ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሀሩፋዊ ~
Haruphite:
‘ሰልካካ፣ ቀጭን፣ ሸንቃጣ’ ማለት ነው። በጺቅላግ ዳዊትን ከተቀላቀሉ
ወታደሮች አንዱ፥
“ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥
ኢያሪሙት፥ በዓልያ፥
ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥” (1 ዜና 12:5)
ሀደሳ ~
Hadassah:
አደስ፣ አደሴ፣ አደሷ... ማለት ነው። [አደስ- ለቅባት ማዘጋጃ የሚሆን ጥሩ ሽታ ያለው ተክል ነው።]
ከመጽሐፈ አስቴር፣ የአስቴር ሌላ ስም፥ (አስ 2:7)
ሀዶራም፣ አዶራም ~ Hadoram: የአደራ፣ የተከበረ... ማለት ነው። ሀዶራም: የዮቅጣን
ሦስተኛ ልጅ፥
“ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥” (ዘፍ
10:27፥ 1
ዜና 1:21)
አዶራም:
1. የንጉሥ
ቶዑ ልጅ፥
“ቶዑም ከአድርአዛር ጋር
ሁል ጊዜ
ይዋጋ ነበርና
ዳዊት አድርአዛርን
ወግቶ ስለመታው
ደኅንነቱን ይጠይቅ
ዘንድ ይመርቀውም
ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው ...” (1 ዜና 18:10)
2.
የእስራኤል ንጉሥ፣
የሮብዓም አስገባሪ
የነበረ፥ “ንጉሡም ሮብዓም
አስገባሪውን አዶራምን
ሰደደ የእስራኤልም ...” (2 ዜና 10:18)
ሁለት ወንዞች ~ Padan-aram: ‘ለም መሬት’ ማለት ነው። “ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።” (ዘፍ 25:20፥ 28:2፣ 5-7፥ 31:18)
ሁል ~
Hul:
‘ክብ’
ማለት ነው። የአራም ሁለተኛ ልጅ፥ የሴም የልጅ ልጅ፥
“የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።” (ዘፍ 10:23)
ሂሌል ~
Hillel:
ህልል፣ እልልታ፣ ተደጋጋሚ ጥሪ፣ ጩኽት፣ መዝሙር፥ አምላክን ማመስገን፣ ደስታን መግለጽ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሀሌ ሉያ፣
ማዕሌት፣ ማህለህ፣ ይሃሌልኤል]
‘ሃለለ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
በእስራኤል ላይ
ፈራጅ የነበረው
የዓብዶ አባት፣
ሂሌል ፥
(መሣ 12፡13፣15)
ሂዳይ ~ Hiddai: ‘ደስታዬ’
ማለት ነው።
ከሠላሳ ሰባቱ
የዳዊት የክብር ዘበኞች አንዱ፥ “ሂዳይ፥ ዓረባዊው አቢዓልቦን፥ በርሑማዊው” (2 ሳሙ 23:31)
ሃሌሉያ ~ Alleluia, Praise ye the LORD:
ሃሌ ለ ያሕ፣ ለሕያው ጌታ ዘመረ፣ የአምላክን ስም ጠራ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ሂሌል፣ ማህለህ፣ ማህለት፣ ይሃሌልኤል]
‘ሃሌ’ እና ‘ለ’ያሕ’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።
‘ሃሌ’- ሃሎ፣ እልል ማለት፣ መጮህ፣ መጣራት፣ ማመስገን፣ መዘመር፣ መዝፈን ማለት ነው።
‘ያ’-
ያሕ፣ ያሕዊ፣
ሕያው፣ ዘላለማዊ
አምላክ፣ እግዚአብሔር
ማለት ነው።
[ሃሌታና እልልታ በምሥጢር አንድ ነው፥ ሰብሑ፡ እግዚእ ፤ ሰብሑ፤ ያሕ እግዚእ አምላክ
/ ኪወክ / አ]
[በዕብራይስጥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ” ማለት
ነው። /
የመቅቃ]
ሃሌ ሉያ / Alleluia: ነቢዩ ዮሐንስ በራእይ ያየውን ሲናገር የተጠቀመው ቃል፥ (ራእ 19፡1፣3፣ 4፣ 6)
ሃሌሉያ / Praise
ye the LORD:
ንጉሥ ዳዊት በመዝሙር ያመሰገነበት ቃል፥ ሃሌሉያ፥ (መዝ 116:19)
ሃሜአ ~
Meah: ማያ፣ መመልከቻ፣ መጠበቂያ... ማለት ነው። [‘መቶ ማለት ነው።’ ተብሎም ይተረጎማል] በነህምያ ዘመን፥ የኢየሩሳሌም
ቅጥር እንደገና
ሲገነባ፥ ለአንደኛው
ማማ የተሰጠ
ስም፥ “… ሳንቃዎቹንም
አቆሙ እስከ
ሃሜአ ግንብና
እስከ ሐናንኤል
ግንብ ድረስ
ቀደሱት”
(ነህ 3:1፥ 12:39)
ሃሩም ~ Harum: ራማ፣ከፍተኛ... ማለት
ነው። የይሁዳ
ወገን፥ “ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።” (1 ዜና 4:8)
ሃራ ~ Hara: ተራራማ
መሬት፣ ከፍተኛ ቦታ... ማለት
ነው። [ነጻ፣ ሐርነት
የወጣ፣ ጭዋ
ማለት ነው።
/ አ /
ኪወክ]
፥ “... የሮቤልንና የጋድን
ልጆች የምናሴንም
ነገድ እኵሌታ
አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።” (1 ዜና 5:26)
ሃቃጣን ~ Hakkatan: ሕጻን፣ ወጣት፣ ታዳጊ... ማለት ነው። ከባቢሎን
ከምርኮ ከተመለሱ
የሃቃጣን ልጅ
ይገኝበታል፥ “ከዓዝጋድ ልጆች
የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን፥ ከእርሱም ጋር መቶ አሥር ወንዶች።” (ዕዝ 8:12)
ሃዳድ ~ Hadad: የተወደደ ማለት ነው።
1.
የባዳድ ልጅ፥
“ሑሳምም ሞተ፥ በስፍራውም
የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የመታ
የባዳድ ልጅ
ሃዳድ ነገሠ
የከተማውም ስም
ዓዊት ተባለ።” (ዘፍ
36:35፤ 1 ዜና1:46)
2.
የኤዶማውያን ንጉሥ፥
“በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም
ፋንታ ሃዳድ ነገሠ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች
ሃዳድም ሞተ።” (1 ዜና 1:50፣51)
3.
“እግዚአብሔርም ከኤዶምያስ
ነገሥታት ዘር የኤዶምያስን ሰው ሃዳድን ጠላት አድርጎ
በሰሎሞን ላይ
አስነሣው።”
(1 ነገ 11:14-22)
4.
“ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥” (1 ዜና 1:30)
ሃጽሌልፎኒ ~ Hazelelponi: ‘ጥላዬ፣ ጠለላዬ፣ ከለላዬ፣ መጽናኛዬ’ ማለት ነው። በይሁዳ የዘር ሐረግ፥ የኤጣም ልጅ፥ “እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ”
(1 ዜና 4:3)
ሄማን፣ ኤማን ~ Heman: ሃማን፣ አማን፣ ያመነ፣ የታመነ፣ ሰላም ያገኘ፣ እርቅ የፈጠረ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች: - ሐማ፣ አሒማን፣ አማና፣ አሜን፣ አሞን፣ አኪመን፣ ያሚን]
‘አመነ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
ሄማን: በጥበበኛነቱ የሚታወቀው፥
የኢይዝራኤላዊው የኤታን
ልጅ፥ “...ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።” (1 ነገ 4:31፤ 1 ዜና 2:6)
ኤማን: የሳኦል የልጅ ልጅ፥ ኤማን፥ “አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ እርሱም የኢዮኤል ልጅ...” (1 ዜና 6:33፥ 15:17)
ሄርማን ~ Hermas: ‘ሜርኩሪ’
ማለት ነው።
በሮሜ የነበረ
ክርስቲያን፥ ቅዱስ
ጳውሎስ በመልእክቱ ሰላምታ
ያቀረበለት፥ (ሮሜ 16:14) “ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ለጳጥሮባም ለሄርማንም ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ።”
ሄርሜን ~ Mercurius:
መርቆሪዎስ፣ ምሩቀ
ዋስ፣ ጥበብን
ነጋሪ፣ የምሥራችን አብሳሪ ማለት ነው። [ሜርኩሪ በጥንት ሮማውያን ዘንድ የንግድ አምላክ ተብሎ
የሚታመን ሲሆን፤
በሰው እና
በአምላክ መካከልም
መልእከተኛ ሆኖ
ያገለግል ነበር።] “በርናባስንም
ድያ አሉት፤
ጳውሎስንም እርሱ
በመናገር ዋና
ስለ ነበረ
ሄርሜን አሉት።” (ሐዋ 14:12)
[ስመ ጣዖት፥ በመንታ መንገድ ላይ የሚያቆሙት። መሪ፣ አስተማሪ፣ ትርጁማን፣ አፈ በሃማን ማለት ነው። /
ኪወክ/ አ]
ሄርዋጌኔስ ~ Hermogenes: ‘ከሜርኩሪ የተወለደ’ ማለት
ነው። በሐዋርያው
ጳውሎስ የእስያ
ጉዞ ደቀመዝሙር
የነበረ፥ በኋላ
ግን ተለይቶ
ሄዷል፥ ወደ
ጢሞቴዎስ በላከው
ሁለተኛ መልእክት
ጠቅሶታል፥ “በእስያ ያሉቱ
ሁሉ ከእኔ
ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፥ ከእነርሱም ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ናቸው።” (2 ጢሞ 1:15)
ሄሮድስ ~ Herod: ‘ጀብደኛ’
ማለት ነው።
ሮማዊ ንጉሥ፥
ጌታ በተወለደበት
ዘመን ፍልስጥኤምን
ይገዛ የነበረ፥
“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ
ልሔም በንጉሡ
በሄሮድስ ዘመን
በተወለደ ጊዜ፥
እነሆ፥ ሰብአ
ሰገል...” (ማቴ 2:1)
ሄሮድዮና ~ Herodion: ‘የጀግና ዝማሬ’ ማለት
ነው። [ሄሮድዮና ~
በጥንት ዘመን የመንግሥት ጠባቂና አማካሪ አምላክ፥ ተብላ የምትታመን፥] በሮሜ
የነበረች ክርስቲያን፥
ቅዱስ ጳውሎስ
በላከው የሰላምታ
ደብዳቤ የተጠቀሰች፥ “ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሰላምታ
አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ
ቤተ ሰዎች
በጌታ ላሉት
ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16:11)
ሄና ~ Hena: ‘በጥባጭ’ ማለት
ነው። የሶሪያ
ከተማ የነበረ፥
“የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?” (2 ነገ
19:13፤ ኢሳ 37:13)
ሄኖሕ ~
Enoch:
እጩ፣ የተመረጠ፣ ቅዱስ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሄኖኅ ፣ ሄኖክ]
[ሐዲስ ቅዱስ
ማለት ነው።
/ ኪወክ /
አ] በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -
1.
የቃየል ልጅ ሁኖ፣ የጋይዳድ አባት፥ ሄኖሕ፥ (ዘፍ 4:17)
2.
አብርሃም ከኬጡራ የወለደው የምድያም ልጅ ሄኖኅ፥ (ዘፍ 25:4)
3.
የያዕቆብ በኵር፣ የሮቤል ልጅ፥ ሄኖኅ፥ (ዘፍ 46:9)
ሄኖኅ ~
Hanoch:
‘ጽኑ ብርቱ’ማለት ነው።
1.
የምድያም ሦስተኛ ልጅ፥ “የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።”(ዘፍ 25:4)
2.
የሮቤል ልጅ፥
“የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ፥
ፈሉሶ፥ አስሮን፥
ከርሚ።” (ዘፍ
46:9፤ ዘጸ 6:14፤ ዘኊ 26:5፤ 1 ዜና 5:3)
ሄኖም ~ Hinnom: ‘ሐዘን’
ማለት ነው።
“ድንበሩም በሄኖም ልጅ
ሸለቆ አጠገብ
ኢየሩሳሌም ወደምትባለው
ወደ ኢያቡሳዊው
ወደ ደቡብ
...” (ኢያ 15:8)
ሄኖስ ~ Enos: ‘ሥጋዊ፥ ምድራዊ
ሰው፣ ሟች’
ማለት ነው።
የአዳም ሦስተኛ
ልጅ፥ የሴት
ልጅ፥ “ሴትም ሁለት
መቶ አምስት
ዓመት ኖረ፥
ሄኖስንም ወለደ።”
(ዘፍ 5:6-
11፤ ሉቃ 3:38)
ሄኖን ~ AEnon: ዓይኑን፣ አይኖቹ... ማለት
ነው። በሳሌም
አቅራቢያ፥ ዮሐንስ
ያጠምቅበት የነበረ ቦታ፥ “ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ
ነበርና ያጠምቅ
ነበር፥”
(የሐዋ 3:22)
ሄኖክ ~
Enoch:
... [ሄኖሕ-
ከሚለው ጋር አንድ አይነት ትርጉም አለው። የማቱሳላ አባት ሁኖ፣ የያሬድ ልጅ፥ ሄኖክ፥ (ዘፍ 5:18)
ሄኖክ፣ ሄኖኅ ~ Henoch: ‘ቅዱስ’ ማለት ነው።
1.
የያሬድ ልጅ ሁኖ፥ የማቱሳላ አባት፥ “ያሬድ፥ ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥” (1 ዜና 1:3)
2.
አብርሃም ከኬጡራ የወለደው የምድያም ልጅ፥ ሄኖኅ ~ የምድያምም
ልጆች ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ...” (1 ዜና 1:33)
ሄጌ ~
Hegai, Hege: ሃጌ፣ ሐጊ፣ ህጋዊ፣ ሕግ አክባሪ፣ ሕግን የጠበቀ ማለት ነው።
‘ሐገ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
ሄጌ / Hegai: የንጉሡ የአርጤክስስ ጃንደረባ፥ ሄጌ፥ (አስ 2፡8)
ሄጌ / Hege:
(አስ 2፡3)
ህንደኬ ~ Candace: ‘እመቤት፣ የአገልጋዮች
ንግሥት’
ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ንግሥት፥
“ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥
ህንደኬ የተባለች
የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ ... ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤” (ሐዋ 8:27)
ህንድ ~
India:
‘እንዲያ፣ ምስጋና’ ማለት ነው። ህንድ አገር፥ (አስ 1:1 እና
8:9) “በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ
ሆነ ይህም
አርጤክስስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባት አገሮች ላይ ነገሠ።”
ሆሃም ~ Hoham:
‘አምላክ ያበጀው’
ማለት ነው።
ከነዓን በእስራኤላውያን እጅ በወደቀችበት ዘመን
የነበረ የኬብሮን ንጉሥ፥
“ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ
አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥ ...” (ኢያ 10:3)
ሆሣዕና ~ Hosanna: ዋሴ
ና፣ አዳኜ
ና፣ ጠባቂዬ
ድረስ... ማለት ነው።
‘ዋስ’ እና ‘ና’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።
ጌታ ወደ
ኢየሩሳሌም በገባ
ጊዜ ሕጻናት ካዜሙት
ቃል፥ ሆሣዕና ፥ “...ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” (ማቴ 21፡9)
[አድነና፥ አድነንኮ፡ እባክኽ አድነን...
መድኀኒትነት፤ መሆን ወይም መባል። / ኪወክ /
አ]
ሆሴዕ ~ Hosea: ዋሴ፣
አዳኜ፣ መዳኒቴ... ማለት ነው።
ከደቂቀ ነቢያት
አንዱ፥ የበሪ
ልጅ።“...በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ
ልጅ በኢዮርብዓም
ዘመን ወደ
ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።” (ሆሴ 1:1፣2) ፥ [አድኀነ፥ ባልሐ፥ ረድአ፥ አውፅኣ፥ እመሥገርት ማለት ነው። / ኪወክ /
አ]
ሆራም ~
Horam:
‘ራማ፣ ከፍተኛ፣ ተራራማ’ ማለት ነው። የደቡባዊ ምዕራብ ፍልስጥኤም፥ በእስራኤል በተያዘበት ወቅት የነበረ፥ የጌራራ ንጉሥ፥ “በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ ...”
(ኢያ10:33)
ሆር፣ ሖር፣ ሑር ~ Hur: ‘ዘዋሪ፣ መሿለኪያ፣ ጠባብ መስኮት የመሰለ’ ማለት ነው።
1. የካሌብ ልጅ፥ “ዓዙባም ሞተች፥
ካሌብም ኤፍራታን አገባ እርስዋም ሆርን ወለደችለት።” (1 ዜና 2:19፣ 50፥ 4:1፣4፤ 2 ዜና 1:5)
2. የሙሴ እኅት ፣
የማርያም ባል፥
ሖር፥ “... ሙሴና
አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ
ወጡ።”
(ዘጸ 17:10-12)
3. ከምድያም ነገሥታት አንዱ፥ ሑር፥ “...የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥
ሑር፥ ሪባ
ነበሩ የቢዖርንም
ልጅ በለዓምን
ደግሞ በሰይፍ
ገደሉት።”
(ዘኊ 31:8)
ሆሻማ ~
Hoshama:
ሆሴ ሰማ፣ ዋሴ ሰማ፣ አዳኜ ሰማ፣ አምላኬ አዳመጠኝ... ማለት ነው።
‘ዋስ’ እና ‘ሰማ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
የምርኮኛው የኢኮንያ ልጅ፥ ሆሻማ፥ “ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።” (1 ዜና 3፡18)
ሆሻያ ~
Hoshaiah:
ዋሰ ያሕ፣ ሕያው ዋስ፣ አምላክ ያዳነው... ማለት ነው።
1. የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመጠገን በተደረገው ሂደት ተባባሪ የነበረ፥ “ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኵሌታ፥”
(ነህ 12:32)
2. “የጭፍራ አለቆችም ሁሉ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ ሕዝብም ሁሉ
ከታናሹ ጀምሮ
እስከ ታላቁ
ድረስ ቀረቡ፥” (ኤር
42:1፥ 43:2)
ሆቲር ~ Hothir:
‘በላጭ፣ የሚበልጥ...’
ማለት ነው።
የኤማን ሦስተኛ
ልጅ፥ “ከኤማን የኤማን
ልጆች ቡቅያ፥
መታንያ፥ ... ሐናኒ፥
ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥
ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥
መሎቲ፥ ሆቲር፥
መሐዝዮት”
(1 ዜና 25:4፣28)
ሆዲያ ~
Hodijah:
ሆደ ያሕ፣ ውደ ሕያው፣ ጌታ የወደደው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ሆዳይዋ፣ ሆድ]
‘ውድ’ እና ‘ሕያው’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -
1. ከዕዝራ ጋር ሕዝቡን ሕግ ያስተምሩ ከነበሩ ሌዋውያን አንዱ፥ ሆዲያ፥ (ነህ 8፡7)
2. ሌዋዊ፥ ሆዲያ፥ (ነህ 10:13)
3. በነህምያ ዘመን የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት አንዱ፥ ሆዲያ ፥ (ነህ 10:18)
ሆዳይዋ ~ Hodaiah, Hodaviah: ሆደ ያሕ፣ ውደ ሕያው፣ ጌታ የወደደው፣ የእግዚአብሔር ወዳጅ... ማለት ነው። (‘ምስጉን’ ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስሞች- ሆዲያ፣ ሆድ]
‘ውድ’ እና ‘ያሕ’
(ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ሆዳይዋ / Hodaiah: የኤልዮዔናይ ልጅ፥ ሆዳይዋ፥ (1 ዜና 3፡24)
ሆዳይዋ / Hodaviah:
1. ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች አንዱ፥ ሆዳይዋ፥ (1 ዜና 5፡24)
2. የብንያም ወገን የሐሰኑ ልጅ ፥ ሆዳይዋ፥ (1 ዜና 9:7)
3. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ፣ የሌዊ ወገን የሆነ፥ ሆዳይዋ፥ (ዕዝ 2:40)
ሆድ ~ Hod: ውድ፣
የተወደደ፣ የተመሰገነ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሆዲያ፣ ሆዳይዋ]
‘ውድ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው። ከአሴር ነገድ የሆነ፣ የጾፋ ልጅ፥ ሆድ፥ “ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ፥
ይትራን፥ ብኤራ
ነበሩ”
(1 ዜና 7፡37)
[ዕብ፥ ጸዳል፣ ውበት፣ ምስጋና። በቁሙ ከርሥ። (አማርኛ) /
ኪወክ /
አ]
No comments:
Post a Comment