ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ከለዳ ~
Chaldea:
‘ባለዛር፣ ጠንቋይ፣ ክፉ መንፈስ’ ማለት ነው። እስራኤላውያን የአምላክን ትእዛዝ
በመተላለፋቸው በግዞት
የተወሰዱበት አገር፥
“አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ
ካስቈጡ በኋላ
በከለዳዊው በባቢሎን
ንጉሥ በናቡከደነፆር
እጅ አሳልፎ
ሰጣቸው፥ ... ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ” (ዕዝ 5፥12)
ከልቀድ ~ Chalcol: ‘መጋቢ’
ማለት ነው።
የንጉሥ ሰሎሞንን
ጥበብ ታላቅነት ለማነጻጸር ከተጠቀሱ ሰዎች፥ “ከሰውም ሁሉ ይልቅ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።” (1 ነገ 4:31)
ከልኮል ~
Calcol:
‘ቃለቃል፣ መመገብ’ ማለት ነው። የይሁዳ ሰው የዛራ ልጅ፥ “ከልኮል፥ ዳራ ሁሉም አምስት ነበሩ። የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም
ሰርቆ የበደለ
አካን ነበረ” (1 ዜና 2:7)
ከመዓም ~ Chimham: ‘ምኞት፣ ፍላጎት፣ ጉጉት’ ማለት ነው። ከዳዊት
ጋር ከዮርዳኖ ስ ማዶ የተመለሰ፥ የገለዓዳዊው የቤርዜሊ ልጅ፥ “እኔ ባሪያሕ ተመልሼ ... ነገር
ግን ባሪያሕን
ከመዓምን እይ
እርሱ ከጌታዬ
ከንጉሡ ጋር
ይለፍ፥ ደስ
የሚያሰኝህንም ለእርሱ
አድርግ።”
(2 ሳሙ 19:37፣38፣40)
ከሞስ ~
Chemosh: ‘ትሑት፣ ልዝብ’ ማለት ነው። የሞዓባውያን
ብሔራዊ ጣዖት፥
“ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤
ወንዶች ልጆቹን
ለሽሽት፥ ሴቶች
ልጆቹንም ለምርኮ፥
ለአሞራውያን ንጉሥ
ለሴዎን ሰጠ” (ዘኊ
21:29፤ ኤር 48:7፣13፣46)
ከስሉሂም ~ Casluhim: ‘ደፋር፣ ብርቱ፣
ጽኑ ምሽግ’ ማለት
ነው። የምጽራይም ወገኖች፥ “ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም
ወለደ።”
(ዘፍ 10:14፤ 1 ዜና 1:12)
ከስሎት ~ Chesulloth:
‘አናብስት’ ማለት ነው። ከይሳኮር ከተሞች አንዱ፥ “ወደ ከስሎት፥ ወደ ሱነም፥ ወደ ሐፍራይም፥ ...” (ኢያ 19:18)
ከስቢ ~ Cozbi: ‘ቀጣፊ፣ ከሃዲ’
ማለት ነው። የምድያማዊው የሱር ልጅ፥ “የተገደለችውም ምድያማዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ፤ እርስዋም የሱር ልጅ ነበረች፤ እርሱም በምድያም ዘንድ የአባቱ ቤት ወገን አለቃ ነበረ” (ዘኊ 25:15፣18)
ከርሚ ~
Carmi:
ቃርሚያዬ፣ የእርሻ ቦታዬ... ማለት ነው።
1.
ከአራቱ የሮቤል ልጆች የመጨረሻው፥ “የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥
ከርሚ።”
(ዘፍ 46:9)
2.
የይሁዳ ልጅ፥ “የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚ፥ ሆር፥ ሦባል ናቸው።”
(1 ዜና 4:1)
3.
የዘንበሪ ልጅ፥ “ዘንበሪም ተለየ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ
የዛራ ልጅ
አካን ተለየ።” (ኢያ
7:18)
ከርከሚሽ ~ Charchemish: ‘የተወሰደ፥ የተነጠቀ’ ማለት
ነው። “ከዚህም ሁሉ በኋላ፥ ኢዮስያስም ቤተ መቅደሱን ካሰናዳ በኋላ፥ የግብፅ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ባለው በከርከሚሽ ላይ ይዋጋ ዘንድ ወጣ ኢዮስያስም ሊጋጠመው
ወጣ።”
(2 ዜና 35:20)
ከርከስ ~ Carcas: ‘ግልጽ’ ማለት ነው። ከሰባቱ
የንጉሥ አርጤክስስ
ጃንደረባዎች፥ “...የመንግሥቱን ዘውድ ጭነው ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥
ዜታርን፥ ከርከስን
አዘዛቸው።”
(አስ 1:10)
ከባስን ~ Habaziniah: ‘ያምላክ ብርሃን’ ማለት
ነው። የሬካባውያንን
ወገን አባት፥ “የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን ወንድሞቹንም ልጆቹንም ሁሉ የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኋቸው” (ኤር 35:3)
ከቦን ~ Cabbon: ‘ጥልቅ ግንዛቤ’ ማለት
ነው። በታችኛው
የይሁዳ ግዛት
ያለ አገር፥ “ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ
ስድስት ከተሞችና
መደሮቻቸው።”
(ኢያ 15:40)
ከነዓን ~
Canaan:
ከናን፣ ቅነን፣ ማቅናት፥ ቃናን፣ ቃናዊ፣ የቃና አገር ሰው... ማለት ነው።
የኖኅ ልጅ፣ የካም ልጅ፥ አገሩም በስሙ ተጠራ፥ (ዘፍ 10:6)
ከፊራ ~ Chephirah: ‘ሰፈር፣ መንደር’ ማለት ነው። እስራኤላውያን ካረፉባቸው አራት ከተሞች አንዱ፥ “የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ
ከተሞቻቸው መጡ
የከተሞቻቸውም ስም
ገባዖን፥ ከፊራ፥
ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም
ነበረ።”
(ኢያ 9:17)
ከፍቶር ~ Caphtor: ‘ግዝት፣ ጠፍር፣ ማሰሪያ’
ማለት ነው።
ፍልስጥኤማውያን ቀደም
ብሎ በግዞት
የነበሩበት አገር።
“እስከ ጋዛም ድረስ
በመንደሮች ተቀምጠው
የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።”
(ዘዳ 2:23፤ ኤር 47:4፤ አሞ 9:7)
ኵሰርሰቴም ~ Chushan-rishathaim: ‘እጥፍ ድርብ፥ ካሽ’ ማለት ነው። የመስጴጦምያ ንጉሥ፥ ከኢያሱ ዘመን አከታትሎ እስራኤላውያንን አስጨንቆ የገዛ፥
“ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ
በእስራኤል ላይ
ነደደ፥ በመስጴጦምያ
ንጉሥ በኵሰርሰቴም እጅ
አሳልፎ ሰጣቸው
የእስራኤልም ልጆች
ለኵሰርሰቴም ስምንት
ዓመት ተገዙለት።” (መሣ 3:8)
ኩሲ ~
Cushi, Hushai:
ኩሺ፣ ካሺ፣ ካሽ፣ ካሳ የሚከፍል፣ ኩሻዊ፣ ኢትዮጵያዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኵሲ፣ ኩሽ]
Cushi-
‘ካሺ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ኩሲ፥ (2 ሳሙ 15:32)
2.
ወደ ንጉሥ
ዳዊት ኢዮአብ
የላከው ልጅ፥
(2 ሳሙ 18፡21)
ኩሲ / Hushai: ካሲ፣
ካሽ፣ ከፋይ... ማለት
ነው። “ዳዊትም ለእግዚአብሔር ... አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው
መጣ።”
(2 ሳሙ 15:32)
ኩሳታዊ ~
Hushathite:
ኩሻዊ፣ የኩሽ አገር ሰው... ማለት ነው። “ከዚህም በኋላ እንደ
ገና በጎብ
ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ፥
ኩሳታዊውም ሴቦካይ
ከራፋይም ... ሳፍን
ገደለ።”
(2 ሳሙ 21:18፤ 1 ዜና 11:29፥ 20:4፥27:11)
ኩሽ ~ Cush: ኩሺ፣
ካሺ፣ ካሽ፣
ካሳ የሚክስ፣
ኩሻዊ፣ ኢትዮጵያዊ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኩሲ፣ ኵሲ]
Cush-
‘ካሽ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
ከሦስቱ የኖኅ ልጆች፣ የካም ልጅ፥ “የካምም ልጆች ኩሽ...” (ዘፍ 10:6)፣ “ኩሽም
ናምሩድን ወለደ
...” (ዘፍ 10፡8)
ኩታ ~
Cuth:
‘ቁጣ፣ ቃጠሎ’ ማለት ነው። “የባቢሎንም ሰዎች ሱኮትበኖትን ሠሩ የኩታም ሰዎች ኤርጌልን ሠሩ” (2 ነገ 17:30)
ኩን ~ Chun: ‘ክውን፣ ሁን፣
ዝግጁ’
ማለት ነው።
ከአድርአዛር ከተሞች
አንዱ፥ ንጉሥ ዳዊት ለቤተመቅደስ ማሠሪያ፥ ናስ ያስመጣበት አገር፥ “ከአድርአዛርም ከተሞች
ከጢብሐትና ከኩን ዳዊት እጅግ ብዙ
ናስ ወሰደ
ከዚህም ሰሎሞን
የናሱን ኵሬና
ዓምዶች የናሱንም
ዕቃ ሠራ።” (1 ዜና 18:8)
ኩዛ ~
Chuza:
‘ነቢይ’ ማለት ነው። የሄሮድስ ረዳት፥ “የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ... በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር።” (ሉቃ 8:3)
ኩዳን ~ Hadar: ‘ኃይል፥ ብርታት’ ማለት ነው።
1.
የእስማኤል ልጅ፥ “ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ”
(ዘፍ 25:15)
2.
ከኤዶም ነገሥታት አንዱ፥ “ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን”
(ዘፍ 36:39)
ኪልማድ ~
Chilmad:
‘አጥር፣ የተከለለ’ ማለት ነው። ከአሴር ጋር የተጠቀሰ
አገር፥ “ካራንና ካኔ
ዔድንም ነጋዴዎችሽ
ነበሩ አሦርና
ኪልማድ ነጋዴዎችሽ
ነበሩ”
(ሕዝ 27:23)
ኪልቅያ ~ Cilicia: ‘መዘወሪያ’
ማለት ነው።
በታንሿ እስያ
የደቡባዊ ምሥራቅ ክፍል፥ የምትገኝ የወደብ ግዛት፥ “የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና
ከእስክንድርያም ሰዎች
ከኪልቅያና ከእስያም
ከነበሩት አንዳንዶቹ
ተነሥተው እስጢፋኖስን
ይከራከሩት ነበር፤” (ሐዋ 6:9)
ኪሲል ~
Chesil:
‘እምነተ ቢስ፣ አምልኮት የሌለው’ ማለት ነው። በይሁዳ በስተደቡብ
የሚገኝ ከተማ፥
“ኪሲል፥ ሔርማ፥
ጺቅላግ፥ ማድማና፥
ሳንሳና”
(ኢያ 15:31)
ኪስሎን ~
Chislon:
‘አስተማማኝ፣ እርግጠኝነት’ ማለት ነው። የኤልዳድ አባት፥ የከነዓንን መሬት
በነገድ ሲከፋፈሉ
የረዳ፥ የቢንያም
ነገድ የሆነ
ፈራጅ፥ “ከብንያም ነገድ
የኪስሎን ልጅ
ኤልዳድ፥”
(ዘኊ 34:21)
ኪራም ~ Hiram: ራማ፣ ከፍተኛ፣ ክቡር... ማለት ነው።
1.
የቤት መሥሪያ ዕቃና ሠራተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም የላከ፥ የጢሮስ ንጉሥ፥ “የጢሮስም ንጉሥ
ኪራም ወደ
ዳዊት መልእክተኞችን
የዝግባ እንጨትንም
አናጢዎችንም ጠራቢዎችንም
ላከ ለዳዊትም
ቤት ሠሩለት።”
(2 ሳሙ 5:11፥ 1 ዜና 14:1)
2.
“ንጉሡም ሰሎሞን
ልኮ ኪራምን
ከጢሮስ አስመጣ”
(1 ነገ 7:13፣40)
ኪቲም
~ Kittim:
“የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥
ተርሴስ፥ ኪቲም፥
ሮድኢ ናቸው።” (ዘፍ
10:4፤ 1
ዜና 1:7)
ኪትሊሽ ~
Kithlish:
‘ቅጥር፣ አጥር’ ማለት ነው። በደልዳላው የይሁዳ ክፍል የነበረ ከተማ፥ “ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ አሥራ ስድስት ከተሞችና መደሮቻቸው።” (ኢያ 15:40)
ኪዩ ~ Chios: ኬዎስ፣
ቀውስ፣ ብጥብጥ፣
መዛባት፣ መፋለስ፣ ክፍተት... ማለት ነው። የደሴት ስም፥ ጳውሎስ በሦስተኛ ሐዋርያዊ ጉዞው ያረፈበትና ያደረበት ወደብ፥ “በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ ...” (ሐዋ
20:15)
ኪዶን ~ Chidon: ‘ቀስት’
ማለት ነው።
ታቦቱን የተሸከመውን
ሰረገላ ይጎትቱ የነበሩት በሬዎች የፋነኑበት አውድማ ባለቤት፥ “ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ
ጊዜ በሬዎቹ
ይፋንኑ ነበርና
ታቦቱን ሊይዝ
ዖዛ እጁን
ዘረጋ።”
(1 ዜና 13:9)
ካለህ ~ Calah:
ቃለህ፣ ቃልህ፣ ቃላዊ... ማለት ነው።
‘ቃለ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው። ከጥንታዊ ከተሞች አንዷ)፥ (ዘፍ 10:11)
ካሌብ ~
Caleb:
‘ከልብ’ ማለት ነው። (‘ካሌብ፣ ቃላብ፣ ቀለብ፣ ቃል አብ፣ ቃለ ሕያው፣ ቃለ እግዚአብሔር፣
የጌታ ቃል
ማለት ነው።’ ተብሎም
ይተረጎማል።)
[ተዛማጅ ስም-
ካልብ]
‘ቃል’
እና ‘አብ’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች እና አንድ ቦታ አሉ ።
1.
የዮፎኒ ልጅ፥
(ዘኁ13፡6) ፣ (ኢያ 14:6 ፣ 14) ፣ (ዘኁ 13:6 ፣32:12)
2.
የኤስሮም ልጅ፥ (1 ዜና 2:18)፣ (1 ዜና 2:50)
3.
የቦታ ስም፥ “...በይሁዳም ምድር፥ በካሌብም ደቡብ ላይ...” (1 ሳሙ 30:14)
ካልብ ~
Chelubai:
ከልብ፣ ሁሉን ቻይ፣ የማይሳነው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ካሌብ]
የኤስሮም ልጅ፥ “ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች ይረሕምኤል፥ አራም፥ ካልብ ነበሩ” (1 ዜና 2፡9፣18፡42)
ካልኔ ~
Calneh:
‘ምሽግ፣ ጠንካራ ይዞታ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ካኔ]
የናምሩድ ግዛት ወሰን፥ የቦታ ስም፥ (ዘፍ 10፡10)፣ (አሞ 6:2)
ካም ~ Ham: ‘ሞቃት፣ ትኩስ፣
ጠይም’
ማለት ነው። ከሦስቱ
የኖኅ ልጆች
ሁለተኛው፥ “ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ” (ዘፍ 5:32)
ካሲፍያ ~ Casiphia:
‘ብራማ፣ ነጭ’
ማለት ነው።
በባቢሎን እና
በኢየሩሳሌም መካከል
ያለ የቦታ
ስም፥ “... ለአምላካችን
ቤት አገልጋዮችን
ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለአዶና ...” (ዕዝ 8:17)
ካሴሉ ~ Chisleu:
‘አስተማማኝ፣ እርግጠኝነት፣
ጽናት’
ማለት ነው።
የእስራኤላውያን የወር ስም፥ “የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሀያኛው ዓመት በካሴሉ ወር እንዲህ ሆነ” (ነህ
1:1፣ ዘካ 7:1)
ካሪም ~ Harim: ‘በአምላክ የጠፋ፣ ጌታ ያወደመው’ ማለት ነው።
1.
በሦስተኛ ተርታ የተመደበ የመቅደሱ አገልጋይ፥ “ሦስተኛው ለካሪም፥”
(1 ዜና 24:8)
2.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ “የካሪም ልጆች፥
ሺህ አሥራ
ሰባት” (ዕዝ
2:39፤ ነህ 7:42)
3.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ “ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥”
(ነህ 12:15)
4.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፥ “የካሪም ልጆች፥
ሦስት መቶ
ሀያ።” (ዕዝ
2:82፤ ነህ 7:35)
ካራን ~ Charran: ‘መዘመር፣ መጣራት’ ማለት
ነው። አብርሃም
ከከለዳዊያን ወጥቶ
ወደ ከነዓን
ከመሄዱ በፊት
የኖረበት፥ “...የክብር
አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ሳይቀመጥ ገና በሁለት ወንዝ መካከል ሳለ ታየና።”
(ሐዋ 7:2፣4)
ካቡል ~ Cabul: ‘ጉብል፣ ትንሽ’ ማለት ነው።
1.
በአሴር ምሥራቃዊ ድንበር የሚገኝ የቦታ ስም፥ “... በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ
ንዒኤልም ደረሰ
በስተ ግራ
በኩልም ወደ
ካቡል ወጣ” (ኢያ
19:27)
2.
ከቡል፥ “እርሱም፦ ወንድሜ ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድር ናቸው?
አለ። እስከ
ዛሬም ድረስ
የከቡል አገር
ተብለው ተጠሩ” (1 ነገ
9:13)
ካኔ ~
Canneh:
ካነህ፣ ካነ፣ ሠራ፣ አከናወነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ካልኔ]
ስለጢሮስ የተነገረ፥ “ካራንና ካኔ ዔድንም ነጋዴዎችሽ ነበሩ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ
ነበሩ”
(ሕዝ 27፡23)
ኬሌዎን ~ Chilion:
‘መጨረሻ፣ ፍጻሜ’
ማለት ነው።
የአቤሜሌክ እና
የኑኃሚን የመጨረሻ
ልጅ፥ የሩት
ባል የነበረ፥
“የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥
የሚስቱም ስም
ኑኃሚን፥ የሁለቱም
ልጆች ስም
መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ...” (ሩት 1:2፣ 4:9)
ኬሌግ ~
Helek:
‘ልክ፣ መጠን’ ማለት ነው። ከምናሴ ወገን፥ የገለዓድ ልጆች፥ “የገለዓድ ልጆች
እነዚህ ናቸው
ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን
ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን”
(ዘኊ 26:30)
ኬሌግ ~ Hoglah: ‘ጅግራ’ ማለት ነው። የገለዓድ ወገን፥
“የገለዓድ ልጆች እነዚህ
ናቸው፤ ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን” (ዘኊ 26:33፥
27:1፥ 36:11)
ኬልቅያ ~ Chelluh:
‘ሁሉ፣ ሙሉ’ ማለት ነው። “ኡኤል፥ በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ” (ዕዝ 10:35)
ኬሎን ~ Helon: ኃይልነ፣
ብርታታችን... ማለት ነው።
ከዛብሎን ነገድ፥
የኤልያብ አባት፥
“ከዛብሎን የኬሎን ልጅ
ኤልያብ፥ ከዮሴፍ
ልጆች ከኤፍሬም
የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፥ ከምናሴ የፍዳሱ ልጅ ገማልኤል፥” (ዘኊ 1:9፥ 2:7፥
7:24፣29፥10:16)
ኬብሮን ~
Hebron:
ሄብሮን፣ ኅብርነ፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ፣ ማኅበርተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔብሮን፣ ዔቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር]
[ኅብረት ማለት
ነው / መቅቃ]
በዚህ ስም
የሚታወቁ አንድ
ሰውና ሁለት
ቦታዎች አሉ።
1.
አብራም ከሎጥ ተለይቶ የሰፈረበት፥ የቦታ ስም፥ “አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ ...” (ዘፍ 13፡18)
2.
የአሴር ልጆች ነገድ ድንበር፥ “ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ...” (ኢያ
19:28)
3.
የቀዓት ልጅ፥ “የቀዓትም ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ...” (ዘጸ 6:18) ፣ (1
ዜና 6:2፣ 18) ፣ (1
ዜና 23:12)
ኬጢ ~ Heth: ‘ቀጢ፣ መንቀጥቀት፣
መውረግረግ…’ ማለት ነው።
የከንዓን ልጅ፥
የኬጢያውያን አባት፥ “ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥” (ዘፍ
10:15)
ኬጢያውያን ~
Hittites:
ሄታይት፣ የኬጢ ወገኖች፣ የኬጢ አገር ሰዎች ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም-
ቄኔዛዊው]
የከነዓን ልጅ፥
“ቀድሞናውያንንም ኬጢያውያንንም”
(ዘፍ 15:19)
ኬፋ ~ Cephas: ‘ዓለት፣ ድንጋይ፣
ጭንጫ’
ማለት ነው።
ጌታ ስምዖንን
የጠራበት ስም፥ “ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ። አንተ የዮና ልጅ ስምዖን
ነህ፤ አንተ
ኬፋ ትባላለህ
አለው፤ ትርጓሜው
ጴጥሮስ ማለት
ነው።”
(ዮሐ 1:42)
ክሉብ ~ Chelub: ‘ቅርጫት’
ማለት ነው።
ከዳዊት ሹሞች፥
የዔዝሪ አባት፥
“መሬቱን የሚያበጃጁትና እርሻውን በሚያርሱት ላይ የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ”
(1 ዜና 27:26)
ክላል ~
Chelal:
‘ፍጹም፣ እንከን አልባ’ ማለት ነው። በምርኮ አገር ሲኖሩ፥ እንግዳ ሚስቶችን
ካገቡት አንዱ፥
“ከፈሐት ሞዓብ ልጆችም፤
ዓድና፥ ክላል፥
በናያስ፥ መዕሤያ፥
ሙታንያ፥ ባስልኤል፥
ቢንዊ፥ ምናሴ።” (ዕዝ 10:30)
ክራን ~ Cheran: ‘ቁጣ’
ማለት ነው።
ከዲሶን ልጆች
አንዱ፥ “ዲሶን፥ አህሊባማም የዓና ሴት ልጅ። የዲሶንም ልጆች እነዚህ ናቸው ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥
ክራን”
(ዘፍ 36:26; 1 ዜና 1:41)
ክርስቶስ ~ Christ: ‘የተሾመ፣ የተሰየመ፣
የተቀባ ንጉሥ፣
መንግሥት የመሠረተ’
ማለት ነው።
“ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ
እንዲቀበልና ከሙታን
እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፤ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበር።” (ሐዋ 17:3፥ 18:5፤ ማቴ 22:42)
ክናንያ ~
Chenaiah:
ከነነ ያሕ፣ የሕያው ክንውን፣ የአምላክ ሥራ፣ የሕያው ሥራ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ክንዓና፣ ኮናንያ]
‘ከነነ’ እና ‘ያሕ’
(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሌዊያውን አላቃ፣ ዜማ ያስተምራቸው የነበር፥ (1 ዜና 15፡22)
ክንዓና ~
Chenaanah:
ከነዓና፣ ከናን፣ ቀኛኝ፣ አቅኝ፣ ሻጭ፣ ነጋዴ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስሞች- ክናንያ፣ ኮናንያ]
‘ቀና’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ሲሆን ትርጉሙ ሻጭና ገዥ ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የቢልሐን ልጅ፥
(1 ዜና 7፡10)
2.
የሴዴቅያስ አባት፥
(1 ነገ 22:11፣ 24)
ክንክራኦስ ~ Cenchrea: ‘ዘንጋዳ’ ማለት ነው። ጳውሎስ ራሱን የተላጨበት የወደብ ከተማ፥ “...ስለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራኦስ ተላጨ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ” (ሐዋ 18:18)
ኮልሖዜ ~ Colhozeh: ‘ቃለ ያዚ፣ ሁሉን የሚያይ’ ማለት
ነው። በነህምያ
ዘመን የነበረ፥
የይሁዳ ሰው፥
“የምጽጳም ግዛት አለቃ
የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን
በር አደሰ
ሠራው፥ ከደነውም፥
ሳንቃዎቹንም አቆመ፥
...” (ነህ 3:15፥ 11:5)
ኮሎዶጎምር ~ Chedorlaomer: ‘ነዶ’
ማለት ነው።
በአብርሃም ዘመን የነበረ
የኤላም ንጉሥ፥
“ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር
የነበሩትን ነገሥታት
ወግቶ ከተመለሰ በኋላም የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ”
(ዘፍ 14:17)
ኮራት ~ Cherith: ቆራጥ፣
መቁረጥ፣ መብሳት፣
ማረድ...
ማለት ነው።
በሦስቱ ዓመት የድርቅ ወቅት፥ ነቢዩ ኤልያስ የተሸሸገበት ገደል፥ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፥ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ።” (1 ነገ 17:3፣5)
ኮራዚ ~ Chorazin: ‘ምሥጢር’
ማለት ነው።
“ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ
ቤተ ሳይዳ፤
በእናንተ የተደረገው
ተአምራት በጢሮስና
በሲዶና ...” (ማቴ 11:21)
ኮሬብ ~
Horeb:
ሖረ አብ፣ ያባቶች ጉዞ... ማለት ነው። ‘ምድረ በዳ ማለትነው ነው፥’ ተብሎም
ይተረጎማል። የእስራኤላውያን አባቶች፥ በምድረ ባዳ
በዞሩበት ወቅት ከተጓዙባቸው ቦታዎች አንዱ፥ “ሙሴም የዮቶርን የአማቱን የምድያምን ካህን በጎች
ይጠብቅ ነበር
ወደ ምድረ
በዳ ዳርቻም
በጎቹን ነዳ፥
ወደ እግዚአብሔርም
ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ” (ዘጸ 3:1፥ 17:6፥ 33:6፤ መዝ 106:19)
ኮቦር ~ Chebar: ክብር፣
ብርታት፣ ጥንካሬ... ማለት
ነው። በከላዳውያን
ምድር ያለ ወንዝ፥ “ከወሩም በአምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን አገር
በኮቦር ወንዝ
ወደ ቡዝ
ልጅ ወደ
ካህኑ ...” (ሕዝ 1:3፥ 3:15፣23)
ኮታም ~ Hotham: ‘እትም፣ አርማ፣ የቀለበት ማኅተም’
ማለት ነው።
የአሴር ወገን፥
የሔበር ልጅ፥
የበረያ ቤተሰብ፥
“ሔቤርም ያፍሌጥን፥ ሳሜንር፥
ኮታምን፥ እኅታቸውንም
ሶላን ወለደ።” (1 ዜና 7:32)
ኮናንያ ~
Conaniah:
ከነነ ያሕ፣ የሕያው ክንውን፣ የአምላክ ሥራ፣ የሕያው ሥራ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ክናንያ፣ ክንዓና]
‘ከነነ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በንጉሡ ሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ፥ “የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ...” (2 ዜና 35፡9)
ኮዛት ~
Chesed:
‘መስፋፋት፣ መጨመር’ ማለት ነው። የናኮር አራተኛ ልጅ፥ “ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላፍ፥ ባቱኤል ናቸው” (ዘፍ 22:22)
ኮዜባ ~
Chozeba:
‘ደፈጣ’
ማለት ነው። በይሁዳ የታችኛው ግዛት ያለ ቦታ፥ “ዮቂም፥ የኮዜባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ ሞዓብን የገዛ ሣራፍ፥ ያሹቢሌሔም ነበሩ”
(1 ዜና 4:22)
No comments:
Post a Comment