ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ተሐሸ ~ Thahash:
‘ታጋሽ፣ ታዛዥ፣ ጭምት’ ማለት ነው።
የአብርሃም ወንድም፣ የናኮር
ልጅ፥ (ዘፍ
22:24) “ሬሕማ የሚሉአት ቁባቱ
ደግሞ ጥባህን፥ ገአምን፥
ተሐሸን፥
ሞክሳን ወለደች”
ተሒናን ~ Tehinnah:
‘አቤቱታ’ ማለት ነው። የዒርናሐሽን
አባት፥ “ኤሽቶንም ቤትራ ፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች
ናቸው።”
(1 ዜና 4:12)
ተላሚ፣ ተልማይ ~
Talmai: መግድል፣ ቦይ፣ ትልም... ማለት ነው።
1. የዔናቅ ልጅ፥ በካሌብ በኩል በይሁዳ ሰዎች ከተገደሉ፥ “በደቡብም በኩል ውጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ...” (ዘኊ 13:22፤ ኢያ 15:14፤ መሣ 1:10)
2. የመዓካ አባት፥ ተልማይ፥ “ሁለተኛውም የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው ...” (2 ሳሙ 3:3፥ 13:37)
ተላሳር ~ Telassar: ‘መነጠቅ’
ማለት ነው።
የአሦርያ ደቡባዊ
ምሥራቅ ክፍለ ግዛት፥ (ኢሳ 37:12፤ 2 ነገ 19:12) “አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?”
ተሙዝ ~ Tammuz: ‘የሕይወት ቅንጣቢ’ ማለትነው።
ሕዝቅኤል ባየው
በራእይ ሴቶች
ተሰብስበው የሚያለቅሱለት፥ እግዚአብሔርን ያላስደሰተ ተግባር፥
“ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው
ወደ እግዚአብሔር
ቤት በር መግቢያ አመጣኝ
እነሆም፥ ሴቶች
ለተሙዝ እያለቀሱ
በዚያ ተቀምጠው
ነበር።”
(ሕዝ 8:14)
ተምና ~ Timnah: ተመን፣
መጠን፣ ድርሻ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስም- ቲምናዕ]
‘ተመነ’
ከሚለውቃል የተገኘ
ስም ነው።
ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው፥ (ኢያ 15:10) ፣ (ኢያ
15:57)
ተምና ~ Timnah: ተመን፣ ድርሻ... ማለት ነው።
1. የይሁዳ ከተማ፥
(ኢያ 15:10)
“ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ ወደ ቤትሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።”
2. በይሁዳ ተራራ ላይ
ያለ ከተማ፥
(ኢያ 15:57) “ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና አሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።”
3. የኤዶም መስፍን፥ ቲምናዕ፥ (ዘፍ 36:40) “የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ”
ተምናሔሬስ ~ Timnath-heres: ‘የፀሓይ ክፋይ’ ማለት ነው። የኢያሱ የቀብር ቦታ፥ “በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው
በርስቱ ዳርቻ በተምናሔሬስ
ቀበሩት።”
(መሣ 2:9)
ተሰሎንቄ ~Thessalonic: ጳውሎስ በሐዋርያዊ ጉዞው ካለፈባቸው ከተሞች፥ “በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።” (ሐዋ 17:1-4፤ 1 ተሰ 1:9)
ተራፊም ~ Teraphim: ትርፋም፣
ትርፍ፣ ጸጋን
ሰጭ፣ ሀብት የሚያድል...
ማለት ነው።
የጣዖት ስም፥ “ሰውየውም ሚካ የአምላክ ቤት ነበረው ኤፉድና ተራፊም አደረገ፥ ከልጆቹም
አንዱን ቀደሰው፥
ካህንም ሆነለት።” (መሣ 17:5)
ተርሴስ ~ Tarshish: ‘ምርመራ’ ማለት ነው።
1. የያዋን ልጅ፥ “የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።”
(ዘፍ 10:4፤ 1 ዜና 1:7)
2. የአገር ስም፥ “ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፊር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ የተርሴስን መርከቦች ሠራ። ነገር ግን መርከቦቹ በዔጽዮንጋብር ተሰበሩ እንጂ አልሄዱም” (1 ነገ
22:48፤ 2
ዜና 9:21)
ተርታቅ ~ Tartak: ‘የጨለማው ልዑል’ ማለት
ነው። በሰማርያ
የነበሩ ሰዎች
ያመልኩት የነበረ፥
የጣዖት ስም፥
“የሐማትም ሰዎች አሲማትን
ሠሩ አዋውያንም ኤልባዝርንና ተርታቅን ሠሩ ... ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ
ነበር”
(2 ነገ 17:31)
ተርታን ~ Tartan:
የጦር አዛዥ ማለት ነው።
1. የአሦር ንጉሥ ወደ ሕዝቅኤል ከላካቸው አንዱ፥ “የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ
ኢየሩሳሌም ላከ።
...” (2 ነገ 18:17)
2. የአሦር ንጉሥ፣ የሳርጎን የጦር አዛዥ፥ (ኢሳ 20:1) “የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜ እርሱም ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ
በያዛት ጊዜ፥”
ተርአላ ~ Taralah: ‘መጠምጠም፣ ማጠቃለል’ ማለት ነው።
ለብንያም ልጆች
የተሰጠ፥ የቦታ
ስም፥ “ሬቄም፥ ይርጵኤል፥
ተርአላ፥ ጼላ፥
ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም
የምትባል የኢያቡስ
... የብንያም ልጆች
ርስት በየወገኖቻቸው
ይህ ነበረ።” (ኢያ
18:27)
ተቤራ ~ Taberah: ተበራ፣ በራ፣ ነደደ፣ ተቃጠለ... ማለት
ነው። እስራኤል
በማጉረምረማቸው እሳት
የወረደበት፥ በፋራን
ምድረ በዳ
የነበረ፥ የቦታ
ስም፥ “የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው።” (ዘኊ
11:3፤ ዘዳ 9:22)
ተንሑሜት ~ Tanhumeth: ‘ማጽናናት’
ማለት ነው።
በጎዶልያስ ዘመን የነበረ፥
የሠራያ ልጅ፥
“የጭፍሮቹም አለቆች ሁሉ፥
የናታንያ ልጅ
እስማኤል፥ የቃሬያም
ልጅ ዮሐናን፥
የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ
ሠራያ፥ የማዕካታዊውም
ልጅ ያእዛንያ፥
ሰዎቻቸውም ... ወደ
ምጽጳ መጡ።” (2 ነገ
25:23፤ ኤር40:8)
ተንትናይ ~ Tatnai: ‘ስጦታ’
ማለት ነው።
የሰላትያል ልጅ
ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም
ልጅ ኢያሱ
ተነሥተው በኢየሩሳሌም
ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ሲጀምሩ
መጥተ ከጠየቋቸው
አንዱ፥ “በዚያም ዘመን
በወንዝ ማዶ
የነበረው ገዥ
ተንትናይ፥ ደግሞ
ሰተርቡዝናይ፥ ...” (ዕዝ 5:3፣6፥ 6:6፣13)
ተድሞር ~
Tadmor:
‘ተምራም፣ የተምር ከተማ’ ማለት ነው። ሰሎሞን በምድረ በዳ የገነባው ከተማ፥ “በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን
ከተሞች ሁሉ
ሠራ።”
(2 ዜና 8:4)
ቱሚም ~ Thummim: ‘ትሙን፣ የታመነ፣
እውነተኛ’
ማለት ነው።
“በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ አሮንም በእግዚአብሔር ...” (ዘጸ 28:30፤
ዘዳ 33:8፤ መሣ 1:1፥ 20:18፤ 1 ሳሙ 14:3፣18፥ 23:9፤ 2
ሳሙ 21:1)
ቱባልቃይን ~ Tubal-cain: ‘ምድራዊ ሀብት’ ማለት ነው። የላሜሕን ልጅ፥ “ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች” (ዘፍ 4:22)
ቲሎን~ Tilon: ጥሎሽ፣
ስጦታ... ማለት ነው።
ከሲሞን አራት
ልጆች አንዱ፥
“የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት
ነበሩ።”
(1 ዜና 4:20)
ቲምናዕ ~
Timnah:
ተመን፣ መጠን፣ ድርሻ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ተምና]
ከዔሳው የአለቆች
ስም፥ (ዘፍ 36:40)
ቲርሐቅ ~ Tirhakah: ‘የከበረ፣ ከፍተኛ’ ማለት ነው። የኢትዮጵያ
ንጉሥ፥ “እርሱም፦ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ
ወደ ሕዝቅያስ
መልእክተኞችን ላከ፥
እንዲህ ሲል” (2 ነገ
19:9፤ ኢሳ 37:9)
ቲርያ ~
Tiria:
ጥሪ፣ ጩኽት... ማለት ነው። ከይሁዳ ነገድ፥ የይሃሌልኤል ልጅ፥
“... የይሃሌልኤል
ልጆች ዚፍ፥
ዚፋ፥ ቲርያ፥
አሣርኤል ነበሩ” (1 ዜና
4:16)
ቲርጻ ~ Tirzah:
‘ደስታ’ ማለት ነው። የሰለጰዓድ
ትንሿ ልጅ፥
“የኦፌርም ልጅ ሰለጰዓድ ... የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።”
(ዘኊ 26:33፥ 27:1፥ 36:11፤ ኢያ 17:3)
ቲቁዋ፣ ቴቁዋ ~ Tikvah: ‘ተስፋ’ ማለት ነው።
1. ልብስ ጠባቂው፥ የሐስራ ልጅ፥ የሴሌም አባት፥ “እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢያቱ ...” (2 ነገ 22:14)
2. የሕዝያ አባት፥ “ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊውም ሳባታይ ረዱአቸው።” (ዕዝ
10:15)
ቲቶ ~ Titus: ‘የተከበረ’
ማለት ነው።
ከጳውሎስና ከባርናባስ
ጋር በኢየሩሳሌም
ጉባኤ የነበረ፥
“ከዚያ ወዲያ ከአሥራ
አራት ዓመት
በኋላ ከበርናባስ
ጋር ቲቶን ደግሞ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም ሁለተኛ ወጣሁ፤” (ገላ 2:1-3፤ ሐዋ 15:2)
ቲኪቆስ ~ Tychicus: ‘ወሳኝ፣ ቁርጥ’ ማለት ነው። የእስያ
ሰው፥ ቅዱስ
ጳውሎስን በጉዞው የተባበረ፥ “የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም
አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ” (ሐዋ 20:4፥ 21:29፤ 2 ጢሞ 4:20)
ቲድዓል ~ Tidal: ‘ታደል፣ ታደለ፣ ተድላ፣ የታደለ’ ማለት
ነው። የአሕዛብ
ንጉሥ የነበረ፥
“በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥
በእላሳር ንጉሥ
በአርዮክ፥ በኤላም
ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥
በአሕዛብ ንጉሥ
በቲድዓል ዘመን
እንዲህ ሆነ” (ዘፍ
14:1፣9)
ቲፍሳ ~ Tiphsah: ‘መተላለፊያ፣ መሻገሪያ’ ማለት
ነው። ሰሎሞን
የነገሠበት የግዛት
ድንበር፥ “ከወንዙ ወዲህ ባሉት ነገሥታት ሁሉ ከወንዙም ወዲህ ባለው አገር ሁሉ ላይ ከቲፍሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር ...” (1 ነገ 4:24)
ታሐት ~ Tahath:
‘መስፈሪያ፣ ማረፊያ፣ መነኻሪያ’ ማለት ነው።
1. የእስራኤል ልጆች በጉዞ ካረፉባቸው ቦታዎች፥ “ከመቅሄሎትም ተጕዘው
በታሐት ሰፈሩ” (ዘኊ 33:26)
2. ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ከነበሩ፥ “የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥” (1 ዜና
6:37፥ 9:22)
3. “የኤፍሬም ልጆች ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሽቱላ” (1 ዜና 7:20)
4. “የኤፍሬም ልጆች ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሽቱላ” (1 ዜና 7:20)
ታሐን ~ Tahan: ‘ሰፈራ’
ማለት ነው።
የኤፍሬም ልጅ፥
“በየወገናቸው የኤፍሬም ልጆች እነዚህ ናቸው። ከሱቱላ የሱቱላውያን ወገን፥ ከቤኬር የቤኬራውያን ወገን፥
ከታሐን የታሐናውያን
ወገን።”
(ዘኊ 26:35)
ታማር ~
Tamar:
ተምር፣ የተምር ዛፍ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ትዕማር]
የቦታ ስም፥ “የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ...” (ሕዝ 47:19፣ 48:28)
ታምኒ ~ Tibni: ታማኒ፣ ታማኝ... ማለት
ነው። የጎናትን
ልጅ፥ “በዚያም ጊዜ
የእስራኤል ሕዝብ
በሁለት ተከፈለ። የሕዝቡም
እኩሌታ የጎናትን
ልጅ ታምኒን
ያነግሡት ዘንድ
ተከተለው እኩሌታውም
ዘንበሪን ተከተለ።” (1 ነገ
16:21፣22)
ታራ ~ Tarah, Terah: ‘ተራ’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን ከግብፅ
ከወጡ በኋላ፥ በርቀት ከሰፈሩባቸው ቦታዎች አንዱ፥ “ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ” (ዘኊ 33:27)
ታራ /
Terah:
‘ተራ፣ ሰፈራ’
ማለት ነው። የአብራም፣ የናኮር፣ የሐራን አባት፥
“ታራም መቶ
ዓመት ኖረ፥
አብራምንና ናኮርን
ሐራንንም ወለደ” (ዘፍ
11:24-32)
ታሬዓ ~
Tahrea, Tarea: ‘ንዴት፣ ጥላቻ’
ማለት ነው። የሚካ ልጅ፥
“የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።” (1 ዜና 9:41)
ታሬዓ /
Tarea:
‘ጠራ፣ ተጣራ፣ ጮኽ’
ማለት ነው። የሚካ ልጅ፥
“የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።” (1 ዜና 8:35)
ታቦር ~
Tabor:
‘ኮረብታ’ ማለት ነው። የዛብሎን ልጆች ርስት የተሰጠ የቦታ ድንበር፥
“ድንበሩም ወደ ታቦርና
ወደ ሻሕጹማ፥
ወደ ቤትሳሚስ
ደረሰ፥ የድንበራቸውም
መውጫ ዮርዳኖስ
ነበረ። አሥራ ስድስት
...” (ኢያ 19:22)
ታዕናክ ~ Taanach, Tanach: ‘ትሑት’
ማለት ነው።
የከነናውያን ጥንታዊ ከተማ፥ ንጉሡን ኢያሱ የያዘው፥ “የአዚፍ ንጉሥ፥ የታዕናክ ንጉሥ፥ የመጊዶ ንጉሥ፥” (ኢያ 12:21)
ታዕናክ / Tanach: “ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው” (ኢያ 21:25)
ታዴዎስ ~ Thaddeus:
ተወዳሽ፣ ተወዳጅ፣ ተመስጋኝ... ማለት ነው። ልብድዮስ ለተባለው ሐዋርያ መጠሪያ ስም፥ “ፊልጶስም ... የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥”
(ማቴ 10:3፤ ማር 3:18)
ታጱዋ ~ Tappuah: ‘የፍራፍሬ ከተማ’ ማለት ነው።
1. በይሁዳ ሸለቆ የነበረ የከተማ ስም፥ ቀደም ብሎ የከነናውያን መናገሻ የነበረ፥ “የታጱዋ ንጉሥ፥ የኦፌር ንጉሥ፥ የአፌቅ ንጉሥ፥” (ኢያ 12:17)
2. በኤፍሬም ድንበር የሚገኝ ከተማ፥ “ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ
ቃና ወንዝ
ድረስ አለፈ፥
መውጫውም በባሕሩ
አጠገብ ነበረ።
የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።” (ኢያ 16:8)
3. “የምናሴም ድንበር ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ነበረ፤ ድንበሩም በቀኝ በኩል ወደ ዓይንታጱዋ ሰዎች
አለፈ።”
(ኢያ 17:7)
ቴላ ~
Telah:
ጠል፣ ጥላ፣ ጠለል፣ ርጥበት... ማለት ነው። የኤፍሬም ወገን፥ የኢያሱ ቅድመ አያት፥ “ወንዶች ልጆቹም ፋፌ፥ ሬሴፍ፥ ልጁ ቴላ፥” (1 ዜና 7:25)
ቴላሬሳ~Telharsa: የባቢሎናውያን ከተማ፥ “ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ። ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ... ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም” (ዕዝ 2:59፤ ነህ 7:61)
ቴልሜላ ~ Tel-melah: ‘የጨው ክምር’ ማለት
ነው። የባቢሎናውያን
ከተማ፥ “ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ። ነገር ግን
የአባቶቻቸውን ቤቶችና
ዘራቸውን ወይም
ከእስራኤል ወገን
መሆናቸውን ያስታውቁ
ዘንድ አልቻሉም” (ዕዝ
2:59፤ ነህ 7:61)
ቴልአቢብ ~ Telabib: ‘የእሸት ክምር፣ የአበባ ሐውልት’
ማለት ነው።
ሕዝቅኤል ባየው
ራእይ የተጠቀሰ፥ የከተማ ስም፥ “በቴልአቢብም ወዳሉ በኮቦርም ወንዝ አጠገብ ወደ ተቀመጡ ምርኮኞች
መጣሁ፥ በተቀመጡበትም
ቦታ ተቀመጥሁ፤ በዚያም
ሰባት ቀን
በድንጋጤ በመካከላቸው
ተቀመጥሁ።”
(ሕዝ 3:15)
ቴማ ~
Tamah:
‘ሳቂታ’ ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የቴማ ልጆች ይገኙበታል፥
“የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥
የሐጢፋ ልጆች።” (ዕዝ 2:54)
ቴማ ~
Thamah:
‘ልጅ’ ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የቴማ ልጆች ይገኙበታል፥
“የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥
የሐጢፋ ልጆች።” (ዕዝ 2:54)
ቴማን ~ Tema, Teman:
‘ደቡብ’ ማለት ነው። የእስማኤል
ልጅ፥ “ዱማ፥ ማሣ፥
ኩዳን፥ ቴማን፥
ኢጡር፥ ናፌስ፥
ቄድማ”
(ዘፍ 25:15፤ 1 ዜና 1:30፤ ኢዮ 6:19፤ ኢሳ 21:14፤ ኤር 25:23)
ቴማን /
Teman: ‘የደቡብ’
ማለት ነው።
1. የዔሳው ልጅ፣
የኤልፋዝ ልጅ፥
“የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው
ቴማን፥ ኦማር፥
ስፎ፥ ጎቶም፥
ቄኔዝ”
(ዘፍ 36:11፣15፣41፤ 1 ዜና 1:36)
2. “ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን?” (ኤር 49:7፣8፤
ሕዝ 25:13)
ቴስብያዊው ~
Tishbite:
‘የሚይዝ፣ የሚገንዝ’
ማለት ነው። ነቢዩ ኤልያስ በዚህ ስም
ተጠርቷል፥ “በገለዓድ ቴስቢ
የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፦ በፊቱ
የቆምሁት የእስራኤል
አምላክ ሕያው
እግዚአብሔርን!
ከአፌ ቃል
በቀር በእነዚህ
ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም አለው” (1 ነገ 17:1፥ 21:17፣28)
ቴርጋማ ~ Togarmah: ‘አጥንታም’ ማለት ነው። የጋሜርም ልጅ፥ “የጋሜርም ልጆች
አስከናዝ፥ ሪፋት፥
ቴርጋማ
ናቸው” (ዘፍ 10:3)
ቴቁሔ ~ Tekoa: ‘እውጅ’ ማለት ነው።
1. በይሁዳ ነገድ የነበረ ከተማ፥ “በይሁዳና በብንያም ያሉትንም የተመሸጉትን ከተሞች፥ ቤተ ልሔም፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥” (2 ዜና 11:6)
2. በይሁዳ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የአሽሑር ልጅ፥ “ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።” (1 ዜና
2:24፥ 4:5)
ቴቄል ~
Tekel:
ተክል፣ ልክ፥ ለካ፣ መዘነ፣ መጠነ፣ ክብደት... ማለት ነው።
የሰው እጅ
ጣቶች ወጥተው
በንጉሡ ቤት
በተለሰነው ግንብ
ላይ በመቅረዙ
አንጻር ጻፉ
ንጉሡ ብልጣሶር
የሚጽፉትን ጣቶች
አየ፥ የተጻፈውም
ጽሕፈት፥ “ቴቄል ማለት፥
በሚዛን ተመዘንህ፥
ቀልለህም ተገኘህ
ማለት ነው።”
(ዳን 5:27)
ቴቄምናስ ~ Tahpenes: የፈርዖን
ሚስት፥ “የሚስቱንም የእቴጌይቱን
የቴቄምናስን እኅት እስኪያጋባው ድረስ ሃዳድ በፈርዖን ፊት እጅግ ባለምዋል ሆነ።”
(1 ነገ 11:19፣20)
ቴቤስ ~ Thebez:
‘ግልጥ፣ ዕውቅ’ ማለት ነው።
አቤሜሌክ የሞተበት ቦታ፥“አቤሜሌክም ወደ ቴቤስ መጣ፥ ቴቤስንም ከብቦ ያዛት” (መሣ 9:50)
ቴዎዳስ ~
Theudas:
ተወዳሽ፣ ተመስጋኝ... ማለት ነው። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ የተነሣ፥
ገማልያ በኢየሩሳሌም
ባደረገው ንግግር
የጠቀሰው። “ከዚህ ወራት
አስቀድሞ ቴዎዳስ።
እኔ ታላቅ
ነኝ ብሎ
ተነሥቶ ነበርና፥
አራት መቶ
የሚያህሉ ሰዎችም
ከእርሱ ጋር
ተባበሩ፤ እርሱም
ጠፋ የሰሙትም
ሁሉ ተበተኑ
እንደ ምናምንም
ሆኑ”
(ሐዋ 5:36)
ቴዎፍሎስ ~ Theophilus: ‘የአምላክ ወዳጅ፣ የጌታ ጓደኛ’
ማለት ነው።
ሉቃስ ወንጌልን
የጻፈለት ሮማዊ
ክርስቲያን፥ “የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን
ያዩትና የቃሉ
አገልጋዮች የሆኑት
እንዳስተላለፉልን፥ በኛ
ዘንድ ስለ
ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው
ቃል እርግጡን
እንድታውቅ በጥንቃቄ
ሁሉን ከመጀመሪያው
ተከትዬ በየተራው
ልጽፍልህ መልካም
ሆኖ ታየኝ።” (ሉቃ 1:3)
ትዕማር ~
Tamar:
ትማር፣ ተማረ፣ ይቅር ተባለ፣ ምሕረት አገኘ... ማለት ነው። (‘ታምር ፥ ተምር፣ የተምር ዛፍ ማለት ነው’ ተብሎም ተተርጉሟል)
[ተዛማጅ ስም-
ታማር]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የይሁዳም የበኵር ልጁ፣ የዔር ሚስት፥ (ዘፍ 38:8-30)
2. የዳዊት ልጅ፣ የአቤሴሎም እኅት፥ (2
ሳሙ13:1-32)፣ (1 ዜና 3:9)
3. የአቤሴሎም ልጅ፥ (2 ሳሙ 14:27)
ትያጥሮን ~ Thyatira: ‘ሽቶ’ ማለት ነው። (የሳቅ የጨዋታ ቤት፥ ብዙ ዓይነት የጥጋብ ጨዋታ፥ ምሳሌና ተረት፥ ምትሀትና ውሸት’ ማለት ነው። ኪወክ /አ) በታናሽቱ እስያ የነበረ ከተማ፥ “እንዲሁም። የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ
ሰምርኔስ ወደ
ጴርጋሞንም ወደ
ትያጥሮንም ወደ
ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ... ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ” (ራእ 1:11፥2:18-28)
ቶሑ ~ Tohu: ‘የበታች፣ ትሑት፣ ምስኪን’
ማለት ነው።
የነቢዩ ሳሙኤል
ቅድመ አያት፥
“በተራራማው በኤፍሬም አገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ስሙ ሕልቃና የተባለ ... የኢያሬምኤል ልጅ የኢሊዮ ልጅ የቶሑ ልጅ የናሲብ ልጅ ነበረ።” (1 ሳሙ 1:1)
ቶላ ~ Tola: ትል
ማለት ነው።
1. የይሳኮር ልጅ፥ “የይሳኮርም ልጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ ዮብ፥ ሺምሮን።”
(ዘፍ 46:13)
2. የፎሖ ልጅ፥ “ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ
የፎሖ ልጅ
ቶላ እስራኤልን
ለማዳን ተነሣ
በተራራማውም በኤፍሬም
አገር ባለችው
በሳምር ተቀምጦ
ነበር።”
(መሣ 10:1፣2)
ቶላድ ~
Tolad:
ትውልድ፣ ልጅ፣ ዘር... ማለት ነው። በይሁዳ ደቡብ፥ የስምዖን ከተማ፥
“በቶላድ፥ በቤቱኤል፥ በሔርማ፥
በጺቅላግ፥”
(1 ዜና 4:30)
ቶማስ ~
Thomas:
‘መንታ’ ማለት ነው። ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ፥ “ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ
ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ
ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥” (ማቴ 10:3፤ ማር 3:18)
ቶቤል ~ Tubal: ‘ምድር’
ማለት ነው።
የያፌት ልጅ፥
“የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።” (ዘፍ 10:2)
ቶዑ ~ Toi: የሐማት
ንጉሥ፥ የዳዊትን
ድል ማድረግ
ሲሰማ የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ስጦታን አስይዞ የላከ፥ “የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ
እንደ መታ
ሰማ።”
(2 ሳሙ 8:9፣10)
ቶኬን ~
Tochen:
‘የተመተረ፣ የተለካ’ ማለት ነው። የስምዖን ከተማ፥
“መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ...” (1 ዜና 4:32)
ቶዋ ~
Toah:
‘ጦር መሣሪያ፣ ቀስት’ ማለት ነው። የዘማሪው የኤማን ቅድመ አያት፥ “የሳሙኤል ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ ... የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥” (1 ዜና 6:34)
ቶፌት ~ Tophet: ጥፋት
ማለት ነው።
ለጣዖት አምልኮ
ልጆቻቸውን ያቃጥሉበት
የነበረ ቦታ፥
“...ወንዶችና ሴቶች
ልጆቻቸውን በእሳት
ያቃጥሉ ዘንድ
በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠርተዋል።” (ኤር 7:31)
No comments:
Post a Comment