ሐሊ ~ Hali: ሐብል፣ ድሪ፣ ያንገት ጌጥ ማለት ነው። የአሴር ድንበርተኛ፥ በሔልቃት እና በቤጤን መካከል ያለ ከተማ፥ ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ ቤጤን፥ አዚፍ፥” (ኢያ 19:25)

ሐልሑል ~ Halhul: ሐዘንማለት ነው። በይሁዳ የተራራማው ክፍል የነበረ ከተማ፥ ሐልሑል ቤትጹር፥ ጌዶር፥ ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:58)

ሐመዳቱ ~ Hammedatha: ሕገ ወጥ አጥፊማለት ነው። የሐማ አባት፥ ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሡ አርጤክስስ የአጋጋዊውን ሐመዳቱ ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው፥ አከበረውም ... (አስ 3:110 8:5 924)

ሐሙል ~ Hamul: አምላካዊ፣ ይቅር ባይማለት ነው። የይሁዳ ልጅ፥ የፋሬስ ሦስተኛ ልጅ፥ የይሁዳም ልጆች ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም ... የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል” (ዘፍ 46:12 1 ዜና 2:5)

ሐማ ~ Haman: ሐማን፣ አማን፣ ታማኝ፣ ሰላማዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ሄማን፣ አሒማን፣ አማና፣ አሜን፣ አሞን፣ አኪመን፣ ያሚን] የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ‘Haman ~ ሐማን ሲል፥ የአማኛው በማሳጠር ሐማ ይላል።

Haman- ሐማን ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ሲሆን፥ የቃሉ ምንጭ ደግሞ አመነ የሚለው ግስ ነው።

የአጋጋዊው የሐመዳቱን ልጅ የፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ ከፍተኛ ሥልጣን የሰጠው የአይሁድ ጠላት። አይሁድን ለማጥፋት አቅዶ ነበር፥ ነገር ግን ባዘጋጀው መስቀል ራሱ ተሰቀለ፥ (አስ 31)

ሐማት ~ Hamath: ምሽግ ማለት ነው። ከሶርያ ታላላቅ ከተሞች አንዱ፥ ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ ሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።” (ዘኊ 13:21)

ሐማትሱባ ~ Hamath-zobah: በዘብ የሚጠበቅ ጠንካራ ምሽግማለት ነው። ሰሎሞንም ወደ ሐማትሱባ ሄደ አሸነፋትም። (2 ዜና 8:3)

ሐሞና ~ Hamonah: የብዙ ብዙማለት ነው። በነቢዩ ሕዝቅኤል የተጠቀሰ ከተማ፥ ደግሞም የከተማይቱ ስም ሐሞና ይባላል። እንዲሁ ምድሪቱን ያጸዳሉ።” (ሕዝ 39:16)

ሐሞን ~ Hammon: ፍል ውኃማለት ነው።

1. የአሴር ከተማ፥ ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።” (ኢያ 19:28)

2. ፍታሌም ርስት ተወስዶ ለሌዊያውያን ከተማነት የተሰጠ፥ (1 ዜና 6:76)

ሐሞንጎግ ~ Hamon-gog: ብዙ ተራራማለት ነው። የተገደሉ የጎግ ሠራዊት መቀበሪያ ሸለቆ፥ ... በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።” (ሕዝ 39:1115)

ሐሱም ~ Hashum: ሀብታምማለት ነው።

1. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት...” (ነህ 7:22)

2. ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ሲያነብ በስተግራ ከቆሙት፥ (ነህ 8:4) “... መልክያ፥ ሐሱም ሐሽበዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።

ሐሡፋ ~ Hashupha: እርን፣ እራቁትማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ ናታኒም፥ የሲሐ ልጆች፥ ሐሡፋ ልጆች...” (ነህ 7:46)

ሐሳድያ ~ Hasadiah: አምላክ የረዳውማለት ነው። ከፈድያ ልጆች አንዱ፥ ሐሹባ፥ ኦሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ ዮሻብሒሴድ አምስት ናቸው” (1 ዜና 3:20)

ሐሴሶንታማር ~ Hazezon-tamar: ተምር መግረዝማለት ነው። የቀድሞ ስሙ ዓይንጋዲ የነበረ ቦታ፥ ...ዓይንጋዲ በተባለች ሐሴሶን ታማር ናቸው ብለው ለኢዮሣፍጥ ነገሩት።” (2 ዜና 20:2)

ሐሴቦን ~ Heshbon: ውስጣዊ፣ በልብ ያለ፣ የታሰበ፣ ሐሳባዊ... ማለት ነው። የስሙ ምንጭ ሐሳብ የሚለው ቃል ነው። የአሞራውያን ንጉሥ፥ የሴዎን ዋና መቀመጫ የነበረ፥ የቦታ ስም፥ ...እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ ሐሴቦን በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ። (ዘኊ 21:26)

ሐስረሞትን ~ Hazarmaveth: ሐሰረ ሞት፣ የሞት እሥር የአሳር፣ የስቃይ የመከራ ሞት... ማለት ነው። የዮቅጣን ሦስተኛ ልጅ፥ ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥” (ዘፍ 10:26)

ሐስራ ~ Hasrah: አሳሩን ያየ፣ መከራን የተቀበለ፣ ምስኪን ድሃ... ማለት ነው። የስሙ ምንጭ አሳር የሚለው ቃል ነው። የቲቁዋ አባት፥ ኬልቅያስና እነዚያ ንጉሥ ያዘዛቸው ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ...” (2 ዜና 34:22)

ሐሩስ ~ Haruz: ቅንማለት ነው።አሞጽም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዮጥባ ሰው ሐሩስ ልጅ ሜሶላም ነበረች።” (2 ነገ 21:19)

ሐራን ~ Haran: ተራራማማለት ነው።

1. የታራ ልጅ፥ ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።” (ዘፍ 11:26)

2. የሰሜኢ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጆች ሰሎሚት፥ ሐዝኤል፥ ሐራን ሦስት ነበሩ። እነዚህ የለአዳን አባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። (1 ዜና 23:9)

3. የካሌብ ልጅ፥ የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች” (1 ዜና 2:46)

4. የታራ ልጅ፥ ካራን፥ ...የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም ካራን ሳይቀመጥ ገና በሁለት ወንዝ መካከል ሳለ ታየና... (ሐዋ 7:24)

ሐራዳ ~ Haradah: ራደ፣ ፈራ፣ ተንቀጠቀጠ... ማለት ነው። እስራኤል ከግብፅ ወጥተው በምድረ በዳ ካለባቸው ቦታዎች፥ ከሻፍር ተራራም ተጕዘው ሐራዳ ሰፈሩ።” (ዘኊ 33:2425)

ሐሬፍ ~ Hareph: መፈልፈል፣ መጠርጠር፣ ፍሬን ከገለባ መለየትማለት ነው። በይሁዳ የዘር ሐረግ፥ የካሌብ ልጅ፥ የቤትጋዴር አባት የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዴር አባት ሐሬፍ” (1 ዜና 2:51)

ሐርሃያ ~ Harhaiah: የፈጣሪ ቁጣማለት ነው። የዑዝኤል አባት፥ በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው ሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል አደሰ...” (ነህ 3:8)

ሐርሑር ~ Harhur: ሐሩር፣ ያረረ፣ የሞቀ፣ የሚያቃጥል... ማለት ነው። ሐሩርከሚለው ቃል የተገኘ ስም ሲሆን፥ የቃሉ ምንጭ ደግሞ አረረየሚለው ግስ ነው። ሐረርእና ሐራሬየመሳሰሉ ስሞች የመጡት ከዚህ ቃል ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች መካከለ ሐርሑር ልጆች ይገኙበታል፥ (ዕዝ 2:51) (ነህ 7:53)

ሐርሳ ~ Harsha: አራሽ፣ ሠራተኛ፣ በግብርና የሚተዳደር... ማለት ነው። አረሰከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱት የሐርሳ ልጆች ይገኙበታል፥ ሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች (ዕዝ 2:53 ነህ7:54)

ሐርቦና ~ Harbonah: ሐርበኛ፣ ርበኛ፣ ጦረኛ፣ ተዋጊ... ማለት ነው። ሐርብከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ስም ነው። በንጉሡም ፊት ካሉት ጃንደረቦች አንዱ፥ በንጉሡም ፊት ካሉት ጃንደረቦች አንዱ ሐርቦና እነሆ ሐማ ለንጉሡ በጎ ለተናገረው ለመርዶክዮስ ያሠራው ርዝመቱ አምሳ ክንድ የሆነው ግንድ በሐማ ቤት ተተክሎአል አለ...” (አስ 7:9)

ሐርኔፍር ~ Harnepher: ‘ማለህለህማለት ነው። ከአሴር ነገድ፥ የጾፋ ልጅ፥ የጾፋም ልጆች ሱዋ፥ ሐርኔፍር” (1 ዜና 7:36)

ሐሮድ ~ Harod: መራድ፥ መንቀጥቀጥ፥ መናወጥ... ማለት ነው። የጌዲዎን ሠራዊት፥ ከምዳማውያን ባደረጉት ፍልሚያ፥ የሰፈሩበት ምንጭ፥ ...ሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።” (መሣ 7:1)

ሐሸቢያ ~ Hashabiah: ሐሳበ ያሕ፣ አሳበ ሕያው፣ እግዚአብሔር ያሰበው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ሐሸብያ፣ ሐሹባ አሳብያ]

ሐሳብ እና ያሕ’(ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የቃሉ ምንጭ ደግሞ አሰበየሚለው ግስ ነው።

1. በዳዊት ዘመን በሌዊ ላይ የተሾመ የቀሙኤል ልጅ፥ ሐሸቢያ (1 ዜና

27:17)

2. ከሌዋውያኑ አለቆች አንዱ፥ (2 ዜና 35:9)

3. በመጽሐፈ ዕዝራ የተጠቀሰው ሊቀ ካህን፥ (ዕዝ 8:24)

ሐሸብያ ~ Hashabiah: ሐሳበ ያሕ፣ አሳበ ሕያው፣ እግዚአብሔር ያሰበው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ሐሸቢያ ሐሹባ አሳብያ]

ሐሳብ እና ያሕ’(ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ሐሸብያ በሚል ስም የሚጠሩ ሰዎች።

1. ከሜራራ ወገን የሆነ ሐሸብያ (1 ዜና 6:45)

2. ከኤዶታም የኤዶታ ልጅ ሐሸብያ (1 ዜና 25:3)

3. በመጽሐፈ ነህምያ የተጠቀሰ ሐሸብያ (ነህ 3:17)

4. የሌዋውያን አለቃ የነበረ ሐሸብያ (ነህ 10:11 12:24)

5. በመጽሐፈ ነህምያ የተጠቀሰ ሌላ ሐሸብያ (ነህ 11:22)

ሐሹባ ~ Hashubah: አሳቢ፣ አስታዋሽ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ሐሸብያ፣ ሐሸቢያ አሳብያ]

አሰበከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። ከዘሩባቤል ልጆች አንዱ፥ ሐሹባ (1 ዜና 3:20)

ሐሽሞን ~ Heshmon: ‘ለም አፈርማለት ነው። በይሁዳ የታችኛው መጨረሻ ክፍል የሚገኝ ቦታ፥ አማም፥ ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ ሓጸርጋዳ፥ ሐሽሞን” (ኢያ 15:27)

ሐቁፋ ~ Hakupha: አቃፊ፣ ደጋፊ፣ ተቀባይ... ማለት ነው። አቀፈከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። ከግዞት ከተመለሱ ሐቁፋ ልጆች ይገኙበታል፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ ሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች...” (ዕዝ 2:51 ነህ 7:53)

ሐታት ~ Hathath: ሐቲት፣ ፍርሃት፣ ድንጋጤ ማለት ነው። የቄኔዛዊው የጎቶንያል ልጅ፥ የጎቶንያልም ልጅ ሐታት ነበረ” (1 ዜና 4:13)

ሐቴርሰታ ~ Tirshatha: ገዥ፣ አስተዳዳሪማለት ነው። ሐቴርሰታ: - በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው” (ዕዝ 2:63 ነህ 7:6570)

ሐኒኤል ~ Hanniel: ሐና ኤል፣ አምላከ ሐና... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም - አኒኤል]

ሐናእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ትርጉሙ ሐናማለት በረከት፣ ቸርነት፣ ስጦታ ማለት ሲሆን፥ ኤልደግሞ ኃያል አምላክ ማለት ነው። ስለዚህ ሐኒኤል የሚለው የበረከት አምላክ፣ የቸርነት ጌታ፣ የእግዚአብሔር ጦታ ተብሎ ይተረጎማል። የአሴር ነገድ አለቃ የሆነ፥ የዑላ ልጅ፥ (1 ዜና 7:39)

ሐና ~ Anna, Annas, Hannah: ጸጋ፣ ቸርነት፣ በረከት፥ ልገሳ፣ ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሐናኒ፣ ሐናን፣ ሐኖን፣ አናኒ]

የቃሉ ምንጭ ሆነየሚለው ግስ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐና በሚለው ስም የሚታወቁ ሦስት ሰዎች አሉ።

       ሐና / Anna: ከአሴር ወገን የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ነቢይት ሐና (ሉቃ 236 37)

       ሐና / Annas: የአይሁድ ሊቀ ካህን የነበረው፥ ሐና (ዮሐ 18 13) (ሉቃ 3:2)

        ሐና / Hannah: የሕልቃና ሚስት፣ የነቢዩ ሳሙኤል እናት፥ ሐና (1 ሳሙ 114-16)

[የቃሉ ትርጉም ጸጋማለት ነው። / መቅቃ]

[ምሕረተ እግዚአብሔር ማለት ነው። / ደተወ / ]

ሐናቶን ~ Hannathon: የጸጋ በረከትማለት ነው። ከዛብሎን ከተሞች አንዱ፥ ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ።” (ኢያ 19:14)

ሐናኒ ~ Hanani: ሐናኔ፣ ሐናዬ፣ ጸጋዬ፣ ጦታዬ፣ ሀብቴ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሐና፣ ሐናን፣ ሐኖን፣ አናኒ]

ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆች ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት ከሚናገሩት ሰዎች ለማገልገል ከተለዩ፥ በአገልግሎታቸው ሥራ ከሠሩ መካከል፥ (1 ዜና 25:4 25:25)

ሐናን ~ Hanan: ሐነን፣ ጸጋ የተሰጠው፣ ምሕረት ያገኘ፣ ይቅር የተባለ ማለት ነው። [ተዛማች ስሞች- ሐና፣ ሐናኒ፣ ሐኖን፣ አናኒ]

በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከአለቆች አንዱ፥ ከብንያም ወገን የሆነ፥ ሐናን (1 ዜና 824)

2. የሳ ወገን ከሆነው ከኤሴል የተወለደው ሐናን (1 ዜና 8:38)

3. የንጉሥ ዳዊት ጭፍራ የነበረ፥ ሐናን (1 ዜና 11:43)

4. የእግዚአብሔር ሰው የጌዴልያ ልጅ ሐናን (ኤር 35:4)

5. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች፥ ሐናን (ዕዝ 2:46)

6. ዕዝራን ከተባበሩት ሌዋውያን አንዱ፥ ሐናን (ነህ 8:7)

7. በነህምያ የተጠቀሰ፣ የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት አንዱ፥ ሐናን

(ነህ 10:22 23)

ሐናንኤል ~ Hananeel: ሐናነ ኤል፣ የሐና አምላክ፣ የአምላክ እግዚአብሔር ስጦታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሐኒኤል፣ ሐናንያ፣ አናንያ፣ አኒኤል]

ሐናንእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በኢየሩሳሌም ቅጥር አቅራቢያ የነበረ የግንብ መጠሪያ፥ (ነህ 31)

ሐናንያ ~ Hananiah: ሐነነ ያሕ፣ የሕያው እግዚአብሔር ስጦታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሐኒኤል፣ ሐናንኤል፣ አናንያ፣ አኒኤል]

ሐናን እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዘሩባቤል ልጅ፥ ሐናንያ (1 ዜና 3:19 21)

2. የብንያም ወገን አለቃ ሐናንያ (1 ዜና 824)

3. የሄማን ልጅ ሐናንያ (1 ዜና 25:4 23)

4. ለዖዝያን በሠራዊት ውስጥ የሰልፈኞች አለቃ የነበረው ሐናንያ (2 ዜና

26:11)

5. የሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ፣ አያት፥ (ኤር 37:13)

6. የሴዴቅያስ አባት፥ ሐናንያ (ኤር 36:12)

7. “ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ አሱብ፥ (ኤር 10:23)

8. የቤባይ ልጅ፥ ሐናንያ (ዕዝ 10:28)

9. ካህኑ የኤርምያስ ልጅ፣ ሐናንያ (ነህ 12:1213)

10. ሽቱ ቀማሚ የነበረ፥ ሐናንያ (ነህ 3:8)

11. የሰሌምያ ልጅ፥ ሐናንያ (ነህ 3:30)

12. ሐሰተኛው ነቢይ፣ ሐናንያ፥ (ኤር 28:17)

. አናንያ (ዳን 1:67)

ሐናንያ ~ Ananias: የሕያው ታላቅ በረከት አምላክ የለገሰው... ማለት ነው።

1. ሊቀ ካህኑ፥ (ሐዋ 23:2-5 24:1)

2. በኢየሩሳሌም የነበረ አማኝ፥ ጴጥሮስም፦ ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?” (ሐዋ 5:1-11)

3. በደማስቆ የነበረ አንድ ደቀ መዝሙር፥ በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ...” (ሐዋ 9:10-17)

ሓኔስ ~ Hanes: ‘ጸጋ ቢስማለት ነው። በግብፅ አገር ያለ፥ የቦታ ስም፥ አለቆች ምንም በጣኔዎስ ቢሆኑ፥ መልክተኞችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደርሱ (ኢሳ 30:4)

ሐኖን ~ Hanun: ሐናን፣ እግዚአብሔር የሰጠው፣ ይቅር የተባለ፣ ባለ ጸጋ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሐና፣ ሐናኒ፣ ሐናን፣ አናኒ]

በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የናዖስ ልጅ ሐኖን (2 ሳሙ 101-14)

2. የኢየሩሳሌምን ቅጥር በማደስ ከተባበሩት አንዱ፥ ሐኖን (ነህ 3:30)

3. ከዛኖዋ ሰዎች ጋር የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ የሸለቆውን በር ያደሰ ሐኖን

(ነህ 3:13)

ሐካልያ ኤኬላ ~ Hachaliah: አምላክ ያነቃውማለት ነው። የነህምያ አባት፥ ሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሀያኛው ዓመት በካሴሉ ወር እንዲህ ሆነ” (ነህ 1:1 10:1)

ኤኬላ~ Hachaliah: ዳዊት ከሳዖል ሸሽቶ ከተሸሸገባቸው ባዎች አንዱ። (ሳሙ 23:19)

ሐውራን ~ Hauran: ዋሻ ማለት ነው። የፍልስጥኤም ክፍለ ግዛት የሆነ፥ በሕዝቅኤል የተጠቀሰ ቦታ፥ ...በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ ሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን” (ሕዝ 47:1617)

ሐዞ ~ Hazo: ራእይማለት ነው። ናሆር ከሚልካ የወለደው ልጅ፥ ኮዛት፥ ሐዞ ፊልዳሥ፥ የድላፍ፥ ባቱኤል ናቸው (ዘፍ 22:22)

ሐዲ ~ Addi: ጌጥማለት ነው። በጌታ የዘር ሐረግ፥ የዮሳስ ልጅ፥ የሚልኪ አባት፥ የሚልኪ ልጅ፥ ሐዲ ልጅ፥ የዮሳስ ልጅ፥ የቆሳም ልጅ፥ የኤልሞዳም ልጅ፥ የኤር ልጅ” (ሉቃ 3:28)

ሐዲድ ~ Hadid: መውደድ ማፍቀር... ማለት ነው። በብንያም ነገድ፥ በሎድ አቅራቢያ፥ ያለ ቦታ፥ የሎድና ሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት።” (ዕዝ 2:33 ነህ 7:37)

ሐዳሻ ~ Hadashah: ሀዲስ፣ አዲስ፣ ያላረጀ፣ እንግዳ፣ ቀድሞ ያልነበረ፣ አሁን የመጣ... ማለት ነው። አደሰ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። ከይሁዳ ከተሞች አንዱ፥ ጽናን፥ ሐዳሻ ሚግዳልጋድ፥ ዲልዓን፥” (ኢያ 5:37)

ሐዳድሪሞን ~ Hadadrimmon: ሪሞን ለተባለ አምላክ መጸለይማለት ነው።ለንጉሥ ሲያ ሞት ብሔራዊ ሃዘን የተካሄደበት፥ የመጊዶን ሸለቆ፥ በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል” (ዘካ 12:11)

ሐድላይ ~ Hadlai: ያምላክ ዕረፍትማለት ነው። የኤፍሬም አገር ሰው፥ ... የሰሎምም ልጅ ይሒዝቅያ፥ ሐድላይ ልጅ ዓሜሳይ ከሰልፍ በተመለሱት ላይ ተቃወሙአቸው።” (2 ዜና 28:12)

ሐጊ ~ Haggi: ሐጊ፣ ሐጋጊ፣ ሐገገ፣ ሕጋዊ ሆነ፣ ሕግ አከበረ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስም- ሐጌ፣ ሐግያ]

ሐገከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። የጋድ ሁለተኛ ልጅ ሐጊ (ዘፍ 6:16)

ሐጌ ~ Haggai: ሕጌ፣ ሕጋዊ፣ ሥርዓት ተከታይ፣ ትእዛዝ ተቀባይ፣ ሰንበትን የሚጠብቅ፣ በዓላትን የሚያከብር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሐጊ፣ ሐግያ]

ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ፥ ነቢዩ ሐጌ (ዕዝ 614)

[የሰው ስም፡ ነቢይ፡ ካሥራ ኹለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ። በዓል ዘተወልደ በዓል ማለት ነው / ኪወክ/ ]

ሐግሪ ~ Haggeri: ሐገሬ፣ አገሬ፣ አገራዊ ማለት ነው። [አገረ፣ እግር፣ መንገደኛ፣ እንግዳ ማለት ነውተብሎም ይተረጎማል።]

አገርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። ከዳዊት ኃያላን አንዱ፣ የሚብሐር አባት፥ ሐግሪ (1 ዜና 1138)

ሐግያ ~ Haggiah: ሕገያ፣ ሕገ ያሕ፣ ሕገ ሕያው፣ የሕያው እግዚአብሔር ሕግ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሐጌ፣ ሐጊ]

ሕግ እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሜራሪ ልጅ፥ ሐግያ (1 ዜና 630)

ሐጡስ ~ Hattush: ከኃጢ የነፃማለት ነው።

1. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ መሉክ፥ ሐጡስ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥” (ነህ 12:3)

2. “ሐጡስ፥ ሰበንያ፥ መሉክ ካሪም፥” (ነህ 10:4)

ሐጢል ~ Hattil: ትልቅ ማለት ነው። (ዕዝ 2:57) “የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።

ሐጢጣ ~ Hatita: ሐጢጣ፥ ኃጢ... ማለት ነው። ከበረኞች ልጆች አንዱ፥ የበረኞች ልጆች የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ ሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች... (ዕዝ 2:42 ነህ 7:45)

ሐጸርሃቲኮን ~ Hazar-hatticon: የታጠረ መካከለኛ መንደርማለት ነው። ከሐማት አለፍ ብሎ ሐውራን ከመደ በፊት ያለ መንደር፥ ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን” (ሕዝ 47:16)

ሐጸርሹዓል ~ Hazar-shual: አጥረ ሳዖል፣ አጥ ሺህ አውል፣ ሺህ ሰውን መያዝ የሚችል... ማለት ነው። ቤትጳሌጥ፥ ሐጸርሹዓል ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ” (ኢያ 15:28 ነህ 11:27)

ሐጸርአዳር ~ Hazar-addar: አጥር አደር፣ የታጠረ የታሰረ፣ በግዞት ያለ ትውልድማለት ነው። በፍልስጥኤም የደቡባዊ አዋሳኝ ያለ መንደር፥ ... መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል (ዘኊ 34:4)

ሐጼሮት ~ Hazeroth: አጥራት፣ አጥሮች፣ ክልል፣ መንደር... ማለት ነው። አጥርከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ካረፉባቸው ቦታዎች፥ ሕዝቡም ከምኞት መቃብር ወደ ሐጼሮት ተጓዙ በሐጼሮትም ተቀመጡ።” (ዘኊ 11:35 12:16 33:17, 1:1)

ሐጽሮ ~ Hezrai: አጥር፣ ዙሪያ፣ የታጠረ፣ የተከለለ የተከበበ... ማለት ነው። አጠረከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። ከሠላሳው የዳዊት ኃያ አንዱ፥ ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ አርባዊው ፈዓራይ፥” (2 ሳሙ 23:35)

ሐጾር ~ Hazor: አዙር፣ ዙሪያ፣ አጥር... ማለት ነው። አጥር ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

1. ከመሮን ሐይቅ በስተሰሜን ተራራዎች፥ የከነናውያን ጠንካራ ምሽግ፥ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ ቃዴስ፥ ሐጾር ዪትናን፥ (ኢያ 15:23)

2. አሶር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...” (ኤር 49:28-33)

3. “ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥” (ኢያ 15:25)

ሐፍሴባ ~ Hephzibah: ደስታዬነሽ ማለትነው።

1. የእስራኤል ንጉሥ፥ የምናሴ እናት፥ ምናሴም ... አምሳ አምስት ዓመት ነገሠ የእናቱ ስም ሐፍሴባ ነበረ” (2 ነገ 21:1)

2. ስለ ጽዮን በምሳሌነት የተነገረ፥ ደስታዬ፥ ... እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ። ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም ባል ያገባች ትባላለች።” (ኢሳ 62:4)

ሑራም ~ Huram: ራማ ከፍተኛ፣ የተከበረ፣ የትልቅ ሰው ዘርማለት ነው።

1. የቤላ ልጅ፥ ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም” (1 ዜና 8:4)

2. ኪራምአቢ፥ አሁንም ከብልሃተኞችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ኪራምአቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ሰድጄልሃለሁ።” (2 ዜና 2:13 4:1116)

ሑሻም ~ Hushah: ፈጥኖ ደራሽ፣ ሰላም ጠባቂማለት ነው። በይሁዳ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ ሑሻም አባት ኤጽር እነዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጆች ናቸው። (1 ዜና 4:4)

ሑቆቅ ~ Hukkok: ቅኑን፣ ቀኖና፣ የተቀነነ፣ ደንብ ዐዋጅ ... ማለት ነው። ከዮርዳ አቅራቢያ፥ የናፍታሊ አዋሳኝ፥የብሎን ከተማ፥ ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ ... (ኢያ 19:34)

ሑፊም ~ Huppim: የተጠበቀ ማለት ነው። የብንያምም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ፥ ናዕማን፥ አኪ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ” (ዘፍ 46:21 1 ዜና 7:12)

ሑፋም ~ Hupham: የዳ አገር ሰውማለት ነው። የብንያም ልጅ፥ ሑፋም የሑፋማውያን ወገን” (ዘኊ 26:39)

ሒልባ ~ Helbah: ለም ማለት ነው። የአሴር ከተማ፥ አሴርም የዓኮንና የሲዶንን የአሕላብንም የአክዚብንም ሒልባንም የአፌቅንም የረአብንም ሰዎች አላወጣቸውም።” (መሣ 1:31)

ሔልቃይ ~ Helkai: ለም ምላስ፥ አንደበተ ቱዕ ማለት ነው። በኢዮቄም ዘመን የነበረ ሊቀ ካህን፥ ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ” (ነህ 12:15)

ሔልዳይ ~ Heldai: ዓለማዊማለት ነው።

1. ለአሥራ ሁለተኛው የመቅደስ አገልግሎት የተመደበ አለቃ፥ ለአሥራ ሁለተኛው ወር አሥራ ሁለተኛው አለቃ ከጎቶንያል ወገን የነበረው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። (1 ዜና 27:15)

2. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ሔልዳይ ከጦብያ ከዮዳኤም ውሰድ በዚያም ቀን ... (ዘካ 6:10)

ሔማም ~ Homam: መም፣ እክል ጉዳት ማለት ነው። የሎጣን ልጅ፥ የሎጣንም ልጆች ሖሪ፥ ሔማም ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች” (1 ዜና 1:39)

ሔሬስ ~ Heres: ማለት ነው። የተራራ ስም፥ አሞራውያን ሔሬስ ተራራና በኤሎን በሸዓልቢምም በመቀመጥ ጸኑ ... (መሣ 1:35)

ሔሬብ ~ Oreb: ቁራማለት ነው። የምድያም መስፍን፥ የምድያምን ሁለቱን መኳንንት ሔሬብንና ዜብን ያዙ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት አጠገብ ገደሉት፥ ዜብንም በዜብ መጥመቂያ ላይ ገደሉት ምድያምንም አሳደዱ...” (መሣ 7:20-25)

ሔርማ ~ Hormah: እዳሪ መሬት፣ የተተወ፣ የማይታረስማለት ነው። ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፥ በጽፋት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፥ ፈጽመውም አጠፉአት። የከተማይቱንም ስም ሔርማ ብለው ጠሩአት።” (መሣ 1:17)

ሔቤር ~ Heber: ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማ ስሞች- ዔቦር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔብሮን፣ አቤር፣ ዔቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር፣ ኬብሮን]

አበረከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

1. ከአሴር ወገን፣ የበሪዓ ልጅ፥ ሔቤር (ዘፍ 4617)

2. የአይሁዳዊው፣ የሦኮን አባት፥ ሔቤር (1 ዜና 4:18)

3. ከብንያም ወገን የሆነው፥ ሔቤር (1 ዜና 8:1718)

4. ሲሣራን የገደለች (ኢያዔል) ባል፥ ሔቤር (መሣ 4:21)

ሔትሎ ~ Hethlon: ስርቻ፣ ስውር ሥፍራማለት ነው። በፍልስጥኤም ሰሜናዊ ድንበር፥ የቦታ ስም፥ የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ ሔትሎ መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ (ሕዝ 47:15 48:1)

ሔዋን ~ Eve: ሕያዋን፣ ሕያው፣ የማይሞት፣ የማያልፍ፣ ለሁልጊዜ የሚኖር... ማለት ነው።

ከአዳም አጥንት ለአዳም የተፈጠረች የመጀመሪያዋ ሴት፥ አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።” (ዘፍ 320 2:21 22)  

[በቁሙ፡ መጀመሪያ ሴት፡ የአዳም ሚስት፡ ሕያት፡ እመ ሕያዋን/ ኪወክ / ]

ሕልቃና ~ Elkanah: ኤል ቀና፣ ለአምላክ የቀና፣ ለእግዚአብሔር ታዛዥ... ማለት ነው።

ኤል እና ቀና ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ካወጣቸው፥ የቆሬ ልጅ፥ ሕልቃና (ዘጸ 624) (1 ዜና 6 26 35)

2. የነቢዩ ሳሙኤል አባት፥ ሕልቃና (1 ዜና 6:27 34)

3. የሌዊ ወገን፣ የአሳ አባት፥ ሕልቃና (1 ዜና 9:16)

4. ቆርያዊው፥ ሕልቃና (1 ዜና 12:6)

5. የይሁዳ ንጉሥ የአሐዝ የቤቱ አዛዥ የነበር፥ በዝክሪ የተገደለ፥ ሕልቃና (2 ዜና 28:7)

ሕልዳ ~ Huldah: በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን፥ ልብስ ጠባቂ የነበረው የሴሌም ሚስት፥ ነቢይት ሕልዳ፥ ...ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢያቱ ወደ ሕልዳ ሄዱ እርስዋም በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር ከእርስዋም ጋር ተነጋገሩ።” (2 ነገ 22:14 2 ዜና 34:22)

[ፋሮ ታናሽ አውሬ፥ ምድር የሚፍር፣ የሚቆፍር። / ኪወክ / ]

ሕዝቂ ~ Hezeki: ሕዝቄ፣ ኃይሌ፣ ብርታቴ፣ ጉልበቴ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሕዝቅኤል፣ ሕዝቅያስ]

ሕዝቅከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የኤልፍዓል ወገን የሆነ፣ ብንያማዊው ሕዝቂ ሕዝቂ ሔቤር፥ ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ የኤልፍዓል ልጆች (1 ዜና 8 17 18)

ሕዝቅኤል ~ Ezekiel: ሕዝቀ ኤል፣ የአምላክ ኃይል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሕዝቂ፣ ሕዝቅያስ]

ሕዝቅ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በይት ነቢያት፣ የቡዝ ልጅ፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል፥ “...ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ ...” (ሕዝ 13 24:24)

[እግዚአብሔር ብርታት ይሰጣል / መቅቃ]

ሕዝቅያስ ~ Ezekias, Hezekiah, Hizkiah, Hizkijah:

ሕዝቀ ዋስ፣ ብርቱ አዳኝ፣ ኃያል አምላክ፣ ኃይለ መለኮት፣ ሕያው ኃይል ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሕዝቂ፣ ሕዝቅኤል]

ሕዝቀ እና ዋስ’(ሕያው፣ ኤል) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ሕዝቅያስ / Ezekias: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰው፥ ሕዝቅያስ

(ማቴ 19)

       ሕዝቅያስ / Hezekiah:

1. የአካዝ ልጅ፣ ንጉሥ፥ ሕዝቅያስ (2 ነገ 18:1)

2. ከነገሥታት ወገን የሆነ፣ የነዓርያ ልጅ፥ ሕዝቅያስ (1 ዜና 3:23)

       ሕዝቅያስ / Hizkiah: የነቢዩ ሶፎንያስ አያት፥ ሕዝቅያስ (ሶፎ 1 1)

       ሕዝቅያስ / Hizkijah: ከነምያ ጋር የቃ ኪዳኑን ደብዳቤ ከአተሙት አንዱ፥ ሕዝቅያስ (ነህ 1017)

ሖሎን ~ Hilen, Holon: ዋሻ፣ ስውር ቦታ ማለት ነው። በይሁዳ ከተማ፥ ለካህናት የተለየ ክፍል፥ ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥ ሖሎንንና መሰምርያዋን፥ ዳቤርንና መሰምርያዋን፥” (1 ዜና 6:58)

       ሖሎን / Holon: አሸዋማማለት ነው።

1. ከይሁዳ ተራራማ ከተሞች አንዱ፥ ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ ጎሶም፥ ሖሎን ጊሎ አሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:51 21:15)

2. የሞዓባውያን ከተማ፥ በሜዳ ላይ፥ ሖሎን በያሳ፥ በሜፍዓት ላይ፥” (ኤር 48:21)

ሖሳ ~ Hosah: ዋሴ፣ ዋስ፣ ዋስትና፣ አዳኝ፣ መጠጊያ... ማለት ነው።

ዋሰከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በዚህ ስም የሚጠሩ አንድ ሰው እና አንድ ቦታ አሉ።

. የመራሪ ወገን የሆነው፣ በረኛው ሖሳ (1 ዜና 16:38)

. በአሴር ወገን ድንበር የሆነ የቦታ ስም፥ ሖሳ (ኢያ 19:29)

ሖሪ፣ ሱሬ ~ Hori: ዘላን፣ ዘዋሪ፣ ከርታታ... ማለት ነው። በዋሻ የሚኖሩ ማለት ነው።ተብሎም ይተረጎማል።

1. የሖሪያው የሴይር ልጅ፥ የሎጣን ልጅ፥ የሎጣን ልጆችም ሖሪ ሄማም ናቸው የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ናት።(ዘፍ 36:221 ዜና 1:39 ዘፍ36:30)

2.የሰፈጥ አባት፥ ሱሬ፥ ከስምዖን ነገድ ሱሬ ልጅ ሰፈጥ (ዘኊ 13:5)

ሖሬም ~ Horem: የተቀደሰ፣ የተለየ ማለት ነው። ከታጠሩ ፍታሌም ከተሞች አንዱ፥ ቃዴስ፥ ኤድራይ፥ ዓይንሐጾር፥ ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም ቤትዓናት፥ ቤትሳሚስ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 19:38)

ሖር ~ Hor: ሑረት፣ መሖር፣ መሔድ፣መራመድ፣ መሽከርከር... ማለት ነው።

1. እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ፥ በምድረ በዳ ከሰፈሩባቸው ቦታዎች፥ የተራራ ስም፥ ከቃዴስም ተጓዙ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ወደ ሖር ተራራ መጡ።” (ዘኊ 20:22-29 33:37)

2. ከፍልስጤማውያን ድንበሮች አንዱ፥ የሰሜንም ዳርቻችሁ ይህ ይሆናል ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ ምልክት ታመለክታላችሁ” (ዘኊ 34:78)

[ኀረወ፥ ኆር። የሰው ስም፥ ኽያጅ፣ ዘዋሪ። / ኪወክ / ]

ሖሮናይም ~ Horonaim: ሁለት ዋሻማለት ነው። በአርሞን በስተደቡብ የተገነባ የሞዓባውያን ከተማ፥ ... በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፥ ሖሮናይም መንገድ የዋይታ ጩኸት ያነሣሉ።” (ኢሳ 15:5 ኤር 48:3534)

ሖባ ~ Hobah: ስውር ስፍራ ማለት ነው። በደማስቆ በስተሰሜን የነበረ ቦታ፥ አብርሃም፥ ወንድሙን ሎጥን ከምርኮ ለማስለቀቅ የዘመተበት ታ፥ ብላቴኖቹንም ከፍሎ በሌሊት እርሱ ከባሪያዎቹ ጋር ወረደባቸው፥ መታቸውም፥ በደማስቆ ግራ እስካለችውም እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። (ዘፍ 14:15)

ሖዛ ~ Azzan: በጣም ብርቱ ማለት ነው። የፈልጢኤል አባት፥ ከይሳኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፥ (ዘኊ 34:26)

ሖዴሽ ~ Hodesh: አዲስ ማለት ነው። በብንያም የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ ከሚስቱ ሖዴሽ ዮባብን...” (1 ዜና 8:9)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ