ’ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዳዊት በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡት፥ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ (1 ዜና 124)

ሰማይ ~ Heaven: ዋነ፣ የሕያው ቦታ፣ የዘላለማውያን ማረፊያ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- በቅዱስ ማደሪያው፣ መቅደሱ ከፍታ]

Heaven- ሕያዋንከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. መንፈሳዊ ለም፣ የሕያዋን መኖሪያ፥ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 11)

. ከመሬት በላይ ያለ፥ ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ” (መዝ 18:16) ሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፥ ...ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።” (ኢሳ 24:18) ስለዚህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ። እግዚአብሔር በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያው ሆኖ ድምፁን ያሰማል በበረቱ ላይ እጅግ ... ይጮኻል። (ኤር 25:30)

. ሰማየ ሰማያት፥እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና (መዝ 102:19) ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል ...በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል (ሕዝ 17:23 33:26) ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት። (ኢዮ 35:5)

. ሰማየ ሰማያት፥ “... እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ። (2 ቆሮ 12:2)

ሰሜበር ~ Shemeber: እልፍኝማለት ነው። የሰቦይ ንጉሥ፥ ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፥ ከሰቦይም ንጉሥ ሰሜበር ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ።” (ዘፍ 14:2)

ሰሜኢ ~ Shimei, Shimhi, Shimi: ስሜ፣ ስም፣ ዝና፣ መጠሪያ፣ መታወቂያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሳሚ]

ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

ሰሜኢ /Shimei:

1. የኢዮኤል ልጅ፥ ሰሜኢ (1 ዜና 5:45)

2. ከሌዊ ልጆች፥ ጌድሶን ልጅ፥ ሰሜኢ (ዘኁ:18) (1 ዜና 6:1729)

3. የፈዳያ ልጅ፥ (1 ዜና 3:19)

4. የዘኩር ልጅ፥ (1 ዜና 4:26 27)

5. የሌዊያዊው የጌድሶን ልጅ፥ የኢኤት ልጅ፥ (1 ዜና 6:42 43)

6. የጎዶልያስ ልጅ፥ (1 ዜና 25:17)

7. በዳዊት የወይን ቦታ የተሾመው፥ ሰሜኢ (1 ዜና 27:27)

8. የኤማን ልጅ፥ (2 ዜና 29:14)

9. ካህኑ ሰሜኢ (2 ዜና 31:12 13)

10. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የሐሱም ልጅ ሰሜኢ (ዕዝ

10:33)

11. ብንያማዊ የአስቴር አጎት የመርዶክዮስ ወገን፣ የቂስ ልጅ ሰሜኢ (አስ 2:5)

. የኤላ ልጅ፥ በብንያም የኤላ ልጅ ሳሚ (1 ነገ 4:18)

. የጌራ ልጅ-ሳሚ (1 ነገ 1:8)

       ሰሜኢ / Shimhi: "ኤሊዔናይ፥ ... ሺምራት፥ ሰሜኢ ልጆች (1ዜና 8:21)

       ሰሜኢ / Shimi: የሌዊ ልጅ ከጌድሶን ልጆች፥ የጌድሶንም ልጆች እንደ ወገኖቻቸው ሎቤኒ፥ ሰሜኢ ናቸው። (ዘጸ 6:17)

ሰሜጋር ~ Shamgar: እግር፣ መንገደኛ፣ እንግዳ... ማለት ነው። የእስራኤል ፈራጅ የነበረ፥ የዓናት ልጅ፥ ከእርሱም በኋላ የዓናት ልጅ ሰሜጋር ተነሣ፥ ከፍልስጥኤማውያንም... ደግሞ እስራኤልን አዳነ።” (መሣ 3:31)

ሰምላይ ~ Shalmai: ሰላምታ፣ ምስጋና ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የሰምላይ ልጆች ይገኙበታል፥ የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ ሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ (ዕዝ 2:46 ነህ 7:48)

ሰምርኔስ ~ Smyrna: እጣንማለት ነው። በታናሽቱ እስያ ምዕራባዊ ወደብ፥ በኤፍራጠስ ወደብ በስተሰሜን ከተማ፥ ሰምርኔስ ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል።” (ራእይ 2:8-11)

ሰምዔ ~ Shuham: ጉድጓድ ቆፋሪማለት ነው። የዳን ልጅ፥ በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው ሰምዔ የሰምዔያውያን... (ዘኊ 26:42)

ሰሳብሳር ~ Sheshbazzar: እሳተ መለኮትማለት ነው። ለዘሩባቤል ፋርሳዊ ስም፥ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስም በመዝገቡ ላይ በነበረው በሚትሪዳጡ እጅ አወጣቸው፥ ለይሁዳም መስፍን ሰሳብሳር ቈጠራቸው።” (ዕዝ 1:811 6:14 18)

ሰራብያ ~ Sherebiah: ሸር አብያ፣ ቸር አብ ያሕ፣ ቸር አምላክ፣ ሕያው አባት... ማለት ነው።

Sherebiah- ቸር አብ እና ያሕ (ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

ዕዝራ እና ነህም በአደረጉት አገልግሎት ስሙ አብሮ የሚጠቀሰ ካህን፥ (ዕዝ 8: 18 24-30 ነህ 9:4 5 10:12)

ሰራኩስ ~ Syracuse: ሥራ ቀውስ፣ አፍራሽ፣ ተገንጣይ፣ በአመ የተለየ... ማለት ነው። በሲሲሊ በስተ ደቡባዊ ምሥራቅ የነበረ የወደብ ከተማ፥ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮም ጉዞው ለሦስት ቀናት ያረፈበት፥ ወደ ሰራኩስ በገባን ጊዜ ሦስት ቀን ተቀመጥን” (ሐዋ 28:12)

ሰራፕታ ~ Sarepta, Zarephath: የአንጠረኛ ሱቅማለት ነው። ነቢዩ ኤልያስ የገባበት መንደር ስም፥ ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም (ሉቃ 4:26)

       ሰራፕታ / Zarephath: ማቅለጫማለት ነው። ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ ወደ ከተማይቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልቴት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር እርሱም ጠርቶ። የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ አላት።” (1 ነገ 17:10 ሉቃ 4:26)

ሰርዴስ ~ Sardis: የደስታ ልዑል ማለት ነው። በዮሐንስ ራእይ የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ (ራእይ 3:1-6) ሰርዴስ ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል። ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ ሞተህማል።

ሰርግ ~ Feast: ፌስታ፣ ግብዣ፣ ድግስ፣ ዓመት በዓል፣ የደስታ ቀን፣ ውደ ዓመት... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ማዕድ፣ በዓል፣ ግብዣ]

ላባም የዚያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ሰርግ አደረገ። (ዘፍ 29:22)

ሰሮና ~ Saron: በለምለም መስክነቱ የሚታወቅ ቦታ፥ ... በልዳና ሰሮና የሚኖሩ ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ዘወር አሉ። (ሐዋ 9:35)

ሰቅል~ Bekah, shekel: ሰቁል፣ ሰቀለ፣ ሚዛን ላይ አወጣ... ማለት ነው። ብር ማለት ነው። የእራኤላውያን የመገበያያ ገንዘብ፥ ከብር ቀልጦ የሚ ሳንቲም፥ (ዘጸ 38:26) እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የሰቅል ግማሽ ከተቈጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው ከሀያ ዓመት ጀምሮ ... (ዘፍ 23:15)

ሰበንያ ~ Shebaniah: ሰባነ ያሕ፣ ሰባነ ሕያው፣ ሳባውያን፣ የአምላክ ሰዎች፣ የጌታ ወገኖች፣ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት] ሰበን እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

በእግዚአብሔር ታቦይ ፊት መለከት ይነፉ ከነበሩ አንዱ፥ ሰበንያ (1ዜና 15:24)

2. ሌዋዊው፥ ሰበንያ (ነህ 9:4 5)

3. ካህኑ፥ ሰበንያ ዘኩር፥ ሰራብያ፥ ሰበንያ ሆዲያ፥ ባኒ፥ ብኒኑ:” (ነህ

10:12)

4. ሌላ ሌዋዊ፥ ሰበንያ (ነህ 10:4)

ሰብታ ~ Sabtah: ሰብ ቤት፣ ሰባት፣ ሳባት፣ ሳባ ቤት፣ የሰው ልጅ፣ ሰብዊ፣ ቤተ ሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

ሰብ እና ቤት ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የኩሽ ሦስተኛ ልጅ፥ የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ ራዕማ፥ ሰበቃታ ...” (ዘፍ 10:7)

ሰተርቡዝናይ ~ Shethar-boznai: ስውር ጠላትማለት ነው። ቤተመቅደሱ እንዳይታነጽ ጥረት ካደረጉ ሰዎች አንዱ፥ የፋርስ ወታደር፥ (ዕዝ 5:3 6 6:6 13) “ዚያም ዘመን በወንዝ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ ተባባሪዎቻቸውም ወደ እነርሱ መጥተው ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንኑም ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው? አሉአቸው።

ሰቱር ~ Sethur: ሰጡር፣ መሰጠር፣ መሰወር፣ መደበቅ፣ ምሥጢር ማድረግ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ምሥጢር]

ሰጠረከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

ሙሴ የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ከላካቸው፥ ከአሴር ነገድ የሆነ የሚካኤል ልጅ ሰቱር (ዘኁ 13:13)

ሰነአብ ~ Shinab: መልካም አባት ማለት ነው። በአብርሃም ዘመን የነበረ፥ የአዳማ ንጉሥ፥ ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ሰነአብ ከሰቦይም ንጉሥ ...ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ።” (ዘፍ 14:2)

ሰናዖር ~ Shinar: የሁለት ወንዞች አገር ማለት ነው። በባቢሎን አቅራቢያ የሚገኝ የቦታ ስም፥ (ዘፍ 11:3) “ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ ሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ በዚያም ተቀመጡ።

ሰናክሬም ~ Sennacherib: ኃጢአትማለት ነው። በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን፥ ይሁዳን የወረረ የአሦር ንጉሥ፣ በንጉሡም በሕዝቅያስ በአሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ... (2 ነገ 18:13)

ሰንበት ~ Sabbath: ሰብ ቤት፣ ሰባት፣ ሳባ ቤት፣ቤተ ሳባ፣ ቤተ ሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

Sabbath- ሰብ እና ቤት ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[ሰብኣት፥ ሰዎች፣ ወገኖች ፣የቅርብ ዘመዶች / ኪወክ / ]

[ሰብአ ቤት ቤተ ሰብ ዘመድ ወገን ነገድ፥ ሎሌ፥ ገረድ... / ደተወ / ] [ብራይስጥ የቃሉ ትርጉም ማቆም፡ መተው ማለት ነው / መቅቃ] (ዕረፍት፣ የዕረፍት ቀን ... ተብሎም ይተረጎማል።)

ሰባተኛው ቀን፥ እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው። ነገ ዕረፍት ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው።” (ዘጸ 16:22-30)

ሰንባላጥ ~ Sanballat: ብርታትማለት ነው። ነህምያ ኢየሩሳሌምን ለመጠገን በተነሣሣበት ዘመን በሰማርያ ባለልጣን የነበረ፥ ሖሮናዊውም ሰንባላጥ ባሪያው አሞናዊ ጦብያ ለእስራኤል ... ተበሳጩ።” (ነህ 2:1019 4:1-12 6)

ሰዓር ~ Zohar: ‘ጮራ፣ ብርሃናማ፣ ነጭማለት ነው።

1. የኤፍሮን አባት፥ ...ሬሳዬን ከፊቴ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ፥ ሰዓር ልጅ ከኤፍሮንም ለምኑልኝ (ዘፍ 23:8 25:9)

2. የስሞዖን ልጅ፥ የስሞዖን ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። (ዘፍ 46:10 ዘጸ 6:15)

ሰኰት፣ ሶኮ ~ Socoh: ድንኳን ማለት ነው። በይሁዳ ነገድ የነበሩ ሁለት ከተሞች ስም፥

1. ዓዶላም፥ ሰኰት ዓዜቃ፥ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። (ኢያ

15:36 1 ሳሙ17:1 2 ዜና 11:7 8:18)

2. የይሁዳ ከተማ፥ ሶኮ፥ሶኮ ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና” (ኢያ 15:49)

ሰኮት ~ Shochoh: [ደባባይ፣ መተላለፊያ ማለት ነው። / ] የቦታ ስም፥ ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን በይሁዳ ባለው ሰኮት አከማቹ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በኤፌስደሚም ሰፈሩ።” (1 ሳሙ 17:1)

ሰይጣን~ Satan: ጠላት፣ተቃዋሚ... ማለት ነው። ታላቁ   ዘንዶ፣ የቀደመው እባብ፤ የዚህ ዓለም ገዥ እና በመሳሰሉት መጠሪያዎች ይታወቃል፥ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ” (ራእይ 12:920:2) (ዮሐ 12:31 14:30)

ሰዱቃውያን ~ Sadducees: ጻድቃን፣ የሰዶቅ ተከታዮች ማለት ነው። ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች ... ማን አመለከታችሁ?” (ማቴ 3:7)

ሰዲ ~ Sodi: ውዴ፣ ወዳጄ፣ ጓደኛዬማለት ነው። ከነዓንን እንዲሰልሉ ከተላኩ፥ ከዜብሎን የሄደው፥ የጋዲኤል አባት፥ ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ ከዛብሎን ነገድ ሰዲ ልጅ ጉዲኤል (ዘኊ 13:10)

ሰዲዮር ~ Shedeur: ጨረር ጮራማለት ነው። የኤሊሱር አባት፥ ከእናንተም ጋር የሚቆሙት ሰዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው ከሮቤል ሰዲዮር ልጅ” (ዘኊ 1:5 2:107:3035 10:18)

ሰዶም ~ Sodom: በክፉ ሥራቸው ከሰማይ በወረደ እሳት ከጠፋት ከተሞች አንዱ፥ ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።” (ዘፍ 13:1014:1-16)

ሰጢም ~ Shittim: ሰጢም፣ ሸለቆ... ማለት ነው። የቦታ ስም፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ ...” (ኢያ 2:1)

ሰጲራ ~ Sapphira: ዕንቁ፣ ልዑል፣ ቆንጆ፣ ውብ ማለት ነው። ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፥ (ሐዋ 5:1)

ሰፈጥ ~ Shaphat: ስፍነት፣ መስፈን፣ ት፣ መፍረድ፣ መዳኘት... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሳፋጥ፣ ሻፋጥ፣ ሻፍጥ] ስፍነትከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ አራት ሰዎች አሉ።

. ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ፥ ሰፈጥ (ዘኁ 13:5)

. የኤልሳዕ አባት፥ ሳፋጥ (1 ነገ 19:16-19)

. የሸማያ ልጅ፥ ሻፋጥ (1 ዜና 3:22)

. የዳዊት እረኞች አለቃ፣ የዓድላይ ልጅ፣ ሻፍጥ (1 ዜና 27:29)

ሰፉፋም ~ Shephuphan: ሰፋፋ፣ ጨመረ፣ ደመረማለት ነው። የባላ ልጅ፥ ... አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም ሑራም።” (1 ዜና 8:4)

ሰፋጥያስ፣ ስፋጥያስ ~ Shephatiah: ሕያው ገዥ፣ ሕያው ዳኛ... ማለት ነው።

1. ንጉሥ ዳዊት ከአቢጣል የወለደው፥ አራተኛውም የአጊት ልጅ አዶንያስ፥ አምስተኛውም የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ ነበረ (2 ሳሙ 3:4)

2. በጺቅላግ ከዳዊት ሠራዊት ጋር ከተቀላቀሉ፥ ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት ... ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ (1 ዜና 12:5)

3. በእስራኤልም ነገዶች ላይ አለቃ ከነበሩ፥ የመዓካ ልጅ፥ .. ልጅ አልዓዛር አለቃ ነበረ በስምዖናውያን የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ (1 ዜና 27:16)

4. የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ፥ ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ ...” (2 ዜና 21:2)

5. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሰፋጥያስ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።” (ዕዝ 2:4)

6. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ... (ዕዝ 2:57 ነህ 7:59)

7. የማታን ልጅ፥ ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ ... (ኤር 38:1-4)

ሱሔ ~ Shoa: ሽዋ፣ ሺህ፣ ብዙ፣ ሀብታም፣ ባለጸጋ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሱሳ፣ ሱዋ፣ ሱሔ ሴዋ]

Shoa- ሺህ፣ ከሚለው ቁጥር የመጣ ስም ነው።

ስለ ኦሖሊባ ትንቢት ሲነገር ተያይዞ የተጠቀሰ፥ (ሕዝ 23:23)

ሱሲ ~ Susi: ከአሥራ ሁለቱ ሰላዮች የአንዱ፣ የጋዲ አባት፥ ከዮሴፍ ነገድ እርሱም የምናሴ ነገድ ሱሲ ልጅ ጋዲ (ዘኊ 13:11)

ሱሲጳጥሮስ ~ Sopater: ጋሻ አርበኛማለት ነው። ጳውሎስ ከግሪክ ወደ እስያ ባደረገው ጉዞ ከሸኙት፥ የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ...ነበሩ (ሐዋ 20:4)

ሱሳ ~ Sheva: ሸቫ፣ ሳባ፣ ሰብዓ፣ ሰብ፣ ሰው... ማለት ነው። (ሸባ፣ ሺህ አባ፣ የብዙዎች አባት ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስሞች- ሱሔ፣ ሱዋ፣ ሱሔ ሴዋ]

Sheva- ሰብከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

1. የዳዊት ጸሐፊ፥ ሱሳ (2 ሳሙ 20:26)

2. የጊብዓ አባት ሱሳ (1 ዜና 2:49)

ሱሳ ~ Shushan: አበባ ማለት ነው። ዳንኤል ራእዩን ያየበት ቦታ፥ በራእዩም አየሁ ባየሁም ጊዜ በኤላም አውራጃ ባለው ሱሳ ግንብ ... (ዳን 8:2)

ሱሪሰዳይ ~ Zurishaddai: የአምላክ ወገን፣ አምላክ የረዳው... ማለት ነው። የሰለሚኤል አባት፥ ኤሊሱር፥ ከስምዖን ሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፥ (ዘኊ 1:6 2:12)

ሱሪኤል ~ Zuriel: ዘረ ኤል፣ የጌታ ወገን፣ ረዳት፣ መመኪያ... ማለት ነው።

Zuriel- ዘር እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

የሜራሪ ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ፥ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል (ዘኁ 335)

ሱራፌል ~ Seraphim: ነበልባልማለት ነው። ኢሳይያስ በአየው ራእይ፥ በጌታ ዙፋን ላይ የቆሙ መላእክት፥ ሱራፌል ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር (ኢሳ 6:2)

ሱር ~ Shur, Zur: ዙር፣ ዙሪያ፣ አጥር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዱር] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ: -

       ሱር / Shur: የቦታ ስም፥ አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥ በቃዴስና ሱር መካከልም ተቀመጠ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ” (ዘፍ 20:1) (ዘጸ 15:22)

       ሱር / Zur:

. የንጉሥ ስም፥ የተገደለችውም ምድያማዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ እርስዋም ሱር ልጅ ነበረች...” (ዘኁ 2515) (ዘኁ 31:8)

. ብንያማዊው፥ ዱር- (1 ዜና 8:30)

ሱባ ~ Zobah: ዘብ፣ ጠባቂ፣ ወታደር... ማለት ነው። የአሦርያ ክፍለ ግዛት የነበረ፥ ሳኦል እና ዳዊት ከሱባ ንጉሥ ጋር ጦርነት አካሂደዋል፥ ሳኦልም ... ከኤዶምያስም፥ ሱባ ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።” (1 ሳሙ 14:47 2 ሳሙ 8:3 10:6)

ሱባኤ ~ Shebuel: ሰባ ኤል፣ የአምላክ ሰው፣ የሰንበት ጌታ፣ የእግዚአብሔር ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሱባኤል]

Shebuel- ሰብ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የኤማን ልጅ፥ (1 ዜና 25:4 5)

ሱባኤል ~ Shebuel, Shubael: ሰባ ኤል፣ የሳባ አምላክ፣ የሰንበት ጌታ፣ የእግዚአብሔር... ሰው ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሱባኤ]

ሰብ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

. ሱባኤል / Shebuel: የጌርሳም ልጆች አለቃ ሱባኤል (1 ዜና 23:16)

. ሱባኤል / Shubael: አሥራ ሦስተኛው ሱባኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፥” (1 ዜና 25:20)

ሱቱላ ~ Shuthelah: የኤፍሬም ልጅ፥ እነዚህ ሱቱላ ልጆች ናቸው ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን።” (ዘኊ 26:35)

ሱነማይቱ ~ Shunammite: ሰላማዊት፣ አማናዊት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሱነማዊት]

ሰላምከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. ንጉሡ ዳዊት በሸመገለ ጊዜ ያገባት፥ በእስራኤልም አገር ሁሉ የተዋበች ቈንጆ ፈለጉ ሱነማይቱ አቢሳንም አገኙ፥ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ።” (1 ነገ 1:3)

. ሱነማዊት- [2 ነገ 4:12]

ሱነም ~ Shunem: እጥፍ ማረፊያማለት ነው። ለይሳኮር የተሰጠ ከተማ፥ ወደ ከስሎት፥ ወደ ሱነም ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺኦን፥ ወደ አናሐራት፥” (ኢያ 19:19)

ሱኮት ~ Succoth: ድንኳን መቅደስ፣ ማደሪያ፣ መጸለያማለት ነው።

1. ከጥንታዊ ከተሞች አንዱ፥ ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶችም ዳሶችን አደረገ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው።” (ዘፍ 35:17)

2. እስራኤል ልጆች ከግብፅ ሲሔዱ ካረፋባቸው፥ እስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያሕል እግረኛ ነበረ።” (ዘጸ 12:37 13:20 ዘኁ33:56)

ሱኮትበኖት ~ Succoth-benoth: የልጆች ድንኳን ማለት ነው።

የባቢሎናውያን ጣዖት ስም፥ የባቢሎንም ሰዎች ሱኮትበኖት ሠሩ የኩታም ሰዎች ኤርጌልን ሠሩ” (2 ነገ 17:30)

ሱዋ ~ Shua, Suah: ው፣ ሺህ፣ የብዙ ቁጥር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሱሔ ሴዋ]

Shua- ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

. የአሴር ልጅ፥ (1 ዜና 7:30 32)

. ከነዓናዊቱ ሴዋ- (1 ዜና 2:3)

       ሱዋ / Suah: የጾፋ ልጅ፥ (1 ዜና 7:36) የጾፋም ልጆች ሱዋ ሐርኔፍር፥

ሲሐ ~ Ziha: ድርቅማለት ነው።

1. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የናታኒም ልጅ፥ ናታኒም ሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ (ዕዝ 2:43 ነህ 7:46)

2. “ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር ሲሐ ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ።” (ነህ 11:21)

ሲላ ~ Silla: ሰላ ተስተካከለ፣ ቀና፣ ተመቻቸ ማለት ነው። ባሪያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፥ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት። (2 ነገ 12:21)

ሲላስ ~ Silas: ልስ፣ ሠላሽ፣ ሦስተኛ ማለት ነው። ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ... ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። (ሐዋ 15:22)

ሲምሳይ ~ Shimshai: ፀሓያማማለት ነው።

Shimshai- ስም እና ሺህ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

ከግዞት ሲመለሱ የቤተ መቅደሱን እንደገና መታነጽ ከተቃወሙ፥ ጸሐፊው ሲምሳይ (ዕዝ 4:8 13 17 23...) (ዕዝ 4:7)

ሲሞን ~ Simon: ስማን፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳ፣ ታዘዘ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ስምዖን፣ ሲሞን፣ ሺሞን]

ስማከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። [ሰማ ከሚለው ግስ የተገኘ ነው / መቅቃ]

ሐሰተኛ ነቢይ የነበረ፥ ግን አምኖ በሐዋርያት የተጠመቀ፥ ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ...” (ሥራ 8:9)

ሲሣራ ~ Sisera: የጦርነት ልፍማለት ነው።

1. የከነዓን ንጉሥ፣ የኢያቢስ ሠራዊት አለቃ፥ እግዚአብሔርም ... የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተቀመጠው ሲሣራ ነበረ (መሣ 4:2)

2. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የሲሣራ ልጆች፥ ሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።” (ዕዝ 2:54 ነህ 7:55)

ሲስማይ ~ Sisamai: የኤልዓሣ ልጅ፥ ኤልዓሣም ሲስማይ ወለደ” (1 ዜና 2:40)

ሲባ ~ Ziba: ዘብ፣ ዘበኛ፣ ጠባቂ ማለት ነው።

በሳዖል ቤት አገልጋይ የነበረ፥ (2 ሳሙ 9:2-18)

ሲኒም ~ Sinim: ን፣ የደቡብ አገርማለትነው። (ኢሳ 49:12) “እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ሲኒም አገር ይመጣሉ

ሲና ~ Sinai: ቁጥቋጦ እሾሃማማለት ነው። የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብፅ አገር ከወጡ በኋላ ካለባቸው ቦታዎች አንዱ፥ ...በኤሊምና ሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ (ዘጽ 17:8-13)

ሲን ~ Sin: ቋጥኝማለት ነው። የግብፅ ከተማ ስም፥ በግብፅም ምሽግ ሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፥ የኖእንም ብዛት አጠፋለሁ።” (ሕዝ 30:1516)

ሲንጤኪን ~ Syntyche: እድለኛ፣ ተግባቢማለት ነው። የፊሊ ቤተ ክርስቲያን አባል የነበረች፥ ጳውሎስ ወደ ፊሊጵስዮስ በላከው ደብዳቤ የጠቀሳት፥ በአንድ አሳብ በጌታ እንዲስማሙ ኤዎድያንን እመክራለሁ ሲንጤኪንንም እመክራለሁ።” (ፊሊ 4:23)

ሲአራ ~ Sherah: ዘር፣ ዘመድ ማለት ነው። የኤፍሬም ሴት ልጅ። ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የሠራች ሲአራ ነበረች።” (1 ዜና 7:24)

ሲዓ ~ Sia: ሃጅ ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ የሲዓ ልጆች ይገኙበታል፥ የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ ሲዓ ልጆች፥ (ነህ 7:47)

ሲካር ~ Sychar: ፍጻሜማለት ነው። ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ የነበረ፥ የቦታ ስም፥ ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤” (ዮሐ 4:5)

ሲኮንዱስ ~ Secundus: ሰከንድ፣ ቅጽበት፣ ደቃቅ... ማለት ነው። በተሰሎንቄ የጳውሎስ ተከታይ የነበረ ክርስቲያን፥ ሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ... ነበሩ፤” (ሐዋ 20:4)

ሲዎን ~ Sion: ጽዮን፣ ጽኑዓን፣ ብርቱ፣ ኃያል፣ መከታ፣ አምባ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ጽዮን]

ጽኑከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የተራራ ስም፥ “... ሲዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ድረስ (ዘዳ 4:48)

ሲዲም ~ Siddim: መስክ፣ ደልዳላ ሥፍራማለት ነው። የሸለቆ ስም፥ እነዚህ ሁሉ ሲዲም ሸለቆ ተሰብስበው ተባበሩ ይኸውም የጨው ባሕር ነው።” (ዘፍ 14:3810)

ሲድራቅ ~ Shadrach: ግርማዊማለት ነው። ከሦስቱ ጻድቃን አንዱ በጃንደረቦቹም አለቃ የተጠራበት ስም፥ አናንያ፥ የጃንደረቦቹም አለቃ ስም አወጣላቸው ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያንም ሲድራቅ ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።” (ዳን 1:7)

ሲዶን ~ Sidon, Zidon: ማደን ማለት ነው። ከነዓን የበኵር ልጁ፥ (ዜና 10:15) ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥

       ሲዶን / Zidon: አዳኝ፣ አሳ አስጋሪማለት ነው። የከነዓን የበኲር ልጅ፥ ከተማውም በስሙ ተጠራ፥ ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም” (ዘፍ 10:1519)

ሲፋይ~ Sippai: የራፋይም ወገን፥ ከዚህም በኋላ በጌዝር ... ሰልፍ ሆነ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፋይ ገደለ። (1 ዜና 20:4)

ሲፓራ ~ Zipporah: የመስቀል ወፍ ማለት ነው። ኪወክ /

ሲጶራ- ሲፎራ (የሙሴ ሚስት- ኢትዮጵያዊት)

የኢትዮጵያዊው ካህን ራጉኤል ልጅ፣ የሙሴ ሚስት፥ ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ ልጁንም ሲፓራ ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። (ዘጸ 2 21) ሙሴም ኢትዮጵያይቱ አግብቶአልና ባገባት ኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። (ዘኁ 12:1)

ሳላይ ~ Sallai: ቅርጫት ሠሪማለት ነው።

1. የብንያም ወገን፥ ከእርሱም በኋላ ጌቤና ሳላይ ዘጠኝ መቶም ሀያ ስምንት።” (ነህ 11:8)

2. “ሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥(ነህ 12:20)

ሳሌም ~Salem, Salim: ሳሌም፣ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ጸጥታ፣ ንነት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌሚ፣ ሴሌም፣ ሺሌም] ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ቦታዎች አሉ።

       ሳሌም / Salem: ካህኑ ንጉሥ መልከጻድቅ ያስተዳድረው የነበር አገር፥ ሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ ...” (ዘፍ 14:18)

       ሳሌም / Salim: ነብዮ ዮሐንስ ያጠምቅበት የነበረ አካባቢ የቦታ ስም፥ (ዮሐ 3:23)

ሳሙስ ~ Shammua, Shimea: ሽሚ፣ ሰሚ፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሙኤል፣ ሳምዓ ሰሙኤ]

Shammua, Shimea- ሰማ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳሙስ / Shammua:

1. በጸሎት ጊዜ ምስጋናን የሚያቀነቅን የነበር፣ የአብድያ አባት ሳሙስ (ነህ

11:17)

2. ከቢልጋ ነገድ የሆነ ካህን፥ ሳሙስ (2 ሳሙ 5:14)

       ሳሙስ / Shimea:

. ንጉሥ ዳዊት ከቤርሳቤህ የወለደው፥ (1 ዜና 3:5)

. የዳዊት ወንድም፥ ሳምዓ - (1 ዜና 20:7)

ሳሙስ ~ Shammuah: ሰማ፣ አዳመጠ፣ ታዘዘማለት ነው። የዳዊት ልጅ፥ በኢየሩሳሌምም የተወለዱለት ስማቸው ይህ ነው ሳሙስ (2 ሳሙ 5:14)

ሳሙኤል ~ Samuel: ሰማ ኤል፣ ሰማ አምላክ፣ ጌታ ሰማ፣ እግዚአብሔር አዳመጠ፣ ጸሎትን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሽሙኤል]

ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[ሳሙ ኤል ማለት የእግዚአብሔር ስም አምላካዊ ስም ማለት ነው / መቅቃ] የሕልቃና እና የሐና ልጅ፣ ነቢዩ ሳሙኤል የመፅነስዋም ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም፦ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው:” (1 ሳሙ 1:20)

ሳሚ ~ Shimei: ስሜ፣ ስም፣ ዝና፣ መጠሪያ፣ መታወቂያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሜኢ፣ ሣማ፣ ሳምአ ሳምዓ]

ስመከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ንጉሥ ዳዊትን ይራገም የነበር ከሳ ቤት የሆነ የጌራ ልጅ፥ (2 ሳሙ 16:5-13)

2. ንጉሡ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ በነበር ጊዜ ከነበሩት አለቆች አንዱ፥ በብንያም የኤላ ልጅ ሳሚ (1 ነገ 4:18)

ሳማ ~ Shamma, Shammah, Shimea: ስምዓ፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳት... ማለት ነው።

መዐከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

        ሳማ / Shamma: ማለት ነው። የጾፋ ልጅ፥ (1 ዜና 7:37)

       ሣማ / Shammah: ማለት ነው።

1. የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጅ፥ (ዘፍ 36:13 17)

2. የእሴይ ልጅ፣ የዳዊት ወንድም፥ እሴይም ሣማ አሳለፈው ...” (1 ሳሙ 16:9 17:13)

3. የአጌ ልጅ፥ (2 ሳሙ 23:11-17)

4. “ልጅ ኤልያናን፥ አሮዳዊው ሣማ ሒሮዳዊው ኤሊቃ፥ (2 ሳሙ

23:25)

5. “የአሳን ልጆች፥ ዮናታን፥ አሮዳዊው ሣማ (2 ሳሙ 23:33)

        ሣማ / Shimea: የዳዊት ወንድም፥ እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም ሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው። (2 ሳሙ 21:21)

ሳማያ ~ Shemaiah: ሰማ ያሕ፣ ሰማ አምላክ፣ ሕያው ሰማ፣ እግዚአብሔር አዳመጠ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሜኢ፣ ሸማያ]

ሰማ እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. ነቢዩ ሳማያ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ...” (1 ነገ 12:22-24)

. ከባቢሎን ከተመለሱ የሴኬንያ ልጅ፥ ሸማያ (ነህ 3:28 29)

. ከስምዖን ወገን የሆነ፥ ሰሜኢ (1 ዜና 4:27)

ሳሜር ~ Shamer, Shomer: ሺህ መሪ፣ የሺህ መሪ፣ የሺህዎች አለቃ፣ የብዙዎች ጠባቂ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- (ሳሜንር) ሳምር፣ ሾሜር] Shamer, Shomer- ሺህ እና መሪ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

       ሳሜር / Shamer: አሴራዊው፥ ሳሜር ልጆች አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሑባ፥ አራም ነበሩ።” (1 ዜና 7:34)

       ሳሜንር / Shomer: የሔቤር ልጅ፥ ሳሜንር (ሳሜር) (1 ዜና

7:32)

. ሾሜር - (2 ነገ 12:21)

ሳምር ~ Shemer: ሺህ መሪ፣ የሺህ መሪ፣ የሺህዎች አለቃ፣ የብዙዎች ጠባቂ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሳሜር፣ ሰማርያ]

በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዘንበሪ በእስራኤል ላይ አሥራ ሁለት ዓመት ሲነግሥ በገንዘብ የገዛው የተራራ ስም፥ ሳምር በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ... ሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው” (1 ነገ 16:24)

ሳምር፣ ሻሚር ~ Shamir: ህ፣ ሹል፣ ጫፍማለት ነው።

1. በይሁዳ ተራራማ ክፍል የነበረ ከተማ፥ በተራራማውም አገር ሳምር የቲር፥” (ኢያ 15:48)

2. በተራራማው የኤፍሬም አገር የነበረ፥ የእስራኤል ዳኛ፥ ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን

...በኤፍሬም አገር ባለችው ሳምር ተቀምጦ ነበር። (መሣ 10:12)

3. የሚካ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ሻሚር የሚካ ወንድም ይሺያ (1 ዜና 24:25)

ሳምናስ ~ Shebna: ሽብና፣ ሰብእ ሰውነት፣ ህልውና፣ ብርታማለት ነው። በሕዝኤል መንግሥት፥ ከፍተኛ ባለልጣን የነበረ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቤቱ ውስጥ ወደ ተሾመው ወደዚህ አዛዥ ወደ ሳምናስ ሂድ እንዲህም በለው” (ኢሳ 22:15)

ሳምአ ~ Shimea, Shimeah, Shimeam: የቃሉ ትርጉም ሁለት ነው:- ስም እና ሰማ። [ተዛማጅ ስሞች- ሳምዓ፣ ሳሙስ]

መዐ ከሚለው ግስ የመጣ: ሲሆን- ሰምዓ፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳ ማለት ነው። ሰየመከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን:- ስምዓ፣ ሴማዊ፣ ስማዊ፣ ዝና፣ መለያ፣ መታወቂያ ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳምዓ / Shimea:

1. የዳዊት ወንድም፥ እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም ሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው” (1 ዜና 20:7)

2. የሜራሪ ልጅ፥ (1 ዜና 6:30)

3. የሚካኤል ልጅ፥ (1 ዜና 6:3940)

       ሳምአ / Shimeah:

1. የሚቅሎት ልጅ፥ ሚቅሎት ሳምአ ወለደ ...” (1 ዜና 8:32)

2. የዳዊት ወንድም፥ ለአምኖንም የዳዊት ወንድም ሳምዓ ልጅ ...” (2 ሳሙ13:3)

       ሳምአ / Shimeam: ሚቅሎትም ሳምአ ወለደ ...” (1 ዜና 9:38)

ሳሞት ~ Shammoth: ሽማት፣ ስማት፣ ስሞች ማለት ነው።

ስምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ከዳዊት የዘበኞቹ አለቃ አንዱ፥ ሃሮራዊው ሳሞት (1 ዜና 11:27)

ሳሞትራቄ ~ Samothracia: ሰማርያውያንና ተርሴሳውያን የሚኖሩበት ማለት ነው። ጳውሎስ በሐዋርያዊ ጉዞው ካለፈባቸው ቦታዎች፥ ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤” (ሐዋ 16:11)

ሳሞን ~ Samos: ኮረኮንማለት ነው። ጳውሎስ በሐዋርያዊ ጉዞው ካለፈባቸው ቦታዎች፥ በማግሥቱም ... ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን” (ሐዋ 20:15)

ሳራሳር ~ Sharezer, Sherezer: ቸር ዘር፣ ምስጉን፣ አምላካዊ፣ መልካም ወገን፣ የንጉሥ ወገን፣ መለኮታዊ... ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳራሳር /  Sharezer: የአሦር ንጉሥ የሰናክሬ ልጅ፥ በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አደራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት (2 ነገ 19:37)

       ሳራሳር / Sherezer: ከቤቴል ሰዎች ወደ አምላክ የተላከ፥ (ዘካ 7:2)

ሳርጎ ~ Sargon: ጎ፣ ጅ፣ ጠላቂ፣ የባሕር ልዑልማለት ነው። ከታዋቂ የአሦር ነገሥታት አንዱ፥ የአሦር ንጉሥ ሳርጎ ተርታንን በሰደደ ጊዜ እርሱም ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥ (ኢሳ 20:1)

ሳሮን ~ Sharon: ደልዳላ፣ ረባዳ፥ የለመለመ መስክ... ማለት ነው። የቅድስት አገር ክፍለ ግዛት፥ የቦታ ስም፥ በገለዓድም ምድር በባሳን በመንደሮቹም ሳሮን መሰምርያዎች ሁሉ እስከ ዳርቻቸው ድረስ ተቀምጠው ነበር። (1 ዜና 5:16 ኢሳ 33:9)

ቢላኒ ~ Abilene: ሜዳማ አገርማለት ነው። በጌታ የልደት ዘመን፥ ሊሳኒዮስ ገዥ የነበረበት ከተማ፥ ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት ... ሊሳኒዮስም በሳቢላኒ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሆነው ሳሉ” (ሉቃ 3:1)

ሳባ ~ Seba, Sheba: ሰባ፣ ሰብዓ፣ ሰብ፣ ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

ሰብዓከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳባ / Seba:

1. የኩሽ ልጅ ሳባ፥ የኩሽም ልጆች ሳባ ኤውላጥ ...” (ዘፍ 10:7)

2. ሳባውያን፥ (ኢሳ 43:3)

       ሳባ / Sheba:

1. የራዕማ ልጅ፥ “... የራዕማ ልጆችም ሳባ ድዳን ናቸው (ዘፍ 10:7)

2. የዮቅጣ ልጅ፥ (ዘፍ 10:2829)

3. የአብርሃም ልጅ፥ የዮቅሳን ልጅ፥ ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። ...” (ዘፍ 25:3)

4. “እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም ሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል...” (ኢሳ 45:14)

5. “… የዓረብና ሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። (መዝ 72:10)

. የብንያማዊ የቢክሪ ልጅ፥ ሳቤዔ - (2 ሳሙ 20:1)

. ሤባ- (ኢያ 19:2)

ሳባ ሰዎች (የሳባ ሰዎች) ~ Sabeans: ሰባያን፣ ሳባውያን፣ ሳባቤት፣ የሰው ልጅ፣ የሳባ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

ሳባውያን፥ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም ሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ...” (ኢሳ 45:14)

. የሳባ ሰዎች፥ “...ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ (ኢሳ 43:3)

. ሰው፥ ሰዎች እንስሶችም በማቅ ይከደኑ...” (ኢዮ 3:8)

. ሰው፥ የደስተኞችም ድምፅ በእርስዋ ዘንድ ነበረ ከብዙም ሰዎች ጉባኤ ...” (ሕዝ 23:42)

. ሳባውያን፥ ሳባ ሰዎች አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ...” (ኢዮ 1:15)

ሳባታይ ~ Shabbethai: ሳባተያ፣ ሳባዊያት፣ የሳባ ወገን፣ የሳባ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ ከነበሩ የሌዋውያን አለቆች፥ ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ሰራብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባታይ ... ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር። (ነህ 8:7) (ዕዝ 10:15) (ነህ 11:16)

ሳባጥ ~ Sebat: ሰባት፣ ሳባ ቤት፣ የሳባ ልጅ፣ የሰው ልጅ፣ ቤተ ሳብ፣ ቤተ ሰብ፣ የሳባ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

Sebat- ሰብዓ እና ቤት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የወር ስም፥ (ዘካ 1:7)

ሳቤህ ~ Shebah: ሰብዓ፣ ሳባ፣ ሰብ፣ ሰው፣ የሰው ልጅ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤዔ፣ ጸባዖት]

የቦታ ስም፥ የቤርሳቤህ የማሳጠር ስም፥ ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው (ዘፍ 26:33)

ሳቤዔ ~ Sheba: ሰብዓ፣ ሳባ ሰብ፣ ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባ ሰዎች፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሴባ፣ ሤባ፣ ጸባዖት]

ብዐከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ (2 ሳሙ 20:1) (ዘፍ 10:7)

ሳብያ ~ Zibiah: ዘብ ያሕ፣ የተጠበቀ፣ ታላቅ፣ የተከበረ ማለት ነው።

Zibiah- ዘብእና ያሕ’ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የንጉ የኢዮአስ እናት፥ (2 ነገ 12:1)

ሳኔር ~ Senir, Shenir: ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል።” (ዘዳ 3:9)

       ሳኔር / Shenir: ማሾ ፋኖስማለት ነው የኤርሞን ተራራ የሶደናውያን መጥሪያ፥ ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል። (ዘዳ 3:9 መኃ 4:8)

ሳንሳና ~ Sansannah: የዘንባባ ቅርንጫፎችማለት ነው። በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል የነበረ ከተማ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና (ኢያ 15:31)

ሳኡል፣ ሳኦል ~ Shaul: ሺህ አውል፣ ኃይለኛ፣ ጀግና... ማለትነው።

1. የስምዖን ልጅ፥ የስሞዖን ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል” (ዘፍ 48:10 ዘጸ 6:15 ዘኊ 26:13 1 ዜና 4:24)

2. “ሠምላም ሞተ፥ በስፍራውም በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርሆቦት ሳኦል ነገሠ።” (ዘፍ 36:37)

ሳኦል፣ ሳውል ~ Saul: ሺህ አውል፣ ብርቱ፣ ጀግና... ማለት ነው።

1. ከቀደሙ የኤዶም ነገሥታት አንዱ፥ በስፍራውም በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርሆቦት ሳኦል ነገሠ። (ዘፍ 36:37381 ዜና 1:48)

2. የመጀመሪያው የእስራኤላውያን ንጉሥ፥ (2 ሳሙ 1:25)

3. የሐዋርያው ጳውሎስ የቀድሞ ስም፥ ሳውል

ሳዶቅ ~ Sadoc, Zadok: ሳዲቅ፣ ዛዲቅ፣ ጻድቅ፣ እውነተኛ፣ ሕያው ማለት ነው።

ጸደቀከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳዶቅ / Sadoc: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የአኪም ልጅ፥ (ማቴ 1:14)

       ሳዶቅ / Zadok:

1. የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ከመጡ፣ የአኪጦብ ልጅ፥ ሳዶቅ (1 ዜና 24:3)

2. የንጉሥ ዖዝያ አያት፣ የኢየሩሳ አባት፥ (2 ነገ 15:33 2 ዜና 27:1)

3. የኢየሩሳሌምን አጥር ከጠገኑት፣ የበዓና ልጅ፥ ሳዶቅ (ነህ 3:4 29)

4. የመራዮት ልጅ፥ ሳዶቅ (1 ዜና 9:11)

ሳፋጥ ~ Shaphat: ሽፍት፣ ስፍነት፣ መስፈን፣ መፍረድ፣ መዳኘት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሣፋጥ፥ ሻፋጥ፣ ሰፈጥ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሳፋጥ / Shaphat:

. የነቢዩ የኤልሳዕ አባት፥ (1 ዜና 5:12)

. የሱሬ ልጅ፥ ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ (ዘኁ 13:5)

. የሸማያ ልጅ፥ “... የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግኣል፥ ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ።” (1 ዜና 3:22)

       ሣፋጥ / Shaphat: የነቢዩ የኤልሳዕ አባት፥ (1 ነገ 19:1819)

ሴሊድ ~ Seled: ደስታ፣ ፈንጠዝያማለትነው። የናዳብ ልጅ፥ (1 ዜና 2:30) “የናዳብም ልጆች ሴሊድ አፋይም ነበሩ ሴሌድም ያለ ልጆች ሞተ

ሴላ ~ Zillah: ጥላ፣ ጠለላ ግርዶሽማለት ነው። ከላሜሕም ሚስቶች አንዷ፥ ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበረ።” (ዘፍ 4:1922)

ሴሌሚ ~ Shelomi: ሰሎሜ፣ ሰላሜ፣ ንነቴ፣ አማኔ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌም፣ ሺሌም]

ሰላምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ከአሴር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የአሒሁድ አባት፥ ሴሌሚ (ዘኁ 34:27)

ሴሌም ~ Shallum: ሰላም፣ ስምምነት፣ እርቅ፣ አንድነት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰሎሜ፣ ሰሎም፣ ሴሌሚ፣ ሺሌም]

ሰለመከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የቲቁዋ ልጅ፣ የነቢያቱ የሕልዳና ባል፥ (2 ነገ 22:14 2 ዜና 34:23)

2. የንፍታሌም ልጅ፥ (1 ዜና 7:13)

ሴሌስ ~ Helez: ጉልበትማለት ነው።

1. ከሠላሳ የዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ ፈልጣዊው፣ፈሎናዊው፣ፍሎናዊው (the Paltite) ሴሌስ የቴቁሐዊው” (2 ሳሙ 23:26 1 ዜና 11:27)

2. ኬሌስ፥ ዓዛርያስም ኬሌስ ወለደ ኬሌስም ኤልዓሣን ወለደ (1 ዜና 2:39)

ሴሌውቅያ ~ Seleucia: ውጥ፣ ሞገደኛማለት ነው። የአንጾኪያ የባሕር ወደብ፥ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።” (ሐዋ 13:4)

ሴሌፍ ~ Zalaph: ቁስልማለት ነው። የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን የተባበረ፥ ከእርሱ በኋላ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና ሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም ...” (ነህ 3:30)

ሴሎ ~ Shiloh: ማለት ነው። የቦታ ስም፥ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ...” (ኢያ 18:1)

ሴሎም ~ Shelah: መፍታት፣ ማላቀቅማለት ነው።

1. የይሁዳ ትንሹ ልጅ፥ እንደ ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች፥ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው እርሱንም በወለደች ጊዜ ክዚብ በሚባል አገር ነበረች።” (ዘፍ 38:5111426 46:10 ዘኊ 26:20 1 ዜና 2:3 4:21)

2. ሳላን፥ አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ ቃይንምም ሳላን ወለደ ሳላም ዔቦርን ወለደ።” (1 ዜና 1:1824)

ሴሜር ~ Shamer: ሽሕ መር፥

ሌዋዊው የሞሖሊ ልጅ፥ (1 ዜና 6:46 47)

ሴሜይ ~ Semei: ሴሚ፣ ሰሚ፣ አዳማጭ፣ ታዛዥ... ማለት ነው።

ሰማከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ (ሉቃ 3:26)

በጌታ የዘር ሐረግ፥ የማታትዩ ልጅ። የናጌ ልጅ፥ ... ልጅ ሴሜይ ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥” (ሉቃ 3:26)

ሴም ~ Sem, Shem: ሴም፣ ስም፣ ዝና፣ እውቅና ማለት ነው።

ስምከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

       ሴም / Sem: ከሦስቱ የኖኅ ልጆች የአንዱ ስም፥ (ሉቃ 3:36)

       ሴም / Shem: የኖኅ ልጅ፥ (ዘፍ 5:32)

ሴሲ ~ Sheshai: ክቡር ማለት ነው። በኬብሮን የሚኖረው፣ የዔናቅ ልጅ፥ በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ...ነበር።” (ዘኊ 13:22)

ሴሴይ ~ Shashai: ማለት ነው። በዕዝራ ዘመን የነበረ፥ ከባኒ ልጆች አንዱ፥ ሴሴይ ሸራይ፥ ኤዝርኤል፥ ሰሌምያ፥ ሰማራያ፥ ሰሎም፥ ...” (ዕዝ 10:41)

ሴሬድ ~ Sered: ፍርማለት ነው። የዛብሎን ልጅ፥ የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ ኤሎን፥ ያሕልኤል። (ዘፍ 46:14 ዘኊ 26:26)

ሴሮህ ~ Saruch: ች፣ ቅርንጫፍ... ማለት። በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የራጋው ልጅ፥ የናኮር ልጅ፥ ሴሮህ ልጅ፥ የራጋው ልጅ፥ የፋሌቅ ልጅ፥ የአቤር ልጅ፥ የሳላ ልጅ” (ሉቃ 3:35)

ሴሮሕ ~ Serug: ቅርንጫፍማለት ነው። የአብርሃም ቅድመ አያት፥ የራግው ልጅ፥ ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ (ዘፍ 11:20-23)

ሴባ ~ Shisha: ተፎካከረ ተገዳደረማለት ነው። የኤልያፍና አኪያ አባት፥ ጸሐፊዎቹም ሴባ ልጆች ኤልያፍና አኪያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ” (1 ነገ 4:3)

ሴባማ ~ Shebam: ሽቶማለት ነው። ለጋድ እና ለሮቤል ልጆች፥ ለከብቶቻቸው መሰማሪያ እንዲሆን የተሰጠ፥ የቦታ ስም፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው ... (ዘኊ 32:3)

ሴባማ ~ Shibmah: ሽቶማለት ነው። በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሮቤል ከተማ፥ ቂርያታይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማ ሠሩ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች ...” (ዘኊ 32:38)

ሴባማ ~ Sibmah: ምርኮማለት ነው። በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ፥ የሞዓባውያን ግዛት፥ የሮቤል ከተማ፥ ሜፍዓት፥ ቂርያታይም፥ ሴባማ በሸለቆውም ተራራ ያለችው ጼሬትሻሐር፥” (ኢያ 13:19)

ሴቦካይ ~ Sibbechai: ዘዋሪ፣ ሸማኔማለት ነው። የዳዊት ዘበኛ፥ የስምንተኛው ወር ስምንተኛ አለቃ፥ ከዚህም በኋላ ...ሰልፍ ሆነ፥ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሳፍን ገደለ። (2 ሳሙ 21:18 1 ዜና 20:4)

ሴት ~ Seth, Sheth: ሴተ፣ ሰጠ፣ ተካ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሤት] ሰጠከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

       ሴት / Seth: የአዳምና የሔዋን ሦስተኛ ልጅ፥ አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፦ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው” (ዘፍ 4:25) (ዘፍ 4:25 6:3) (1 ዜና 1:1)

       ሤት / Sheth: (ዘኁ 24:17)

ሴናዓ ~ Senaah: እሾሐማ የሾለ፣ የሰላማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ”(ዕዝ 2:35 ነህ 7:38)

ሴኔ ~ Seneh: ግራርማለት ነው። ዮናታንም ... ሊሻገርበት በወደደው መተላለፊያ መካከል በወዲህ አንድ ሾጣጣ በወዲህ አንድ ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ የአንዱም ስም ቦጼጽ የሁለተኛውም ስም ሴኔ ነበረ (1 ሳሙ 14:45)

ሴኬም ~ Shechem: ሸክም ... ማለት ነው።

1. አብርሃም የመቃብር ቦታ የገዛበት፥ የኤሞር ልጅ፥ ... የእርሻውን ክፍል ሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው። (ዘፍ 33:19 34)

2. የምንናሴ ወገን፥ ሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን። (ዘኊ26:31 ኢያ 17:2)

3. በሰማርያ የነበረ ከተማ፥ ያዕቆብም ... ወደ ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ።” (ዘፍ 33:18)

ሴኬም ~ Sichem: ሸክም ጭነት፣ ትክሻ ላይ የሚያዝ... ማለት ነው። አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ የከነዓን ... ነበሩ።” (ዘፍ 12:6)

ሴኬንያ ~ Shecaniah: ሺህ ቅነ ያሕ፣ የሕያው ወዳጅ ለአምላክ የቀረበ... ማለት ነው።

1. ከዳዊት የካህናት ምድብ፥ አሥረኛ እጣ የወጣለት፥ ካህን፥ አሥረኛው ሴኬንያ አሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ አሥራ ...” (1 ዜና 24:12)

2. በሌዋዊው የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ በቆሬ ሥር ሆነው የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ከተመደቡ ካህናት አንዱ፥ በካህናቱም ከተሞች ... በየሰሞናቸው ክፍላቸውን በእምነት ይሰጡ ዘንድ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ ከእጁ በታች ነበሩ። (2 ዜና 31:15)

ሴዊ ~ Shaveh: ደልዳላማለት ነው። የሸለቆ ስም፥ ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰ በኋላም የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነ ሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ። (ዘፍ 14:17)

ሴዋ ~ Shua, Shuah: ሽዋ፣ ሺህ፣ ብዙ ቁጥር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሱሔ፣ ሱዋ፣ ስዌሕ]

Shua, Shuah- ሽዋከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

       ሴዋ / Shua: የነከዓናዊቱ የይሁዳ ሚስት፣ አባት፥ (1 ዜና 2:3)

       ሴዋ / Shuah: የይሁዳ ሚስት ሴዋ ልጅ ሞተች ይሁዳም ተጽናና፥ የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ...” (ዘፍ 38: 12)

ሴዌኔ ~ Syene: ክፍተትማለት ነው። በኢትዮጵያና በግብፅ ድንበር ላይ የነበረ የግብፅ ከተማ፥   የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።” (ሕዝ 29:10 30:6)

ሴዎን ~ Sihon: ጦረኛ ማለት ነው። እስራኤላውያን ወደ ቃል ኪዳን አገር በቀረቡ ጊዜ የነበረ፥ የአሞራውያን ንጉሥ፥ እስራኤልም። በምድርህ ላይ እንለፍ ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላኩ። (ዘኊ 21:21)

ሴይር ~ Seir: ር፣ ሳር፣ ሥራ ሥር... ማለት ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ተራራ አሉ።

. የሰው ስም፥ በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው ሴይር ልጆች ...” (ዘፍ 36:20-30)

. የተራራ ስም፥ የኤዶም አገር፥ የሖር ሰዎችንም ሴይር ተራራቸው በበረሐ አጠገብ እስካለች እስከ …” (ዘፍ 14:6)

ሴዴቅያስ ~ Zedekiah, Zidkijah: ጸደቀ ያሕ፣ ጽድቀ ዋስ፣ ሕያው ጻድቅ፣ እውነተኛ አምላክ፣ የጽድቅ አምላክ... ማለት ነው።

Zedekiah, Zidkijah- ጽድቅ እና ሕያው (ዋስ) ከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴዴቅያስ ተብለው የተጠሩ ሦስት አሉ። ለማገናዘብ እንዲረዳ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥቅሶች ማነጻጸር ይበጃል።

       ሴዴቅያስ / Zedekiah:

1. የባቢሎን ንጉሥ የዮአኪን አጎት ማታንያን፥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው፥

(2 ነገ 24:18)

2. የክንዓና ልጅ፥ (1 ነገ 22:11)

       ሴዴቅያስ / Zidkijah: ቃልኪዳኑን አትመው ከሰጡ አለቆች አንዱ፥ ካህኑ ሴዴቅያስ (ነህ 10:1)

ሴድራክ ~ Hadrach: ‘ማደሪ፣ መኖሪያማለት ነው። በነቢዩ ዘካሪያስ የተጠቀሰ፥ የሲሪያ አገር፥ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል (ዘካ 9:1)

ሴጎር ~ So: የእህል ሚዛን ማለት ነው። የግብፅ ንጉሥ፥ የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዓመፅ አገኘ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ይዞ በወህኒ ቤት አሰረው።” (2 ነገ 17:4)

ሴፈርዋይም ~ Sepharvaim: ሰፋሪያም ማለት ነው። ሰናክሬም ለሕዝቅያስ በላከው ደብዳቤ የተጠቀሰ፥ የአገር ስም፥ የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ ሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?” (2 ነገ 19:13 ኢሳ 37:13)

ሴፎር ~ Zippor: የመ ወፍ፣ ብርቅዬ፣ ትንሽ ወፍ ማለት ነው። የሞዓብ ንጉሥ፥ ሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ።(ዘኊ 22:24)

ስልማና ~ Salamis: በቆጵሮስ ደቡባዊ ምሥራቅ የነበረ ከተማ፥ ስልማና በነበሩ ጊዜ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፤ አገልጋይም ዮሐንስ ነበራቸው” (ሐዋ 13:5)

ስልማና ~ Zalmunna: ግርሽ፣ ጥላማለት ነው። ሱኮትንም ሰዎች። የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማና ሳሳድድ፥ ደክመዋልና እኔን ለተከተሉ ሕዝብ እንጀራ፥ እባካችሁ፥ ስጡ አላቸው (መሣ 8:5-21)

ስልምናሶር ~ Shalmaneser: እሳት አምላኪማለት ነው። የአሦር ንጉሥ፥ የአሦርም ንጉሥ ስልምናሶር በእርሱ ላይ ወጣ ሆሴዕም ተገዛለት፥ ግብርም አመጣለት።” (2 ነገ 17:3)

ስልዋኖስ ~ Silvanus: ዱረኛ፣ ጫካ የሚወድማለት ነው። በእኛ ማለት በእኔና ስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል።” (2 ቆሮ 1:19)

ስምንት ~ Sheminith: ሽምንት፣ ስምንት (8) ሳምንት፥ ከሰባት በመቀጠል ከዘጠኝ በፊት የሚመጣ ቁጥር... ማለት ነው።

Sheminith- ሳምንት ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

የበገና አውታር (ቅኝት) ቁጥር ለመግለጽ የተጠቀሰ፥ መቲትያ፥ ኤልፍሌሁ፥ ሚቅኒያ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል፥ ዓዛዝያ ስምንት አውታር ባለው በገና ይዘምሩ ነበር” (1 ዜና 15:21)

ስምዖን ~ Shimeon, Simeon, Simon: ሰማነ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳ፣ ተገነዘበ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሲሞን]

ስማንከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

[ሰማ ከሚለው ግስ የተገኘ ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ስምዖን / Shimeon: በነቢዩ ዕዝራ ዘመን፥ በባቢሎን በምርኮ፥ እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው፥ አያሌ ልጆችን ከወለዱ ካህናት፥ (ዕዝ 10:31)

       ስምዖን / Simeon: ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ልጅ፥ ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው። (ዘፍ 29:33)

       ስምዖን / Simon:

1. ቀነናዊው ስምዖን (ማቴ 10:4)

2. የጌታ ወንድም ተብሎ የተጠቀሰው የያቆብና የዮሳ ወንድም፥ ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖን ይሁዳም አይደሉምን?” (ማቴ 13:55) ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም ስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ …” (ማር 6:3)

3. ጌታን ተቀብሎ ያስተናገደ ለምጻሙ ስምዖን (ማቴ 26:6)

4. የአስቆሮቱ ይሁዳ አባት፥ ስምዖን (ዮሐ 6:71 13:2 26) (ሥራ 2:10)

5. ቆርበት ፋቂው ስምዖን (ሥራ 9:43)

ስንጣክን ~ Stachys: ስንር፣ ስንጣቂ... ማለት ነው። በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ጳውሎስ በሰላምታ ደብዳቤው የጠቀሰው፥ በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ ለኢሩባኖን ለምወደውም ስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16:9)

ስካካ ~ Secacah: አጥርማለት ነው። በይሁዳ ምድረ በዳ ከነበሩ ስድስት ከተሞች አንዱ፥ በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ (ኢያ 15:61)

ስዌሕ ~ Shuah: ሽዋህ፣ ሽዋ፣ ሺህ፣ ብዙ ቁጥር... ማለት ነው።

ሺህከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

አብርሃም ከኬጡራ የወለደው፥ እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕ ወለደችለት” (ዘፍ 25:2) (1 ዜና 1:32)

ስጥና ~ Sitnah: ጣናዊ፣ ጠብ፣ ጥላቻ... ማለት ነው። ይስሐቅ ካስቆፈራቸው የውኃ ጉድጓዶች፥ ሁለተኛው፥ ሌላ ጕድጓድም ማሱ፥ ስለ እርስዋም ደግሞ ተጣሉ ስምዋንም ስጥና ብሎ ጠራት።” (ዘፍ 26:21)

ስፋራድ ~ Sepharad: የተለየ፣ የተከፈለማለት ነው። ይህምሰራጵታ ድረስ ይወርሳል ስፋራድ የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።”(አብ 1:20)

ስፋር ~Sephar: ስፍር፣ ልክ፣ መጠን፣ ቁጠር... ማለት ነው።

ሰፈረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

የዮቅጣን ልጆች ከኖኅ የጥፋት ውኃ በኋላ የኖሩበት የቦታ ስም፥ (ዘፍ 10:30)

ስፎ ~ Shephi, Shepho, Zepho: እራቁትማለት ነው። የሦባል ልጆች ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ አውናም ዓና። (1 ዜና 1:40)

       ስፎ / Shepho: ደቦ ማለት ነው። የሦባል ልጆችም እነዚህ ናቸው ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ አውናም። (ዘፍ 36:23)

        ስፎ / Zepho: ማማ ማለት ነው። የዔሳው የልጅ ልጅ፥ የኤልፋዝ ልጅ፥ የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው ስፎ ጎቶም፥ ቄኔዝ። (ዘፍ 36:11)

ሶምሶን ~ Samson: ፀሓያማ፣ ፀሓይ የመሰለ ማለት ነው። ናዝራዊው፥ የማኑሄ ልጅ፥ ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ሶምሶ ብላ ጠራችው ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው።” (መሣ 13:3-5)

ሶሳን ~ Sheshan: ክቡርማለት ነው። የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ ሶሳን ልጅ አሕላይ ነበረ።” (1 ዜና 2:313435)

ሶስቴንስ ~ Sosthenes: አዳኝ፣ መከታማለት ነው። በቆሮንጦስ የምኩራብ አለቃ የነበረ፣ ጳውሎስን ባለመቃወሙ በአድመኞች የተደበደበ፥ የግሪክ ሰዎችም ሁሉ የምኩራብ አለቃ ሶስቴንስ ይዘው በወንበሩ” (ሐዋ 18:12-17)

ሶስና ~ Susanna: አበባ ጽጌሬዳማለት ነው። የጌታን ትምህርት ይከታተሉ ከነበሩ፥ የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስና ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር (ሉቃ 8:3)

ሶሬቅ ~ Sorek: ወይን ጠጅ ቀለም ማለት ነው። ደሊላ የነበረችበት አገር፣ የሸለቆ ስም፥ ከዚህም በኋላ ሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ደሊላ የተባለች አንዲት ሴትን ወደደ።” (መሣ 16:4)

ሶርያ ሶሪያ ~ Syria: ሥራ ያሕ፣ የሕያው ሥራ፣ ያምላክ ሰራተኛ፣ የጌታ ሠራዊት... ማለት ነው።ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፤ እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ ሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።” (ኦሪት ዘፍጥረት 25: 20)

ያዕቆብም ሶርያውን ሰው ላባን ከድቶ ኮበለለ፥ መኮብለሉንም፥ አልነገረውም።” (ኦሪት ዘፍጥረት 31
20
)

       ሶሪያ / syria: የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ አለ።” (“2 ዜና 18: 10)

ሶባብ ~ Shobab: ሺህ አባብ፣ ሽባብ፣ የሚያባባ፣ አስፈሪ... ማለት ነው።

ሺህ እና አባብ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ የተወለደ፥ ሶባብ (2 ሳሙ 5:14)

2. የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ የወለደው፥ (1 ዜና 2:18)

ሶባክ ~ Shobach: መስፋፋትማለት ነው። የሶርያ ንጉሥ የወታደሮቹ አዛዥ፥ አድርአዛርም ልኮ በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን፥ አመጣ ወደ ኤላምም መጡ፥ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶባክ በፊታቸው ነበረ።” (2 ሳሙ 10:16)

ሶባይ ~ Shobai: ሺህ አባይ፣ የሺህ አባ፣ የብዙዎች አለቃ፣ መሪ... ማለት ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ ሶባይ ልጆች ይገኙበታል፥ (ነህ 7:45) (ዕዝ 2:42)

ሶቤቅ ~ Shobek: መተው፣ መልቀቅ ማለት ነው። የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ከፈረሙት አንዱ፥ አሎኤስ፥ ፈልሃ፥ ሶቤቅ ሬሁም፥ ሐሰብና፥ (ነህ 10:24)

ሶገር ~ Zuar: ትንሽነት ማለት ነው። የናትናኤል አባት፥ ከይሳኮር ሶገር ልጅ ናትናኤል፥” (ዘኊ 1:8 2:57:1823 10:15)

ሶጣይ ~ Sotai: ተለዋዋማለት ነው።ከምርኮ ከተመለሱ፥ የሰሎሞን አገልጋዮች፥ የሶጣይ ልጆች ይገኙበታል፥ የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች ሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች” (ዕዝ 2:55 ነህ 7:57)

ሶፋር ~ Zophar: ድምቢጥማለትነው። ከሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች አንዱ፥ ...ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ። (ኢዮ 2:11 11:1 20:1 42:9)

ሶፌሬት ~ Sophereth: ስፍት፣ ሰፋሪያት፣ ቆጣሪያት፣ ጸሐፍት... ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የሶፌሬት ልጆች ይገኙበታል፥ የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች የሶጣይ ልጆች፥ ሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ (ዕዝ 2:55 ነህ 7:57)

ሶፎንያስ ~ Zephaniah: ጸፋነ ዋስ፣ ጭፈነ ያሕ፣ ፋነ ያሕ፣ በሕያው የጠፋ፣ አምላክ የጋረደው፣ ጌታ የሸሸገው... ማለት ነው።

1. የኵሲ ልጅ፥ ነቢዩ፥ በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። (ሶፎ 1:1)

2. የኢዮስያስ አባት፥ ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ከሔልዳይና ከጦብያ ከዮዳኤም ውሰድ በዚያም ቀን መጥተህ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ግባ።(ዘካ 6:10)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ