ለሃይሮኢ ~ Lahairoi: ያለ እና የሚያየኝማለት ነው። አጋር ደረ በዳ ስትንከራተት ካለፈችባቸው ቦታዎች፥ ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና። (ዘፍ 24:62)

ለሕሚ ~ Lahmi: ጦረኛማለት ነው። የጎያድ ወንድም፥ ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚ ገደለ (1 ዜና 20:5)

ለሕማስ ~ Lahmam: መኖ፣ ቀለብ፣ ምግብ ማለት ነው። በይሁዳ ደልዳላው ክፍል የነበረ ከተማ፥ ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ ስድስት ከተሞችና መደሮቻቸው” (ኢያ 15:40)

ለቁም ~ Lakum: ለመቆም፣ ለመነሣት፣ ለመጽናት፣ ለመመከትማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ ቁሚ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]

ቆመ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። ለንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት የተሰጠ፥ የቦታ ስም፥ (ኢያ 19:33)

ለቦና ~ Lebonah: ልቦና፣ ልባም፣ ደፋር፣ ጀግና፣ አስተዋይ ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ልባዎት፣ ልብና፣ ልብድዮስ]

ልብ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። በሴሎ አጠገብ ከቤቴል በስተ ሰሜን የሚገኝ የከተማ ስም፥ (መሣ 21:19)

ለአዳን ~ Laadan: ለዳን፣ ለዳኛ፣ ለፍርድ፣ ለሥርዓት ማለት ነው።

ዳኘከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኤፍሬም ልጅ፥ (1 ዜና 7:26)

2. “ከጌድሶናውያን ለአዳን ሰሜኢ ነበሩ።” (1 ዜና 23:7 8 9 26:21)

ለኡማውያን ~ Leummim: ሕዝብማለት ነው። የድዳን ልጅ፥ ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን፥ ለጡሳውያን፥ ለኡማውያን ናቸው።” (ዘፍ 25:3)

ለዓዳ ~ Laadah: መመሪያማለት ነው። የሴሎ ልጅ፥ የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ ከአሽቤዓ ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥” (1 ዜና 4:21)

ለኪሶ ~ Lachish:

የማበገር፣ የማይናወጥ፣ የማይሰበር፣ የማይታጠፍ፣ ጠንካራማለት ነው። የአሞራውያን ግዛት የሆነ፥ የስምዖን አዋሳኝ፥ በኢየሩሳሌም በስተደቡብ የሚገኝ ከተማ፥ ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ ... ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ። ወደ እኔ ውጡ፥” (ኢያ 10:3 5)

ለጡሳውያን ~ Letushim: ውቅር፣ ቅጥቅጥማለት ነው። የድዳን ሁለተኛ ልጅ፥ “... የድዳንም ልጆች አሦርያውያን፥ ለጡሳውያን ለኡማውያን ናቸው” (ዘፍ 25:3)

ለፊዶት ~ Lapidoth: ብርሃን፣ ስልጡን፣ ንቁ ማለት ነው። በዚያ ጊዜም ነቢይቱ ለፊዶት ሚስት ዲቦራ በእስራኤል ላይ ትፈርድ ነበረች (መሣ 4:4)

ሉሒት ~ Luhith: ርብራብ ማለት ነው። በሞዓብ የነበረ የቦታ ስም፥ ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ ከእርስዋም የሚሸሹ ወደ ዞዓር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኰበለሉ ሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ... (ኢሳ 15:5)

ሉቃስ ~ Lucas, Luke: ሊቅ ዋስ፣ ሊቅ፣ ዋቂ፣ አስተዋይ፣ የተማረ፣ ቀዳሚ፣ መንገድ መሪ፣ አስተማሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሉክዮስ፣ ሉቂዮስ፣ ሊቅሒ፣ ሌካ]

ሊቅ እና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው

        ሉቃስ / Lucas: የቅዱስ ጳውሎስ አገልጋይ የነበረ፥ ሉቃስ (ፊል 1:24)

        ሉቃስ / Luke: ሐኪም የነበረ፣ ወንጌላዊው ሉቃስ (ቆላ 4:14)

ሉክዮስ ~ Lucius: ሊቅ ዋስ፣ ዋቂ፣ አስተዋይ፣ የተማረ፣ መንገድ መሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሉቃስ፣ ሉቂዮስ፣ ሊቅሒ፣ ሌካ]

ሊቅ እና ዋስ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

. በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢይና መምህር የነበረ፥ ሉክዮስ (ሥራ 13:1)

. የጴጥሮስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች የጻፈ፥ ጤርጥዮስ የጠቀሰው አገልጋይ፥ ሉክዮስ (ሮማ 16:21)

ሉድ ~ Lud: ግጭት፣ ብጥብጥማለት ነው። ከሴም ልጆች አራተኛው፥ የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ አራም ናቸው። (ዘፍ 10:22)

ሊሳኒዮስ ~ Lysanias: ልሳነ ዋስ፣ አጽናኝ ንግግር፣ ሐዘንን የሚያርቅ... ማለት ነው። በሳቢላኒስ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረ፥ ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት ... ሊሳኒዮስ በሳቢላኒስ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሆነው ሳሉ” (ሉቃ 3:1)

ሊቃኦንያ ~ Lycaonia: የተኩላ አገርማለት ነው። በታንሿ እስያ የሚገኝ ደሴት፥ ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ... ሊቃኦንያ ቋንቋ። አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ (ሐዋ 14:11)

ሊቅሒ ~ Likhi: ሊቅ፣ ቀዳሚ፣ አስተዋይ፣ ዋቂ፣ ምሁር፣ መሪ፣ ተመራማሪ በዕድሜ የበለጠ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሉቃስ፣ ሉክዮስ፣ ሉቂዮስ፣ ሌካ]

ላቀከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። የምናሴ ወገን፣ የሸሚዳ ልጅ፣ ሊቅሒ (1 ዜና 7:19)

ሊቢያ ~ Libya: ልበያ፣ ልብ ያሕ፣ ልበ ሕያው፣ የአምላክ ልብ፣ እግዚአብሔር የወደደው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ልባዎት፣ ልብና፣ ልብድዮስ]

ልብ እና ያሕ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ያገር ስም ነው።

በሰሜን ምሥራቅ አፍሪቃ የሚግኝ ግዛት (ግብፅን ሳይጨምር) (ሥራ 2:10)

ሊባኖስ ~ Lebanon: ነጭማለት ነው። ከፍተኛና ረጅሙ የሶሪያ ተራራ፥ እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ወና ከሆነው ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች ሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው ... (ኢያ 11:17)

[ፍችው፥ ቧሒት እንደማለት፤ ነጭ ነጮ ወይም ነጫም ማለት ነው። / ኪወክ / ]

ሊኖስ ~ Linus: በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ...ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስ ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።” (2 ጢሞ 4:21)

ላሃድ ~ Lahad: ማመን፣ ማመስገንማለት ነው። የኢኤት ልጅ፥ የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድ ወለደ...” (1 ዜና 4:2)

ላህቢም ~ Lehabim: ነበልባልማለት ነው። የአገር ስም፥ ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን...” (ዘፍ 10:13)

ላልተማሩ ~ Barbarian: በር በሪያን፣ የባሪያ ልጅ፣ ሕገ ኦሪትን ያላወቀ፣ ነጻ ያልወጣ፣ እንደተፈጠረ ያለ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት እንግዳ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- አረማውያን፣ እንግዳ]

Barbarian- በር በረ እና ያሕ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። ሕገ እግዚአብሔርን ያላወቁ፥ ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ማያስተውሉ ዕዳ አለብኝ፤” (ሮሜ 1:14)

ላማ ~ Lama: ለምን፣ ለምንድን ነው፣ ስለ ምን... ማለት ነው።

ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ ከተናገራቸው ቃላት፥ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።” (ማቴ 27:46)

ላሜሕ ~ Lamech: የሚመታ፣ ምች፣ መች፣ ብርቱ... ማለት ነው።

Lamech- ‘ለመችከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

. የቃየን አምስተኛ ትውልድ የሆነው፥ (ዘፍ 4:18-24)

. የማቱሳላ ልጅ ሁኖ የኖኅ አባት፥ (ዘፍ 5:25-31 ሉቃ 3:36)

ላሲያ ~ Lasea: ጠቢብማለት ነው። የከተማ ስም፥ በጭንቅም ጥግ ጥጉን አልፈን ላሲያ ከተማ ወደ ቀረበች ...ስፍራ መጣን። (ሐዋ 27:8)

ላባ ~ Laban: ነጭ፣ አንጸባራማለት ነው። የይስሐቅ ሚስት፣ የርብቃ ወንድም፥ (ዘፍ 24:1029-60 27:43 29:5) ለርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ምንጭ ወደ ሰውዮው ሮጠ

ሌሒ ~ Lehi: መንጋጋ አገጭ... ማለት ነው። በይሁዳ የነበረ የቦታ ስም፥ ፍልስጥኤምማውያንም ወጡ፥ ... ሌሒ ላይም ተበታትነው ተቀመጡ (መሣ 15:91419)

ሌሳ ~ Laish: አንበሳማለት ነው። የፈልጢ አባት፥ የዳዊት ሚስት፥ የሚልካ የመጀመሪያ ባል፥ ሳኦል ግን የዳዊትን ሚስት ልጁን ሜልኮልን አገሩ ጋሊም ለነበረው ሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።” (1 ሳሙ 25:44 2 ሳሙ 3:15)

ሌሼም ~ Leshem: ለሽም፣ ለስም፣ ለመጠሪያ፣ ለመታወቂያ... ማለት ነው። ስም ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። ዳን ተብላ የተጠራች፥ የቦታ ስም፥ የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም የዳንም ልጆች ሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥

...በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት። (ኢያ 19:47)

ሌካ ~ Lecah: ሊቅ፣ ቀዳሚ፣ ዋቂ፣ የተማረ፣ ንቁ፣ አስተዋይ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሉቃስ፣ ሉክዮስ፣ ሉቂዮስ፣ ሊቅሒ]

ላቀከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። በይሁዳ የዘር ሐረግ የተጠቀሰው ሌካ (1 ዜና 4:21)

ሌዊ ~ Levi: ሊቬ፣ ልቤ፣ ልባዊ፣ ተወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሊቢያ፣ ልባዎት፣ ልብና፣ ልብድዮስ፣ ሌዋውያን]

ልብከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

1. የያቆብና የልያ ሦስተኛ ልጅ፥ ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። (ዘፍ 29:34)

2. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የሚልኪ ልጅ፥ (ሉቃ 3:24 29)

3. የእልፍዮስ ልጅ፣ ሐዋያው ሌዊ፥ (ማር 2:14) (ሉቃ 5:27 29)

[ስሙ ይጠጋልማለት ነው። / መቅቃ]

ሌዋውያን ~ Levites: ልባውያን፣ ልባዊ፣ የተወደዱ፣ የሌዊ ወገን፣ የሌዊ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሌዊ]

. የአሮን የልጅ ልጅ ፊንሐስ የሌዋውያን አባት ተብሎ ተጠራ፥ (ዘጸ 6:25)

. ለእግዚአብሔር በኩራት ሆነው ስለተለዩ በእስራኤል ርስት አልነበራቸውም፥ (1 ነገ 8:4 ዕዝ 2:70)

ልሄኔሲፎሩ ~ Onesiphorus: አትራፊማለት ነው። በኤፌሶን የነበረ ክርስቲያን፥ ለጳውሎስ በሮም በጎ ነገርን ያደረገ፥ ጌታ ልሄኔሲፎሩ ቤተ ሰዎች ምሕረትን ይስጥ፥ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፤” (2 ጢሞ 1:16-184:19)

ልስጥራን ~ Lystra: የተበተኑማለት ነው። ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ” (ሐዋ 14:1)

ልቅሶ ~ Baca: በፍልስጥኤም አገር ያለ ሸለቆ፥ ወደ ሕያው ቤተ መቅደስ የሚሸሹበት፥ እስራኤላ ዓይ ሊናቸው ያዩት ቦታ፥ ልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።” (መዝ 84:6)

ልባዎት ~ Lebaoth: ልባት፣ ልባም፣ ደፋር፣ ጀግና፣ አስተዋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሊቢያ፣ ሌዊ፣ ልብና፣ ልብድዮስ]

ልብከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። በነቢዩ ኢያሱ የተጠቀሰ የከተማ ስም፥ ልባዎት (ኢያ 15:32)

ልብና ~ Libnah: ልቦና፣ ልቡና፣ ልባዊ፣ አስተዋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሊቢያ፣ ሌዊ፣ ልባዎት፣ ልብድዮስ]

ልብ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። ሌበናንየሚለው የአገር ስም የተገኘው ከዚህ ነው።

እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ካለባቸው ቦታዎች፥ ልብና (ዘኁ 33:20 21) (ኢያ 10:29-32 12:15)

ልብድዮስ ~ Lebbaeus: ልበ ዋስ፣ ልባዊ ዋስ፣ ደፋር፣ አስተዋይ፣ ጀግና... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሊቢያ፣ ሌዊ፣ ልባዎት፣ ልብና]

Lebbaeus- ልብ እና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።

ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው፣ የሐዋርያው የታዴዎስ ሁለተኛ ስም፥ “...ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ (ማቴ 10:3)

ልያ ~ Leah: ጠውላጋ ማለት ነው። የላባ ትልቋ ልጅ፥ የያዕቆብ ሁለተኛ ሚስት፥ ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ።” (ዘፍ 29:16)

ልዳ ~ Lydda: ግጭት፣ ብጥብጥ ማለት ነው። ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር ልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ።” (ሐዋ 9:323538)

ሎሩሃማ ~ Lo-ruhamah: ምሕረት ያጣ፣ ይቅርታ የሌለው የተረገመማለት ነው። ደግሞ ፀነሰች ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፦ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምርምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት” (ሆሴ 1:6 2:23)

ሎቤኒ ~ Libni: ነጭማለት ነው። የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ወገን፥ የጌድሶንም ልጆች እንደ ወገኖቻቸው ሎቤኒ ሰሜኢ ናቸው (ዘጸ 6:17 ዘኊ 3:1821)

ሎዓሚ ~ Lo-ammi: ኢአማንያን፣ ያላመነ፣ ሕዝቤ ያልሆነ ማለት ነው። (ሆሴ 1:9 10) “እግዚአብሔርም፦ ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላክ አልሆናችሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው አለው።

ሎዛ ~ Luz: ለውዛ፣ ለውዝ፣ የለውዝ ተክል... ማለት ነው።

. ቤቴል ተብላ የተጠራች፥ ጥንታዊ የከነዓን ከተማ፥ ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ። (ዘፍ 28:19 35:6)

. በኬጢያውያን አገር የነበረ የቦታ ስም፥ “... ስምዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት...” (መሣ 1:26)

[...ለውዝ፥ ለውዛም፥ የለውዝ ቦታ... / ኪወክ / ]

ሎይድ ~ Lois: ቅን ተግባቢ ማለት ነው። የጢሞቴዎስ አያት፥ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን ... በአያትህ ሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ” (2 ጢሞ 1:5)

ሎድ ~ Lod: ልድ፣ ልጅ፣ ውልድ፣ ትውልድ... ማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ የሎድ ልጆች ይገበታል፥ ሎድ የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት።” (ዕዝ 2:33)

ሎዶቅያ ~ Laodicea: ፍትዊ፣ እውነተኛ ሕዝብማለት ነው። ሎዶቅያ ወዳለው ... አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል። (ራእይ 3:14)

ሎጥ ~ Lot: ልጥ፣ ነጠላ፣ ሻሽ፣ የፊት መሸፈኛ ማለት ነው። የታራ ልጅ፣ የናኮር ልጅ፣ የሐራን ልጅ፥ የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ ሐራንም ሎጥ ወለደ” (ዘፍ 11:2731)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ