ዓብዳ ~ Abda: አገልጋይ፣ ተላላኪ፣ ታዛዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አብዲ፣ አቤድ]

አብዴከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. የአዶኒራም አባት፥ (1 ነገ 4:6)

. የሳሙስ ልጅ፥ አብድያ- (ነህ 11:17)

ዐናሚም ~ Anamim: ፏፏቴማለት ነው።

የግብጻውያን ወገን፥ የምጽራይም ልጅ፥ ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥” (ዘፍ 10:13 1 ዜና 1:11)

ዓዛርያስ ~ Azariah: ዘረ ሕያው፣ ዘረ ዋስ፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛሪያስ፣ ዔዛርያስ]

Azariah- ዘር እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ንጉሡ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ በነገሠበት ዘመን አለቃ የነበረ፥ የሳዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛርያስ (1 ነገ 4:2)

2. የኬልቅያስ ልጅ፥ (ዕዝ7:1 2) የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ

ዓዛርያስ (1 ዜና 9:11 ነህ 3:23) (1 ዜና 6:36)

3. የዖዴድ ልጅ፥ (2 ዜና 15:1)

4. የአኪማአስ ልጅ፥ (1 ዜና 6:9 1 ነገ 4:2)

5. የዮሐናን ልጅ፥ (1 ዜና 6:10 11)

6. የአሜስያስ ልጅ፥ (2 ነገ 14:21 2 ዜና 26:17-20)

ዐግ ~ Og: ትልቅማለት ነው። ግዛቱ በስድሳ ከተሞች የተስፋፋ፥ የአሞራውያን ንጉሥ፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን ዐግ መንግሥት ሁሉ እርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።” (ኢያ 13:12)

ዑላ ~ Ulla: ቀንበር ማለት ነው። የአሴር ልጅ፥ ዑላ ልጆች ኤራ፥ ሐኒኤል፥ ሪጽያ ነበሩ።” (1 ዜና 7:39)

ዑማ ~ Ummah: ደትማለት ነው። ለአሴር ነገድ፥ ድርሻ የተሰጠ ከተማ፥ ዑማ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ ሀያ ሁለት ከተሞችና ...” (ኢያ 19:30)

ዑሪ ~ Huri: ሸማኔ፣ ዘዋሪ፣ ዝሐ ዘጊ፣ ተሽከርካሪ፣ ተመላላሽ ማለት ነው። የጋድ ወገን፥ የአቢካኢል ልጅ፥ እነዚህም የቡዝ ልጅ የዬዳይ ልጅ ... የሚካኤል ልጅ የገለዓድ ልጅ የኢዳይ ልጅ ዑሪ ልጅ የአቢካኢል ልጆች ነበሩ።” (1 ዜና 5:14)

ዑር ~ Ur: ኡር፣ ብርሃን፣ የብርሃን መውጫ፣ ምሥራቅ አገር ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኡሪ፣ ኡር]

በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰው እና አንድ አገር አሉ።

1. የኤሊፋል አባት፥ (1 ዜና 11:36)

2. ሐራን የተወለደበት አገር፥ (ዘፍ 11:28 31)

ዑታይ ~ Uthai: ተባባሪ፣ ረዳትማለት ነው።

1. የይሁዳ ወገን፥ የዓሚሁድ ልጅ፥ ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኒ ልጅ የአምሪ ልጅ የፆምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀመጠ” (1 ዜና 9:4)

2. ከምርኮ ከተመለሱ፥ ከበጉዋይ ልጆች ዑታይ ዘቡድ፥ ከእነርሱም ጋር ሰባ ወንዶች።” (ዕዝ 8:14)

ዑኒ~ Unni: ጭንቀታምማለት ነው።

1. ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ ... በረኞችንም ዖቤድኤዶምንና ይዒኤልን አቆሙ። (1 ዜና 15:1820)

2. ቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ።” (ነህ 12:9)

ዑፅ ~ Huz: አሸዋማ ማለት ነው። የናኮርና ሚልካ ትልቁ ልጅ፥ እነርሱም በኵሩ ዑፅ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ (ዘፍ 22:21)

ዑፅ ~ Uz: እዝ፣ ትእዛዝማለት ነው።

1. የአራም ልጅ የአራምም ልጆች ዑፅ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።” (ዘፍ 22:21)

2. የዲሳን ልጅ፥ የዲሳን ልጆችም እነዚህ ናቸው ዑፅ አራን (ዘፍ 36:28)

3. የናኮር ልጅ፥ እነርሱም በኵሩ ዑፅ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥” (ዘፍ 22:21)

ዒስካ ~ Ikkesh: የካሽ፣ የከፋይ ፈቃደኛ፣ ጽኑዕ ማለት ነው። የቴቁሐዊው የዒራስ አባት፥

ዒስካ ልጅ ዒራስ፥ ዓናቶታዊው (2 ሳሙ 23:26 1 ዜና 11:28 27:9)

ዒሪ ~ Iri: ብር ማለት ነው።የቤላ ልጅ፥ የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሪሙት፥ ዒሪ አምስት ነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ በትውልድ የተቈጠሩ ሀያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።” (1 ዜና 7:712)

ዒራም ~ Iram: ከተሜማለት ነው። የኤዶማውያን መሪ፥ መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ይህ ዔሳው ነው። (ዘፍ 36:43 1 ዜና 1:54)

ዒር ~ Ir: ከተማ ማለት ነው። ደግሞም ሳፊን፥ ሑፊም ዒር ልጆች፥ ሑሺም የአሔር ልጆችም ነበሩ።” (1 ዜና 7:12)

ዒርሼሜሽ ~ Irshemesh: የፀሓይ ከተማማለት ነው። የዳን ነገድ ከተማ፥ የርስታቸውም ዳርቻ ... ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ” (ኢያ 19:41)

ዒዋ ~ Ivah: ቅሪት፣ ባድማ፣ ውድቅዳቂማለት ነው። የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይምና የሄና ዒዋ አማልክት ወዴት አሉ? (2 ነገ 18:34 19:13)

ዒዪም ~ Iim: ባድማ፣ ውዳቂ፣ ፍርስራሽ፣ ቅሬትማለት ነው። በይሁዳ የደቡብ ወሰን የሚገኝ ከተማ፥ በኣላ፥ ዒዪም ዓጼም፥ ኤልቶላድ፥ (ኢያ 15:29)

ዒዮን ~ Ijon: ባድማ፣ ውዳቂ፣ ፍርስራሽ፣ ቅሬት ማለት ነው። ፍታሌም ርስት የሆነ ሰሜናዊ የፍልስጥኤም ክፍል፥ ወልደ አዴርም ... ከተሞች ላይ ሰድዶ ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልቤት መዓካንና ኪኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም አገር ሁሉ መታ።” (1 ነገ 15:20 2 ዜና 16:4)

ዒዶ ~ Iddo: ውድ፣ ተወጃጅማለት ነው።

1. የአናዳብ አባት፥ በመሃናይም ዒዶ ልጅ አሒናዳብ (1 ነገ 4:14)

2. የጌድሶን ልጅ፥ አዶ፥ ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ ልጁ ዛራ... (1 ዜና 6:21)

3. በዳዊት ዘመን፥ በዮ ርዳኖስ በስተምሥራቅ የምናሴ ነገድ ገዥ፣ የዘካርያስ ልጅ፥ በገለዓድ ባለው በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የዘካርያስ ልጅ አዶ በብንያም ላይ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል” (1 ዜና 27:21)

4. ባለ ራእዩ፥ ነቢዩ ኢዶ፥ የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በኦሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ አዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?” (2 ዜና 9:29)

5. የነቢዩ የዘካርያስ አባት፣ የበራክዩ አባት፥ ... የእግዚአብሔር ቃል ወደ

አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ (ዘካ 1:17)

6. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ በካሲፍያ ስፍራ ወደ ነበረው ወደ አለቃው ወደ አዶ ላክኋቸው ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን ያመጡልን ዘንድ... (ዕዝ 8:17)

ዓሌሜት ~ Alameth: ዓለማት ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ጋሌማት] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የቤኬር ልጅ፥ (1 ዜና 78)

2. የይሆዓዳ ልጅ፥ (1 ዜና 8:32)

3. የዕራ ልጅ፥ (1 ዜና 9:42)

ዓልዋን ~ Alian: ዓላይነ፣ ዕላይ፣ ከፍተኛ፣ ትልቅ፣ የበላይ... ማለት ነው። የሦባል ልጅ፥ የሦባል ልጆች ዓልዋን ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም። የጽብዖንም ልጆች አያ፥ ዓና።” (1 ዜና 1:40)

ዓልዋ ~ Alvah: ላይኛ የበላይ ማለት ነው። ከኤዶማውያን አለቆች አንዱ፥ የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥” (ዘፍ 36:40)

ዓሚሁድ ~ Ammihud: አሚ ድ፣ አም ውድ፣ የተወደደ፣ የተዋ... ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የአዳን ልጅ፥ የኤሊሳማ አባት፥ (1 ዜና 7:26) (ዘኁ 1:10)

2. ከስምዖን ነገድ የሰላሚኤል አባት፥ (ዘኁ 34:20)

3. ከንፍታሌ ነገድ፣ የፈዳሄል አባት፥ (ዘኁ 34:28)

4. የጌሹር ንጉሥ የተልማይ አባት፥ (2 ሳሙ 13:37)

5. የፆምሪ ልጅ፥ (1 ዜና 9:4)

ዓሚኤል ~ Ammiel: አሚ ኤል፣ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአምላክ ሕዝብ... ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሙሴ ከላካቸው፥ የገማሊ ልጅ፥ (ዘኁ

13:12)

2. የሳዖል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ከንጉሥ ዳዊት ሸሽቶ የሔደበት ሰው፥ የማኪር አባት፥ (2 ሳሙ 17:27) (2 ሳሙ 9:4)

3. የዳዊት ሚስት የቤርሳቤህ አባት፥ (1 ዜና 3:5)

4.የዖቤድኤዶም ልጅ፥ (1 ዜና 26:5)

ዓሚዛባድ ~ Ammizabad: የሕዝብ ስጦታ፣ ጥሎሽማለት ነው። በሠላሳው ኃያላን ላይ የሦስተኛው ክፍል አለቃ የነበረ፣ የበናያስ ልጅ፥ ይህ በናያስ በሠላሳው መካከል ኃያል ሆኖ በሠላሳው ላይ ነበረ በእርሱም ክፍል ልጁ ዓሚዛባድ ነበረ።” (1 ዜና 27:6)

ዓማል ~ Amal: ል፣ ጠባይ ሥራ፣ ሱስማለት ነው። የኤላም ልጅ፥ የወንድሙም የኤላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ።” (1 ዜና7:35)

ዓማሣይ ~ Amasai: ያመጸ፣ የሸፈተ፣ አልታዘዝም ያለ፣ ቢተኛ፣ ትምክትኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አማሢ አማሳይ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ ዓሜሳይ]

መፀከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከዳዊት ጋር ከተቀላቀለ ሠራዊት የሠላሳ አለቃ የነበረ፥ (1 ዜና 12:18)

2. በእግዚአብሔር ታቦ ፊት መለከት ይነፉ ከነበሩ ካህናት፥ (1 ዜና 15:24)

. የሕልቃና ልጅ፥ አማሢ- (1 ዜና 62535)

. የእግዚአብሔርን ቤት ያነጹ ዘንድ ወደ ውስጥ ከገቡ ካህናት፣ የቀዓት ልጅ፥ አማሢ- (2 ዜና 29:12)

ዓማስያ ~ Amasiah: አማሲ ያሕ፣ ሕያው፣ ኃጢተኛ፣ ጌታን የሚበድል፣ የአምላክን ሕግ የጣሰ፣ አሻፈረኝ ያለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓማሣይ፣ አማሢ አማሳይ፣ አሜሳይ፣ ዓሜሳይ]

እና ያሕ’ (ያሕዌ) ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ፣ የዝክሪ ልጅ፥ (2 ዜና 1716)

ዓሜሳይ ~ Amasa: አመሳ፣ መፃ፣ የሚያምስ፣ የሚበጠብጥ፣ የሚረብሽ፣ ተቃዋሚ፣ የማይታዘዝ፣ የማይገዛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓማሣይ፣ አማሢ አማሳይ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ]

መፀከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዳዊት እኅት የአቢግያ ልጅ፣ የዬቴር ልጅ፥ (1 ዜና 217)

2. ከኤፍሬም ልጆች አለቆች፣ የሐድላይ ልጅ፥ (2 ዜና 28:12)

ዓምዓድ ~ Amad: አማድ፣ አዕማድ፣ ምድ፣ መሠረት፣ ምሰሶ... ማለት ነው።

አምደ ከሚለው ግስ የመጣ የቦታ ስም ነው። የአሴር ልጆች ነገድ ድንበር፥ (ኢያ 19:26)

ዓሞቅ ~ Amok: አሞቅ፣ አመቅ፣ መቅ፣ መቀመቅ፣ ጥልቅ ጉድጓድ፣ መቃብር... ማለት ነው።

አመቀከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር ከወጡ ካህናትና ሌዋውያን፥ (ነህ 12:7 20)

ዓሢኤል ~ Asiel: አሥ ኤል፣ የጌታ ሥራ፣ ግብረ ኤል፣ እሥራ ኤል፣ የአምላክ ሥራ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓሣያ፣ ዓሳያ]

የሠራያ ልጅ፥ (1 ዜና 435)

ዓሣያ ~ Asaiah: ያሕ፣ አሳይ ያሕ፣ የሕያው ሥራ፣ ጌታ ሠራ፣ አምላክ አከናወነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓሳያ፣ ዓሢኤል]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የሠራያ ልጅ የዓሢኤል ልጅ፥ ዓሣያ (1 ዜና 436)

2. ዳዊት ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ካቆማቸው የመዘምራን አለቆች፥ የሐግያ ልጅ፥ ዓሣያ (1 ዜና 630) (1 ዜና 156)

3. የሴሎናዊያን ልጅ፥ ዓሣያ ከሴሎናዊያንም በኵሩ ዓሣያ ልጆቹ (1ዜና 95)

4. “ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ ... የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን።” (2 ዜና 34:20)

ዓረባ ~ Arabah: ረባ፣ ረባዊ፣ ረብ አገር፣ ምድረ ባዕዳ፣ በረ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓረባዊ፣ ዓረብ]

ረባከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

.በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ ዓረባ ውስጥ በኤርትራ ባሕር ፊት ለፊት ... ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የነገራቸው ቃል ይህ ነው። (ዘዳ 1:1)

.በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ…” (ኢያ 1818)

ዓረባዊ ~ Arbathite: ረባያት፣ ረባዊያት፣ ረብ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓረባ፣ ዓረብ]

ከዳዊት ወታደሮች አንዱ፣ አቢዓልቦን፥ (2 ሳሙ 23:31 1 ዜና 11:32) (ኢያ 15:61)

ዓረብ ~ Arabia: ረባዊ፣ ረባውያን፣ ረብ አገር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓረባ፣ ዓረባዊ]

ከምድሩ ሹማምንት ወደ ሰሎሞን ወርቅና ብር ግብር ካመጡ፥ (1 ነገ 1015)

ዓራድ ~ Arad: የሜዳ አህያ ማለት ነው። ዝባድያ፥ ዓራድ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች (1 ዜና 8:15)

ዓሻን ~ Ashan: ጭስ ማለት ነው። በይሁዳ የታችኛው ክፍል የነበረ ከተማ፥ ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን ይፍታሕ፥ አሽና፥ (ኢያ 15:42)

ዓቁብ ~ Akkub: ቁብ፣ ቁብ፣ ቃቢ ቀበ፣ ጠበቀ፣ ከለከለ፣ አገደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ያቆብ፣ ያዕቆባ፣ ያዕቆብ]

ቀበከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከዘሩባቤል ወገን፣ የኤልዮዔናይ ልጅ፥ (1 ዜና 3:24)

2. ከነቢዩ ዕዝራ ጋር ከባቢሎን ከተመለሱ፣ የአጋባ ልጅ፥ (ዕዝ 2:45 46)

3. ከምርኮ ተመልሰው በረኛ ከነበሩ፥ (1 ዜና 9:17) (ዕዝ 2:42 ነህ

7:45)

ዓቃን ~ Jakan: ጠቢብ፣ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ፣ ቅን ፈራጅ ማለት ነው። የኤጽር ልጅ፥ የኤጽር ልጆች ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን የዲሳን ልጆች ... (1 ዜና 1:42)

ዓባሪም ~ Abarim: አባሪ፣ ተባባሪ፣ ረዳት፣ አጋዥ... ማለት ነው። በሞዓብ ምድር፥ በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ፥ በእያሪኮ አቅጣጫ፥ የዮርዳኖስ ሸለቆ አዋሳኝ፥ የሆነ ተራራማ ቦታ። ከተራራዎቹ ጎልቶ የሚታየው ኔቦ በመባል የሚታቀው ሲሆን፥ ሙሴ ሊሞት ሲል ወደዚያ ተራራ በመውጣት ከዚያ የተስፋውን አገር ይኑ ለመቃኘት በቅቷል። እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ (ዘኊ 27:12 33:4748) እና (ዘዳ 32:49)

ዓብዳ ~Abda: አገልጋይ፣ ተላላኪ፣ ታዛዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አብዲ፣ አቤድ]

አብዴከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. አስገባሪ የነበረ፣ የአዶኒራም አባት፥ (1 ነገ 4:6)

. የሳሙስ ልጅ፥ አብድያ- (ነህ 11:17)

ዓብድኤል ~ Abdeel: አብ ኤል፣ የአምላክ አገልጋይ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- አብዲኤል፣ አብድያ፣ አብድያስ]

አብ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የሰሌምያ አባት፥ ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን ዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው (ኤር 36:26)

ዓብዶን ~ Abaddon, Abdon: አብ ዶን፣ አባ ዳኛ፣   

የመጨረሻ ፍርድ አስፈጻሚ... ማለት ነው። አብደ እና ዳኘ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዓብዶን / Abaddon:

. የገሃነም መልአክ ስም፥ በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮ ይባላል” (ራእ 911)

. በኢዮብ መጽሐፍ ጥፋት ይላል፥ ጥፋትና ሞት- (ኢዮ 26:6)

. የመረሻ ፍርድ፥ ሲኦልና ጥፋት- (ምሳ 15:11) ሲኦልና ጥፋት- (ምሳ 27:20)

       ዓብዶን / Abdon:

1. በእስራኤል ላይ ፈራጅ የነበረ፣ የሂሌል ልጅ፥ (መሣ 1213)

2. የይዒኤል ልጅ፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ ዓብዶን ዝክሪ፥ (1 ዜና 8:23)

3. “የበኵር ልጁ ዓብዶን የበኵር ልጁም ዓብዶን፥ (1 ዜና 8:30) (9:35 36)

4. የሚክያስ ልጅ፥ (2 ዜና 34:20)

5. የቦታ ስም፥ “...ዓብዶንንና መሰምርያዋን፥ (ኢያ 21:30) (1 ዜና 6:74)

ዓታክ ~ Athach: የመንገደኛ ማረፊያ ማለት ነው። በይሁዳ አገር የታችኛው አካባቢ የነበረ የቦታ ስም፥ በሔርማ ለነበሩ፥ በቦራሣን ለነበሩ፥ ዓታክ ለነበሩ፥ በኬብሮን ለነበሩ፥” (1 ሳሙ 30:30)

ዓታይ ~ Attai: እጣ የደረሰው፣ ጊዜ የሰጠው፣ ደለኛማለት ነው።

1. የሶሳን የልጅ ልጅ፥ ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርስዋም ዓታይ ወለደችለት።” (1 ዜና 2:3536)

2. ያንበሳ ገጽ ካላቸው የጋድ ጦረኞች አንዱ፥ የዳዊት የጦር አዛዥ፥ (1 ዜና

12:11)

3. የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም፥ ከመዓካ የወለደው፥ ከእርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት።” (2 ዜና 11:20)

ዓኑብ ~ Anub: መተባበር፣ መረዳዳት፣ ብረት መፍጠር ማለት ነው። የይሁዳ ወገን የሆነ፥ የቆጽ ልጅ፥ ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።” (1 ዜና 4:8)

ዓኒም ~ Anim: ፏፏቴ ማለት ነው። በይሁዳ ተራራዎች የነበረ ከተማ፥ ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ አሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:50)

ዓና~ Anah: ታዛዥማለት ነው። የዔሳው ሚስት አባት፥ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ፥ ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን አህሊባማን፥ (ዘፍ 36:21425)

ዓናብ ~ Anab: የዘቢብ ከተማማለትነው። ከይሁዳ ተራራማ ከተሞች አንዱ፥ ዓናብ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ አሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:50)

ዓናቶት ~ Anathoth: ሥምረት፣ እለ የደረሰ፣ ልመናው የተሰማ ማለት ነው።

1. የቤኬርም ልጅ፥የቤኬርም ልጆች ዝሚራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ አብያ፥ ዓናቶት ዓሌሜት እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።” (1 ዜና 7:8)

2. በነህምያ ዘመን ቃል ኪዳን ከተፈራረሙትአንዱ፥ሐሪፍ፥ ዓናቶት ኖባይ፥ መግጲዓስ፥ ሜሱላም” (ነህ 10:19)

ዓናኒ ~ Anani: አምላክ የጠበቀው ማለት ነው። ከይሁዳ ነገሥታት ወገን፥ የኤልዮዔናይ ልጅ፥ የኤልዮዔናይም ልጆች ሆዳይዋ፥ ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ። (1 ዜና 3:24)

ዓኔም ~ Anem: መንታ ምንጭማለት ነው። የይሳኮር ከተማ፥ ራሞትና መሰምርያዋ፥ ዓኔምና መሰምርያዋ” (1 ዜና 6:73)

ዓኔር ~ Aner: ጎልማሳማለት ነው። ለቀዓት ልጆች ወገን የተሰጠ የምናሴ ከተማ፥ ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰምርያዋን፥ ... ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ። (1 ዜና 6:70)

ዓንቶትያ ~ Antothijah: የሕያው መልስማለት ነው። የይሮሐም ልጅ፥ ሐናን፥ ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ ይፍዴያ፥ ... የሶሴቅ ልጆች” (1 ዜና 8:24)

ዓክሳ ~ Achsah: ካሳ፣ ጥሎሽ፣ ስጦታ... ማለት ነው። (አምባር ማለት ነው፥ ተብሎም ይተረጎማል) የካሌብ ሴት ልጅ ዓክሳ፥ (1 ዜና 2:49) “ደግሞም የመድማናን አባት ሸዓፍንና የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች የካሌብም ሴት ልጅ ዓክሳ ነበረች።ካሌብ፥ ቂርያትሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ በማለቱ ለቄኔዝ ልጅ ለጎቶንያል አጋባው። (ኢያ 15:16-19 መሣ 1:9-15)

ዓክቦር~ Achbor: የከበደ፣ የጠጠረ፣ የጠነከረ... መከራ ማለት ነው።

1. የኤዶም ንጉሥ የኣልሐናን አባት፥ ሳኦልም ሞተ፥ በስፍራውም ዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ።” (ዘፍ 36:3839 1 ዜና 1:49)

2. በኢዮስያ ንግሥ የነበረ፥ የሚክያስ ልጅ፥ ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን። (2 ነገ 22:1214 ኤር 26:22 36:12) ዓብዶንተብሎም ተጠርቷል፥ (2 ዜና34:20)

ዓዊት ~ Avith: አውድማ፣ ፍርስራሽ፣ ቅሪት ማለት ነው። የባዳድ ልጅ ሃዳድ የነገሠበት ከተማ ስም፥ ሑሳምም ሞተ፥ በስፍራውም ... ሃዳድ ነገሠ የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ። (ዘፍ 36:351 ዜና 1:46)

ዓዙር ~ Azur, Azzur: አዘር፣ ዘር፣ ወገን፣ ዘመድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዕዝራ]

ዘርከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዓዙር / Azur:

1. ነቢዩ የገባዖን ሰው፣ የሐናንያ አባት፥ (ኤር 281)

2. የያእዛንያን አባት፥ (ሕዝ 11:1)

       ዓዙር / Azzur: ከነቢዩ ነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተመ፥ (ነህ 10:17 18)

ዓዙባ ~ Azubah: ዛባ የተጣለ፣ የተረሳማለት ነው።

1. የኤስሮም ልጅ የካሌብ ሚስት፥ የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ ... (1 ዜና 2:1819)

2. የንጉሥ ኢዮሣፍጥ እናት፥ ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ... እናቱም ዓዙባ የተባለች የሺልሒ ልጅ ነበረች። (1 ነገ 22:42 2 ዜና 20:31)

ዓዛሪያስ ~ Azariah: ዘረ ዋስ፣ ዘረ ያሕ፣ ዘረ ሕያው፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አዛርያ፣ ዓዛርያስ፣ ዔዛርያስ]

Azariah- ዘር እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

ከሳዶቅ ወገን የሆነ ዋነኛ ካህን፥ (2 ዜና 31:10-13)

ዓዛርኤል ~ Azareel: ዘረ ኤል፣ ዘረ አምላክ፣ ዘረ ሕያው፣ የእግዚብሔር ቤተሰብ፣ የአምላክ ዘር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤዝርኤል፣ አዛርኤል]

ዘረእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኤማን ልጅ፥ (1 ዜና 25:4)

2. የይሮሐም ልጅ፥ (1 ዜና 27:22)

3. በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ አዛርኤል (1 ዜና 12)

. ኤዝርኤ (ዕዝ 10:41)

. የአሕዛይ ልጅ፥ ኤዝርኤል (ነህ 11:13)

ዓዛርያስ ~ Azariah: ዘረ ዋስ፣ ዘረ ያሕ፣ ዘረ ሕያው፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛሪያስ፣ ዔዛርያስ፣ ኤዝርኤል፣ አዛርኤል፣ ዓዛርኤል]

ዘር እና ዋስ፣ ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የአኪማአስ ልጅ፥ አኪማአስም ዓዛርያስ ወለደ” (1 ዜና 6:9) (1 ነገ 4:2)

2. የንጉሥ ሰሎሞን የሹሞች አለቃ የነበረ፣ የናታን ልጅ፥ (1 ነገ 4:5)

3. የይሁዳ ንጉሥ፣ የአሜስያስ ልጅ፥ (2 ነገ 14:21 15:16817

2327 1 ዜና8:12)

4. የኢዩ ልጅ፥ ኢዩም ዓዛርያስ ወለደ (1 ዜና 2:3839)

5. የዮሐናን ልጅ፥ (1 ዜና 6:10)

6. የኬልቅያስ ልጅ፥ (1 ዜና 6:1314)

7. የሶፎንያስ ልጅ፥ (1 ዜና 6:36)

8. የዖዴድ ልጅ፥ (2 ዜና 15:1)

9. የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ፥ (2 ዜና 21:2)

10. ሌላ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ፥ (2 ዜና 21:2)

11. የይሮሐም ልጅ፥ (2 ዜና 23:1)

12. ካህኑ ዓዛርያስ (2 ዜና 26:17-20)

13. የዮሐናን ልጅ፥ (2 ዜና 28:12)

14.ኢዮኤል አባት፥ (2 ዜና 29:12)

15. የይሃሌልኤል ልጅ፥ (2 ዜና 29:12)

16. በንጉሡም በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ ካህን፥ (2 ዜና 31:1013)

17. በነህምያ ዘመን የኢየሩሳሌምን ቅጥር ከጠገኑ፣ የመዕሤያ ልጅ፥ (ነህ

3:2324)

18. ከዘሩባቤል ጋር ከምርኮ ከተመለሱ፥ (ነህ 7:7)

19. ከነቢዩ ዕዝራ ጋር የሕጉን መጽሐፍ ካስተማሩ፥ (ነህ 8:7)

20. ከነቢዩ ነህምያ ጋር የቃልኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት፥ (ነህ 10:2) “ዓዛርያስ ዕዝራ” (ነህ 12:33)

21. የሆሻያ ልጅ፥ (ኤር 43:2)

22. ከነቢዩ ዳንኤል ጋር ወደ ምርኮ ከተወሰዱ ሦስት ልጆች፥ የአብዲኔጎ ስም፥ (ዳን 1:671119)

ከይሁዳ ወገን፣ የኤታን ልጅ፥ የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ። (1

ዜና 2:8)

ዓዜቃ ~ Azekah: መከታ ብርቱ ግንብ ማለት ነው። በይሁዳ የታችኛ ኮረብቶች የሚገኝ ከተማ፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:36)

ዓዝሞት ~ Azmaveth: አዘ ሞት፣ እንደሞት የበረታ... ማለት ነው።

1. ከዳዊት ሠላሳ ኃያላን አንዱ፥ ዓዝሞት ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ (2 ሳሙ 23:32)

2. በንጉሥ ዳዊትና ሰሎሞን ዘመን የነበረ፥ የመዝገብ ቤት ላፊ፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ ... (1 ዜና 27:25)

3. በኢየሩሳሌም አቅራቢያ የነበረ፥ የይሁዳ ነገድ ከተማ፥ ...የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። (ነህ 12:29 ዕዝ 2:24)

4. የዓሌሜት ልጅ፥ አካዝም ይሆዓዳን ወለደ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። (1 ዜና 8:36)

ዓዝሪቃም ~ Azrikam: አዛረ ቆመ፣ ዘረ ቋሚ፣ ቋሚ ዘር፣ ለወገን ደራሽ፣ ረዳት... ማለት ነው።

ዘረ እና ቆመ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከይሁዳ ነገድ የዘረባቢሎን ወገን፣ የነዓርያ ልጅ፥ (1 ዜና 323)

2. ከሳ ወገን፣ የኤሴል ልጅ፥ (1 ዜና 8:38 9:44)

3. በነህምያ ዘመን የኖረ፣ ከሜራሪ ልጆች፣ የአሳብያ (1 ዜና 9:14) (ነህ11:15)

4. በንጉሥ አካዝ ዘመን፣ ዝክሪ የገደለው፥ (2 ዜና 28:7)

ዓዝሪኤል ~ Azriel: አዛረ ኤል፣ ዘረ ኤል፣ ዘረ አምላክ፣ የጌታ ወገን፣ የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝርኤል፣ ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ አዛርኤል ዓዛርኤል]

ዘረእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በንፍታሌም ላይ አለቃ የነበር፣ የኢያሪሙት አባት፥ (1 ዜና 27:19)

ዓዝርኤል ~ Azriel: አዛረ ኤል፣ ዘረ ኤል፣ ዘረ አምላክ፣ የጌታ ወገን፣ የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ አዛርኤል፣ ዓዛርኤል]

ዘረ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አለቃ፥ (1 ዜና 524)

2. የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም ያዘዘው፥ የሠራያ ልጅ፥ (ኤር 6:26)

ዓዝጋድ ~ Azgad: እዘ ገድ፣ በገድ የታዘዘ... ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የዓዝጋድ ልጆች ይገኙበታል፥ ዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት።” (ነህ 7:17)

ዓይናም ~ Enam: አይናም፣ የሚታይ፣ ገላጣ ስፍራ... ማለት ነው። በረባዳው የይሁዳ ክልል ያለ የይሁዳ ከተማ፥ ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም የርሙት (ኢያ 15:35)

ዓይን ~ Ain: ምንጭማለት ነው።

1. የፍልስጥኤም ምሥራቃዊ ዳርቻ የሆነ ጉልህ ሥፍራ፥ ዳርቻውም ከሴፋማ ዓይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ ሪብላ ይወርዳል ... (ዘኊ 34:11)

2. የይሁዳ የመጨረሻ ደቡባዊ ከተማ፥ ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን ሪሞን ሀያዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 15:32)

ዓይንሀቆሬ ~ En-hakkore: ይን አቆረ፥ የሚታይ የተጠራቀመ ውኃ፥ የጸሎት ምንጭ ጠበልማለት ነው። ምሶን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ባደረገው ፍልሚያ፥ በተጠማና ጉልበቱ በዛለ ጊዜ፥ የጸለየበት ቦታ፥ እግዚአብሔርም ... የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ።” (መሣ 15:19)

ዓይንሮጌል ~ En-rogel: ዮናታንና አኪማአስ የተሸሸጉበት ቦታ፥ ዮናታንና አኪማአስ ተገልጠው ወደ ከተማ ይገቡ ዘንድ አልቻሉም ነበርና ዓይንሮጌል ተቀምጠው ነበር፤ ...” (2 ሳሙ 17:17)

ዓይንኤግላይም ~ En-eglaim: የሁለት እምቦሶች ፏፏቴማለት ነው። በነቢዩ ሕዝቅኤል የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ አጥማጆችም በዚያ ይቆማሉ ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ መረብ መዘርጊያ ...” (ሕዝ 47:10)

ዓይንገኒም ~ En-gannim: የገነት ፏፏቴማለት ነው።

1. በይሁዳ መስክ የነበረ ከተማ፥ ዓይንገኒም ታጱዋ፥ ዓይናም፥ የርሙት” (ኢያ 15:34)

2. የዛብሎን ልጆች ርስት፥ የሆነ ከተማ፥ ወደ ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋኒም ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤትጳጼጽ ደረሰ (ኢያ 19:21)

ዓዲና ~ Adina: ማለት ነው።

አዱከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በዮርዳኖስ ማዶ የዳዊት ወታደሮች የሮቤላውያ አለቃ የነበረ፣ የሺዛ ልጅ፥ (1 ዜና 1142)

ዓዲን ~ Adin: አዲነ፣ አደን፣ ደን፣ ደኔ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዲና፣ ዓዳን፣ አዳን]

የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 21) (ነህ 1016)

ዓዲኤል ~ Adiel: አም ያሳመረው፣ የአምላክ ጌጥማለት ነው።

1. የዓዝሞት አባት፥ በንጉሥ ሰለሞን እና ዳዊት ዘመን የመዝገብ ቤት ሐላ የነበረ፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ ዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ በሜዳውም ... ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ (1 ዜና 27:25)

2. “ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል ዩሲምኤል፥ በናያስ፥” (1 ዜና 4:36)

3. የየሕዜራ ልጅ፥ ካህኑ፥ የመልኪያ ልጅ የጳስኮር ... ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ ዓዲኤል ልጅ መዕሣይ (1 ዜና 9:12)

ዓዳ ~ Adah: ጌጥ፣ ውበትማለት ነው።

1. ከላሜሕ ሁለት ሚስቶች፥ ሁለት ልጆችን የወለደችለት፥ የአንደኛዋ ስም፥ ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ የአንዲቱ ስም ዓዳ ... (ዘፍ 4:19)

2. ከዔሳው ሦስቱ ሚስቶቹ አንዷ፥ የኤልፋዝ እናት፥ ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን አህሊባማን፥” (ዘፍ 36:2101216)

ዓዳን ~ Addan, Addon: አዲነ፣ አደን፣ ደን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አዳን፣ ዓዲና፣ ዓዲን፣ ዓድና]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታዎች:-

       ዓዳን / Addan: ከምርኮ ከተመለሱባቸው ከተሞች፣ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ ካልቻሉ፥ (ዕዝ 259)

       ዓዳን / Addon: (ነህ 7:61)

ዓድላይ ~ Adlai: አድ ሚዛን፣ ፍርድ፣ ፍት... ማለት ነው። የዳዊት እረኞች አለቃ፣ የሻፍጥ አባት፥ ... በሸለቆቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ ዓድላይ ልጅ ሻፍጥ ሹም ነበረ” (1 ዜና 27:29)

ዓድና ~ Adna, Adnah: አዲነ፣ አደን፣ ደን፣ ደኔ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዲና፣ ዓዲን፣ ዓዳን፣ አዳን]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዓድና / Adna:

1. ከካህናቱ ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ፥ ከፈሐት ሞዓብ ልጅ፥

(ዕዝ 10:30)

2. በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ከነበሩ፥ (ነህ 1215)

       ዓድና / Adnah:

1. ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከከዱ፥ (1 ዜና 1220)

2. የኢዮፍጥ በኢየሩሳሌም ጽኑዓን ኃያላን ሰልፈኞች ከነበሩ፥ (2 ዜና 17:14)

ዓድዓዳ ~ Adadah: በይሁዳ ደቡባዊ ዳርቻ የሚገኝ ከተማ፥ ቀብስኤል፥ ዔዴር፥ ያጉር፥ ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን፥ ( 15:22)

ዓዶላም ~ Adullam: ዓድ ዓለም፣ ዝብ ፍርድ፣ የዓለም ፍትኅ ማለት ነው። ከጥንታዊ የከነናውያን የመናገሻ ከተማ፥ የዓራድ ንጉሥ፥ የልብና ንጉሥ፥ ዓዶላም ንጉሥ (ኢያ 12:1515:35)

ዓጣራ ~ Atarah: ዘውድማለት ነው። የይረሕምኤል ሚስት፥ የኦናም እናት፥ ለይረሕምኤልም ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው እርስዋም የኦናም እናት ነበረች።” (1 ዜና 2:26)

ዓጽሞን~ Azmon: ጽኑ፣ ብርቱ፣ ጠንካራ ማለት ነው። የቅድስት አገር ደቡባዊ ዳርቻ፥ ዳርቻችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ያልፋል መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞን ያልፋል (ዘኊ 34:45 ኢያ 15:4)

ዔሊዮዔናይ ~ Elioenai: ኤል የነ፣ አምላክ ያየው፣ ጌታ ያየው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤሊሆዔናይ፣ ኤሊዔናይ፣ ኤልዮዔናይ]

ኤል እና ይን ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በግዞት ሲኖሩ እንግዳ ሚስቶች ካገቡ፣ የዛቱዕ ልጅ፥ (ዕዝ 10:27)

ዔሳው ~ Esau: እሱ፣ ሹ፣ የእሱ ሽው... ማለት ነው። የይስሐቅ ልጅ፥ የያዕቆብ ወንድም፥ በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንተናውም ጠጕር ለብሶ ነበር ስሙም ዔሳው ተባለ። (ዘፍ25:25)

ዔሪ ~ Eri: እረኛዬ፣ ጠባቂዬ ማለት ነው። የጋድ ልጅ፥ ከሹኒ የሹናውያን ወገን፥ ከኤስናን የኤስናናውያን ወገን፥ ዔሪ የዔራውያን ወገን፥ (ዘኊ 26:16)

ዔር ~ Ar, Er: መባነ መገለጥ ማለት ነው። በሞዓባውያን ዘንድ ያለ ቦታ፥ እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ የሞዓብን ዔር የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ (ዘኊ 21:28 ኢሳ 15:1)

       ዔር / Er: እረኛ፣ ጠባቂ ማለት ነው።

1. የይሁዳ ትልቁ ልጅ፥ ፀነሰችም ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። (ዘፍ 38:3-7 ዘኊ 26:19)

2. የሴሎም ወገን፥ የሌካ አባት፥ የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ ... (1 ዜና 4:21)

3. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የኤልሞዳም አባት፥ የሚልኪ ልጅ፥ የሐዲ ልጅ፥ የዮሳስ ልጅ፥ ... ኤር ልጅ፥ (ሉቃ 3:28)

ዔቄር ~ Eker: መካን፣ ጥፍ፣ የገበረ መሬትማለት ነው። የይሁዳ ወገን፥ የይረሕምኤል የበኵሩ የራም ልጆች መዓስ፥ ያሚን፥ ዔቄር ነበሩ (1 ዜና 2:27)

ዔባል፣ ዖባል ~ Ebal: ድንጋይ ዓለትማለት ነው።

1. ከሦባል ልጆች አንዱ፥ የሦባል ልጆችም እነዚህ ናቸው ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል ስፎ፥ አውናም። (ዘፍ 36:23 1 ዜና 1:40)

2. የዮቅጣን ልጅ፥ አውዛልን፥ ደቅላን፥ ዖባልን፥ አቢማኤልን፥ (1 ዜና 1:22)

ዔቤር ~ Eber: እብር፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔብሮን፣ አቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን]

Eber- ኅብር ከሚለው ቃል የመጣ ስም ሲሆን አበረ ከሚለው ግስ የተገኘ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ (ነህ 12:20)

2. የኤልፍዓል ልጅ፥ (1 ዜና 8:12)

3. የሰሜኢ ልጅ፥ (1 ዜና 8:2223)

. የሳላ ልጅ፥ ዔቦር (ዘፍ 1024) አቤር (ሉቃ 3:35)

ዔብሪ ~ Ibri: እብር፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሮን፣ ዔቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን] ኅብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በዳዊት ዘመን የነበረ፣ የሜራሪ ልጅ፥ ዔብሪ (1 ዜና 2427)

ዔብሮና ~ Ebronah: ኤብረን፣ አብረን፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ ዔብሪ፣ አቤር፣ ዔቤር፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን]

ኅብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ፥ ከአለፉባቸው ቦታዎች፥ ከዮጥባታም ተጕዘው ዔብሮና ሰፈሩ...” (ዘኁ 333435)

ዔብሮን ~ Hebron: ሄብሮን፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ተባባሪ፣ ማኅበርተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔቤር፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን]

[ኅብረት ማለት ነው / መቅቃ]

. አብራም የሰፈረበት የቦታ ስም፥ “.. ኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ (ዘፍ 1318)

. የቀዓት ልጅ፥ (ዘጸ 6:18) (ዘኁ 3:19) (1 ዜና 6:2 18) (1 ዜና23:12)

ዔቦር ~ Eber: እብር፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔብሮን፣ ዔቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን]

ኅብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. የሳላ ልጅ፥ (ዘፍ 1024) አቤር - (ሉቃ 3:35)

. በዮአቂም ዘመን ከአባቶች ቤቶች አለቆች፣ ካህን፥ ዔቤር- (ነህ 12:20)

. የኤልፍዓል ልጅ፥ ዔቤር- (1 ዜና 8:12)

. የሰሜኢ ልጅ፥ ዔቤር- (1 ዜና 8:2223)

ዔቴር ~ Ether: ተራ ማለት ነው። በደልዳላው የይሁዳ ክፍል ያለ የይሁዳ ከተማ። ልብና፥ ዔቴር ዓሻን፥ ይፍታሕ፥ አሽና፥ (ኢያ 15:42)

ዔናቅ ~ Anak: አነቅ፥ አንገት... ማለት ነው። የአርባቅ ልጅ፥ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ... ድርሻ አድርጎ ሰጠው እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ ዔናቅ አባት ነበረ። (ኢያ 15:13 21:11)

ዔናን ~ Enan: ዓይን፣ ይናማ ማለት ነው። ራኤላውያን በሲና ምድረ ባዳ፥ የሕዝብ ቆጠራ በተደረገ ጊዜ፥ አለቃ የነበረ፥ የአኪሬ አባት፥ ከንፍታሌም ዔናን ልጅ አኪሬ” (ዘኊ 1:15)

ዔዝሪ ~ Ezri: እዝሬ፣ ዘሬ፣ ወገኔ፣ ዘመዴ፣ ረዳቴ... ማለት ነው። [ተዛማች ስም- አዛርያ]

ዘር ከሚለው ቃል ጋር የተገኘ ስም ነው። የክሉብ ልጅ፥ (1 ዜና 2726)

ዔዴር ~ Eder: እድር ማኅበር፣ መንጋ... ማለት ነው።

1. በደቡብ በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ካሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች፥ ቀብስኤል፥ ዔዴር ያጉር፥ ቂና፥” (ኢያ 15:22)

2. በዳዊት ዘመን የነበረ፥ የመራሪ ወገን፥ የሙሲ ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር ኢያሪሙት ሦስት ነበሩ።” (1 ዜና 23:23 24:30)

ዔዴን ~ Eran: እረኛ፣ ጠባቂማለት ነው። የኤፍሬም የትልቁ ልጅ፥ የሱቱላ ልጅ፥ እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው ዔዴን የዔዴናውያን ወገን። ከዔዴን የዔዴናውያና ወገን” (ዘኊ 26:36)

ዔድን ~ Eden: አስደሳችማለት ነው።

1. የመጀመሪ ሰዎች መኖሪያ፥ እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ ዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው። (ዘፍ 2:8-17)

2. ካራንና ካኔ ዔድን ነጋዴዎችሽ ነበሩ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ ነበሩ።” (ሕዝ 27:23)

3. የዩአክ ልጅ፥ ሌዋውያኑም፥ ... የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች የዛማት ልጅ ዩአክና የዩአክ ልጅ ዔድን” (2 ዜና 29:12)

ዔግላ ~ Eglah: ጊደርማለት ነው። ዳዊት በሔብሮን በነገሠ ጊዜ የነበረችው ሚስት፥ ስድስተኛውም የዳዊት ልጅ ሚስት ዔግላ ልጅ ይትረኃም ነበረ። እነዚህም ለዳዊት በኬብሮን ተወለዱለት።” (2 ሳሙ 3:5 1 ዜና 3:3)

ዔግሎም ~ Eglon: ጥጃ፣ እምቦሳ... ’ ማለት ነው።

1. የሞባውያን ንጉሥ፥ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎም በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። (መሣ 3:12)

2. የይሁዳ የታችኛው ግዛት ከተማ፥ ኦዶላም፥ ኦዶላም ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ ስድስት ከተሞችና መደሮቻቸው።” (ኢያ 15:39)

ዔጼም ~ Ezem: አጽም፣ አጥንት... ማለት ነው። ከሺሞን ከተሞች አንዱ፥ በሐጸርሹዓል፥ በቢልሃ፥ ዔጼም” (1 ዜና 4:29)

ዔጽዮንጋብር ~ Eziongaber: ጽዬን ገብር፣ ገብረ ጽዮን፣ የጽዮን አገልጋይ፣ መመኪያ... ማለት ነው።

ጽዮንእና ገብርከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ ወጡ ጊዜ፥ ያለፉበት የቦታ ስም፥ ከዔብሮናም ተጕዘው ዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።” (ዘኁ 3335)

ዔፋ ~ Ephah: የጠወለገ፣ የደከመማለት ነው።

1. በይሁዳ የዘር ሐረግ፥ የካሌብ ቁባት የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች።” (1 ዜና 2:46)

2. ሔፋ፥ ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። የያዳይም ልጆች ሬጌም፥ ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ ሸዓፍ ነበሩ። (1 ዜና 2:47)

ዔፌር ~ Epher: አፈር፣ ትቢያ፣ አቧራ... ማለት ነው።

አፈርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የምድያም ልጅ፥ (ዘፍ 25:4)

2. ከጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበረ፥ (1 ዜና 5:24)

ዕላም ~ Jaalam: የለም፣ ጠፋ፣ ተሰወረ... ማለት ነው። የዔሳው ልጅ፥ አህሊባማም የዑስን፥ ዕላምን፥ ቆሬን ወለደች በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው።” (ዘፍ 36:51418)

ዕሢኤል ~ Jaasiel, Jasiel: የሢ ኤል፣ የአምላክ ሥራ ያምላክ ኃይል... ማለት ነው።

       ዕሢኤል / Jaasiel: የዳዊት ጭፍራ፣ የአበኔር ልጅ፥ (1 ዜና 27:21)

       ዕሢኤል / Jasiel: ኤልኤል፥ ዖቤድ፥ ምጾባዊው ዕሢኤል:” (1

ዜና 11 47)

ዕቃ ቤቱ ~ Asuppim: ማከማቻ፣ ማጠራቀሚያማለት ነው። የካህናቱ አልባሳትና የንዋየ ቅዱሳት ማስቀመጫ ክፍል፥ በምሥራቅ በኩል ስድስት ሌዋውያን ነበሩ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ዕቃ ቤቱ ሁለት ሁለት ነበሩ።” (1 ዜና 26:1517)

ዕብራዊ ~ Hebrew: ብሪው፣ ዕብር፣ ዕብራዊ፣ ብራይስጥ... ማለት ነው።

ኅብር ከሚለው ቃል የመጣ የነገድ ስም ነው።

አብራም ዕብራዊ ተብሎ ተጠራ፥ አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ዕብራዊ ለአብራምም ነገረው እርሱም ...” (ዘፍ 14:13)

. ዮሴፍ ዕብራዊ ተብሎ ተጠራ፥ (ዘፍ 4112)

. የአማቴ ልጅ፣ ነቢዩ ዮናስ፥ እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ ...” (ዮና 1:9)

. ሐዋርያው ጳውሎስ፥ “... ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ” (ፊል 3:5)

ዕንባቆም ~ Habakkuk: ንባ አቁም፣ አጽናኝ፣ አስተዛዛኝ፣ ለመከራ ደራሽ፣ የሐዘን አስረሽ፣ ከጭንቅ አዳኝ... ማለት ነው።

ንባ እና አቁም ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት በስምንተኛ ተራ ላይ ይገኛል፥ ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው። (ዕንባ1:1)

ዕዝራ ~ Ezra: እዝራ፣ ዘረ፣ ዘር፣ ወገን፣ ዘመድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዓዙር]

ዘረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር ከምርኮ የተመለሰ፣ የሠራያ ልጅ፥ (ዕዝ7: 1) (ነህ 122)

ዖሜጋ ~ Omega: የግሪክ የመጨረሻው ፊደል። የሁሉ ነገር ፍጻሜና መጨረሻ መግለጫ ሁኖ ያገለግላል፥ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል (ራእ 1:811)

ዖምሪ ~ Omri: ኦማር፣ ማሪ፣ ሪ፣ ይቅር ባይ፣ አምላካዊ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ኦማር፣ አምሪ]

በዚህ ስም የሚታወቁ አራት ሰዎች አሉ።

1. የቤኬር ልጅ፥ (1 ዜና 7:8)

2.የሚካኤል ልጅ (1 ዜና 27:18)

3. የባኒ ልጅ፥ (1 ዜና 9:4)

. ኦማር- (1 ነገ 16:15-27)

ዖርፋ ~ Orpah: አንገትማለት ነው። የኑኃሚን፥ ምራት፥ የልጇ ሚስት፥ እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። በዚያም አሥር ዓመት ተቀመጡ” (ሩት 1 2:414)

ዖባል ~ Obal: እራቁትማለት ነው። የዮቅጣን ልጅ፥ ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥” (ዘፍ 10:28)

ዖቤድኤዶም ~ Obed-Edom: የኤዶም አገልጋይ ማለት ነው።

1. ሌዊያዊ፥ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ጠባቂዎች አንዱ እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥” (1 ዜና 26:14-8)

2. የደቡባዊውን መግቢያ ከሚጠብቁ፣ ከቤተመቅደሱ በረኞች አንዱ፥ ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ... በረኞችንም ዖቤድኤዶምንና ይዒኤልን አቆሙ።” (1 ዜና 15:182126:4815)

3. የቤተ መቅደሱ ዕቃ ቤትና የንጉሡን መዛግብት አለቃ፥ ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ የንጉሡን ቤት መዛግብት፥ ...” (2 ዜና 25:24)

ዖትኒ ~ Othni: የሕያው አንበሳ ማለት ነው። የሸማያ ልጅ፥ ለሸማያ ልጆች ዖትኒ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም... (1 ዜና 26:7)

ዖዛ ~ Uzzah: ጥንካሬ ማለት ነው። የአሚናዳብ ልጅ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት ... የአሚናዳብ ልጆችም ዖዛ እና አሒዮ አዲሱን ሰረገላ ይነዱ ነበር” (2 ሳሙ 6:3)

ዖዛዝ ~ Azaz: ዥ፣ ብርቱ ማለት ነው። የቤላ አባት፥ ዘካርያስ፥ እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዮኤል ልጅ የሽማዕ ልጅ ዖዛዝ ልጅ ቤላ” (1 ዜና 5:8)

ዖዛያ ~ Hazaiah: ሕያው አምላክ ያየውማለት ነው። የሴሎናዊውያን ወገን የሆነ የይሁዳ ሰው። የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ ዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። (ነህ 11:5)

ዖዝያ ~ Uzziah: የሕያው ኃይልማለት ነው።

1. የይሁዳ ንጉሥ፥ አባቱም ዖዝያ እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር።” (2 ዜና 27:2)

2. ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡሩኤል፥ ልጁ ዖዝያ ልጁ ሳውል።” (1 ዜና 6:24)

3. የካሪም ልጅ፥ ከካሪም ልጆችም መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤል፥ ዖዝያ” (ዕዝ 10:21)

4. የዘካርያስ ልጅ፥ ...ከይሁዳ ልጆች ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ ዖዝያ ልጅ አታያ (ነህ 11:4)

5. የዮናታን አባት፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ በሜዳውም ... ላይ ዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ” (1 ዜና 27:25)

ዖዝያን ~ Ozias: የጌታ ኃይል ማለት ነው። አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያን ወለደ፤” (ማቴ 1:89)

ዖዴድ ~ Oded: ማዋደድ፣ ማስማማት፣ ማነጽ፣ መጠገን... ማለት ነው።

1. የነቢዩ ዓዛርያስ አባት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ ዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ ሆነ” (2 ዜና 15:18)

2. በንጉሥ አካዝ ዘመን የነበረ ሌላ ነቢይ፥ በዚያም ዖዴድ የተባለ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበረ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ ...” (2 ዜና 28:9-15)

ዖፌል ~ Ophel: ኮረብታማለት ነው። የጥንታዊ ኢየሩሳሌም ክፍል፥ የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ ዖፌል ቅጥር ...” (2 ዜና 27:3)

ዖፍኒ ~ Ophni: ሻጋታ ማለት ነው። የብንያማውያን ከተማ፥ ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥ ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ ጋባ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 18:24)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ