ረሐም ~ Raham: ርኅሩኅ አዛኝ፣ ወዳ ማለት ነው። ከካሌብ ወገኖች አንዱ፥ ሽማዕም የዮርቅዓምን አባት ረሐም ወለደ ...” (1 ዜና 2:44)

ረቃት ~ Rakkath: ናት፣ ባዶዎ ማለት ነው። የቤተ መቅደስ አለቃ የነበረ፥ ረቃት ኬኔሬት፥ አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥” (ኢያ 19:36)

ረቡኒ ~ Rabboni: አባት የሆነ፣ ታላቅ፣ መሪ፣ መምህር... ማለት ነው። ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ። ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም። መምህር ሆይ ማለት ነው።” (ዮሐ 30:18)

ረቢ ~ Rabbi: ረቢ፣ የሚራባ፣ የሚባዛ፣ የሚዋለድ፣ ትልቅ አባት፣ ታላቅ ሕዝብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ረቢት፣ ረባት]

ረባከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

ከዮሐንስ ጋር የነበሩ ሐዋርያት፥ ጌታን የጠሩበት ስም፥ እርሱም፦ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ ትርጓሜው መምህር ሆይ ማለት ነው።” (ዮሐ 1:38 49)

ረቢት ~ Rabbith: ረብዓት፣ ረባ፣ ተራባ፣ ተባዛ፣ ተዋለደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ረቢ፣ ረባት]

ረባከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የቦታ ስም፥ ወደ ረቢት ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥ (ዮሐ 19:20)

ረባት ~ Rabbah: ረብዓት፣ ረባ፣ ተራባ፣ ተባዛ፣ ተዋለደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ረቢ፣ ረቢት]

ረባከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ቦታዎች አሉ።

1. ሙሴ ለጋድ ነገድ ለጋድም ልጆች በየወገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው የቦታ ድንበር፥ (ኢያ 13:25)

2. በይሁዳ ተራራ አቅራቢያ የሚገኝ ከተማ፥ (ኢያ 15:60)

ረአሶን ~ Rezin: ጽኑ ብርቱ፣ ጠንካራማለት ነው። ከፋቁሔ ጋር የተባበረ የሶርያ ንጉሥ፥ በዚያም ወራት እግዚአብሔር የሶርያን ንጉሥ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ፋቁሔን በይሁዳ ላይ መስደድ ጀመረ። (2 ነገ 15:37 16:5-9 ኢሳ 7:1-8)

ረአብ ~ Rehob: ስፋት፣ መስፋፋትማለት ነው።

1. የሱባ ንጉሥ የአድርአዛር አባት፥ ዳዊትም ደግሞ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ ረአብ ልጅ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን መታ።” (2 ሳሙ 8:312)

2. የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙ፥ ከሌዋውያኑ ወገን የሆነ፥ የኤንሐዳድ ልጅ፥ ፌልያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረአብ ሐሸብያ፥ (ነህ 10:11)

3. የሶርያ ከተማ፥ የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ተሰለፉ የሱባና ረአብ ሶርያውያን፥ የጦብና የመዓካም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።” (2 ሳሙ 10:68 መሣ 18:28)

4. የአሴር ከተማ፥ ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ። (ኢያ 19:28)

5. ሌላ የአሴር ከተማ፥ ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 19:30)

ረዓምያ ~ Raamiah: ሕያው ነጎድጐድ ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ አለቆች አንዱ፥ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ረዓምያ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ... ከበዓና ጋር መጡ።” (ነህ 7:7)

ረዓብ ~ Rahab: ትእቢት፣ ትምክህትማለት ነው። የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ። (መዝ 87:4 89:10 ኢሳ 51:9)

ረዓብያ ~ Rehabiah: ረብዓ ያሕ፣ ረበ ያሕ፣ ጌታ ያበረከተው፣ አምላክ ያራባው፣ የተባዛ... ማለት ነው።

ረባከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የአልዓዛር ልጅ፥ የአልዓዛርም ልጆች አለቃ ረዓብያ ነበረ አልዓዛርም ሌሎች ልጆች አልነበሩትም ረዓብያ ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ። (1 ዜና 23:17)

ረዕላያ ~ Reelaiah: የሕያው አገልጋይማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱት፥ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ረዕላያ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።” (ዕዝ 2:2)

ረፋያ ~ Rapha, Rephaiah: ረፋያ፣ ረፈ ያሕ፣ ረፍተ ሕያው፣ ዘላለማዊ ዕረፍት፣ የአምላክ ሰላም... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሪፋት ራፋያ፣ ራፋይ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ረፋያ / Rapha: የሳዖል ወገን የሆነ የቢንዓ ልጅ፥ (1 ዜና 8:2 37) (1 ዜና 9:43)

       ረፋያ / Rephaiah:

1. የዘረሩባቤል ወገን፥ ረፋያ (1 ዜና 3:21)

2. ከስምዖን ልጆች አለቆች አንዱ፥ ረፋያ (1 ዜና 4:42)

3. የኢየሩሳሌም ግዛት እኵሌታ አለቃ የሆር ልጅ፥ ረፋያ (ነህ 3:9)

4. የቢንዓ ልጅ፥ ረፋያ (1 ዜና 9:43)

5. የቶላ ልጅ፥ ረፋያ (1 ዜና 7:2)

ሩሃማ ~ Ruhamah: መማር፣ ምሕረትን ማግኘትማለት ነው። ወንድሞቻችሁን፦ ዓሚ፥ እኅቶቻችሁንም። ሩሃማ በሉአቸው” (ሆሴ 2:3)

ሩማ ~ Rumah: መ፣ ቆመ፣ ተነሣ፣ ከፍ አለ... ማለት ነው። የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኢዮአቄም እናት፥ የፈዳያ ልጅ፥ ኢዮአቄምም ...አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ዘቢዳ ትባል ነበር እርስዋም ሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች። (2 ነገ 23:36)

ሩት ~ Ruth: ርቱዕ፣ ርትዕ፣ ርትዒት፣ ርትዑ፣ ርኡት፣ ቅን፣ እውነተኛ፣ አሸናፊ... ማለት ነው።

ረታከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

የኑኃሚን ምራት፥ በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰች፥ እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። ...” (ሩት 1:4) (ማቴ 1:5)

ሩፎስ ~ Rufus: ቀይማለት ነው። የቀሬና ስምዖን ልጅ፥ አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና ሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።” (ማር 15:21)

ሪሞን ~ Remmon: ፍራፍሬ የሞላበት፥ የስምዖን ነገድ ርስት የሆነ ከተማ፥ ዓይን፥ ሪሞን ዔቴር፥ አሻን አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው (ኢያ 19:7)

ሪሳ ~ Rissah: ሪሳ፣ ሬሳ፣ ሙት፣ አስከሬን፣ በድን... ማለት ነው። እስራኤላውያን፣ የሰፈርበት፣ የቦታ ስም፥ ከልብናም ተጕዘው ሪሳ ሰፈሩ (ዘኁ 33:21 22)

ሪባ ~ Reba: ረባ፣ ተዋለደ፣ አራት... ሆነ ማለት ነው። ...አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።” (ዘኊ 31:8 ኢያ 13:21)

ሪባይ ~ Ribai: ጠቃሚ፣ ላፊነት የሚበቃ... ማለት ነው። አምላክን ተማፃኝ ማለት ነውተብሎም ይተረጎማል። ከጊብዓ ሪባይ ልጅ ኢታይ፥ ጲርዓቶናዊው በናያስ፥ የገዓስ ወንዝ ሰው” (2 ሳሙ 23:29 1 ዜና 11:31)

ሪብላ ~ Riblah: ለም፥ ዘርን የሚቀበል፥ የሚሰጥማለት ነው። በሰሜናዊ ፍልስጥኤም ፊተኛ፥ የነበረ የከተማ ስም፥ በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ባለችው ሪብላ አሰረው በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት (2 ነገ 23:33 25:620 21 ኤር 39:5 52:10)

ሪትማ ~ Rithmah: ጤናማለት ነው። እስራኤላውያን በምድረ በዳ ካረፋባቸው ቦታዎች፥ ከሐጼሮትም ተጕዘው ሪትማ ሰፈሩ።” (ዘኊ 33:1819)

ሪና ~ Rinnah: ደስታ፣ ዘፈንማለት ነው። ከይሁዳ ልጆች አንዱ፥ የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ።” (1 ዜና 4:20)

ሪጽፋ ~ Rizpah: ከሰማለት ነው። የንጉሥ ሳኦል ቁባት፥ የኢዮሄል ልጅ፥ የሳኦልም ቁባት የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ለዳዊት ነገሩት (2 ሳሙ 21:8-11)

ሪፋት ~ Riphath: ዕረፍት፣ ነት፣ ምሕረት፣ ይቅርታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ረፋያ፣ ራፉ፣ ራፋኤል፣ ራፋይ]

ረፍከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የኖኅ ልጅ፥ የያፌት ልጅ፥ የጋሜር ልጅ፥ ሪፋት (ዘፍ 10:3)

ራሔል ~ Rachel: ማለት ነው። የያዕቆብ ሚስት፥ (ዘፍ 29:628) “እርሱ። ደኅና ነውን? አላቸው። እርሱም፦ አዎን ደኅና ነው አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት።

ራማ፣ ሬማት፣ ርማቴ ~ Ramah: ከፍተኛ ማለት ነው።

1. ከብንያም ከተሞች አንዱ፥ ገባዖን፥ ራማ ብኤሮት፥” (ኢያ 18:25)

2. የሕልቃና እና የሐና አገር፥ ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ተመልሰውም ወደ አርማቴ ወደ ቤታቸው መጡ። ...” (1 ሳሙ 1:19 2:11)

3. ፍታሌም ምሽጎች አንዱ፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥ አዳማ፥ ራማ አሶር፥” (ኢያ 19:36)

4. ለአሴር ጉልህ ድንበሮች አንዱ፥ ድንበሩም ወደ ራማ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ” (ኢያ 19:29)

5. ጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን ሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።” (2 ነገ 8:29)

6. ከባቢሎን ምርኮ መልስ፥ የብንያም ወገኖች የሰፈሩበት፥

በሐናንያ፥ በሐጾር፥ ራማ በጊቴም፥ በሐዲድ፥ (ነህ 11:33)

ራማትሌሒ ~ Ramath-lehi: የመንጋጋ ክምር ማለት ነው። ሶምሶን በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ፍልስኤማውያንን የገደለበት፥ መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ መንጋጋውን ከእጁ ጣለ የዚያንም ስፍራ ስም ራማትሌሒ ብሎ ጠራው።” (መሣ 15:15-17)

ራምያ ~ Ramiah: የሕያው ተራራ፣ የጌታ ... ማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ ከእስራኤልም ከፋሮስ ልጆች፤ ራምያ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያ፥ በናያስ።” (ዕዝ 10:25)

ራሞት ~ Ramoth: የተከበረ፣ ከፍተኛ ማለት ነው። በይሳኮር ነገድ፥ የሌዊ ከተማ፥ በቤቴል ለነበሩ፥ ራሞት በደቡብ ለነበሩ (1 ሳሙ 30:27 1 ዜና 6:73)

ራስ ~ Rush: ራሽ፣ ራስ፣ የበላይ፣ ጭንቅላት... ማለት ነው። የእስራኤልን አለቆች ለመግለጽ የተጠቀሰ ቃል፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ራስ

ጅራትን የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።” (ኢሳ 19:14)

ራቆን ~ Rakkon: ርቃን፣ ማለት ነው። የነገደ ዳን ርስት የሆነ፥ ውኃ ገብ ቦታ፥ ይሁድ፥ ብኔብረቅ፥ ጋትሪሞን፥ ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን” (ኢያ 19:46)

ራብማግ ~ Rabmag: አሸናፊ ማለት ነው። ከባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት አንዱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ ከቀሩት ከባቢሎን” (ኤር 39:313)

ራዕማ~ Raamah: ነጎድጓድማለት ነው። የኩሽ ልጅ፥ የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ ሰበቃታ ናቸው (ዘፍ 10:7)

ራኬብ ~ Rachab: ርካብ፣ መሰላል፣ መወጣጫ ማለት ነው። በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰች፥ የቦኤዝ እናት፥ ሰልሞንም ራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ (ማቴ 1:5)

ራያ ~ Reaiah: ራእይ ያሕ፣ የሕያው ራእይ ማለት ነው።

1. የሦባል ልጅ፥ የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው። (1 ዜና 4:2)

2. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የራያ ልጆች ይገኙበታል፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ ራያ ልጆች፥ (ዕዝ 2:47 ነህ 7:50)

ራዳይ ~ Raddai: ዲእ፣ ረዳ፣ ረጅ፣ ረዳት፣ አጋዥ... ማለት ነው። የእሴ ልጅ፥ የዳዊት ወንድም፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም” (1 ዜና 2:14)

ራጉኤል ~ Raguel, Reuel: ረጋ ኤል፣ የአምላክ ዕረፍት፣ የጌታ ወዳጅ፣ ሰንበት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም:- ራጋው]

ረጋ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ራጉኤል / Raguel: የሙሴ አማት፥ ኢትዮጵያዊው ካህን፥ ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል በመጡ ጊዜ ...” (ዘጸ 2:18) (ዘኁ 10:29)

       ራጉኤል / Reuel:

1. የዔሳው ልጅ፣ ከቤሴሞት የወለደው፥ (ዘፍ 36:4 10)

2. የኤሊሳፍ አባት ራጉኤል (ዘኁ 2:14)

3. የዪብንያ ልጅ፣ የሰፋጥያስ አባት ራጉኤል (1 ዜና 9:8)

       ራጉኤል ~ Deuel: ወዳጅ ማለት ነው። በሲና በረ ሲቆጠሩ፥ የጋድ ነገድ አለቃ፥ የኤሊሳፍ አባት፥ ከጋድ ራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ (ዘኊ 1:14 7:42 47 10:20)

ራጋው ~ Ragau: ረጋ፣ መርጋት፣ ማረፍ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም:- ራጉኤል]

Ragau- ‘ረጋከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የሴሮህ ልጅ፥ (ሉቃ 3:35)

ራግው ~ Reu: ረጋ ወዳጅ ማለት ነው። በአብርሃም የዘር ሐረግ፥ የፋሌቅ ልጅ፥ ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ (ዘፍ 11:18 1 ዜና 1:25)

ራፉ ~ Raphu: ረፍ፣ ረፈ፣ ማረፍ፣ ዕረፍት፣ ማቆም፣ አለመሥራት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሪፋት ረፋያ፣ ራፋኤል፣ ራፋይ]

ረፍከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

የእስራኤል ልጆች የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ፥ ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ከላካቸው፥ ከብንያም ነገድ የፈልጢ አባት፥ (ዘኁ 13:9)

ራፊስ ~ Rezeph: ዐለት፣ ትኩስ ድንጋይማለት ነው። የቦታ ስም፥ አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?” (2 ነገ 19:12 ኢሳ 37:12)

ራፊዲም ~ Rephidim: ረፈ ደም ማረፊያ፣ መተኛ አልጋማለት ነው። እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ወጥተው ወደ ሲና እስኪደርሱ ካረፉባቸው፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ ራፊዲም ሰፈሩ ... (ዘጸ 17:1 8 19:2)

ራፋቃ ~ Dophkah: ደፈቃ፣ ረፈቀ፣ ረፈቃ፣ ማረፍ፣ መቀመጥማለት ነው። በቁጥር መጽሐፍ የተጠቀሰ፥ ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው ራፋቃ ሰፈሩ። (ዘኊ 33:12)

ራፋኤል ~ Rephael: ረፈ ኤል፣ የአምላክ ዕረፍት፣ ሰንበት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሪፋት ረፋያ፣ ራፉ፣ ራፋኤል፣ ራፋይ]

ረፍ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የሸማያ ልጅ፥ ለሸማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል ዖቤድ...” (1 ዜና 26:7 8)

ራኬብ ~ Rachab: ርካብ፣ መሰላል፣ ደረጃ፣ መወጣጫ፣ መንኮራኩር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሬካብ]

በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የሰልሞን ራኬብ (ማቴ 1:5)

ራፋያ ~ Rephaiah: ... [ረፋያ / Rapha, Rephaiah- ይመልከቱ] [ተዛማጅ ስሞች-ሪፋት ረፋያ፣ ራፋኤል፣ ራፋይ]

የቶላ ልጅ፥ የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ ይሪኤል ...” (1 ዜና 7:2)

ራፋይ ~ Rapha: ... [ረፋያ / Rapha, Rephaiah- የሚለውን ይመልከቱ።] [ተዛማጅ ስሞች- ሪፋት ረፋያ፣ ራፋኤል፣ ራፋይ]

ከዚህም በኋላ በጌዝር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ራፋይ ወገን የነበረውን ሲፋይን ገደለ።” (1 ዜና 20:4)

ሬሁም ~ Rehum: መሓሪ፣ ይቅር ባይማለት ነው።

1. ከምርኮ ከተመለሱ፥ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ሬሁም ከበዓና ጋር መጡ።” (ዕዝ 2:2)

2. የንጉሡ የአርጤክስስ አዛዥ፥ አዛዡ ሬሁም ጸሐፊውም ሲምሳይ በኢየሩሳሌም ላይ ለንጉሡ ለአርጤክስስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ።” (ዕዝ 4:8-24)

3. ሌዋዊው፥ ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም አደሱ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት... ” (ነህ 3:17)

4. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ አሎኤስ፥ ፈልሃ፥ ሶቤቅ፥ ሬሁም ሐሰብና፥” (ነህ 10:25)

5. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም ሜሪሞት፥” (ነህ 12:3)

ሬሕማ ~ Reumah: ራማ ከፍታማለት ነው። የአብርሃም ወንድም፣ የናኮር ቁባት፥ ሬሕማ የሚሉአት ቁባቱ ደግሞ ጥባህን፥ ገአምን፥ ...” (ዘፍ 22: 24)

ሬምፉም ~ Remphan: ዝግጁማለት ነው። እስራኤላውያን ካመለኳቸው ጣዖታት አንዱ፥ ትሰግዱላቸውም ዘንድ የሠራችኋቸውን ምስሎች እነርሱንም የሞሎክን ድንኳንና ሬምፉም የሚሉትን የአምላካችሁን ኮከብ አነሣችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰዳችኋለሁ ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል።” (ሐዋ 7:43)

ሬሞን~ Rimmon: ከፍተኛማለት ነው።

1. የዛብሎን ከተማ፥ ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞን መሰምርያዋ፥ ... (1 ዜና 6:77 ነህ 11:29)

2. በይሁዳ የታችኛው ክፍል የሚገኝ ቦታ፥ መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች (1 ዜና 4:32)

3. እስራኤላውያን በምድረ በዳ ካረፉባቸው ቦታዎች፥ ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ።” (ዘኊ 33:1920)

4. “ስድስቱም መቶ ሰዎች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፥ ሬሞን ዓለት አራት ወር ተቀመጡ። (መሣ 20:454721:13)

5. ከብንያም ልጆች ብኤሮታዊው፥ የሬካብ አባት፥ ለሳኦልም ... የብኤሮታዊው ሬሞን ልጆች ነበሩ ብኤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር” (2 ሳሙ 4:259)

ሬሲ ~ Rei: ወዳጅ ማለት ነው። አዶንያስ በዳዊት ላይ ባመጸ ጊዜ፥ ከዳዊት ጋር ጸንተው ከቆዩት፥ ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን ሳሚም ሬሲ የዳዊትም ኃያላን ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም። (1 ነገ 1:8)

ሬሴን ~ Resen: ራስ፣ የላይ የወንዝ መነሻ፣ ምንጭ... ማለት ነው። ናምሩድ ከገነባቸው ከተሞች፥ በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴን ሠራ እርስዋም ... ከተማ ናት። (ዘፍ 10:12)

ሬስ ~ Rhesa: ሪስ፣ ራስ፣ ራሴ፣ እንደራሴ፣ እኔ፣ እንደኔ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም:- ሮስ]

በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የዘሩባቤል ልጅ፥ (ሉቃ 3:27)

ሬካብ ~ Rechab: ርካብ፣ መወጣጫ መሰላል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ራኬብ]

ርካብ ማለት እንደ የበቅሎ የፈረስ መወጣጫ ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:- 1.የኢዮናዳብን አባት፥ (2 ነገ 10:15 23 ኤር 35:6-19)

2.የኢያቡስቴ ከጭፍራ አለቆች አንዱ፥ (2 ሳሙ 4:2)

ሬካብ ~ Rechab: ርካብ፣ መሰላል፣ ሰረገላ... ማለት ነው።

1. የሳኦልም ልጅ፣ ኢያቡስቴ ልጅ፥ ከጭፍራ አለቆች አንዱ፥ ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ... (2 ሳሙ 4:2)

2. የኢዮናዳብ አባት፥ ከዚያም በሄደ ጊዜ ሬካብ ልጅ ኢዮናዳብን ተገናኘው ደኅንነቱንም ጠይቆ ልቤ ከልብህ ጋር እንደ ሆነ ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን? አለው።” (2 ነገ 10:15 23 ኤር 35:6-19)

ሬዞን ~ Rezon: ልዑል አለቃ፣ ትልቅ፣ የበላይ፣ መሪማለት ነው። የሶርያዊው፥ የኤልያዳ ልጅ፥ እግዚአብሔርም ... ሬዞን ጠላት አድርጎ አስነሣበት። (1 ነገ 11:23)

ሬጊዩም ~ Rhegium: ክፍተትማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ከጎበኛቸው፥ በደቡባዊ ጣልያን የነበረ ከተማ፥ ከዚያም እየተዛወርን ወደ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ ... ፑቲዮሉስ መጣን።

ሬጌሜሌክ ~ Regem-melech: ረጅ መላክ፣ ተራዳይ፣ አጋዥ፣ የንጉሥ ተጠሪ፣ ረዳት መልእክተኛ... ማለት ነው።

ረጅ እና መላክ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ነቢዩ ዘካርያስ ወደ እግዚአብሔር ከላካቸው፥ (ዘካ 7:2)

ሬጌም~ Regem: ረጅ፥ ረዳት፣ አጋዥ፣ ጓደኛ... ማለት ነው። የያሕዳይ ልጅ፥ ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። የያሕዳይም ልጆች ሬጌም ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ፥ ሸዓፍ ነበሩ።” (1 ዜና 2:47)

ርኆቦት፣ ረሆቦት~ Rehoboth: ርባታ፣ መራባት፣ መባዛት፣ መስፋፋት... ማለት ነው።

1. ይስሐቅ ከቆፈራቸው የውኃ ጉድጓዶች ሦስተኛው፥ ...ስለ እርስዋም አልተጣሉም ስምዋንም ርኆቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን” (ዘፍ 26:22)

2. አሴር የገነባት ከተማ፥ አሦርም ከዚያች አገር ወጣ ነነዌን፥ ረሆቦት ከተማ፥ ካለህን፥” (ዘፍ 10:11)

3. ሳኦል የተባለ የኤዶማውያን ሰው የነገሠበት ከተማ፥ ... በወንዝ አጠገብ ካለችው ርኆቦት ሳኦል ነገሠ። (ዘፍ 36:37 1 ዜና 1:48)

ርብቃ ~ Rebekah: ወጥመድ፣ ሸምቀቅ ማነቆማለት ነው። የባቱኤል ልጅ፥ የይስሐቅ ሚስት፥ ባቱኤልም ርብቃ ወለደ እነዚህን ስምንቱን ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደች።” (ዘፍ 22:23 24:67)

ሮማንቲዔዘር ~ Romamti-ezer: ታላቅ ወገን፣ ከፍተኛ ረዳትማለት ነው። የኤማን ልጅ፥ ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት” (1 ዜና 25:431)

ሮሜ ~ Rome: ኃይል፣ ብርታትማለት ነው። ጌታ በተወለደበት ዘመን የነበረ፥ የዓለም ዋና ከተማ፥ በፍርግያም ... በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ ሮሜ የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥” (ሐዋ 2:10)

ሮሜልዩ ~ Remaliah: ረማ ለያሕ፣ አምላክ የጠበቀው፥ ሕያው የተንከባከበውማለት ነው። የፋቁሔ አባት፥ የሠራዊቱም አለቃ ሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፥ ... በእርሱም ፋንታ ነገሠ። (2 ነገ 15:25-37 16:15)

ሮስ ~ Rosh: ራስ፣ የበላይ አካል፣ አለቃ፣ ዋነኛ... ማለት ነው። (ወንድ ልጅ፥ ማለት ነው ተብሎም ይተረጎማል። ኪወክ / ) [ተዛማጅ ስም:- ሬስ]

ራስከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በግብፅ የተወለደ ከብንያም ወገን የሆነ፣ የቤላ ልጅ፥ (ዘፍ 46:21)

ሮቆም፣ ሬቄም ~ Rekem: የገነነ፣ ያሸበረቀ የተንቆጠቆጠማለት ነው።

1. እስራኤላውያን ካጠፏቸው፥ የምድያም ነገሥታ፣ ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ... ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ ... (ዘኊ 31:8)

2. የኬብሮን ልጅ፥ የኬብሮንም ልጆች ቆሬ፥ ተፉዋ፥ ሬቄም ሽማዕ ነበሩ።” (1 ዜና 2:4344)

3. የብንያም ከተማ፥ ሬቄም ይርጵኤል፥ ተርአላ፥ ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡስ ከተማ፥ ...የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።” (ኢያ 18:27)

ሮቤል ~ Reuben: ረባን፣ ወለድን፣ ልጅ አገኘን፤ ረበ ኤል፣ አምላክ ያበረከተው... ማለት ነው። ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።” (ዘፍ 29:32)

ሮብዓም ~ Rehoboam: ቢ፣ ተራቢ፣ ተባዢ፣ ሰፊ ሕዝብ... ማለት ነው። የይሁዳ ንጉሥ፥ የንጉሥ ሰሎሞን ልጅ፥ የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ነገሠ ሮብዓምም ንጉሥ በሆነ ጊዜ የአርባ አንድ ዓመት ጉልማሳ ነበረ እግዚአብሔርም ስሙን የእናቱም ስም ናዕማ ነበረ እርስዋም አሞናዊት ነበረች።” (1 ነገ 14:2131)

ሮኦጋ ~ Rohgah: ጥሪ፣ አቤቱታ ማለት ነው። የአሴር ወገን፥ የሳሜር ልጅ፥ የሳሜርም ልጆች አኪ፥ ሮኦጋ ይሑባ፥ አራም ነበሩ። (1 ዜና 7:34)

ሮዴ ~ Rhoda: ሮዳ፣ ሬዳ፣ ጽጌሬዳ፣ አበባ... ማለት ነው።

ጴጥሮስ ከእስር ወጥቶ ወደ ማርቆስ እናት ቤት፣ በሄደ ጊዜ በር የከፈተችለት ገረድ፥

(ሥራ 12:12-15)

ሮግሊም ~ Rogelim: እግር፣ እግረኛማለት ነው። የገላያድ ከተማ፥ ዳዊትም ወደ መሃናይም ... የዓሚኤል ልጅ ማኪር፥ ሮግሊም ሰው ገለዓዳዊ ቤርዜሊ፥” (2 ሳሙ 17:27 19:31)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ