ጠርሲዳ ~ Persis: ዊት፣ የፋርስ ሴት... ማለት ነው። በሮም የነበረች ክርስቲያን፥ ጳውሎስ በደብዳቤው የጠቀሳት፥ ... በጌታ እጅግ ለደከመች ለተወደደች ጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16:12)

ጠርሴስ ~ Tarsus: ባለክን ባለላባማለት ነው። በኪልቅያ ያለ ታዋቂ ከተማ፥ ጳውሎስ ግን። እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው ጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤, (ሐዋ 21:39)

ጠርጠሉስ ~ Tertullus: ሳልሣዊ፣ ሦስተኛ... ማለት ነው። ሊቀ ካህናቱ ሐናንያና የአይሁድ ሽማግሌዎች በጳውሎስ ክስ እንዲመሠርት የቀጠሩት ሮማዊ ሰው፥ ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት (ሐዋ 24:1)

ጠባት ~ Tabbath: ጹብ፣ ጹባት፣ ውብ፣ መልካም... ማለት ነው። የኤፍሬም ነገድ ርስት የነበረ፥ የከተማ ስም፥ ሦስቱንም መቶ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ ድረስ ጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።” (መሣ 7:22)

ጠብሪሞን ~ Tabrimon: ዕጹብ ሪሞንማለት ነው። የሶርያ ንጉሥ፥ የወልደ አዴር አባት፥ አሳም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሥ ቤት መዛግብት የቀረውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ በባሪያዎቹ እጅ ሰጣቸው ንጉሡም አሳ በደማስቆ ለተቀመጠው ለአዚን ልጅ ጠብሪሞን ልጅ ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር። (1 ነገ 15:18)

ጢሞቴዎስ ~ Timotheus: ጥሙት ዋስ፣ ታጋሽ፣ ትሑት፣ የታመነ አዳኝ፣ የተከበረ ዋስ፣ የተመሰገነ... ማለት ነው።

ጥሙት እና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ፥ የጳውሎስ ደቀ መዝሙር (ሥራ 16:1)

ጢሞና ~ Timon: ጢሞን፣ ጥሙን፣ ትሙን፣ የታመነ፣ የተከበረ፣ የተመሰገነ... ማለት ነው።

ጥሞናከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። በኢየሩሳሌም ከተመረጡ ዲያቆናት፥ (ሥራ 6:5)

ጢራኖስ ~ Tyrannus: ነጻ አገርማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን በቆየበት ወቅት፥ ለሁለት ዓመት ያሕል ወንጌልን ያስተማረበት ሰው ቤት፥ አንዳንዶች ግንከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስ በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር (ሐዋ 19:9)

ጢሮስ ~ Tyre: ጦር ማለት ነው። ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ” (ኢያ 19:29)

ጢሮአዳ ~ Troas: ጥርስ፣ ጥርሰት፣ ጥሰት በጦር የተወጋ ማለት ነው። በታናሽቱ እስያ ሰሜናዊ ምዕራብ የነበረ የወደብ ከተማ፥ በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ። (ሐዋ 16:8-11)

ጢሮፊሞሳ ~ Tryphosa: ስት እጥፍ ማለት ነው። በሮም የነበሩ እኅትማማች ክርስቲያኖች፥ ጳውሎስ በሰላምታ ከጠቀሳቸው አንዷ፥ በጌታ ሆነው ለሚደክሙ ለፕሮፊሞናና ጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ እጅግ ለደከመች ለተወደደች ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ(ሮሜ 16:12)

ጢባርዮስ ~ Tiberius: ጹብ ራእይ፣ መልካም ራእይ... ማለት ነው። ከአውግስጦስ በኋላ የነገሠ የሮማ ንጉሥ፥ ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥ ጴንጤናዊው ጲላጦስም በይሁዳ ሲገዛ፥ ሄሮድስም በገሊላ ...” (ሉቃ 3:1)

ጣሊታ ~ Tabitha: ጹቢት፣ ጹቢት፣ ውቢት፣ ቆንጅት... ማለት ነው። ጌታ በጥበቡ ከሞት ያስነሣት፥ የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ። ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።” (ማር 5:40)

ጣብኤል ~ Tabeal: ጹበኤል፣ ጹበ ኤል፣ የአምላክ ውብ፣ የጌታ ቅዱስ ማለት ነው። ሶርያና ኤፍሬም ይሁዳን በመውረር በአካዝ ቦታ ሊያነግሡት ያሰቡት ሰው አባት፥ ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ። ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም፥ ጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ” (ኢሳ 7:6)

ጣኔዎስ ~ Zoan: መነሻ፣ መሳፈሪያ፣ መሸኛ ማለት ነው። በታችኛው ግብፅ የነበረ ጥንታዊ ከተማ፥ በደቡብም በኩል ውጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ጣኔዎስ በፊት ሰባት ዓመት ተሠርታ ነበር።” (ዘኊ 13:22)

ጣፈት ~ Taphath: ጠብታ ማለት ነው። የአሚናዳብ ልጅ ያገባት፥ የሰሎሞን ልጅ፥ በዶር አገር ዳርቻ ሁሉ የአሚናዳብ ልጅ፥ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈት አግብቶ ነበር” (1 ነገ 4:11)

ጤሌም ~ Telem: ልም ም፣ ጠለላ፣ ከለላ... ማለት ነው።

1. በዕዝራ ዘመን የመቅደስ ጠባቂ የነበረ፥ ከመዘምራንም፤ ኤልያሴብ፤ ከበረኞችም፤ ሰሎም፥ ጤሌም ኡሪ (ዕዝ 10:24)

2. በይሁዳ ደቡባዊ ድንበር የሚገኝ ከተማ፥ ዚፍ፥ ጤሌም በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥” (ኢያ 15:24)

ጤርጥዮስ ~ Tertius: ሣልሳዊ፣ ሦስተኛ... ማለት ነው። ሮማዊ ክርስቲያን፥ የሐዋርያው ጳውሎስን የሮሜ መልክት በመጻፍ ያገለገለ፥ ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላ ምታ አቀርብላችኋለሁ (ሮሜ 16:22)

ጤግሮስ ~ Hiddekel: ቃጭል ድምፅ፣ እንቢልታ ማለት ነው። ከኤደን ከሚወጡ ወንዞች፥ ወደ ሶሪያ የሚፈሰው፥ የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው” (ዘፍ 2:14)

ጥራኮኒዶስ ~ Trachonitis: ኮረኮንቻማማለት ነው። ... ወንድሙ ፊልጶስም በኢጡርያስ ጥራኮኒዶስ አገር የአራተኛው ክፍል ገዥ፥ ሊሳኒዮስም በሳቢላኒስ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሆነው ሳሉ፥ (ሉቃ 3:1)

ጥሮፊሞስ ~ Trophimus: ምሁርማለት ነው። ከሜቅዶኒያ እስከ እስያ ጳውሎስን በጉዞው ከሸኙት፥ በፊት የኤፌሶኑን ጥሮፊሞስ ከእርሱ ጋር በከተማ አይተውት ነበርና ጳውሎስም ወደ መቅደስ ...” (ሐዋ 21:27-29)

ጥበልያ ~ Tebaliah: ጠበለ ያሕ፣ ጸበለ ያሕ፣ ቅዱስ ጸበል፣ ሕያው ውኃ... ማለት ነው።

ጸበል እና ያሕ (የህዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች ከሰሞነኞች፣ የሖሳ ልጅ፥ ጥበልያ (1 ዜና 26:11)

ጥባህ ~ Tebah: ግድያ፣ እርድ ማለት ነው። የናኮር ትልቁ ልጅ፥ ሬሕማ የሚሉአት ቁባቱ ደግሞ ጥባህን፥ ገአምን፥ ተሐሸን፥ ሞክሳን ወለደች (ዘፍ 22:24)

ጥብርያዶስ ~ Tiberias: ጹብ ራእይ፣ ዕጹብ ራእይ፣ መልካም ራእይ... ማለት ነው። ጌታ በተወለደበት ዘመን የነበረ የገሊላ ከተማ፥ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም ጥብርያዶስ ባሕር ነው።” (ዮሐ 6:123 21:1)

ጦባዶንያ ~ Tobadonijah: ጹብ ዳኝ ያሕ፣ ጦቢያዊ ሕያው አዳኝ፣ ጹባዊ ሕያው ጌታ፣ ቅዱስ አምላካዊ አዳኝ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ፣ ጦብያ፣ ጦብ]

ጹብ ዳኛ እና ያሕ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ እንዲያስተምሩ ከተላኩ፥ (2 ዜና 17:8)

ጦብ ~ Ishtob, Tob: ጡብ፣ ጹብ፣ ውብ፣ መልካም፣ ቅዱስ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ፣ ጦብያ፣ጦባዶንያ]

Ishtob- ሺህ እና ጹብ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

     ጦብ / Ishtob: የአገር ስም፥ (2 ሳሙ 1068)

       ጦብ / Tob: የልዩ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም ብለው ዮፍታሔን ሲያሳድዱት የሸሸበት አገር፥ (መሣ 11:3 5)

ጦብያ ~ Tobiah, Tobijah: ጹብ ያሕ፣ ጹብያ፣ ጦቢያ፣ እጦቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ የሕያው ቅዱሳን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ፣ ጦብ፣ ጦባዶንያ] Tobiah, Tobijah- ጹብእና ያሕ’ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

       ጦብያ / Tobiah: የባቢሎን ንጉ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ፥ (ነህ 7:62)

       ጦብያ / Tobijah: በንጉሥ ኢዮሣፍጥ ዘመን የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበሩ፥ (2 ዜና 17:8 2 ዜና 17:8)

ጦፌል ~ Tophel: ጥፈ ኤል፣ አምላክ ያጠፋው፣ ጠፍ ብልሹ... ማለት ነው። በሲና ምድረ በዳ የነበረ፥ የቦታ ስም፥ በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በዓረባ ውስጥ በኤርትራ ባሕር ፊት ለፊት፥ በፋራን ጦፌል በላባንም በሐጼሮትም በዲዛሃብም መካከል ሳሉ፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የነገራቸው ቃል ይህ ነው” (ዘዳ 1:1)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ