ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
መሐት ~
Mahath:
‘መያዝ’
ማለት ነው።
የቀዓት ወገን፥ “የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ”
(1 ዜና 6:35)
መሃናይም ~ Mahanaim: ‘የእግዚአብሔር ሠራዊት’ ማለት
ነው። ያዕቆብ የእግዚአብሔርን መላእክት ያየበትን ስፍራ የሰየመበት፥ “ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ።
እነዚህ የእግዚአብሔር
ሠራዊት ናቸው
አለ የዚያንም
ስፍራ ስም
መሃናይም ብሎ
ጠራው።”
(ዘፍ 32:1፣2)
መሐዝዮት ~ Mahazioth: ‘ራእይ’ ማለት ነው። የኤማን ልጅ፥ “ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ፥ መታንያ ... ሆቲር፥ መሐዝዮት” (1 ዜና 25:4፣30)
መሔጣብኤል ~ Mehetabeel, Mehetabel: ማህተበ ኤል፣ ማኅተመ ኤል፣ የጌታ ማዕተብ፣ የአምላክ ቃልኪዳን ማረጋገጫ፣ የአምላክ ማህተም... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- መሄጣብኤል]
Mehetabeel- ‘ማሐተበ’
እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -
መሔጣብኤል / Mehetabeel:
ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንዳይሠራ ለማስፈራራት ጦብያና ሰንባላጥ ከላኩት፥ የድላያ አባት፥ የሸማያ ቅድመ አያት፥ መሔጣብኤል፥ (ነህ 6:10)
መሄጣብኤል / Mehetabel:
የንጉሥ ሃዳር ሚስት፥ የመጥሬድ ልጅ፥ መሔጣብኤል፥ (ዘፍ 36:39)
መሕላ ~
Mahalah: መሐላ፣ መጮህ፣ መማል፣ መጣራት፣ መዘመር... ማለት ነው። የገለዓድ
እኅት ፥
የመለኬት ልጅ፥
(1 ዜና 7:18)
“እኅቱ መለኬት
ኢሱድን፥ አቢዔዝርን፥
መሕላን ወለደች።”
መሕሤያ ~ Maaseiah: መሳያሕ፣ ምሰ ያሕ፣ ምሰ ሕያው፣ የአምላክ መድሐኒት፣ የጌታ ፈውስ፣ ሕያው መፍትሄ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
መዕሤያ]
‘መሲሕ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ስሞች የተመሠረተ ስም ነው።
.
የባሮክ እና የሠራያ አያት፥ ካህኑ የኔርያ ልጅ፥ መሕሤያ ፥ (ኤር 32:12፣ 51:59)
.
መዕሤያ-(1
ዜና 15:18፣ 20)
መለኬት ~ Hammoleketh: ምሉኪት፣
ሀማልክት፣ አማልኪት፣ መለኪት፣
ገዥ (ለሴት)
፣ ንግሥቲት፥
የምትመለክ፣ የምትገዛ... ማለት
ነው። Hammoleketh- ‘አምልኮት’
ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
የማኪር ልጅ፥ የገለዓድ እኅት ፥ መለኬት፥ (1 ዜና 7፡18)
መሉኪ ~ Melicu:
መላኩ፣ መልእክተኛ፣ አገልጋይ
ማለት ነው።‘መላክ’ ከሚለው
ቃል የተገኘ
ስም ነው።
የሜራራውያን ወገን የሆነ፥ መሉኪ፥ (ነህ 12:14)
መሉክ ~
Malluch:
መሉክ፣ ምሉክ፣ የሚመለክ፣ ገዥ፣ ንጉሥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መለኬት ፣ ሚልኪ፣ ማሎክ፣ ሜሌክ፣ ሞሎክ]
‘መለከ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከባቢሎን ግዞት ከተመለሱት መካከል፥ (ነህ 12:2፣3)
2.
የባኒ ልጅ፥
መሉክ፥ (ዕዝ 10:29)
3.
ከካሪም ወገን የሆነ፥ መሉክ፥ (ዕዝ 10:32)
4.
ካህኑ መሉክ፥
(ነህ 10:4)
5.
ከነህምያ ጋር
የቃል ኪዳኑን
ደብዳቤ ካተሙት
አንዱ፥ መሉክ፥ (ነህ
10:27)
.
የሜራራውያን ወገን የሆነ፥ ማሎክ- (1 ዜና 6:44፣45)
መላልኤል ~ Mahalaleel: መሐለ ለኤል፣ ማለ ለኤል፣ በአምላክ መማል፣ ጌታን መጥራት፣ ያምላክን ስም መጥራት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሃሌሉያ፣ ሂሌል፣ ማህለህ፣ ማህለት]
‘መሐለ’ እና ’ኤል’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የቃሉ ምንጭ ‘ሃለ’ የሚለው ግስ ሆኖ ትርጉሙም ጮኸ ፣ ተጣራ፣ ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከአዳም ጀምሮ አራተኛ ትውልድ የሆነው፥ የቃይናን ልጅ፥ መላልኤል፥
(ዘፍ 5:12-17) ፣ (1
ዜና 1:2) ፣ (ሉቃ 3:37)
2.
ከይሁዳ ወገን፣ የፋሬስ ልጅ፥ መላልኤል፥ (ነህ 11:4)
መላልኤል ~
Maleleel:
ማለ ለኤል፣ ለአምላክ ማለ፣ የአምላክን ስም ጠራ... ማለት
ነው። የቃይናን
ልጅ፥ “ቃይናንም መቶ
ሰባ ዓመት
ኖረ፥ መላልኤልንም
ወለደ”
(ዘፍ 5:12)
መላጥያ ~
Melita:
‘ማር፣ ጣፋጭ...’ ማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በጉዞው ያረፈበት፥ የሜዲትራንያን ደሴት፥ “በደኅና ከደረስን በኋላ በዚያን ጊዜ ደሴቲቱ
መላጥያ እንድትባል
ዐወቅን።” (ሐዋ 27/28:1)
መልእክተኞች ~ Ambassador: አምባሳደር፣
አምባ አሳዳሪ፣
ባለአምባራስ፣ የአምባ አስተዳዳሪ፥ የንጉሥ ተወካዮች፣ የጌታ መልክተኞች... ማለት ነው።
Ambassador- ‘አምባ’
እና ‘አሳዳር’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. ወደ ይሁዳ መልእክት ያደረሰ፥ “እርሱም፦ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ...
ከእኔ ጋር
ያለው እግዚአብሔር
እንዳያጠፋህ ይህን
በእርሱ ላይ
ከማድረግ ተመለስ
ብሎ መልእክተኞችን
ላከበት” (2 ዜና 35፡21)
. “መልእክተኞችን በባሕር ላይ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥
ከመጀመሪያው አስደንጋጭ
ወደ ሆነ
ወገን፥ ወደሚሰፍርና
ወደሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።” (ኢሳ 18:2)
. “ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በአገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት...” (2 ዜና 32:31 ፣ 2 ዜና 35:21 ፣ ኢሳ 30:4)
. “እነሆ፥ ኃይለኞቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ የሰላም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።” (ኢሳ 33:7) ፣ “እርሱ ግን ... መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ላከ።”
(ሕዝ 17:15)
. “ስለ ቲቶ ... ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።” (2 ዜና 5:20 ፣ 8:23)
መልከጼዴቅ ~ Melchisedec, Melchizedek:
የስሙ ምንጭ መንታ (ሁለት)
ሲሆን፥ ትርጉሙም ሁለት ነው። ይኽውም ‘መላክ’
እና ‘መልክ’ የሚሉት ናቸው።
‘መልክ’
እና ‘ጻድቅ’
ከሚሉ ቃላት
የተገኘው ‘መልከ ጻድቅ’ የሚለው
ስም ነው።
ትርጉሙም፡ መልከ ጼዲቅ፣ የእውነት መልክ፣ የአምላክ መልክ፣ የጌታ አምሳያ... ማለት ነው።
‘መላክ’ እና ‘ጽድቅ’ከሚሉ ቃላት የተገኘው ‘መልአከ ጽድቅ’ የሚለው ስም ነው። ትርጉሙም፡ መልአከ ጻድቅ፣ የሕያው መልአክ፣ የጽድቅ መላክተኛ... ማለት ነው።
[የጽድቅ
ንጉሥ / መቅቃ]
መልከጼዴቅ / Melchisedec: የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን፥ “...አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል።” (ዕብ 5:6)
መልከጼዴቅ / Melchizedek: አብርሃም ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን
ነገሥታት ወግቶ
ከተመለሰ በኋላ
ተቀብሎ የባረከው፥
ዐሥራትንም ከአብርሃም የተቀበለ
ንጉሥና ካህን፥
(ዘፍ 14:18-20)
መልኪኤል ~
Malchiel:
መልከ ኤል፣ የአምላክ መልክ፣ የጌታ አምሳያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መልክያ፣ ሚካኤል፣ ሚካያ፣ ሚክያስ]
‘መልክ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ወደ ግብፅ ከገቡት ከእስራኤል ልጆች ከአሴር ወገን፥ “የበሪዓ ልጅ፥ መልኪኤል፥ (ዘፍ 46:17)
መልክያ ~ Malchiah, Malchijah, Melchiah:
መልከ ያሕ፣ የሕያው መልክ፣ ሕያው አምላክ ፣ ጌታ እግዚአብሔር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
መልኪኤል፣ ሚካኤል፣ ሚካያ፣ ሚክያስ]
‘መልከ’ እና ‘ያሕ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
መልክያ / Malchiah:
1.
የጳስኮር አባት፥
መልክያ፥ (ኤር 38:1)
2.
የጕድፍ መጣያውን
በር ያደሰ፥
መልክያ፥ (ነህ 8:4)
3.
ከወርቅ አንጥረኞቹ አንዱ፥ መልክያ፥ (ነህ 3:31)
4.
የሬካብ ልጅ፥
መልክያ፥ (ነህ 3:14)
መልክያ / Malchijah:
1.
በዳዊት ዘመን፣ ለመቅደሱ አገልግሎት በዕጣ ከተመደቡ፥ መልክያ፥
(1
ዜና 24:9)
2.
በእግዚአብሔር ቤት ቁመው ከሚያመሰግኑ መካከል፥ መልክያ፥ (ነህ 12:42)
3.
የካሪም ልጅ፥
መልክያ፥ (ነህ 3:11)
መልክያ / Melchiah:
የጳስኮር
አባት፥ ካህኑ መልክያ፥ “ይህም
የሆነው ንጉሡ
ሴዴቅያስ፥ የባቢሎን ንጉሥ
ናቡከደነፆር ይወጋናልና
ስለ እኛ፥
እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል ብሎ የመልክያን ልጅ ...
ወደ ኤርምያስ በላከ
ጊዜ ነው” (ኤር 21:1)
መልጥያ ~ Melatiah: ‘ምላተ ሕያው፣ አምላክ ያድናል’ ማለት
ነው። የኢየሩሳሌምን
ቅጥር በመጠገን ከተባበሩ፥ የገባዖን ሰው፥ “በአጠገባቸውም ገባዖናዊው መልጥያና ሜሮኖታዊው
ያዶን... የምጽጳ
ሰዎች አደሱ።” (ነህ 3:7)
መሎቲ ~ Mallothi: ሙላት፣ ሙላት፣ ሙሉነት፣
ሙሉ መሆን... ማለት
ነው። ከኤማን ልጆች አንዱ፥ “ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ ...ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥
ሆቲር፥ መሐዝዮት” (1 ዜና 25:4፣26)
መምሬ ~ Mamre: መመሪ፣ መምሬ፣ መምህር፣ መሪ፣ አስተማሪ... ማለት ነው።
‘መራ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው። አብርሃም በኬብሮን ያረፈበት የቦታ ስም፥ (ዘፍ 14:13፣ 24)
መሢሕ ~ Messiah, Messias: መሣያሕ፣ መሲህ፣
ምስ፣ ምሳ፣
መፍትሄ፣ መድሐኒት... ማለት ነው። [‘የተቀባ ማለት ነው።’ ተብሎም ይተረጎማል] ‘ምስ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
መሢሕ / Messiah:
‘መሢሕ’ የሚለው መጠሪያ በኦሪትና በነቢያት ዘመን ይታወቅ ነበር፥ “ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት
ትእዛዙ ከሚወጣበት
ጀምሮ እስከ
አለቃው እስከ
መሢሕ ድረስ
ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል ...” (ዳን 9:25) ፣ “ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና
መቅደሱን ያጠፋሉ
...” (ዳን 9:26)
መሢሕ / Messias: ሐዋርያው
እንድርያስ ጌታ ኢየሱስን የጠራበት ስም፥ “እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና። መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው” (ዮሐ 1:41፣ 42)
መስመና ~ Mishmanna:
‘መድለብ፣መወፈር’ ማለት
ነው። ያንበሳ
ፊት ከነበራቸውና
ከዳዊት ሠራዊት
ጋር ከተቀላቀሉ፥
ጋዳውያን አራተኛው፥ “ሦስተኛው
ኤልያብ፥ አራተኛው
መስመና፥”
(1 ዜና 12:10)
መሥሬቃ ~ Masrekah: ምሥራቅ፣ የፀሓይ መውጫ... ማለት ነው። የኤዶምዓዊው፥ የሠምላ አገር፥
“ሃዳድም ሞተ፥ በስፍራውም
የመሥሬቃው ሠምላ
ነገሠ”
(ዘፍ 36:36፤ 1 ዜና 1:47)
መስኩ ~ Meadow:
[ሜዳ ~
Meadow የሚለውን ቃል
ይመልከቱ]
ፈርዖን በአየው ሕልም፥ በውኃ ዳር ላሞች የሚሰማሩበት፥ (ዘፍ 41:2)
መስጴጦምያ~ Mesopotamia: ‘በወንዞች መካከል
ያለ አገር’ ማለት
ነው። በሁለቱ
ወንዞች-
ኤፍራጥስ እና
ጤግሮስ - መካከል የነበረ
አገር፥ “...ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ ተነሥቶም ወደ መስጴጦምያ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ” (ዘፍ 24:10፤ ዘዳ 23:4፤ መሣ 3:8፣10)
መሪሳ ~ Mareshah:
መርሻ፣ ምትክ... ማለት
ነው። በደልዳላው
የይሁዳ ግዛት
የነበረ ከተማ፥
“ኢትዮጵያዊውም ዝሪ
አንድ ሚሊዮን
ሰዎችና ሦስት
መቶ ሰረገሎች
ይዞ ወጣባቸው
ወደ መሪሳም መጣ።”
(2 ዜና 14:9፣10)
መሪባ ~
Meribah:
መሪአባ፣ መሪ አባ፣ ፊተኛ አባት፣ የቀደሙ አባቶች... ማለት ነው።
(ክርክር ተብሎም ይተረጎማል።)
“ስለ እስራኤልም
ልጆች ክርክር። እግዚአብሔር
በመካከላችን ነውን
ወይስ አይደለም?
ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።”
(ዘጸ 17:7)
መራዮት ~
Meraioth:
ምሬት፣ መኮምጠጥ፣ መማረር፣ መከፋት፣ ማመጽ... ማለት ነው።
1.
የማርያ አባት፥
ከኤልዛር ወገን
የሆነ ካህን፥
(1 ዜና 6:6፣7፣52)
2.
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ “ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥” (ነህ 12:15)
መርመሲማ ~ Parmashta: ‘የበላይ’
ማለት ነው።
የሐመዳቱን ልጅ
የአይሁድን ጠላት፣ የሐማን ልጅ፥ “በርያ፥ ሰርባካ፥ መርመሲማ፥ ሩፋዮስ፥ አርሳዮስ፥ ዛቡታዮስ
የሚባሉትን፥”
(አስ 9:9)
መርዓላ ~
Maralah: ‘መወዝወዝ፣ መነቅነቅ’ ማለት
ነው። በዛብሎን
ነገድ ድንበር
ያለ፥ ጉልህ
ስፍራ፥ “ድንበራቸውም በምዕራብ
በኩል ወደ
መርዓላ ወጣ፥
እስከ ደባሼትም
ደረሰ በዮቅንዓም
ፊት ለፊት
ወዳለው ወንዝ
ደረሰ”
(ኢያ 19:11)
መርዶክዮስ ~ Mordecai: መርዶ፣
ሐዘንተኛ... ማለት ነው። ከብንያም
ነገድ፥ የኢያዕር
ልጅ፥ “አንድ አይሁዳዊ
የቂስ ልጅ
የሰሜኢ ልጅ
የኢያዕር ልጅ
መርዶክዮስ የሚባል ብንያማዊ በሱሳ ግንብ ነበረ” (አስ 2:5)
መሮዳክ ባልዳን ~ Berodach-baladan, Merodach-baladan: ሜሮዳክ ይፈርዳል ማለት ነው። የባቢሎን ንጉሥ፥ ወደ ሕዝቅያስ የእርቅ መልእክት የላከ፥ “በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት” (ኢሳ 39:1)
መቄዳ ~
Makkedah:
መከዳ፣ ማክዳ፣ መከታ፣ ግንብ፣ አጥር ማለት... ነው። የአገር
ስም፥ “የመቄዳ ንጉሥ፥
የቤቴል ንጉሥ” (ኢያ
12:16)
መቄዶንያ ~ Macedonia: ‘ትርፍ መሬት’ ማለት
ነው። በግሪክ
በስተሰሜን የነበረ በሮማውያን የሚተዳደር አገር፥ ጳውሎስ ባየው ራእይ፥ አንድ ሰው ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ያየበት፥ “ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው። ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር” (ሐዋ
16:9)
መቅሄሎት~ Makheloth:
‘ጉባኤ፣
ማኅበር’ ማለት
ነው። እስራኤላውያን ከግብፅ
ሲወጡ ካረፉባቸው
ስፍራዎች፥ “ከመቅሄሎትም ተጕዘው
በታሐት ሰፈሩ”
(ዘኊ 33:26)
መቅደሱ ከፍታ ~ Heaven: ሒዋን፣
ሕያዋን፣ የሕያው
ቦታ፣ የዘላለማውያን
ማረፊያ... ማለት ነው።
[ተለዋጭ ስሞች-
ሰማይ፣ ቅዱስ
ማደሪያ]
Heaven- ‘ሕያዋን’ ከሚለው
ቃል የመጣ
ስም ነው።
. ከፍተኛ
ቦታ፥ “...እግዚአብሔር
በላይ ሆኖ
ይጮኻል፥ በቅዱስ
ማደሪያውም ሆኖ
ድምፁን ያሰማል
በበረቱ ላይ
እጅግ ... ይጮኻል።”
(ኤር 25:30)፣ ከፍተኛ
ቦታ፥ “እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ
ሆኖ ምድርን
አይቶአልና፥” ( መዝ
102:19)፥ ከፍ
ባለው በእስራኤል
ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል ... በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል” (ሕዝ
17:23)
መብል ~
Mess:
ምሳ፣ ምስ፣ ምስሕ፣ ምግብ፣ ቀለብ... ማለት ነው።
Mess-
‘ምሳ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ነው።
የያቆብ ልጆች በግብፅ አገር በወንድማቸው በዮሴፍ ሲጋበዙ፥ “በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያምም
ፈንታ ከሁሉ
አምስት...”
(ዘፍ 43:34) ፣ (2 ሳሙ11:8)
መብሳም ~ Mibsam:
‘መልካም ጠረን፣ ጥሩ ሽታ፣ ሽቶ’ ማለት ነው።
1.
የእስማኤል ልጅ፥ (ዘፍ 25:14፤ 1 ዜና 1:29) “ነባዮት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥
መብሳም፥ ማስማዕ፥”
2.
የስምዖን ልጅ፥ (1
ዜና 4:25) “ልጁ ሰሎም፥ ልጁ መብሳም፥ ልጁ ማስማዕ”
መና ~ Manna:
ምን፣ ምነ፣
ምነው፣ ምንድን
ነው?
ማለት ነው።
‘ምን’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
ከግብፅ ከወጡ በኋላ የእስራኤላውያን ምግብ፥ እስራኤላውያን ያወጡለት ስም፥ “የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደ ሆነ አላወቁምና እርስ በእርሳቸው፤ ይህ ምንድር
ነው? ተባባሉ።
ሙሴም፦ ትበሉት
ዘንድ እግዚአብሔር
የሰጣችሁ እንጀራ
ነው። የእስራኤልም
ወገን ስሙን
መና ብለው
...” (ዘጸ 16:15)
መናሐት ~ Manahath: ምን
አጣ፣ ሁሉን
ያገኘ፣ የሁሉ
ጌታ... ማለት ነው። ‘ምን’
እና ’አጣ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የቦታ ስም፥
(1 ዜና 8:6፣7)
መዓሳል ~
Mashal:
መሳል፣ መጠየቅ፣ መዋዋል... ማለት ነው። (1 ዜና 6:74) “ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰምርያዋ፥ ዓብዶንና መሰምርያዋ”
መዓራ ~ Mearah: ‘ዋሻ’
ማለት ነው።
የቦታ ስም፥
(ኢያ 13:4)
“በደቡብም በኩል የኤዋውያን፥ የከነዓናውያን ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥”
መዓካ ~ Maachah:
መቅ፣ ማመቅ፣ ወደታች መጫን... ማለት ነው።
1.
በሶርያ ግዛት
ስር የነበረ
አገር፥ “የአሞን ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደተጠሉ ባዩ ጊዜ ... ከመዓካ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎች፥ ከጦብም አሥራ ሁለት ሺህ
ሰዎች ቀጠሩ።” (2 ሳሙ
10:6፣8፤ 1 ዜና 19:7)
2.
የጌሹር ንጉሥ፣ የተልማይ ልጅ፥ “... ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ” (2 ሳሙ 3:3)
3.
ከሠላሳዎች የንጉሥ ዳዊት ዘበኞች የአንዱ፣ የሐናን አባት፥ ማዕካ፥ “ከእርሱም ጋር
ሠላሳ ሰዎች
ነበሩ፥ የማዕካ ልጅ ሐናን፥ ሚትናዊው
ኢዮሣፍጥ፥”
(1 ዜና 11:43)
4.
የአቢሰሎም ልጅ፥
የንጉሥ አቢያ
እናት፥ ሚካያ፥ “ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ...” (2 ዜና 13:2)
5.
የጌት ንጉሥ፥ የአንኩስ አባት፥ “ከሦስት ዓመትም በኋላ ከሳሚ ባሪያዎች
ሁለቱ ወደ
ጌት ንጉሥ ወደ
መዓካ ልጅ
ወደ አንኩስ
...” (1 ነገ 2:39)
መዓይ ~
Maai:
‘ርኅሩኅ’
ማለት ነው። በኢየሩሳሌም ቅጥር እደሳ ወቅት፥ በዜማ አገልግሎት ከተሳተፋ፥ (ነህ 12:36) “ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።”
መዓድያ ~ Maadiah: ማዕደ
ያሕ፣ ሕያው
ምግብ...
ማለት ነው።
ከምርኮ ከተመለሱ
ካህናት አንዱ፥
“መዓድያ፥ ቢልጋ፥
ሸማያ፥ ዮያሪብ፥
ዮዳኤ”
(ነህ 12:6)
መዕሣይ ~ Maasiai:
መሳያ፣ ምሢህ፣ ምስ፣
ምሳ፣ መድኃኒት፣ መፍትሔ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መዕሤያ፣ መሕሤያ]
‘ምስ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ መካከል በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ፣ ካህኑ የዓዲኤል ልጅ፥
መዕሣይ፥ (1 ዜና 9:12)
መዕሤያ ~
Maaseiah:
መሲ ያሕ፣ መሳያሕ፣ የአምላክ መድኃኒት፣ የጌታ መፍትሄ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሕሤያ፣ መዕሣይ]
‘መሢሕ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉት ሁለት ስሞች ተጣምሮ የተመሠረተ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.በንጉሥ ዳዊት ትእዛዝ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ከነበሩ፥ ከሌዋውያን
በሁለተኛ ተራ
የሆነው፥ መዕሤያ፥
(1 ዜና 15:18፣ 20)
2.
የካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ፣ የኢያሱ ልጅ፥ በግዞት ሲኖሩ፣ የሌላ አገር ሴቶችን ካገቡ የእስራኤል ካህናት አንዱ፥ መዕሤያ፥ (ዕዝ 10:18)
3.
ካህኑ የካሪም
ልጅ፥ (ዕዝ 10:21)
4.
ካህኑ የፋስኩር
ልጅ፥ መዕሤያ፥
(ዕዝ 10:22)
5.
የፈሐት ሞዓብ
ልጅ፥ መዕሤያ፥
(ዕዝ 10:30)
6.
የዓዛርያስ አባት፣
የሐናንያ ልጅ፥
መዕሤያ፥ (ነህ3:23)
7.
ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ሲያነብ በጎኑ ከቆሙት አንዱ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 8:4)
8.
ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ሲያነብ በጎኑ ከቆሙት አንዱ ሌዊያዊ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 8:7)
9.
ከነህምያ ጋር
ቃል ኪዳን
ከተፈራረሙት ወገን
አንዱ፥ (ነህ 10:25፣ 26-27)
10.
የባሮክ ልጅ
መዕሤያ፥ (ነህ 11:5)
11.
የብንያም ወገን፣ የቆላያ አባት፥ የኢቲኤል ልጅ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 11:7)
12.
ሌሎች ሁለት ካህናት በዚህ ስም ይታወቃሉ፥ “ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥” ፥ “ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር ... ኤጽር ቆምን፦ መዘምራኑም ...” (ነህ 12:41 ፣ 42) 13. በነቢዩ ኤርምያስ የተጠቀሰ፣ የሴዴቅያስ አባት፥ ሐሰተኛ ነቢይ፥ (ኤር 29:21)
14.
በዮዳሄ ንግሥና ዘመን የመቶ አለቃ የነበረው፥ የዓዳያን ልጅ፥ (2 ዜና
23:1)
15.
በዖዝያ ንግሥና ዘመን አለቃ የነበረ፥ መዕሤያ፥ (2 ዜና 26:11)
16.
በአካዝ ንግሥና ዘመን፥ የንጉሡ ልጅ፣ በዝክሪ የተገደለ፥ መዕሤያ፥
(2
ዜና 28:7)
17.
የኢየሩሳሌም አለቃ የነበረ፥ መዕሤያ፥ (2 ዜና 34:8)
18. በኢዮቄም ንግሥና ዘመን አለቃ የነበረ ሌዊያዊው የሰሎም ልጅ፥ (ኤር 35:4)
ካህኑ የኔርያ ልጅ፥ መሕሤያ፥ (ኤር 32:12፣ 51:59)
መዕዳይ ~ Maadai: ማዕድ፣
ምግብ... ማለት ነው።
ከምርኮ ከተመለሱ፥
እንግዳ ሚስቶችን
ካገቡ፥ (ዕዝ 10:34) “ከባኒ ልጆችም፤
መዕዳይ፥ ዓምራም፥”
መክቢና ~
Machbenah: ‘መሐላ’
ማለት ነው።
በይሁዳ የዘር
ሐረግ፥ የሱሳን
ልጅ፥ “ደግሞም የመድማናን
አባት ሸዓፍንና
የመክቢናንና የጊብዓን
አባት ሱሳን ወለደች የካሌብም ሴት ልጅ ዓክሳ ነበረች” (1 ዜና 2:49)
መክነድባይ ~ Machnadebai:
‘መቀንደቢያ’ ማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ በዕዝራ ትእዛዝ እንግዳ ሚስቶቻቸውን ከፈቱ፥ የባኒ ልጅ፥ “ሰሌምያ፥ ናታን፥
ዓዳያ፥ መክነድባይ” (ዕዝ 10:40)
መጊዶ ~ Megiddo:
‘መናገሻ’ ማለት ነው። “የአዚፍ ንጉሥ፥
የታዕናክ ንጉሥ፥
የመጊዶ ንጉሥ” (ኢያ 12:21)
መጋቢዎች ~
Sheriffs:
ሸሪፍ፣ ሸራፊ፣ ቀራጭ፣ ግብር ሰብሳቢ... ማለት ነው።
Sheriff-
‘ሸረፈ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም
ነው። ለባቢሎን መንግሥት ግብር ሰብሳቢ የነበሩ፥ (ዳን 3:2)
መጌብስ ~ Magbish: ‘ምእመናን’
ማለት ነው።
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ የመጌብስ
ልጆች ይገኙበታል፥
“የመጌብስ
ልጆች፥ መቶ
አምሳ ስድስት”
(ዕዝ 2:30)
መጌዶል ~ Magdala: ገድል፣ ታላቅ ሥራ... ማለት
ነው። በጌልገላ
የነበረ የከተማ ስም፥ “ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ” (ማቴ 15:39)
መጌዶን ~
Migron:
አፋፍ፣ ገደል... ማለት ነው። “ወደ አንጋይ መጥቶአል፤ በመጌዶን
በኩል አልፎአል፤ በማክማስ
ውስጥ ዕቃውን
አኑሮአል”
(ኢሳ 10:28)
መግደላዊት ~ Magdalene: መቅደላዊት
ማለት ነው።
የሌላዋ ማሪያም
መለያ፥ ያገር
ስም፥ “ከእነርሱም መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብና የዮሳ
እናት ማርያም
የዘብዴዎስም የልጆቹ
እናት ነበሩ” (ማቴ
27:56፣61፥ 28:1)
መግዲኤል ~ Magdiel: መግደለ
ኤል፣ ያምላክ
ሥራ፣ የአምላክ
ገድል... ማለት ነው።
ከኢሳው ወገን፥
ከኤዶም አለቆች፥
“መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም
አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም ...” (ዘፍ 36:43፤ 1 ዜና 1:54)
መግጲዓስ ~ Magpiash: ‘መጋፊያ’
ማለት ነው።
የቃል ኪዳኑን
ደብዳቤ ከፈረሙት አንዱ፥
“ሐሪፍ፥ ዓናቶት፥ ኖባይ፥
መግጲዓስ፥ ሜሱላም” (ነህ
10:20)
መጥሬድ ~ Matred: ‘የንጉሥ በትር’
ማለት ነው።
የመሄጣብኤል እናት፥
“...በስፍራውም ሃዳር
ነገሠ፤ የከተማውም ስም
ፋዑ ነው፤ ሚስቱም
የሜዛሃብ ልጅ
መጥሬድ የወለደቻት
መሄጣብኤል ትባላለች” (ዘፍ
36:39፤ 1
ዜና 1:50)\
መጽሐፈ መክብብ ~ Ecclesiastes: ‘ስብከት’
ማለት ነው።
መፍራት ~
Fear:
ፈሪ፣ ፈራ፣ ፍራት፣ ጭንቀት፣ ጥንቃቄ... ማለት ነው።
ፈሪሃ እግዚአብሔር፥ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሰነፎች ...”
(ምሳ 1፡7) ፣ (ኢዮ 28:28 ፣ መዝ 19:9)
ሙሲ ~ Mushi:
መዋሴ፣ ዋሴ፣ አዳኜ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ሙሴ]
‘ዋሰ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው። የሜራሪ ልጅ፥ ሙሲ፥ (ዘጸ 6:19) ፣ (ዘኁ 3:20)
ሙሴ ~
Moses:
መዋሴ፣ ዋስ መሆን፣ ከችግር ማዳን፣ ከግዞት፥ ከእስራት ነጻ ማውጣት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም - ሙሲ]
‘ዋሰ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
ሊቀ ነቢያት
ሙሴ፥ “ሕፃኑም አደገ፥
ወደ ፈርዖንም
ልጅ ዘንድ
አመጣችው፥ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው።” (ዘጸ
2፡10) ፣ (ሥራ 7:22)
ሙራ ~ Myra: በታናሽቷ
እስያ፥ በሉቅያ
ያለ ዋና
ከተማ፥ “በኪልቅያና በጵንፍልያም አጠገብ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላ በሉቅያ ወዳለ ወደ ሙራ ደረስን”
(ሐዋ 27:5)
ሚላላይ ~ Milalai: ማላሊ፣
ተጣሪ፣ እልል ባይ፣ ተደማጭ...
ማለት ነው።
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ የኢያሩሳሌምን
ቅጥር በመጠገን
ከተባበሩ አንዱ፥
“ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥
ሚላላይ፥ ጊላላይ
... ጸሐፊውም ዕዝራ
በፊታቸው ነበረ።” (ነህ
12:36)
ሚልኪ ~
Melchi:
መላኬ፣ መሉኬ፣ ጌታዬ፣ አምላኬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሉኪ፣ መሉክ፣ ማሎክ፣ ሜሌክ፣ ሞሎክ]
‘መለከ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የሐዲ ልጅ፥ ሚልኪ፥ (ሉቃ 3:28)
ሚልኪሳ ~
Malchi-shua:
መልአከ ሽዋ፣ ሺህ መለክ፣ የብዙዎች አምላክ፣ የብዙ
ሕዝብ ንጉሥ... ማለት ነው።
Malchi-shua- ‘መለከ’ እና ‘ሽዋ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የንጉሥ ሳኦል ልጅ፥ ሚልኪሳ፥ (1
ዜና 8:33)
ሚልካ ~
Milcah:
ምሉክ፣ ገዥ፣ ንግሥት... ማለት ነው።
1.
የሐራን ልጅ፥ የናኮር ሚስት፥ “...የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።”
(ዘፍ 11:29፥22:20፣23፥ 24:15፣24፣47)
2.
የኦፌር ልጅ፣
የሰለጰዓድ አራተኛ
ልጅ፥ “የኦፌርም ልጅ ... የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። (ዘኊ 26:33፥27:1፥36:11፤ ኢያ 17:3)
ሚልክያስ ~
Malachi:
መልአከ ዋስ፣ መልአክ፣ ምስክር፣ መልእከተኛ፣ አገልጋይ... ማለት ነው።
‘መልአክ’ እና ‘ዋስ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[መልክተኞች /
መቅቃ]
ከደቂቅ ነቢያት አንዱ፥ ነቢዩ ሚልክያስ፥ (ሚል 1:1-5)
ሚልኮም ~ Malcam, Malcham, Milcom:
ምልካም፣ መልከዓም፥ አምላኪ፣ አምልኮት ያለው፣ አምላክ ያለው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማልካም፣ ሞሎክ]
ሚልኮም / Malcam: “... ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ስለ ምን ሚልኮም ጋድን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ?”(ኤር 49:1)
ሚልኮም / Malcham: በሶፎንያስ የተጠቀሰው፥ የጣዖት ስም“...በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን” (ሶፎ 1:5)
. የሸሐራይ
ልጅ፥ ማልካም፥
(1 ዜና 8:9፣10)
ሚልኮም / Milcom: ንጉሥ ሰሎሞን የሳተበት የጣዖት ስም፥ (1
ነገ 11:5)
ሚሎ ~
Millo:
ሚሉ፣ ሙሉ ፣ ያልጉደለ... ማለት ነው።
“ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት።” (2 ሳሙ 5:9)
ቤተሚሎ- (መሣ 9:6)
ሚሳቅ ~ Meshach:
‘የክብር እንግዳ’
ማለት ነው።
ለሚሳኤል የተሰጠው
መጠሪያ፥ “የጃንደረቦቹም አለቃ
... ዳንኤልን ብልጣሶር፥
አናንያንም ሲድራቅ፥
ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥
አዛርያንም አብደናጎ
ብሎ ጠራቸው” (ዳን
1:7 ፥2:49)
ሚሳኤል ~
Mishael:
ሚሸል፣ ምስለ ኤል፣ ምስለ ኃያል፣ አምላክን የመሰለ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስም-
ሚሽአል]
‘መልከ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተገኘ ስም
ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የሙሴ እና የአሮን ወገን የሆነ የዑዝኤል ልጅ፥ ሚሳኤል፥ (ዘፍ 6:22)
2.
ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ሲያነብ በአጠገቡ ከቆሙት፥ ሚሳኤል፥ (ነህ
8:4)
3.
ወደ ባቢሎን ከተወሰዱ የእስራኤል ልጆች፥ ሚሳኤል፥ (ዳን 1:6)
ሚስያ ~ Mysia: ‘መማሰን፣ መላወስ፣
መዛቀጥ’ ማለት ነው።
ጳውሎስ በሐዋርያዊው ጉዞ ካለፋባቸው ቦታዎች፥ “በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ
ዘንድ ሞከሩ...” (ሐዋ 16:7፣8)
ሚሻም ~ Misham: ‘ማንጻት’
ማለት ነው።
ብንያማዊ፥ የብንያማዊው የኤልፍዓል
ልጅ፥ “የኤልፍዓልም ልጆች
ዔቤር፥ ሚሻም፥
ኦኖንና ሎድን
መንደሮቻቸውንም የሠራ
ሻሚድ”
(1 ዜና 8:12)
ሚሽአል ~ Mishal: መሳል፣መጠየቅ፣ መደራደር... ማለት ነው። የቦታ ስም
… [ተዛማጅ ስም-
ሚሳኤል]
ከአሴር ርስት
የአንደኛው ከተማ
ስም፥ ሚሽአል፥
(ኢያ 19:26)
ሚብሐር ~ Mibhar:
‘ምርጥ’ ማለት
ነው። ከዳዊት
ኃያላን አንዱ፥
የሐግሪ ልጅ፥ “የናታንም ወንድም ኢዮኤል፥ የሐግሪ ልጅ ሚብሐር፥” (1 ዜና 11:38)
ሚብሳር ~ Mibzar: ‘መከልከያ፣ ምሽግ’
ማለት ነው። ኤዶማዊው አለቃ፥ የዔሳው
ወገን፥ “ቄኔዝ አለቃ፥
ቴማን አለቃ፥
ሚብሳር አለቃ፥” (ዘፍ
36:42፤ 1
ዜና 1:53)
ሚትሪዳጡ ~ Mithredath: ‘ሕግ መጣስ’ ማለት ነው።
1.
የፋርስ ንጉሥ የቂሮስ መዝገብ ቤት ሐላፊ፥ “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስም በመዝገቡ ላይ በነበረው በሚትሪዳጡ እጅ አወጣቸው፥ ለይሁዳም መስፍን ለሰሳብሳር
ቈጠራቸው።”
(ዕዝ 1:8)
2.
በሰማርያ ኃላፊ
የነበረ፥ “በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ ደብዳቤውም በሶርያ ፊደልና በሶርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።” (ዕዝ 4:7)
ሚትቃ ~ Mithcah: ‘ጣፋጭ’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን ወደ
ቃል ኪዳን አገር ባደረጉት ጉዞ ካረፋባቸው ቦታዎች አንዱ፥ “ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ” (ዘኊ 33:28፣29)
ሚኒ ~ Minni: ‘መክፈል’
ማለት ነው።
የአርመን ክፍል የሆነ የቦታ
ስም፥ “... የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት አለቃንም በላይዋ አቁሙ፤ እንደ ጠጕራም ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ” (ኤር 51:27)
ሚኒት ~ Minnith: ‘ማከፋፈል’
ማለት ነው።
በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ
የሚገኝ ቦታ፥ “ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሀያ ከተሞችን በታላቅ
አገዳደል መታቸው...”
(መሣ 11:33)
ሚንያሚን ~ Miamin, Miniamin: ምን ያምን፣ የታመነ፣ ቀኝ
እጅ... ማለት ነው።
1.
በሕዝቄል ዘመን የነበረ፥ ሌዊያዊ፥ “በካህናቱም ... ይሰጡ ዘንድ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ ከእጁ በታች ነበሩ።” (2 ዜና
31:15)
2.
የኢየሩሳሌምን ቅጥር
በመጠገን ከተባበሩ ካህናት አንዱ፥ ሚያሚን፥ “ከአብያ ዚክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥” (ነህ 12:17)
ሚካ ~
Micah, Micha: ሚካ፣ ሚልካ፣ መልክ፣ ውበት፣ ቁንጅና... ማለት ነው። ምንጩ
‘መልከ’ የሚለው ቃል ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በዚህ
ስም የሚታወቁ
ሰዎች:-
1.
የመሪበኣል ልጅ፥ ሚካ፥ (1 ዜና 8:34፣ 35)
2.
የተራራማው የኤፍሬማዊ አገር ሰው፥ ሚካ፥ (መሣ 18፣ 19:1-29፣
21:25)
3.
የዑዝኤል ልጆች
አለቃ ሚካ፥
(1 ዜና 23:20)
4.
የኢዮኤል ልጅ፥ ሚካ፥ “ልጁ ጎግ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ሚካ፥” (1 ዜና
5:5)
ሚካ /
Micha: መልክ ማለት ነው።
1.
የሜምፊቦስቴም ልጅ፥
“ለሜምፊቦስቴም ሚካ የተባለ ታናሽ ልጅ
ነበረው...” (2 ሳሙ 9:12)
2.
የቃል ኪዳኑን
ደብዳቤ በማተም
ከተባበሩ፥ “ፌልያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥
ረአብ፥ ሐሸብያ፥” (ነህ 10:11)
3.
የዘብዲ ልጅ፥
“በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ...” (ነህ 11:17፣22)
ሚካኤል ~ Michael: የአምላክ
መልክ እና
የአምላክ መልእከተኛ የሚሉ
መንታ ትርጉሞች አሉት። [ተዛማጅ ስሞች- መልኪኤል፣ መልክያ፣ ሚካያ፣ ሚክያስ] ‘መልከ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ሲሆን ትርጉሙ
‘መልከ ኤል’
ሁኖ፥ አምላክን
የመሰለ... ማለት ነው።
‘መልአከ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ሲሆን፥ ትርጉሙ ‘መልአከ ኤል’
ሆኖ፣ የጌታ መልአክ፣ የአምላክ
መልእከተኛ፣ የእግዚአብሔር
አገልጋይ... ማለት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ አሥር ሰዎች እና አንድ መልአክ አሉ።
1.
የሰቱር አባት፥ ሚካኤል ፥ “ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር”
(ዘኁ13፡13)
2.
ከጋድ ወገን፥
በባሳን ምድር
ከተቀመጡ፥ ሚካኤል፥
(1 ዜና 5:13)
3.
የኢዬሳይ ልጅ፥
ሚካኤል፥ (1 ዜና 5:14)
4.
የሳምዓ ልጅ፥
ሚካኤል፥ (1 ዜና 6:40)
5.
የይዝረሕያ ልጅ፥
ሚካኤል፥ (1 ዜና 7:3)
6.
የብንያማዊው የበሪዓ
ልጅ፥ ሚካኤል፥
(1 ዜና 8:16)
7.
ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከከዱ፥ ሚካኤል፥ (1
ዜና 12:20)
8.
የዖምሪ አባት፥
ሚካኤል፥ (1 ዜና 27:18)
9.
የኢዮሣፍጥ ልጅ፥
ሚካኤል፥ (2 ዜና 21:2,4)
10.
የሰፋጥያስ ልጅ፥
ሚካኤል፥ (ዕዝ 8:8)
11.
ከዋነኞቹ አለቆች
አንዱ፥ ሚካኤል፥
“የፋርስ መንግሥት አለቃ
ግን ሀያ
አንድ ቀን ተቋቋመኝ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ...።”
(ዳን 10፡13)፣ የመላእክት አለቃ፥ (ይሁዳ 1:9)
ሚካያ ~ Michaiah:
... [‘ሚካኤል /Michael’-
ከሚለው ስም ጋር አንድ አይነት ትርጉም አለው] … [ተዛማጅ ስሞች- መልኪኤል፣ መልክያ፣ ሚካኤል፣ ሚክያስ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የይሁዳ ንጉሥ የአብያ እናት ሁና፣ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ፥ ሚካያ፥
(2
ዜና 13:2)
2.
ሌዋዊው የዘኩር ልጅ፥ ሚካያ፥ (ነህ 12:35)
3.
የኢየሩሳሌምን ቅጥር ለመጠገን ቆርጠው ከተነሡ ካህናት አንዱ፥ ሚካያ፥
(ነህ 12:41)
ሚክምታት ~
Michmethah:
መች መታ፣ ምች፣ መች መታህ... ማለት ነው።
‘መች’ እና ‘መታ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የምናሴ ድንበር መጨረሻ፥ የቦታ ስም፥ (ኢያ 17:7)
ሚክሪ ~
Michri:
ምክሪ፣ ምክር፣ ተግሣጽ፣ ትምህርት፣ ቃለ እግዚአብሔር... ማለት ነው። ‘መከረ’ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
ብንያማዊው የኦዚ አባት፥ ሚክሪ፥ (1ዜና 9:8)
ሚክያስ ~ Micaiah, Michaiah:
ሚካ ያሕ፣
መልከ ሕያው፣
መልከ ዋስ፣
የአምላክ አምሳያ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መልኪኤል፣ መልክያ፣
ሚካኤል፣ ሚካያ]
Michaiah- ‘መልከ’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ ፣ ሕያው፣ ዋስ) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
[እንደ እግዚአብሔር
ያለ ማነው
/ መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ሚክያስ /
Micaiah:
የይምላ ልጅ፣ ነቢዩ ሚክያስ፥ (1
ነገ 22:8-28)
ሚክያስ / Michaiah:
1.ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ያስተምሩ ዘንድ፣ ከላካቸው መሳፍንት፥
ሚክያስ፥ (2 ዜና 17:7)
2.
“ንጉሡም ካህኑን
ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን።”
(2 ነገ 22:12)
3.
የገማርያ ልጅ፥
ሚክያስ፥ (ኤር 36:11፣13)
ሚዛህ ~ Mizzah: ‘ፍርሃት’
ማለት ነው።
የራጉኤል ልጅ፥
“የራጉኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች
ናቸው።”
(ዘፍ 36:13፣17፤ 1 ዜና 1:37)
ሚያሚን ~
Miamin, Mijamin: መያምን፣ ማመን፣ የሚያምን፣ የሚታመን፣ታማኝ፣ ቀኝ እጅ... ማለት ነው።
1.
ከግዞት ከተመለሱ እስራኤላውያን፥ በዕዝራ ትእዛዝ እንግዳ ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ ከተደረጉ አንዱ፥ “ከእስራኤልም ከፋሮስ ልጆች፤ ራምያ፥ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያ፥ በናያስ።” (ዕዝ 10:25)
2.
ከዘሩባቢሎን ጋር ከምርኮ ከተመለሱ፥ “አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን” (ነህ 12:5)
ሚያሚን ~ Mijamin: ሚያምን፣ እሚታመን... ማለት ነው።
1.
በዳዊት ከተመሠረቱት የ ሃያ አራት ካህናት ምድብ፥ የስድስተኛው
ተራ አለቃ፥
(1 ዜና 24:10)
“ስድስተኛው ለሚያሚን፥ ሰባተኛው ለአቆስ፥”
2.
(ነህ 10:7) “ሜሱላም፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቤልጋል፥ ሸማያ
እነዚህ ካህናት ነበሩ።”
ሚዲን ~ Middin:
መዳኝ፣ መዳኛ፣ ዳኝነት የሚካሄድበት፣ ፍትሕ የሰፈነበት ቦታ... ማለት ነው።
‘ዳኘ’ ከሚለው ግስ የተገኘ የቦታ ስም ነው።
በመጽሐፈ ኢያሱ ከተጠቀሱትና እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ካለፉባቸው ስድስት
ከተሞች አንዱ፥
(ኢያ 15:61)
ሚግዳልኤል ~ Migdalel:
መግደለ ኤል፣ ያምላክ ገደል፣ የአምላክ ማማ... ማለት
ነው። በንፍታሌም ከተያዙ
ምሽጎች አንዱ፥
(ኢያ 19:38)
“ቃዴስ፥ ኤድራይ፥
ዓይንሐጾር፥ ይርኦን፥
ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥
ቤትዓናት፥ ቤትሳሚስ
አሥራ ዘጠኝ
ከተሞችና መንደሮቻቸው”
ሚግዳልጋድ~ Migdalgad: መግደለ ጋድ፣ ገደለ ጋድ፣ የገድ ማማ... ማለት ነው። የይሁዳ ከተማ፥
“ጽናን፥ ሐዳሻ፥
ሚግዳልጋድ፥ ዲልዓን፥” (ኢያ 15:37)
ሚግዶል ~ Migdol:
ማማ ማለት ነው።
1.
በሰሜን ግብፅ የነበረ፥ ጠንካራ ምሽግ፥ “በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው” (ኤር 44:1፥ 46:14)
2.
“ተመልሰው በሚግዶልና በባሕር መካከል፥ በበኣልዛፎንም ፊት ለፊት ባለው
በፊሀሒሮት ፊት
እንዲሰፍሩ ለእስራኤል
ልጆች ተናገር
ከእርሱም አጠገብ በባሕር ዳር ትሰፍራላችሁ።” (ዘፍ 14:2፤ ዘኊ 33:7፣8)
ሚጢሊን ~ Mitylene:
‘ቁስለኛ፣ አካሉ የጎደለ’ ማለት ነው። ጳውሎስ
ከቆሮንቶስ ወደ ይሁዳ ባደረገው
ሐዋርያዊ ጉዞ
ከአስተማረባቸው አንዱ፥
የደሴት ዋና
ከተማ፥ “...በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን።” (ሐዋ 20:14)
ማህለህ ~
Mahlah:
ማሃላህ፣ መሐላ፣ መማል፣ መጮህ፣ በአምላክ ስም ቃል መግባት፣ ጌታን መጥራት... ማለት ነው።
‘መሃላ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የቃሉ ምንጭ ‘ሃለ’ የሚለው ግስ ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሀሌ ሉያ፣ ሂሌል፣ ማዕሌት፣ ይሃሌልኤል] የሰለጰዓድ ልጅ ማህለህ ፥ (ዘኁ 26:33)
ማሌሴዓር ~ Marsena: ‘የሚያዋጣ፣ ጠቃሚ’ ማለት
ነው። ከሰባቱ
የፋርስና የሜዶን መሳፍንት አንዱ፥ “በመንግሥቱም ቀዳሚዎች ሆነው የሚቀመጡ የንጉሡ ባለምዋሎች ...ሜሬስ፥ ማሌሴዓር፥ ምሙካን በአጠገቡ ሳሉ።” (አስ 1:14)
ማልካም ~ Malcham: ... [ሚልኮም /
Malcham, Molech- የሚለውን ስም ይመልከቱ]
የአባቶች ቤቶች
አለቆች የነበሩ፥
የሸሐራይ ልጅ፥
ማልካም፥ (1 ዜና 8:9፣10)
ማልኮስ ~
Malchus:
መልከ ዋስ፣ መለኩሴ፣ መነኩሴ መሆን፣ የአምላክ መልእከተኛ... ማለት ነው።
‘መልከ’ እና ‘ዋስ’
ከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው።
ጌታን ሊይዙ ከመጡ ካህናት ጋር የነበረ፥ ጴጥሮስ ጀሮውን የቆረጠው፥ የሊቀ ካህናቱ ባርያ፥
ማልኮስ፥ (ዮሐ 18:10)
ማሎክ ~
Malluch:
መለክ፣ መሉክ፣ ምሉኩ፣ ገዥ፣ ንጉሥ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስሞች-
መሉኪ፣ መሉክ፣ ሚልኪ፣ ሜሌክ፣ ሞሎክ]
‘መለከ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው። በሰሎሞን ዘመን፣ ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ከተሰጡ፣ ከሌዊ ነገድ፥ የመራሪ ወገን፥ ማሎክ ፥ (ዜና 6:44)
ማምለጥ ዓለት (የማምለጥ አለት) ~
Sela-hammahlekoth:
ሳለ መለኮት፣ ስለ መለኮት፣ ስለፈጣሪ፣ ስለ እግዚአብሔር... ማለት ነው።
Sela-hammahlekoth-
‘ስለ’ እና ‘መለኮት’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። ፍልስጥኤምማውያን አገሩን በመውረራቸው፥ ዳዊት ከሳዖል ለማምለጥ የቻለበት መንገድ፥
“...ስለዚህ የዚህ ስፍራ
ስም የማምለጥ ዓለት
ተባለ”
(1 ሳሙ 23:28)
ማሣ ~ Massa: ማሰ፣
ማሰነ፣ ተንገላታ...
ማለት ነው።
የእስማኤል ልጅ፥
(ዘፍ 25:15፤ 1 ዜና 1:30) “ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን”
ማሳህ ~ Massah: ምስ፣ ማሳህ፥ መፈታተን፣
መከራከር፣ ማጉረምረም... ማለት
ነው። መሪባ
ተብሎ የተጠራው፥
የእስራኤል አባቶች
በምድረ በዳ
እግዚአብሔርን የተፈታተኑበት፥ “ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፤ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ
አይደለም?
ሲሉ እግዚአብሔርን
ስለተፈታተኑት የዚያን
ስፍራ ስም
ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው” (ዘጸ 17:7፤ መዝ 95:8፣9፤ ዕብ 3:8)
ማሴ ~
Mesha:
‘ማዕከል’ ማለት ነው።
‘ማሴው’ ከሚለው ቃል የተገኘ የቦታ ስም ነው።[ማሴው፥ ኪወክ]
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰው እና አንድ ቦታ አሉ።
. እስራኤላውያን በአረብ ምድር የሰፈሩበት፣ የቦታ ስም፥ (ዘፍ 10:30)
. የአባቶች ቤቶች አለቆች ከነበሩ፥ የሸሐራይ ልጅ፥ (1
ዜና 8:9)
ማሴሮንም ~ Misrephoth-maim: ‘የፈላ ውኃ’ ማለት
ነው። “እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥
ወደ ማሴሮንም፥
... አሳደዱአቸው ... መቱአቸው።” (ኢያ
11:8)
ማስማዕ ~
Mishma:
መሰማ፣ መስማት፣ መረዳት፣ ማዳመጥ... ማለት ነው። ‘ሰማ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በዚህ
ስም የሚታወቁ
ሰዎች:-
1.
የእስማኤል ልጅ፥ ማስማዕ ፥ (ዘፍ 25:14)
2.
የስምዖን ልጅ፥ ማስማዕ ፥ (1 ዜና 4:25)
ማሪያም ~
Miriam:
መሪ እማ፣ ፊተኛ እናት፣ ታላቅ እናት፣ የመጀመሪያ እናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማርያ፣ ማርያም]
‘መሪ’ እና ‘እማ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የአሮን እኅት ማሪያም፥ “የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች ሴቶችም
ሁሉ በከበሮና
በዘፈን በኋላዋ
ወጡ” (ዘጸ
15:20)፥ (1
ዜና 6:3)
ማራ ~ Mara: መራራ፣
ጐምዛዛ፣ ኮምጣጣ... ማለት
ነው። (ሩት 1:20) “እርስዋም፦ ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ”
ማርቆስ ~
Marcus, Mark:
ምሩቅ ዋስ፣ ምሩቅ፣ የተመረቀ፣ የተባረከ፣ ትሑት፣
ምስጉን... ማለት ነው።
‘ምሩቅ’ እና ‘ዋስ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ማርቆስ / Marcus:
የቅዱስ ጳውሎስ
አገልጋይ የነበረ፥ (ጢሞ 4:11) ፣ (ፊል1:24)፣ “ከተገረዙት ወገን
ያሉት፥ የበርናባስ
የወንድሙ ልጅ
ማርቆስ...”
(ቆላ 4:10)
ማርቆስ / Mark: ወንጌላዊ፥ “በእግዚአብሔር መንግሥት ከጳውሎስ ጋር አብረው የሚሠሩት ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ፥”
(ሥራ 12:12)
ማርታ ~ Martha: መሪ እታ፣ መሪ እኅት ፣ የመጀመሪያ ሴት ልጅ፣ ታላቅ እኅት ... ማለት ነው።
‘መሪ’
እና ‘እታ’
ከሚሉ ቃላት
የተገኘ ስም
ነው። የአልዓዛርና የማሪያም እኅት ፥ ማርታ፥ (ሉቃ 10:38)
ማርያ ~
Mary:
መሪ፣ ፊተኛ ፣ ቀዳሚ፣ የመጀመሪያ... ማለት ነው።
‘መሪ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም
ነው። ጳውሎስን
ያስተናገደች፥ ማርያ፥
(ሮሜ 16:6)
ማርያም ~ Mary, Miriam:
መሪ፣ መሓሪ፣
መሪ እማ፣
የመጀመሪያዋ እናት፣ ቀዳሚዋ እመቤት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማሪያም፣ ማርያ]
‘መሪ’ እና ‘እማ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ማርያም / Mary:
1.
የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማርያም፥ “ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት...” (ማቴ 2:11፣ ሥራ 1:14)
2.
መግደላዊት ማርያም፥
(ሉቃ 8:3)
3.
የማርታና የአልዓዛር
እኅት ማርያም፥
“ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ
ልትቀበለው ወጣች፤
ማርያም ግን
በቤት ተቀምጣ
ነበር።”
(ዮሐ 11:20፣ 31፣ 33)
4.
የድንግል ማርያም እኅት ፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ (ዮሐ
19:25)
፣ (ማቴ 27:61፣ ማር 15:47)
5.
የማርቆስ እናት ማርያም፥ “...ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ፥”
(ሥራ 12:12)
ማርያም / Miriam:
1.
የአሮን እኅት ማርያም፥ (ዘጸ15:20) ፣ “የእንበረምም ልጆች አሮን፥ ሙሴ፥
ማርያም።”
(1 ዜና 6:3)
2.
የዕዝራ ልጅ፥ የዬቴር ልጅ ማርያም፥ (1
ዜና 4:17)
ማሮት ~ Maroth: ምሬት፣ የሚመር፣ የሚኮመጥጥ፣ ሐዘን፣ መከራ... ማለት ነው።
‘መረረ’ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። [ተዛማጅ ስም- ሜራሪ]
የቦታ ስም፥ “...
በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች” (ሚክ 1:12)
ማሮን ~ Merom: ‘መራማ፣ ከፍተኛ
ሥፍራ’
ማለት ነው።
ከዮርዳኖስ ወንዝ
በተጠለፈ ውኃ፥
የተፈጠረ ሐይቅ፥ “እነዚህም ነገሥታት
... እስራኤልን ለመውጋት
መጥተው በማሮን ውኃ አጠገብ አንድ
ሆነው ሰፈሩ።” (ኢያ
11:5፣7)
ማቱሳላ ~ Mathusala, Methuselah: ማቱስ አለ፣
ማዕት አለ፣
ብዙ ኖረ... ማለት
ነው። (ሙቶስ አለ፣
ሕያው ሞት፣
ሙቶ የሚኖር
ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስም
- ማቱሣኤል]
‘ማእት’ እና ’አለ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
ማቱሳላ / Mathusala: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የሄኖክ ልጅ ሆኖ፣ የኖኅ ቅድመ አያት፥ (ሉቃ 3:37)
ማቱሳላ / Methuselah: በዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠነኛ ዓመቱ ሲሞት፥ በእድሜ ባለጸጋነቱ ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፥ (ዘፍ 5:21-27)
ማቱሣኤል ~
Methusael:
የጌታ ሞት፣ የአምላክ ሞት፣ የኃያል ሰው ሞት፣ ታላቅ ሞት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም - ማቱሳላ]
‘ሞት’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው። የአዳም ልጅ የቃየል የልጅ ልጅ፥ ማቱሣኤል፥ (ዘፍ 4:18)
ማታትዩ ~
Mattathias: የጌታ ስጦታ ማለት ነው።
1.
የአሞጽ ልጅ፥ “የዮና ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ፥ የአሞጽ ልጅ፥ የናሆም ልጅ፥ የኤሲሊም ልጅ” (ሉቃ 3:25)
2.
የሴሜይ ልጅ፥ “የናጌ ልጅ፥ የማአት ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ የሴሜይ ልጅ፥
የዮሴፍ ልጅ፥” (ሉቃ 3:26)
ማታን ~ Mattan, Matthan: ‘ስጦታ’
ማለት ነው።
1.
በዮዳሄ ዘመን በቤተመቅደሱ የተገደለ፥ የበኣል ካህን፥ “የአገሩም ሕዝብ
ሁሉ... የበኣልንም
ካህን ማታንን
በመሠዊያው ፊት
ገደሉት። ካህኑም
ለእግዚአብሔር ቤት
አስተዳዳሪዎችን ሾመ።” (2 ነገ 11:18)
2.
የአልዓዛር ልጅ፥ የያዕቆብ አባት፥ “ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤” (ማቴ 1:15)
3.
የስፋጥያስ አባት፥ “ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ
ስፋጥያስ፥ የጳስኮርም
ልጅ ጎዶልያስ፥
የሰሌምያም ልጅ
ዮካል፥ የመልክያም
ልጅ ጳስኮር
ሰሙ።”
(ኤር 38:1)
ማታንያ፣ ሙታንያ፣ መታንያ ~
Mattaniah: ማታነ ያሕ፥ የሕያው ስጦታ... ማለት ነው።
1.
የይሁዳ ንጉሥ
የሴዴቅያስ የቀድሞ
ስም፥ “የባቢሎንም ንጉሥ የዮአኪንን አጎት ማታንያን በእርሱ ፋንታ አነገሠ ...” (2 ነገ 24:17)
2.
የሚካ ልጅ፥
“በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥
የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ
ልጅ መታንያ” (1 ዜና 9:15)
3.
የይዒኤል አባት፥
“የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው
በማታንያ ልጅ
በይዒኤል ልጅ
... መጣ”
(2 ዜና 20:14)
4.
“ከኤላም ልጆችም፤
ሙታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞት፥ ኤልያ።” (ዕዝ 10:26)
5.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ የዛቱዕ
ልጅ፥ “ከዛቱዕ ልጆችም፤ ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድ፥ ዓዚዛ።” (ዕዝ 10:27)
6.
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅ፥ “ከፈሐት ሞዓብ ልጆችም ... ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊ፥ ምናሴ።” (ዕዝ 10:30)
7.
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የባኒ ልጅ፥ “ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤልያሴብ፥
መታንያ፥”
(ዕዝ 10:37)
8.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ የዘኩር
አባት፥ “በዕቃ ቤቶችም ላይ
ካህኑን ሰሌምያን፥
ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥
ከሌዋውያኑም ፈዳያን
ሾምሁ ከእነርሱም
ጋር የመታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ
...ማከፋፈል ነበረ” (ነህ
13:13)
9.
የኤማን ልጅ፥ “ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥
ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥
ሐናንያ፥ ሐናኒ
...” (1 ዜና 25:4፣16)
10.
በንጉሥ ሕዝቅያስ
ዘመን፥ ቤተመቅደሱን በማንጻት ከተባበሩ፥ የአሳፍ ልጅ፥ “ከኤሊጸፋንም ልጆች ሺምሪና ይዒኤል፥ ከአሳፍም ልጆች ዘካርያስና መታንያ፥
ከኤማንም ልጆች
...ተነሡ።”
(2 ዜና 29:13)
ማቴዎስ ~
Matthew:
ምአቲ ዋስ፣ መአቲው፣ ማቲ፣ የብዙኃን ዋስ፣ ብዙዎችን የሚያድን... ማለት ነው።
‘መአተ’ እና ‘ዋስ’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ፥ ቀራጩ ማቴዎስ፥ (ማቴ 9:9)
ማትያስ ~ Matthias: የአምላክ
ስጦታ
ማለት ነው።
“ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።” (ሐዋ 1:23)
ማኑሄ ~
Manoah: መኖኅ፣
ማረፍ፣ መረጋጋት፣
መጽናናት...
ማለት ነው።
ዳንዓዊው፥ የሶምሶን
አባት፥ “ከዳን ወገን
የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ
ሰው ነበረ፤ ሚስቱም መካን ነበረች፥ ልጅም አልወለደችም።” (መሣ 13:2)
ማኔ ~ Mene: ‘ቁጥር’
ማለት ነው።
“የነገሩም ፍቺ ይህ
ነው ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን
ቈጠረው ፈጸመውም
ማለት ነው።” (ዳን
5:25፣26)
[ማኒ:
ሰፈረ፣ ቆጠረ፣ ፈጸመ
/ አ/ ኪወክ]
ማንፌን ~
Muppim:
‘መሰሪ፣ እባብ’ ማለት ነው። የብንያም ልጅ፣ የቤላ ልጅ፥ “የብንያምም ልጆች ቤላ... ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ” (ዘፍ 46:21)
ማአት ~ Maath: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ “የናጌ ልጅ፥ የማአት ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ የሴሜይ ልጅ ...” (ሉቃ 3:26)
ማዕሌት ~ Mahalath: መሐላ፣ ማኅለት፣ ማሕሌት፣ የአምላክን ስም መጥራት፣ መዘመር፣ እልል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሐላት፣ ሃሌ ሉያ፣ ሂሌል] ‘ሃሌ’ ፣ ‘መሐላ’
ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
. የያቆብ ወንድም፥ የዔሳው ሚስት፥ ማዕሌት፥ (ዘፍ 28:9)
. መሐላት-
(2 ዜና 11:18)
[ወንጀል፣ ግፍ፣ በደል፣ አሉታ፣ እንቢታ፣ ኃጢአት ክፋት፤ ህመም፣ በሽታ፣ ቁስል
ማለት ነው።
/ ኪወክ /
አ]
ማዕራት ~ Maarath:
ምሬት፣ ፀፀት፣
ሐዘን...
ማለት ነው።
በይሁዳ ተራራዎች የነበረ ቦታ፥ “ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥ ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን ስድስት
ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:59)
ማዕካታውያን ~ Maachathi: ‘መቀጫ’ ማለት ነው። የማዕካ
ነዋሪ፥ “የምናሴ ልጅ
ኢያዕር እስከ
ጌሹራውያንና እስከ
ማዕካታውያን ዳርቻ
ድረስ የአርጎብን
ምድር ሁሉ
ወሰደ ...” (ዘዳ 3:14; ኢያ 12:5፥ 13:11፣ 13) ፤ (2
ሳሙ 23:34፤ 2 ነገ 25:23፤ ኤር 40:8)
ማዕድ ~
Feast:
ፌስታ፣ ደስታ፣ ድግስ፣ ግብዣ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ሰርግ፣ በዓል፣ ግብዣ]
አብርሃም ሥላሴን በቤቱ ተቀብሎ ሲያስተናግድ፥ “ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ
እነርሱም በሉ፥” (ዘፍ 19፡3)
ማኪ ~
Machi:
‘ማነስ’ ማለት ነው። የጉዲኤል አባት፥ የከንዓንን ምድር ለመሰለል ከኢያሱና ከካሌብ ጋር ከሄዱት፥ “ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲኤል።”
(ዘኊ 13:15)
ማኪር ~ Machir: ምክር፣ መካር፣ መካሪ... ማለት ነው።
1.
የምናሴ ትልቁ ልጅ፥ “ለምናሴ ነገድ ዕጣ ይህ ነው የዮሴፍ በኵር እርሱ ነውና።
የምናሴም በኵር
የገለዓድ አባት
ማኪር ብርቱ
ሰልፈኛ ስለ
ነበረ ገለዓድንና
ባሳንን ወረሰ።” (ኢያ 17:1)
2.
ዓሚኤል ልጅ፥
“ንጉሡም። ወዴት ነው?
አለው ሲባም ንጉሡን፦ እነሆ፥ እርሱ በሎዶባር በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት አለ አለው።”
(2 ሳሙ 9:4፣5፥ 17:27-29)
ማዛሮት ~ Mazzaroth: ‘አሥራ ሁለተኛው ምልክት (በኮከብ ቆጠራ)’
ማለት ነው።
“ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን
ከዋክብት በጊዜያቸው
ታወጣ ዘንድ፥
ወይስ ድብ
የሚባለውን ኮከብ
ከልጆቹ ጋር
ትመራ ዘንድ
ትችላለህን?”
(ኢዮ 38:32)
ማይናን ~
Menan:
‘ምኑን፣ መናኒ፣ ዝግጁ’ ማለት ነው። የማጣት ልጅ ሆኖ፥
የሜልያ አባት፥
“የዮናን ልጅ፥ የኤልያቄም
ልጅ፥ የሜልያ
ልጅ፥ የማይናን ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥
የናታን ልጅ” (ሉቃ 3:31)
ማዴ ~ Madai: መዲያ፣
መዳኛ፣ ዳኝነት
የሚካሄድበት አገር፣
ፍርድ የሚሰጥበት ቦታ፣ ዋና ከተማ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማዶ፣ ማዶን፣ ሜዳን፣ ምድያ፣ ምድያም]
የያፌት ልጅ፥
ማዴ፥ (ዘጸ 10:2)
ማድማና ~ Madmannah:
ማእደ መና ማለት ነው። በደቡባዊ የይሁዳ
ግዛት የሚገኝ
ከተማ፥
“ኪሲል፥ ሔርማ፥
ጺቅላግ፥ ማድማና፥
ሳንሳና፥”
(ኢያ 15:31)
ማዶን ~
Madon:
መዳን፣ መዳኝ፣ መዳኛ፣ ዳኝነት ማካሄድ፣ ፍርድ መስጠት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማዴ፣ ማዶ፣ ሜዳን፣ ምድያ፣ ምድያም]
ዮባብ የነገሠበት፥ የአገር ስም፥ (ኢያ 11:1)
ማጎርሚሳቢብ ~ Magor-missabib: “በነጋውም ጳስኮር
ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።” (ኤር 20:3)
ማጎግ ~ Magog: መጓጓት፣
መሳሳት... ማለት ነው።
(ብዙ፣ ማብዛት ማለት
ነው። ተብሎም
ይተረጎማል / ኪወክ / አ)
የያፌት ሁለተኛ
ልጅ፥ “የያፌት ልጆች
ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው” (ዘፍ 10:2)
ማጥሪ ~
Matri:
‘የሕያው ዝናብ’ ማለት ነው። የብንያም ነገድ፥ ወገን የሆነ፥ “የብንያምንም ነገድ
በየወገናቸው አቀረበ፥
ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ።
የማጥሪንም ወገን
በየሰዉ አቀረበ፥
ዕጣውም በቂስ
ልጅ በሳኦል
ላይ ወደቀ
ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።” (1 ሳሙ 10:21)
ሜሌክ ~
Melech:
ምሉክ፣ ገዥ፣ ንጉሥ...ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
መሉኪ፣ መሉክ፣ ሚልኪ፣ ማሎክ፣ ሞሎክ]
‘መለከ’ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። የሚካ ልጅ፥ (1 ዜና 8:35፣ 9:41)
ሜልኪሳ ~ Malchishua, Melchi-shua:
መልከ ዋስ፣ መልአከ ሽዋ፣ የሽዎች አዳኝ፣ የሺህ አምላክ፣ የብዙዎች ጌታ… ማለት ነው።
Melchi-shua- ‘መለከ’
እና ‘ሽዋ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሳኦል ልጅ፣ በፍልስጥኤማውያን የተገደለ፥ (1
ሳሙ 31:2)
ሜልኮል ~
Michal:
መልከ ኤል፣ የአምላክ አምሳያ፣ የሕያው መልክ፣ የተዋበ፣ ያማረ… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሚካኤል፣ ሚካያ]
‘መልከ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
የሳኦል ልጅ፥
“...የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ።” (1 ሳሙ 14:49፣ 50)
ሜልያ ~
Melea:
ሙል፣ ሙሉ፣ ያልጎደለ… ማለት ነው። የኤልያቄም አባት ሆኖ፥ የማይናን
ልጅ፥ “የዮናን ልጅ፥
የኤልያቄም ልጅ፥
የሜልያ ልጅ፥
የማይናን ልጅ፥
የማጣት ልጅ፥
የናታን ልጅ” (ሉቃ 3:31)
ሜልዳር ~
Melzar:
‘መጋቢ’
ማለት ነው። የጃንደርቦቹ አለቃ በዳንኤልና በአናንያ
በሚሳኤልና በአዛርያ
ላይ የሾመው፥
ሜልዳርን፥ (ዳን 1:11፣16)
ሜምፊቦስቴ ~ Mephibosheth: ‘ጣዖታትን ማጥፋት’ ማለት
ነው። የሳኦል ልጅ፥
“ንጉሡም ለሳኦል የወለደቻቸውን
የኢዮሄል ልጅ
የሪጽፋን ሁለቱን
ልጆች ሄርሞንንና
ሜምፊቦስቴን ለመሓላታዊውም
... ወሰደ፥”
(2 ሳሙ 21:8)
ሜምፎስ ~
Memphis:
መንፈስ ማለት ነው። የግብፅ ሰሜናዊ ዋና ከተማ የነበረ፥ “እነሆ፥ ከጥፋት
ሸሽተው ሄዱ፥
ግብፅም ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሳል ...” (ሆሴ 9:6)
ሜምፎስ ~ Noph: ‘የማር ሰፈፍ’ ማለት
ነው። የግብፅ
ከተማ፥ ሜምፎስ ሌላ ስም፥ “የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል ...” (ኢሳ 19:13፤ ኤር.2:16፥ 44:1፣ 46:14፣19፤ ሕዝ 30:13፣16)
ሜሱላም ~ Meshelemiah, Meshullam:
መሳለመ ያሕ፣ የሕያው
ሰላም፣ የአምላክ
ሰላም፣ የሕያው
እርቅ… ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስም- ሜሶላም]
‘መሳለም’
(ሰላም)
እና ‘ያሕ’
(ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉ
ሁለት ቃላት
የተመሠረተ ስም ነው።
ሜሱላም / Meshelemiah: የየሕዜራ አባት፥ ሜሱላም ፥ (1
ዜና 9:21)
ሜሱላም / Meshullam:
1.
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታም ዘመንና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመን፥ ከሰባቱ የአባቶቻቸው ቤቶች ወንድም፥ ሜሱላም፥ (1 ዜና 5:13)
2.
የፈዳያ ልጅ
ሆኖ የዘሩባቤል ልጅ፥
ሜሱላም፥ (1 ዜና 3:19)
3.
ብንያማዊው፣ የበሪዓ ልጆች ፥ሜሱላም፥ (1
ዜና 8:17)
4.
ብንያማዊው የሆዳይዋ ልጅ ሆኖ፣ የሰሉ አባት፥ሜሱላም፥ (1 ዜና
9:7፣ ነህ 11:7)
5.
ከግዞት ተመልሰው በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፥ ሜሱላም፥
(1 ዜና 9:8)
6.
በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን የነበረ፥ ሜሱላም፥ (2 ዜና 34:12)
7.
በዕዝራ ዘመን
የነበረው ሌዊያዊ
አለቃ፥ ሜሱላም፥
(ዕዝ 8:16)
8.
“ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ...
ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ኤልናታን ላክሁ።” (ዕዝ 10:15)
9.
የባኒ ልጅ፥
ሜሱላም፥ (ዕዝ 10:29)
10.
ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ለሕዝቡ ሲያነብ በአጠገቡ ከቆሙት አንዱ፥ (ነህ 8:4)
11.
በነህምያ ዘመን የቃልኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት ካህናት አንዱ፥ (ነህ 10:7)
12.
በነህምያ ዘመን የቃልኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት ካህናት ሌላው፥ ሜሱላም፥
(ነህ 10:20)
13.
ካህኑ የኪልቅያስ ልጅ ሜሱላም ፥ (1
ዜና 9:11)፥ (ነህ 11:11)
14.
ሊቀ ካህኑ ሜሱላም፥ “ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም” (ነህ
12:16)
15.
በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ካህኑ ሜሱላም፥ (ነህ
12:13)
ሜሶላም ~ Meshullam, Meshullemeth:
መሳለም፣ ሰላም ማግኘት፣ እርቅ መፍጠር…
ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሜሱላም]
በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።
ሜሶላም / Meshullam:
የኤዜልያስ አባት፥ (2 ነገ 22:3)
ሜሶላም / Meshullemeth:
የንጉሥ አሞጽ እናት፥ (2 ነገ 21:19)
ሜሪሞት ~ Meremoth: መ’ራማት፣ ከፍ ማለት፣ ወደላይ መውጣት… ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ ካህናት አንዱ፥ “መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥”
(ነህ 12:3)
ሜራሪ ~ Merari, Merarites:
መራሪ፣ መራራ፣ ምሬት፣ የሚመር፣ የሚኮመጥጥ፣ የሚጐመዝዝ… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ማሮት]
‘መረረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
ሜራሪ / Merari: ወደ ግብፅ ከገቡት የእስራኤል ልጆች፥ የሌዊ ልጅ፥ ሜራሪ፥ (ዘፍ 46:11)
ሜራሪ / Merarites: ከሌዊ ወገን፣ የሜራሪ ልጆች፥ (ዘኁ 26:57)
ሜሬስ ~ Meres: መራስ፣ ራስ መሆን፣ ከፍተኛ… ማለት
ነው። ከንጉሥ
አርጤክስስ አማካሪዎች
አንዱ፥“በመንግሥቱም ቀዳሚዎች
ሆነው የሚቀመጡ
... ሼታር፥ አድማታ፥
ተርሺሽ፥ ሜሬስ፥ ማሌሴዓር፥ ምሙካን በአጠገቡ ሳሉ።” (አስ 1:14)
ሜሬድ ~
Mered:
መርድ፣ መራድ፣ መናወጥ፣ መንቀጥቀጥ…
ማለት ነው።
‘ራደ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው። ከይሁዳ ወገን የሆነ፥ የዕዝራ ልጅ፥ ሜሬድ፥ (1 ዜና 4:17)
ሜሮብ ~ Merab: መራብ፣ ረባ፣ መርባት፣ መጨመር፣ መባዛት፣ ርባታ… ማለት ነው።
‘ረባ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
የሳኦል ልጅ፥ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ (1 ሳሙ 14:49)
ሜሮዝ ~
Meroz:
‘መጠለያ፥ መሸሻ፣ መማጠኛ’ ማለት ነው። የቦታ ስም፥ “የእግዚአብሔር መልአክ።
ሜሮዝን እርገሙ፤
እግዚአብሔርን በኃያላን
መካከል ለመርዳት፥ እግዚአብሔርን ለመርዳት ... እርገሙ አለ።” (መሣ 5:23)
ሜሮዳክ ~ Merodach: መርዶ ማለት
ነው። ከባቢሎናውያን ጣዖታት አንዱ፥ “... ባቢሎን
ተወሰደች፥ ቤል
አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ ምስሎችዋ አፈሩ፥
ጣዖታትዋ ደነገጡ
በሉ”
(ኤር 50:2)
ሜቴግ አማ ~ Metheg-ammah:
‘የእናት ሙሽራ’ ማለት ነው። ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ የወሰዳት ከተማ፥ “ከዚህም በኋላ ዳዊት ... ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሜቴግ አማ የተባለችውን ከተማ ወሰደ።” (2 ሳሙ 8:1)
ሜኤል ~ Mehujael: ‘ማየል፣ የአምላክ ቃል ኪዳን፣ የአምላክ ዐዋጅ ...’
ማለት ነው።
የማቱሣኤል አባት፥
“ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ ሜኤልም ማቱሣኤልን ወለደ ማቱሣኤልም
ላሜሕን ወለደ።” (ዘፍ 4:18)
ሜዛሃብ ~ Mezahab: ‘የወርቅ ውኃ’ ማለት ነው። የኤዶ ንጉሥ፥
የሃዳር አማት፥
“የዓክቦር ልጅ በኣልሐናንም
ሞተ፥ በስፍራውም
ሃዳር ነገሠ
የከተማውም ስም
ፋዑ ነው
ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባላለች” (ዘፍ 36:39፤ 1 ዜና 1:50)
ሜያርቆ ~
Mejarkon:
‘አዳኝ’ ማለት ነው። የነገደ ዳን ግዛት የሆነ ቦታ፥ “ይሁድ፥ ብኔብረቅ፥
ጋትሪሞን፥ ሜያርቆን፥
በኢዮጴ ፊት
ለፊት ካለው
ዳርቻ ጋር
ራቆን።”
(ኢያ 19:46)
ሜዳ ~
Meadow:
ሜዳው፣ ሜዳ፣ መስክ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም:- መስኩ]
. የእስራኤል ልጆች ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት የወጡበት ስፍራ፥ የጊብዓ
ሜዳ፥ “...ከእስራኤልም ተደብቀው
የነበሩት ከስፍራቸው
ከጊብዓ ሜዳ ወጡ” (መሣ 20:33)
. ፈርዖን ባየው ሕልም የተጠቀሰ ቃል፥ መስኩ- (ዘፍ 41:2፣ 18)
ሜዳን ~
Medan:
መዳን፣ መዳኝ፣ መዳኛ፣ ዳኝነት የሚካሄድበት፣ ፍርድ የሚሰጥበት ቦታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ማዴ፣ ማዶ፣ ምድያ፣ ምድያም] ‘ዳኘ’ ፣ ‘ዳኛ’ ፣ ‘መዳኛ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
አብርሃም ከኬጡራ የወለደው ልጅ፥ “እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥
የስቦቅን፥ ስዌሕን
ወለደችለት”
(ዘፍ 25:2)
ሜድባ ~
Medeba:
መደብ ማለት ነው። በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የነበረ ከተማ፥
“ገተርናቸው ከሐሴቦን እስከ
ዴቦን ድረስ
ጠፉ ኖፋም
እስኪደርሱ እስከ
ሜድባ አፈረስናቸው።” (ዘኊ 21:30)
ሜዶን ~
Media:
ምድያ፣ ምድያዊ፣ የምድያ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማዴ፣ ማዶን፣ ሜዳን፣ ምድያ፣ ምድያም] የቦታ
ስም፥ (ኢሳ 21:2)
ሜፍዓት ~ Mephaath: ‘ግርማዊ’
ማለት ነው።
“ቅዴሞትንና መሰምርያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰምርያዋን አራቱን ከተሞች ሰጡ።” (ኢያ 21:37)
ምሁማን ~ Mehuman: መሐመን፣
ማመን፣ መቀበል፣
ታማኝ መሆን... ማለት ነው። ‘አመነ’ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
የንጉሥ አርጤክስስ ጃንደረባ፥ ምሁማን፥ (አስ 1:10)
ምሒር ~ Mehir: ምሑር፣
የተማረ፣ ይቅር
የተባለ፥ ምሕረት
ያገኘ ማለት
ነው። “የሹሐም ወንድም ክሉብ የኤሽቶንን አባት ምሒርን ወለደ።” (1 ዜና 4:11)
ምሒዳ ~ Mehida: ‘የታወቀ፣ የተከበረ’ ማለት ነው።
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ “የበስሎት ልጆች፥
የምሒዳ ልጆች” (ዕዝ
2:52፤ ነህ 7:54)
ምሙካን ~ Memucan: ‘መኮንን፣ ክቡር’ ማለት
ነው። ከሰባቱ
የፋርስ መሳፍንት
አንዱ፥ “በመንግሥቱም ቀዳሚዎች
... አርቄስዮስ፥ ሼታር፥
አድማታ፥ ተርሺሽ፥
ሜሬስ፥ ማሌሴዓር፥
ምሙካን በአጠገቡ
ሳሉ።”
(አስ 1:14፣16፣21)
ምስክር ~ Ed: ‘ምስክር’
ማለት ነው።
“የሮቤል ልጆችና የጋድ
ልጆችም። እግዚአብሔር
አምላክ እንደ
ሆነ ይህ
በመካከላችን ምስክር
ነው ሲሉ መሠዊያውን
ምስክር ብለው
ጠሩት።”
(ኢያ 22:34)
ምሥጢር ~
Mystery:
መሰጠር፣ ምሥጢር፣ የተደበቀ ነገር፣ ከብዙዎች የተሰወረ፣ በምሥጢረኞች ዘንድ ብቻ የታወቀ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ሰቱር]
‘ሰጠረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ቃል ነው።
. በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን
ላሉት ቅዱሳን
በክርስቶስ ኢየሱስ
ላሉት ምእመናን
በላከው መልእክት፥
የድኅነት ምሥጢር፥
“በክርስቶስ ለማድረግ እንደ
ወደደ እንደ
አሳቡ፥ የፈቃዱን
ምሥጢር አስታውቆናልና፤” (ኤፌ 1:9፣ 10) ፥ “...ሁሉንም በፈጠረው
በእግዚአብሔር ከዘላለም
የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ
ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፤” (ኤፌ 3:8-11) ፣
ምሥጢረ ሥጋዌ፥ “ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል።” (ቆላ 1:25-27)
. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፥
“እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ...”
(1 ቆሮ 15:51)
መንግሥተ ሰማያት፥ “እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ...” (ማቴ 13:11) ፥
. የድኅነት ምሥጢር፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ ...” (ሮሜ 11:25) ፥ “ትንቢትም ቢኖረኝ
ምሥጢርንም ሁሉና
እውቀትን
ሁሉ ባውቅ፥
...” (1 ቆሮ 13:2)
. ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፥ “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።” (ኤፌ 5:31፣ 32)
. ምሥጢረ ምጽዓት፥ የዓለም
ፍጻሜ ምሥጢር፥
“በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ...” (ራእ 1:20)
. የመጬረሻ ፍርድ ምሥጢር፥
“የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ...።” (2 ተሰ 2:7)
ምራያ ~
Meraiah:
መሪ ያሕ፣ መሪ ሕያው፣ መሪ ጌታ፣ ሕያው አለቃ፣ ሕያው ጌታ፣ አምላካዊ አስተዳዳሪ... ማለት ነው።
‘መሪ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ከነበሩት ካህናት፥ ምራያ፥ (ነህ 12:12)
ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ~ Maher-shalal-hash-baz:
ጥፋት ቀርባለች ማለት ነው። “እግዚአብሔርም፦ ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ”
(ኢሳ 8:1-3)
ምቡናይ ~ Mebunnai: መበን፣ ማነጽ፣ ልጅ መሆን... ማለት ነው። ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ “አቢዔዜር፥ ኩሳታዊው ምቡናይ፥ አሆሃዊው”
(2 ሳሙ 23:28)
ምናሔ ~ Manaen: ‘አጽናኝ’
ማለት ነው።
በአንጾኪያ ባለችው
ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና
መምህራን አንዱ፥
“...እነርሱም በርናባስ፥
ኔጌር የተባለው
ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥
ሳውልም ነበሩ።” (ሐዋ 13:1)
ምናሔም ~ Menahem: ‘ማጽናናት’
ማለት ነው።
የጋዲ ልጅ፥
“የጋዲም ልጅ ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ ... በእርሱም ፋንታ ነገሠ” (2 ነገ 15:14-22)
ምናሴ ~
Manasseh:
ምን ነሴ፣ ምን ነሳ፣ ሁሉን ያገኘ፣ ምንም ያላጣ፣ የቀድሞውን ማስረሻ... ማለት ነው።
‘ምን’ እና ‘ነሳ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የዮሴፍ የመጀመሪያ ልጅ፥ “ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረሳኝ” (ዘፍ
4 1:51)
2.
የሕዝቅያስ ልጅ፥ “ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።” (2 ዜና 32:30)
3.
ከምርኮ ከተመለሱ፥
የፈሐት ሞዓብ
ልጅ፥ “ከፈሐት ሞዓብ ልጆችም ... ባስልኤል፥ ቢንዊ፥ ምናሴ።” (ዕዝ 10:30)
4.
ከምርኮ ከተመለሱ፥
የሐሱም ልጅ፥
(ዕዝ 10:33)
ምናሶን ~ Mnason: ‘መታሰቢያ’
ማለት ነው።
“...እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀ መዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን።”
(ዘፍ 21:16)
ምዑናውያን ~ Meunim: ‘ሰፈራ ጣቢያ’ ማለት
ነው። “የቤሳይ ልጆች፥
የምዑናውያን ልጆች፥” (ነህ 7:52)
ምዖንኒም ~
Meonenim:
‘ጠንቋይ’
ማለት ነው። የዛፍ ጥላ፥ “ገዓልም ደግሞ።
እነሆ፥ ሕዝብ
በምድር መካከል
ይወርዳል፤ አንድም ወገን
በምዖንኒም በአድባሩ ዛፍ መንገድ ይመጣል ብሎ ተናገረ።” (መሣ 9:37)
ምኮና ~ Mekonah: ‘መሠረት’
ማለት ነው።
ከባቢሎን ግዞት
መልስ የይሁዳ
ሰዎች መነኻሪያ
የነበረ ከተማ፥
“በምኮናና በመንደሮችዋ፥ በዓይንሪሞን፥”
(ነህ 11:29)
ምድያም ~ Madian, Midian, Midianites:
መዳኛ፣ ፍርድ የሚሰጥበት፣ ፍትኅ የሚታይበት፣ መናገሻ፣ ፍትሕ የሰፈነበት፣ ዋና ከተማ፣ የምድያም አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ማዴ፣ማዶ፣ ሜዳን፣ ምድያዊ]
ምድያም /
Madian:
ሙሴ በግብፅ ከፈርዖን ፊት ሸሽቶ ለአርባ ዓመት የኖረበት አገር፥ (ሥራ 7:29)
ምድያም / Midian:
የአብርሃም ልጅ፥ ከኬጡራ የወለደው። (ዘፍ 25:2)
ምድያም /
Midianites:
“የምድያም ነጋዶችም አለፉ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት ...” (ዘፍ 37:28፣ 36)
. ሙሴ በግብፅ ከፈርዖን ፊት ሸሽቶ የሄደበት፥ “ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር
ተቀመጠ በውኃም
ጕድጓድ አጠገብ
ዐረፈ።”
(ዘጸ 2:15-21) ፣ “ሙሴም ከዚያ
ሰው ጋር
ሊቀመጥ ወደደ፤ ልጁንም
ሲፓራን ለሙሴ
ሚስት ትሆነው
ዘንድ ሰጠው።” (ዘጸ 2:21)
ምጽራይም ~ Mizraim: ‘ምጽር፣ ምስር፣
ምሽግ፣ መሸሸጌያ’ ማለት
ነው። የግብፅ ሌላ ስም፥ የካም ልጅ፥ “የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን
ናቸው”
(ዘፍ 10:6፣13፤ 1 ዜና 1:8፣11)
ምጽጳ ~ Mizpah: ‘ማማ፣ ክምር’ ማለት ነው።
1.
የመጀመሪያዋ ምጽጳ፥ ያዕቆብ ገለዓድ ያላት፥ ከላባ ጋር የተማማለበት ቦታ፥ (ዘፍ 31:48) “ደግሞም ምጽጳ ተባለ። እኛ በተለያየን ጊዜ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ ብሎአልና”
2.
ሁለተኛዋ፥ ዳዊት እናትና አባቱ እንዲያቆይለት አደራ የሰጠው አገር
ንጉሥ፥ “ዳዊትም ከዚያ
በሞዓብ ምድር
ወዳለችው ወደ
ምጽጳ ሄደ
የሞዓብንም ንጉሥ።
እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን ...” (1 ሳሙ 22:3)
3.
ሦስተኛዋ ምጽጳ ፥ በእስራኤል ላይ ከተባበሩት የኤዊያዊው መቀመጫ፥ “...አገር ወዳለው ወደ ኢያቡሳዊው፥ ከአርሞንዔምም በታች በምጽጳ ወዳለው
ወደ ኤዊያዊው
ላከ።”
(ኢያ 11:3)
4.
ኢያሱ፥ ተባብረው
ሊያጠቋቸው የተነሡትን ጠላቶች ያሳደደበት ሸለቆ፥ (ኢያ 11:8) “እግዚአብሔርም በእስራኤል
እጅ አሳልፎ
ሰጣቸው መቱአቸውም፥
ወደ ታላቂቱም
ሲዶና፥ ወደ
ማሴሮንም፥ በምሥራቅም
በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው ማንንም ሳያስቀሩ መቱአቸው።”
5.
የይሁዳ ከተማ፥ (ኢያ 15:38) “ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ ለኪሶ፥ ቦጽቃት፥”
6.
ከብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች፥ “ምጽጳ፥ ከፊራ፥ አሞቂ”
(ኢያ 18:26፥ 1 ነገ 15:22፤ 2
ዜና 16:6፤ ነህ 3:7)
7. ለብንያም ነገድ ከተሰጡ ከተሞች፥
“ምጽጳ፥ ከፊራ፥
አሞቂ”
(ኢያ 18:26)
ሞሖሊ ~
Mahali:
መሐሊ፣ መሐላ የሚምል... ማለት ነው። የሜራሪ ልጅ፥ “የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ ናቸው። እነዚህ እንደ ትውልዳቸው የሌዊ ወገኖች ናቸው” (ዘጸ 6:19)
ሞሊድ ~
Molid:
መውለድ ማለት ነው።
አቢሱር ከአቢካኢል የወለደው፥
“...አቢካኢል ነበረች አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት።” (1 ዜና 2:29)
ሞላዳ ~ Moladah: መውለድ
ማለት ነው።
በደቡባዊ ይሁዳ
የነበረ ከተማ፥ “አማም፥ ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ ሓጸርጋዳ፥ ሐሽሞን” (ኢያ 15:21-26፥ 19:2)
ሞሎክ ~ Moloch, Molech: መሉክ፣
ምሉክ፣ የሚመለክ፣
የሚገዛ፣ ንጉሥ፣
ጌታ፣ እንደራሴ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሉኪ፣ መሉክ፣
ሚልኪ፣ ማሎክ፣ ሜሌክ]
‘መለከ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
ሞሎክ / Moloch:
የአሞራውያን አምላክ፥ (አሞ 5:26)
ሞሎክ / Molech:
የጣዖት ስም፥ (ዘሌ 18:21)
ሞሳ ~ Mesha:
በዚህ ስም የሚታወቁ:-
1.
የሞዓብ ንጉሥ፥ ሞሳ፥ “የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበረ...” (2 ነገ 3:4)
2.
የዚፍ አባት፥
የካሌብ ልጅ፥
ሞሳ፥ (1 ዜና
2:42)
ሞሴሮት ~ Moserah: ማሰር፣
ማሰሪያ፣ ማሰሪያት፣
ማሰሪያዎች... ማለት ነው።
እስራኤላውያን በጉዟቸው ካለፉባቸው ቦ ታዎች፥ በሆር ተራራ አቅራቢያ የነበረ የቦታ ስም፥ “ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ” (ዘኊ 33:30)
ሞሶሕ ~ Mash: ‘መዋስ፣ መውጣት’
ማለት ነው። የአራም ልጅ፥ “የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው”
(ዘፍ 10:23)
ሞሪያ ~ Moriah:
መሪ ያሕ፣ ሕያው አምላክ የመራው...
ማለትነው። ንጉሥ
ሰሎሞን ቤተ
መቅደስ ያነጸበት
ቦታ፥ “ሰሎሞንም እግዚአብሔር
ለአባቱ ለዳዊት
በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ ...” (2 ዜና 3:1)
ሞሬ ~
Moreh:
መሪ፣ መምህር፣ መሪ ጌታ፣ አስተማሪ... ማለት ነው።
1.
አብራም ከአገሩና
ከወገኑ ተለይቶ
ወደ አዚብ ምድር ባደረገው ጉዞ ካለፈባቸው ቦታዎች፥ “አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ።” (ዘፍ 12:6)
2.
ምድያማውያንና አማሌቃውያን
ከጌዲዮን ጋር ለመዋጋት ከሰፈሩባቸው ቦታዎች፥ “... የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ
አጠገብ በሸለቆው
ውስጥ ነበረ።” (መሣ 7:1)
ሞዓብ ~
Moab: መአብ፣ አባትነት፣ ወላጅነት፣ አባት መሆን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አባ፣ አባት]
‘አበ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ ።
. የሎጥ ልጅ፥ ሞዓብ፥ “ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው” (ዘፍ 19:37)
. የቦታ ስም፥ በሞዓብ ምድር ፥ (ሩት 1:1፥ 2፣ 6) ፥ እሥራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ያለፉባቸው ቦታዎች አንዱ፥ (ነህ 21:11)
ሞዳ ~
Moza:
ሞሳ፣ ህጻን ልጅ፣ ታዳጊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ሞጻ] የካሌብ ልጅ፥ ሞዳ፥ (1
ዜና 2:46)
ሞዳድ ~
Medad:
መውደድ ማለት ነው። ሙሴ በአስተዳደር እንዲአግዙት ከመረጣቸው
አንዱ፥ “ከእነርሱም ሁለት
ሰዎች በሰፈር
ቀርተው ነበር፥ የአንዱም ስም ኤልዳድ የሁለተኛውም ሞዳድ ነበረ ...” (ዘኊ 11:24-29)
ሞጻ ~ Moza: ሞሳ፣ ትንሽ፣ ሕፃን፣ ህፃን ልጅ፣ ታዳጊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሞዳ]
የብንያም ወገን፣ የዘምሪ ልጅ፥ ሞጻ ፥ (1 ዜና 8:36፣37) ፣ (1 ዜና 9:42፣ 43)
No comments:
Post a Comment