ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ነሃሊኤል ~ Nahaliel: ‘ውርስ’
ማለት ነው።
እስራኤል በጉዟቸው
ከሰፈሩባቸው ቦታዎች አንዱ፥ “ከምድረ በዳም ወደ መቴና ተጓዙ ከመቴናም ወደ ነሃሊኤል፥ ከነሃሊኤልም
ወደ ባሞት፥” (ዘኊ 21:19)
ነሐማኒ ~ Nahamani: ናሆማኒ፣ ዕረፍት፣ መረጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ነሐም፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ]
በነህምያ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ፥ ከነሐማኒ፥ (ነህ 7:7)
ነሐም ~ Naham:
ናሆም፣ ዕረፍት፣ መርጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነሐማኒ፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ] የሆዲያ ሚስት፥ ነሐም፥ (1
ዜና 4:19)
ነሃራይ ~ Naharai: ‘እንኩርፊያም’ ማለት ነው። ቤሮታዊው
የዳዊት ወታደር፥ “አሞናዊው ጼሌቅ፥ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ነሃራይ”
(1 ዜና 11:39)
ነሑም ~ Nehum: ናሆም፣ ነሆመ፣ ዐረፈ፣ ዕረፍት፣ መረጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ነሐማኒ፣ ነሐም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ]
የባቢሎን ንጉሥ
ናቡከደነፆር ወደ
ባቢሎን ከማረካቸው
ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች፥ (ነህ 7:7)
ነሑሽታ ~ Nehushtan: ነሐስ፣ ነሐሳት... ማለት ነው። ሙሴ በበረሃ እባብን የሠራበት ብረት፥ “ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።” (ዘኊ 21:9) ፥ በሕዝቅያስ ዘመን ይመለክ ነበር፥ (2
ነገ 18:4)
ነህላል ~ Nahallal:
‘ምስጉን’ ማለት
ነው። በይሳኮር
ድንበር የነበረ፥
የዘብሎን ከተማ፥ “ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም አሥራ ሁለት ከተሞችና
መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 19:15)
ነህምያ ~
Nehemiah:
ናሆመ ያሕ፣ የሕያው ዕረፍት፣ የመረጋጋት ጌታ፣ የመጽናናት ባለቤት፣ ዘላለማዊ ዕረፍት.. ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ነሐማኒ፣ ነሐም፣ ነሑም፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ]
‘ነሆም’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ
ይሁዳ ወደ
እየከተማቸው ከተመለሱ
የአገር ልጆች፥
የሐካልያ ልጅ፥ (ነህ 7:7) ፣ (ዕዝ 2:2፣ ነህ 3:16 ፣ ነህ 1:1)
2.
ከግዞት መልስ ኢየሩሳሌምን ካደሱ፥ የዓዝቡቅ ልጅ፥ (ነህ 3:16)
ነሙኤል ~ Nemuel: ‘የጌታ ቀን’ ማለት ነው።
1. ሮቤናዊው፥ የኤልአብ ልጅ፣
የዳታንና የአቤሮን ወንድም፥ “የኤልያብም ልጆች
ነሙኤል፥ ዳታን፥
አቤሮን እነዚህ
ዳታንና አቤሮን
ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ተጣሉ” (ዘኊ 26:9)
2. “የስምዖን
ልጆች በየወገናቸው
ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን
የያሚናውያን ወገን፥
... የዛራውያን ወገን” (ዘኊ
26:12፤ 1
ዜና 4:24)
ነምራ ~ Nimrah: ‘ንጹሕ’
ማለት ነው።
በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ
የነበረ ከተማ፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥
ነምራ፥ ሐሴቦን፥
ኤልያሊ፥ ሴባማ፥
ናባው፥ ባያን፥
ለእንስሶች የተመቸ
ምድር ነው፤ ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን” (ዘኊ 32:3)
ነባዮት ~ Nebaioth, Nebajoth: ነቢያት፣ ትንቢት፣ የሊቃውንት ቃል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ናቡቴ፣ ናባው፣ ኖባይ]
‘ነቢይ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
ነባዮት / Nebaioth: የእስማኤል የበኵር ልጅ፥ ነባዮት፥ (1
ዜና
1:29)
ነባዮት / Nebajoth:
(ዘፍ 25:13፣14)
ነብዳኤል ~ Adbeel: ‘የአምላክ ተአምር’
ማለት ነው።
የእስማኤል ልጅ፥ “የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር
ልጁ ነባዮት፥
ቄዳር፥ ነብዳኤል፥
መብሳም፥ ማስማዕ” (ዘፍ
25:13፤ 1
ዜና 1:29)
ነታንያ ~
Nethaniah:
ሕያው ስጦታ፣ የአምላክ በረከት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ናታንያ]
‘ናታን’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ህያዊ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል የተለዩ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ፥ (1 ዜና 25:2 ፣ 12)
2. የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ካዘዛቸው አንዱ፥ (2 ዜና 17:8)
. የኤሊሳማ ልጅ፥
ናታንያ-
(2 ነገ 25:23
፣ 25)
. የሰሌምያ ልጅ፥ ናታንያ-
(ኤር 36:14)
ነነዌ ~ Nineveh: ‘ውብ፣ ቅን’ ማለት
ነው። የጥንታዊ
የአሦርያ ዋና
ከተማ የነበረ፥ “አሦርም ከዚያች አገር ወጣ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ... ” (ዘፍ 10:11)
ነአሶን ~ Naashon, Nahshon: ‘ትንበያ፣ ጥንቆላ’ ማለት ነው። የአሮን
ሚስት፣ የኤልሳቤጥ
እኅት፥ “አሮንም የአሚናዳብን
የነአሶንን እኅት
ኤልሳቤጥን አገባ፥
እርስዋም ናዳብንና
አብዮድን አልዓዛርንና
ኢታምርን ወለደችለት” (ዘጸ
6:23)
ነአሶን /
Nahshon: ‘ጠንቋይ፣ አዋቂ’ ማለት ነው። እስራኤላውያን በምድረ
በዳ ለመጀመሪያ
ጊዜ ሲቆጠሩ
የነበረ የይሁዳ
ወገን፥ መስፍኑ
የአሚናዳብ ልጅ፥ “አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፥ እርስዋም ናዳብንና አብዮድን
አልዓዛርንና ኢታምርን
ወለደችለት”
(ዘጸ 6:23)
ነዓም ~
Naam:
‘ተወዳጅ፣ አስደሳች’
ማለት ነው። የዮፎኒ ልጅ፣ የካሌብ ልጅ፥ “የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ።”
(1 ዜና 4:15)
ነዓርያ ~ Neariah: ‘የሕያው አገልጋይ’
ማለት ነው።
1. ከስድስቱ የሸማያ ልጆች አንዱ፥ “...የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግኣል፥ ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ።” (1 ዜና 3:22፣ 23)
2. የይሽዒ ልጅ፥ “የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ” (1 ዜና 4:42)
ነዕማታዊ ~ Naamathite:
ናማታይት፣ ነምታውያን፣ የንዕማን ሰዎች... ማለት ነው።
ከሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች አንዱ፣ ሶፋር ነዕማታዊው ተብሎ ተጠርቷል፥ (ኢዮ 2:11)
ነዕራ ~ Naarah: ‘ወጣት፣ ታዳጊ’ ማለት ነው። የአሽሑር
ሚስት፥ (1 ዜና 4:5፣6)
“ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።”
ነዋት ~ Naioth: ‘ነዋሪያት፣ ነዋሪ፣
ባለአገር፣ አገርተኛ’ ማለት ነው። “ሳኦልም። ዳዊት፥ እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ተቀምጦአል የሚል ወሬ ሰማ።” (1 ሳሙ 19:18፣19፣22፣23)
ነዌ ~
Non, Nun: ‘ዓሳ’
ማለት ነው። “ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ” (1 ዜና 7:27)
ነዌ /
Nun: የእስራኤላውያን መሪ፣ የኢያሱ አባት፥ “እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመለስ ነበር። ነገር ግን ሎሌው ብላቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።” (ዘጸ 33:11)
ነዳብያ~
Nedabiah: ነደ ሕያው፣ ሕያው የነዳው፣ አምላክ የመራው... ማለት ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ፥ የይኮንያ ልጅ፥ “ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።” (1 ዜና 3:18)
ኑኃሚ ~
Naomi:
ናሆሜ፣ ተወዳጅ፣ ቅን፣ ትሑት፣ ተግባቢ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነሐማኒ፣ ነሐም፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ]
[ትርጉሙ ደስታዬ
ማለት ነው
/ መቅቃ]
የአቤሜሌክ ሚስት፥ የሩት አማት፥ (ሩት 1:2 ፣ 20 ፣ 21...)
ኒሳን ~ Nisan, Sivan:
‘እሾህ፣ ቋጥኝ’
ማለት ነው።
የአይሁድ የተቀደሰ
ዓመት የመጀመሪያ
ወር፥ “በንጉሡ በአርጤክስስ
በሀያኛው ዓመት
በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ...” (ነህ 2:1)
ኒሳን /
Sivan:
የአይሁድ የወር ስም፥ “በዚያን ጊዜም ኒሳን በተባለው በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሀያ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ...” (አስ 8:9)
ኒቃሮና ~ Nicanor: ‘አሸናፊ’
ማለት ነው።
በሐዋርያት ቤተ
ክርስቲያን ከተሾሙ፥
ከሰባቱ ዲያቆናት፥
“ይህም ቃል ሕዝብን
ሁሉ ደስ
አሰኛቸው፤ እምነትና
መንፈስ ቅዱስም
የሞላበትን ሰው
እስጢፋኖስን ፊልጶስንም
ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም
ጢሞናንም ... የአንጾኪያውን
ኒቆላዎስንም መረጡ።” (ሐዋ
6:1-6)
ኒቆላውያን ~ Nicolaitanes: ‘የኒቆላዎስ ተከታዮች’ ማለት
ነው። የኤፌሶን
ቤተ ክርስቲያን
አባላት እንዳይከተሉ
ከተነገራቸው እምነቶች፥
“ነገር ግን ይህ
አለህ፤ እኔ
ደግሞ የምጠላውን
የኒቆላውያንን ሥራ
ጠልተሃልና።”
(ራእ 2:6)
ኒቆላዎስ ~ Nicolas: ‘አሸናፊ ሕዝብ፣ የሕዝብ ድል’ ማለት ነው። ከሰባቱ
ዲያቆናት አንዱ፥
“ይህም ቃል ሕዝብን
ሁሉ ደስ
አሰኛቸው፤ ... ጢሞናንም
ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ
የነበረውን የአንጾኪያውን
ኒቆላዎስንም መረጡ።” (ሐዋ
6:5)
ኒቆዲሞስ ~
Nicodemus:
‘አሸናፊ ሕዝብ፣ የሕዝብ ድል’ ማለት ነው። ፈሪሳዊ፥ የአይሁድ መሪና
የሕዝቡ አስተማሪ፥
“ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ
አለቃ የሆነ
ኒቆዲሞስ የሚባል
አንድ ሰው
ነበረ፤ እርሱም
በሌሊት ወደ
ኢየሱስ መጥቶ።” (ዮሐ
3:1፣10)
ኒቆጵልዮ ~ Nicopolis: ‘የድል ከተማ’ ማለት
ነው። ጳውሎስ
ክረምትን ለማሳለፍ
ያሰበበት፥ “አርጢሞንን ወይም
ቲኪቆስን ወደ
አንተ ስልክ፥
ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጬአለሁና” (ቲቶ 3:12)
ኒብሻ ~
Nibshan:
‘ለም አፈር’ ማለት ነው። ከስድስቱ የይሁዳ ከተሞች አንዱ፥ “ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 15:62)
ኒዓ ~ Neah: ‘ዓ፣ ንዐ፣ ና’
ማለት ነው።
የዘብሎን አዋሳኝ
የሆነ፥ ጉልህ
ቦታ፥ “ወደ ዳብራትም
ወጣ፥ ወደ
ያፊዓም ደረሰ። ከዚያም
በምሥራቅ በኩል
ወደ ጋትሔፍርና ወደ
ዒታቃጺን አለፈ
ወደ ሪምንና
ወደ ኒዓ ወጣ።” (ኢያ 19:13)
ኒካዑ ~ Necho: ‘ንክ፣ ስንኩል፣
አንካሳ’
ማለት ነው።
የግብፅ ንጉሥ፥
“ከዚህም ሁሉ በኋላ፥ ኢዮስያስም ቤተ መቅደሱን ካሰናዳ በኋላ፥ የግብፅ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ
ባለው ...” (2 ዜና 35:20፣22፥36:4)
ናሆም ~
Nahum:
ናሆም፣ ዕረፍት፣ መረጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነሐማኒ፣ ነሐም፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ንዕማን፣ ኖሐ፣ ኖኅ]
[ትርጉሙ መጽናናት
ማለት ነው
/ መቅቃ]
ከደቂቀ ነቢያት አንዱ፣ በተራ ሰባተኛ፣ ኤልቆሻዊው ነቢዩ ናሆም፥ “ስለ ነነዌ የተነገረ ሸክም የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው።” (ናሆ 1:1)
ናሆም ~ Naum: ‘መጽናናት፣ መረጋጋት’ ማለት
ነው። በጌታ
የዘር ሐረግ
የተጠቀሰ፣ የኤሊ ልጅ፥ የአሞጽ አባት፣ “የዮና ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ፥ የአሞጽ ልጅ፥ የናሆም ልጅ፥ የኤሲሊም ልጅ” (ሉቃ 3:25)
ናሖት ~ Nahath: ‘ዕረፍት’ ማለት ነው።
1. ከኤዶም መሳፍንት አንዱ፥ የራጉኤል ትልቁ ልጅ፥ “የራጉኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች
ናቸው።”
(ዘፍ 36:13፣17፤ 1 ዜና 1:37)
2. የሕልቃና ልጅ፥ ናሐት፥ “ልጁ ናሐት፥ ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ
ሕልቃና።”
(1 ዜና 6:26)
3. በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን የነበሩ የዕቃ ቤት ተቆጣጣሪዎች አንዱ፥ “በንጉሡም በሕዝቅያስና
በእግዚአብሔር ቤት
አለቃ በዓዛርያስ
ትእዛዝ ይሒዒል፥
ዓዛዝያ፥ ናሖት፥
...ከሰሜኢ እጅ
በታች ተቈጣጣሪዎች
ነበሩ።”
(2 ዜና 31:13)
ናምሩድ ~ Nimrod: ማራድ፣
ማንቀጥቀጥ፣ ኃይለኛ
መሆን... ማለት ነው።
የኩሽ ልጅ፥ “ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ”
(ዘፍ 10:8-10)
ናሳራክ ~ Nisroch: ንስር
ማለት ነው።
የነነዌ ሰዎች ያመልኩት የነበረ
ጣዖት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬ በልጆቹ የተገደለበት ያመልከው የነበረ፥ “በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አደራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን ...ነገሠ” (2 ነገ 19:37፤ ኢሳ 37:38)
ናቡቴ ~
Naboth:
ነቦት፣ ነቢያት፣ ነቢይ፣ ትንቢት ተናጋሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነባዮት፣ ናባው፣ ኖባይ]
‘ነቢያት’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
ኢይዝራኤላዊ፥ “የእስራኤልም ንጉሥ
ኢዮራም የይሁዳም
ንጉሥ አካዝያስ
በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፥ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።” (2 ነገ 9:25፣ 26)
ናቡከደነፆር ~ Nebuchadnezzar: ነቢይ ከዳኛ ዘር፣ የትልቅ ሰው ዘር... ማለት ነው። ከባቢሎን ነገሥታት ሁሉ ኃይለኛውና ታዋቂው፥ “የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።” (ዳን 1:1)
ናቡዘረዳን ~
Nebuzaradan:
ነቡ ዘረ ዳን፣ ነቢይ ዘረ ዳን፣ የዳን ዘር ነቢዩ፣
የባለ ሥልጣን ወገን፣
የትልቅ ሰው
ዘር፣ የመሳፍንት
ወገን... ማለት ነው።
‘ነቢይ’ ፣ ‘ዘር’ እና ‘ዳኝ’
ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. የባቢሎን ንጉሥ ባሪያ የዘበኞቹ አለቃ፥ (2 ነገ 25:8-20)
. “የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ ያዘዘው።” (ኤር 39:11፣ 40:2-5)
ናቢ ~ Nahbi: ‘ስውር፣ ምሥጢረኛ’ ማለት ነው። የከነዓንን
ምድር እንዲሰልሉ
ከተላኩ አሥራ ሁለት ሰዎች አንዱ፥ የንፍታሌም ወገን፥ የያቢ ልጅ፥ “ከንፍታሌም ነገድ
የያቢ ልጅ
ናቢ”
(ዘኊ 13:14)
ናባል ~ Nabal: ‘ቂል’
ማለት ነው።
የካሌብ ወገን፥
“ናባልም ለዳዊት
ባሪያዎች። ዳዊት ማን ነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? እያንዳንዳቸው ከጌቶቻቸው የኰበለሉ ባሪያዎች
ዛሬ ብዙዎች
ናቸው”
(1 ሳሙ 25:10፣11)
ናባው ~
Nebo:
ነቢይ፣ ዐዋቂ፣ ጠቢብ፣ ጠንቋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነባዮት፣ ናቡቴ፣ ኖባይ]
‘ነቢይ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው። [የባቢሎናውያን
የዕውቀት አምላክ
/ መቅቃ]
በዚህ ስም የሚታወቁ የሰው፣ የተራራና፣ የአገር ስሞች አሉ።
1. በእስራኤላውያን ከተደመሰሱ አገሮች፥
(ዘኁ 32:34)
2. ከባቢሎን ጣዖታት አንዱ፥ “ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ ጣዖቶቻቸው ...” (ኢሳ 46:1)
3. በሞዓብ ምድር ሙሴ የቃል ኪዳኑን አገር ለማየት የወጣበት ተራራ ስም፥ (ዘዳ 32:49፣ 34:1)
4. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የአባታቸው ስም ፥ አንዱ፥ “የናባው ልጆች፥ አምሳ ሁለት።” (ዕዝ 2:29)፣ (ነህ 7:33)
ናባጥ ~
Nebat:
‘ገጽታ’ ማለት ነው። የኢዮርብዓም አባት፥ “ከሳሪራ አገር የሆነ የሰሎሞን ባሪያ የኤፍሬማዊው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በንጉሡ ላይ ዐመፀ እናቱም
ጽሩዓ የተባለች
ባልቴት ሴት
ነበረች።”
(1 ነገ 11:26፥ 12:2፣15)
ናታን ~ Nathan: ናታን፣
ስጦታ፣ በረከት፣
ጌታነት... ማለት ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. በነብዮ ዕዝራ ዘመን፥ ከምርኮ መልስ፥ ከካህናቱ ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ካገቡ የባኒ ልጅ፥ (ዕዝ 8:16)
2. የዳዊት ልጅ፥ ናታን፥
(1 ዜና 3:5)
3. ነቢዩ ናታን፥ (2 ሳሙ 7:2፣ 3፣ 17)
ናታንሜሌክ ~ Nathan-melech:
ናታን መላክ፣ የጌታ መልአክ፣ የአምላክ ስጦታ፣ የእግዚአብሔር ንብረት... ማለት ነው።
‘ናታን’ እና ‘መላክ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ የነበረው ጃንደረባ፥ (2ነገ 23:11)
ናትናኤል ~ Nathanael, Nethaneel:
ናታን ኤል፣ የጌታ ስጦታ፣ የአምላክ በረከት፣ ጸጋ እግዚአብሔር፣ ሀብተ መለኮት... ማለት ነው።
‘ናታን’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[የእግዚአብሔር ስጦታ
ማለት ነው
/ መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ናትናኤል / Nathanael: የጌታ ሐዋርያ የሆነው፥ (ዮሐ 21:2)
ናትናኤል / Nethaneel:
የሶገር ልጅ፥ ናትናኤል፥ (ዘኁ 1:8፣ 7:18)
የንጉሥ ዳዊት ወንድም፣ የእሴይ ልጅ፥ ናትናኤል፥ (1 ዜና 2:14)
በዳዊት ዘመን በታቦቱ ፊት እየሄደ መለከት የሚነፋ የነበር፣ ካህኑ፥ ናትናኤል፥
(1 ዜና 15:24)
የጸሐፊው የሸማያ
አባት፥ (1 ዜና 24:6)
የዖቤድኤዶ ልጅ፥
(1 ዜና 26:4)
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሕዝቡን እንዲያስተምሩ ከላካቸው፥ (2
ዜና 17:7)
ለፋሲካ አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ከሰጡ፥
(2 ዜና 35:9)
በዕዝራ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ፣ እንግዳ ሚስቶች ካገቡ፥ (ዕዝ 10:22)
በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች አንዱ፥ (ነህ 12:21)
ዘማሪው፣ የዮናታን
ልጅ፥ (ነህ 12:36)
ናዕማ ~ Naamah: ‘ተወዳጅ’ ማለት ነው።
1. የቱባልቃይንም እኅት፥ የላሜሕ ልጅ፥ (ዘፍ4:22) “ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም
እኅት ናዕማ ነበረች”
2. የይሁዳ ንጉሥ፣ የሰሎሞን
ልጅ፣ የሮብዓም እናት፥ “የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ነገሠ ... የእናቱም ስም ናዕማ ነበረ እርስዋም አሞናዊት
ነበረች።”
(1 ነገ 14:21፣31)
3. በይሁዳ ደልዳላው ክፍል የነበረ ከተማ፥ “ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 15:41)
ናዖስ ~
Nahash:
‘መርዘኛ እባብ፣ ተንኮለኛ ሰው’ ማለት ነው።
1. የአሞራውያን ንጉሥ፥ “አሞናዊውም ናዖስ። ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ
በማውጣት ቃል
ኪዳን አደርግላችኋለሁ በእስራኤልም ሁሉ ላይ
ስድብ አደረጋለሁ
አላቸው።”
(1 ሳሙ 11:2-11)
2. በሳሙኤል መጽሐፍ የተጠቀሰ
ሌላ ሰው፥ “አቤሴሎምም ... የጽሩያን እኅት የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር” (2 ሳሙ 17:25)
ናዖድ ~
Ehud:
ውሕድ፣ ውሑድ፣ እሑድ፣ አሐድ፣ አንድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤሁድ]
Ehud-
‘እሑድ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም
ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የቢልሐን ልጅ፥ (1 ዜና 7፡10)
2.የጌራ ልጅ፥
(መሣ 3:15)
ናኮር ~ Nahor: ‘ማንኮራፋት’ ማለት ነው።
. የአብርሃም አያት፥ የታራን አባት፥ የሴሮሕ ልጅ፥ (ዘፍ 11:22-
25) “ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ”
. (ዘፍ 11:26፣ 27)
“ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።
ናኮን~ Nachon: ‘ዝግጁ’
ማለት ነው።
(2 ሳሙ 6:6)
“ወደ ናኮንም
አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ”
ናዝራዊ ~Nazareth:
ንጽረት፣ ናጽራዊ፣
ነጻሪ፣ አነጣጣሪ፣
አስተዋይ፣ የወደፊቱን አርቆ የሚያይ፣ ነቢይ፣ ባሕታዊ፣ መናኝ ማለት ነው።
‘ነጸረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
“ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው። ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፥” (ዘኁ 6:2-21)
የናዝራዊነት መለያ ባሕርያት:-
. “ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ የወይን
እሸት ወይም
ዘቢብ አይብላ።”
. “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም። ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም
ጠጕር ያሳድጋል”
. “ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ።”
. “ለአምላኩ ያደረገው ስእለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ
ወይም እኅቱ
ሲሞቱ ሰውነቱን
አያርክስባቸው።ራሱን የተለየ
ባደረገበት ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው”
. “ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።”
. “ካህኑም አንዱን
ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርበዋል
በሬሳም የተነሣ
ኃጢአት ሠርቶአልና
ያስተሰርይለታል፥ በዚያም
ቀን ራሱን ይቀድሰዋል”
. “ራሱን የተለየ ያደረገበትን ወራትም ለእግዚአብሔር ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት
ጠቦት ለበደ
መሥዋዕት ያምጣ
ናዝራዊነቱ ግን
ረክሶአልና ያለፈው
ወራት ሁሉ
ከንቱ ይሆናል።”
ናይ ~ Nain: ‘ውበት፣ አስደሳች’ ማለት ነው። በገሊላ
ያለች ከተማ፥
“በነገውም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር አብረው
ሄዱ።”
(ሉቃ 7:11)
ናዳብ ~ Nadab, Nodab: ‘ለጋስ’ ማለት ነው።
1. የአሮንና የኤልሳቤጥ ትልቁ ልጅ፥ “የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። በኵሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።” (ዘጸ 8 13 ዘኊ 3:2)
2. በእስራኤል ላይ የነገሠ፥ የኢዮርብዓም ልጅ፥ “በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሁለተኛው
ዓመት የኢዮርብዓም
ልጅ ናዳብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም
ላይ ሁለት
ዓመት ነገሠ” (1 ነገ 15:25-31)
3. የይሁዳ ነገድ፥ የሸማይ ልጅ፥ “የኦናምም ልጆች ሸማይና ያዳ ነበሩ። የሸማይ ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ።” (1 ዜና 2:28)
4.
ከብንያም ነገድ የሆነ፥ “ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥
ዛኩር በገባዖን
ተቀመጡ።”
(1 ዜና 8:30፥ 9:36)
ናዳብ /
Nodab: ‘ክቡር’ ማለት ነው። “ከአጋራውያንና ከኢጡር ከናፌስና ከናዳብ ጋር ተዋጉ” (1 ዜና 5:19)
ናጌ ~
Nagge:
ነገ፣ ነጋ፣ ንጋት፣ ብርሃን ሆነ፣ ወጋገን መጣ፣ ጨለማው ሄደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ኖጋ]
‘ነገ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የማአት ልጅ፥ (ሉቃ 3:25)
ናጱሌ ~
Neapolis:
ኒው ፖሊስ፣ አዲስ ከተማ... ማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለመጀመሪያ ያረፈበት የአውሮጳ ከተማ፥ “ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን” (ሐዋ 16:11)
ናፌስ ~
Naphish:
ንፋስ፣ ነፍስ፣ ሕይዎት፣ እስትንፋስ... ማለት ነው።
‘ነፈሰ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።
ናፌስ / Naphish:
የእስማኤል ልጅ፥ (ዘፍ 25:15)
ናፌስ / Nephish:
(1 ዜና 5:19)
ናፌግ ~ Nepheg: ‘ንፉግ፣ ደካማ’ ማለት ነው።
1. የይስዓር ልጅ፥ “የይስዓር ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው።”
(ዘፍ 6:21)
2. “ናፌቅ፥
ያፍያ፥ ኤሊሳማ፥
ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።” (2 ሳሙ
5:16፤ 1 ዜና 3:7፥ 14:6)
ኔሔላማዊ ~ Nehelamite:
ነ‘ሕልምያት፣ ሕልማዊ፣ ሕልም አላሚ...
ማለት ነው። ለሐሰተኛው ነቢይ ለሸማያ የተሰጠ መጠሪያ፥ (ኤር 29:24፣31፣32) “ለኔሔላማዊው ለሸማያ እንዲህ በል።”
ኔስታ ~ Nehushta: ነሐስ፣
ነሐሲት... ማለት ነው።
የኤልናታን ልጅ፥
የይሁዳ ንጉሥ
የዮአኪን እናት፥
“ዮአኪን መንገሥ በጀመረ
ጊዜ ... እናቱም
ኔስታ ትባል
ነበር እርስዋም
የኢየሩሳሌም ሰው
የኤልናታን ልጅ
ነበረች።”
(2 ነገ 24:8)
ኔሪ ~
Neri:
‘ብርሃኔ፣ መብራቴ’ ማለት ነው። የሰላትያል አባት፥ የሚልኪ ልጅ፥ “የዮዳ ልጅ፥ ... የዘሩባቤል ልጅ፥ የሰላትያል ልጅ፥ የኔሪ ልጅ፥” (ሉቃ 3:27)
ኔር ~ Ner: ‘ኩራዝ፣ ፋኖስ፣
መብራት’
ማለት ነው።
የንጉሥ ሳኦል
አያት፥ የቂስ አባት፥ “ኔር ቂስን ወለደ ቂስም ሳኦልን ወለደ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥
አስባኣልን ወለደ።” (1 ዜና 8:33)
ኔርያ ~ Nereus, Neriah:
‘ኩራዝ፣ ፋኖስ፣ መብራት’ ማለት
ነው። በሮም
የነበረ ክርስቲያን፥
ጳውሎስ በሰላምታ
ደብዳቤው የጠቀሰው፥
“ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ... ቅዱሳን
ሁሉ ሰላምታ
አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:15)
ኔርያ / Neriah:
‘የአምላክ ብርሃን፣ ሕያው
መብራት’
ማለት ነው።
የመሕሤያ አባት፥
የባሮክ ልጅ፥
“የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥
... አይሁድ ሁሉ
እያዩ የውሉን
ወረቀት ለመሕሤያ
ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።” (ኤር
32:12)
ኔቆዳ ~ Nekoda: ‘ታዋቂ፣ ዝነኛ’ ማለት
ነው። ከምርኮ
ከተመለሱ ነገር ግን ነገዳቸውን ማስረዳት
ካልቻሉ፥ የኔቆዳ
ወገኖች ይገኙበታል፥
“የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥” (ዕዝ 2:48፤ ነህ 7:50)
ኔጌር ~
Niger:
ኒገር፣ ኒጀር፣ ኔግሮ፣ ጥቁር፣ ጠይም... ማለት ነው።
በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ከነበሩ ነቢያትና መምህራን የስምዖን ቅጽል ስም፥ “በአንጾኪያም ባለችው
ቤተ ክርስቲያን
ነቢያትና መምህራን
ነበሩ፤ እነርሱም
በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ ...” (ሥራ 13:1)
ንምፉ ~ Nymphas: ‘የትዳር ጓደኛ’ ማለት
ነው። ጳውሎስ
ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን አባላት ባቀረበው ሰላምታ የጠቀሳት፥ “በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ
ክርስቲያን ሰላምታ
አቅርቡልን።”
(ቆላ 4:15)
ንስያ ~ Neziah: ‘በአምላክ የታወቀ፣ በጌታ የተከበረ’ ማለት ነው። ከባቢሎን
ምርኮ ከተመለሱ፥
የንስያ ልጆች
ይገኙበታል፥ “የሲሣራ ልጆች፥
የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።” (ዕዝ 2:54፤ ነህ 7:56)
ንርቀሱ ~
Narcissus:
‘ቂላቂል፣ የዋህ’ ማለት ነው። ጳውሎስ በመልእክቱ ሰላምታ
ከላከላቸው፥ በሮም
የነበረ ክርስቲያን፥
“ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሰላምታ
አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ ቤተ ሰዎች ... ሰላምታ
አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:11)
ንበላት ~ Neballat: ‘ውስጠ አበድ፣ አላዋቂ፣ ሞኛሞኝ’ ማለት
ነው። የብንያም
ከተማ የነበረ፥
ከግዞት መልስ
ብንያማውያን እንደገና
ከሰፈሩበት ቦታ፥
“በስቦይም፥ በንበላት፥ በሎድ፥
በኦኖ፥ በጌሐራሺም
ተቀመጡ።”
(ነህ 11:34)
ንዒኤል ~ Neiel: ‘በአምላክ የሄደ’ ማለት
ነው። የአሴር
ነገድ ጉልህ
ድንበር የሆነ
የቦ ታ
ስም፥ “ወደ ፀሐይም
መውጫ ወደ
ቤትዳጎን ዞረ፥
ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፥ በስተ ግራ በኩልም ወደ ካቡል ወጣ” (ኢያ 19:27)
ንዕማን ~
Naaman:
ናዕማን፣ ነዓምን፣ ማመን፣ መስማማት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነሐማኒ፣ ኑኃሚን]
‘አመነ’
ከሚለው ግስ
የወጣ ስም ነው።
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ፣ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል
ነበረ፥ ነገር። ግን
ለምጻም ነበረ፥
“...ከንዕማን
በቀር ከእነርሱ
አንድ ስንኳ
አልነጻም”
(ሉቃ 4:27) ፣ (2 ነገ 5:1)
ንፉሰሲም ~ Nephishesim, Nephusim:
‘መስፋፋት’
ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የንፉሰሲም ልጆ ይገኙበታል፥ (ነህ 7:53)
“የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥”
ንፉሰሲም / Nephusim: ‘መስፋፋት’ ማለት
ነው። ከባቢሎን
ምርኮ ከተመለሱ የንፉሰሲም ልጆች ይገኙበታል፥ “የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን
ልጆች፥ የንፉሰሲም ልጆች፥” (ዕዝ 2:50)
ንፍታሌም ~ Naphtali, Nephthalim: ‘ታጋይ፣ ተጋዳይ’ ማለት ነው። የያዕቆብ አምስተኛ ልጅ፥ “ራሔልም። ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።” (ዘፍ 30:8)
ንፍታሌም ~
Nephthalim: ‘ታጋይ፣ ተዋጊ’
ማለት ነው። “ራሔልም። ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው” (ዘፍ 30: 8)
ኖሐ ~ Nohah: ኖኀ፣ ኖኸ፣ ዐረፈ፣ ዕረፍት፣ መረጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ነሐም፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖኅ] አራተኛው የብንያም ልጅ፥ “ሦስተኛውንም አሐራን፥ አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ።” (1 ዜና 8:2)
ኖኅ ~
Noah:
ኖኅ፣ ኖኸ፣ ዐረፈ፣ ዕረፍት፣ መረጋጋት፣ መጽናናት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ነሐም፣ ነሑም፣ ነህምያ፣ ኑኃሚን፣ ናሆም፣ ንዕማን፣ ኖሐ]
. ምድር በግፍ በመሞላቷ፥ እግዚአብሔር በውኃ ሲያጠፋ፥ ቤተሰቦቹን በመርከብ በማድረግ
የተረፈ፥ “ስሙንም፦ እግዚአብሔር
በረገማት ምድር
ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።” (ዘፍ 5:29)
. “ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ ...” (ዘፍ 5፡30) ፣ (2
ጴጥ 2:5)
ኖባይ ~
Nebai:
ነባይ፣ ነቢይ፣ አዋቂ፣ ሊቅ፣ ጠቢብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ነባዮት፣ ናቡቴ፣ ናባው]
‘ነቢይ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው። በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
ሁሉ ፍርዱንም
ሥርዓቱንም ይጠብቁና
ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን ያደረጉ፥ (ነህ 10:19)
ኖብ ~
Nob:
‘ከፍተኛ ስፍራ’ ማለት ነው። በኢየሩሳሌም አቅራቢያ፥ የብንያም ነገድ
የሆነ የተከበረ
መንደር፥ “የካህናቱም ከተማ
ኖብን በሰይፍ ስለት
መታ ወንዶችንና
ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና
ጡት የሚጠቡትን፥
በሬዎችንና አህዮችንም
በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።” (1 ሳሙ 22:19፤ ነህ 11:32)
ኖዓድያ ~ Noadiah: ‘በሕያው የተሰባሰበ’ ማለት ነው።
1. ሌዊያዊው፥ ከባቢሎን ምርኮ
ከመለሱ፥ “በአራተኛውም ቀን ብሩና ... ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።” (ዕዝ 8:33)
2. ሐሰተኛ ነቢይ፥ “አምላኬ ሆይ፥
ስለዚህ ሥራቸው ጦብያንና ሰንባላጥን ያስፈራሩኝም
ዘንድ የወደዱትን
ነቢይቱን ኖዓድያን
የቀሩትንም ነቢያት
አስብ።”
(ነህ 6:14)
ኖኤሬ ~ Maharai: ‘ችኩል’
ማለት ነው።
በይሁዳ ነገድ፥
የንፍታለም ነዋሪ፥ ከዳዊት አለቆች አንዱ፥ “ጸልሞን፥ ነጦፋዊው ኖኤሬ፥ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ወገን” (2 ሳሙ 23:29፤ 1 ዜና 11:30፥ 27:13)
ኖእ ~
No:
‘ክልክል’ ማለት ነው። በግብፅ የነበረ የቦታ ስም፥ “ጳትሮስንም አፈርሳለሁ፥
በጣኔዎስም እሳትን
አነድዳለሁ፥ በኖእ ላይም ፍርድን አደርጋለሁ” (ሕዝ 30:14፣16)
ኖጋ ~
Nogah:
ነገ፣ ነጋ፣ ንጋት፣ ብርሃን መሆን፣ ጥባት፣ ጠኋት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ናጌ]
‘ነገ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። በኢየሩሳሌም ለዳዊት ከተወለዱለት፥ (1 ዜና 3:7)
ኖፋ ~ Nophah: ‘ፍንዳታ’ ማለት ነው። የሞዓብ ከተማ የነበረ፥ በአሞራውያን የተወሰደ፥ “ገተርናቸው ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው።” (ዘኊ 21:30)
No comments:
Post a Comment