ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ቀሄላታ ~
Kehelathah:
ቃህላት፣ ጉባኤ ማለት ነው።
የእስራኤል ልጆች
ጕዞ ከሙሴና
ከአሮን እጅ
በታች በጭፍሮቻቸው
ከግብፅ በወጡ
ጊዜ ካለፉባቸው ቦታዎች፥ “ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ።” (ዘኁ 33:22፣ 23)
ቀለዮጳ ~ Cleophas: ‘ሙሉ ደስታ’ ማለት
ነው። የሌላዋ
ማርያም ባል፥
“...
ነገር ግን
በኢየሱስ መስቀል
አጠገብ እናቱ፥
የእናቱም እኅት፥
የቀለዮጳም ሚስት
ማርያም፥ መግደላዊትም
ማርያም ቆመው
ነበር”
(ዮሐ 19:25)
ቀሌምንጦስ ~ Clement: ‘መሓሪ፣ የማይጎዳ፣ ይቅር ባይ’ ማለት ነው። ጳውሎስን በጉልበቱ ያገለግል የነበረ ሰው፥ “... ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከቀሌምንጦስና ደግሞ ከእኔ ጋር አብረው ከሠሩት ከሌሎቹ ጋር በወንጌል ከእኔ ጋር አብረው ተጋድለዋልና።”
(ፊል4:3) ይህ ቀሌምንጦስ በኋላ ‘የሮም ጳጳስ የሆነው ነው።’
ተብሎ በጥንታዊ ቤተ ክርስቲያናት ታሪክ ይታመናል።
ቀሎዔ ~ Chloe: ‘አረንጓዴ ቅመም’ ማለት ነው። በጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፥ የተጠቀሰች ሴት፥ “ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና” (1 ቆሮ 1:11)
ቀሙኤል ~ Kemuel: ቆመ ኤል፣ ቆመ አምላክ፣ በአምላክ የቆመ፣ በእምነት የጸና... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
‘ቆመ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የአብርሃም ወንድም፣ የናኮር ልጅ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ (ዘፍ 22:21)
2. እግዚአብሔር በከነዓን ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን ይከፍሉ ዘንድ
ካዘዛቸው፥ ቀሙኤል፥ (ዘኁ 34:24)
3. የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ
አለቆች ከየክፍሎች፥ አንዱ ቀሙኤል፥ (1 ዜና 27:17)
ቀራንዮ ~
Calvary:
ቀርን፣ ቀንድ፣ የራስ ቅል ማለት ነው። ጌታን የሰቀሉበት ቦታ፥ “ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።” (ሉቃ 23:33)
ቀሬና ~ Cyrene: ቁር፣ ብርድ፣ ቀዝቃዛ... ማለት ነው። የአፍሪቃ
ክፍል የሆነ አገር፥
የጌታን መስቀል የተሸከመው
ስምዖን የዚህ አገር
ሰው ነው፥ “ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ...” (ማቴ 27:32)
ቀርሜሎስ ~ Carmel:
ቃርሚያ፣ የእርሻ ቦታ... ማለት ነው።
1.
ፍልስጥኤምን በውጫዊ ገጽታው
የሚያሳይ ተራራ፥ “ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፥ ከዚያም
ወደ ሰማርያ ተመለሰ።” (2 ነገ 2:25፥4:25)
2.
በይሁዳ ተራራማ ክፍል
የሚገኝ ከተማ፥ “ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ ኢይዝራኤል፥” (ኢያ 15:55)
ቀርስጶስ ~ Crispus: ‘ዞማ፣ ጠመዝማዛ’ ማለት ነው።
በቆሮንቶስ የአይሁድ ምኩራብ
አለቃ የነበረ፥ “የምኵራብ
አለቃ ቀርስጶስም ከቤተ ሰዎቹ
ሁሉ ጋር በጌታ
አመነ፥ ከቆሮንቶስ ሰዎችም
ብዙ በሰሙ ጊዜ
አምነው ተጠመቁ” (ሐዋ 18:8)
ቀርቀር ~ Karkor: ‘መሠረት’ ማለት ነው።
ዛብሄልና ስልማና በጌዲዎን የተወገዱበት ቦታ፥ “ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ...” (መሣ 8:10)
ቀርቃ ~
Karkaa:
‘መሠረት’ ማለት ነው። የይሁዳ ነገድ፥ የደቡባዊ ዳርቻ፥ ጉልህ ቦታ፥ “ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ ... ድንበራቸው ይህ ነው።” (ኢያ 15:4)
ቀርታ ~
Kartah:
‘ካርታ፣ ቅጥር፣ ስፍር፣ መንደር’
ማለት ነው። የሜራሪ ርስት
የሆነ ከተማ፥ “ቀርታንና መሰምርያዋን፥ ዲሞናንና መሰምርያዋን፥ ነህላልንና
መሰምርያዋን አራቱን ከተሞች
ሰጡ።”
(ኢያ 21:35)
ቀርጤስ ~ Crete: ‘ሥጋዊ’ ማለት ነው።
የደሴት ስም፥ “የቀርጤስናየዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ... እንሰማቸዋለን።”
(ሐዋ 2:11)
ቀብስኤል ~ Kabzeel: እቅብ ዘ
ኤል፣ ለአምላክ የተጠበቀ፣
ለጌታ የተቀመጠ፣ ለእግዚአብሔር የተለየ...
ማለት ነው። [ተዛማጅ
ስም-
ቀብጽኤል]
Kabzeel- ‘እቅበ’፣’ዘ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ የቦታ ስም
ነው። በደቡብ በኩል
በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ
እስከ ኤዶምያስ ድንበር
ያሉት ከይሁዳ ልጆች
ነገድ ከተሞች፥ (ኢያ 15:21)
ቀብጽኤል ~ Kabzeel: እቅብ ዘ ኤል፣ ለአምላክ የተጠበቀ፣ ለጌታ የተቀመጠ፣ ለእግዚአብሔር የተለየ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ቀብስኤል] Kabzeel- ‘ቅበ’፣’ዘ’
እና ‘ኤል’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ የሰው እና የቦታ ስም ነው።
የሰው ስም፥ “በቀብጽኤል የነበረው ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊውን የቀብስኤልን ሁለት ልጆች ገደለ ...” (2 ሳሙ 23:20፣ 1 ዜና 11:22)
ቀነናዊ ~
Canaanite:
ቀነናውያን፣ የከነዓን ሰዎች ማለት ነው።
የከነዓን ወገኖች፣ ስምዖን ቀነናዊ ተብሎ ተጠርቷል፥ “ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም
አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ
ይሁዳ።”
(ማቴ 10:4)
ቀኒዶስ ~ Cnidus: ‘ቀን፣ ዘመን፣ ጊዜ፣ ዕድሜ’ ማለት ነው።
በታናሽቱ ኢስያ የሚገኝ
የወደብ ከተማ። ሐዋርያው
ጳውሎስ ወደ ሮሜ
ባደረገው ጉዞ በዚያ
አልፏል። “ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄደን በጭንቅ ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ነፋስም
ስለ ከለከለን በቀርጤስ ተተግነን በሰልሙና አንጻር ሄድን፤” (ሐዋ 27:7)
ቀናተኛ ~ Zelotes: ‘ቅን’ ማለት ነው። ከስምዖን
ጴጥሮስ ለመለየት፥ የሌላው ስምዖን መጠሪያ፥ “ማቴዎስም
ቶማስም፥ የእልፍዮስ ልጅ
ያዕቆብም ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥”(ሉቃ 6:15)
ቀዓት ~
Kohath:
‘ጉባኤ፣ ማኅበር’ ማለት ነው። “የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።” (ዘፍ 46:11)
ቀያፋ ~ Caiaphas: ‘ጸያፍ፣ ጥንቁቅ’ ማለት ነው።
ኢየሱስን በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉት ከተማከሩ፥ ሊቀ ካህኑ፥ “በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥”
(ማቴ 26:3፣57፤ ዮሐ 11:49፥ 18:13፣14፣24፣28፤ ሐዋ 4:6)
ቀድምኤል ~
Kadmiel:
ቀዳሚኤል፣ ፊተኛ አምላክ፣ በመጀመሪያ ጌታ፣ እግዚብሔርን ማስቀደም... ማለት ነው።
‘ቀደመ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ ስም
ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ
ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች፥ ቀድምኤል፥ አንዱ
ነው፥ (ነህ 9:4)
ቀድሞናውያን ~ Kadmonites: ቀዳማውያን፣ የመጀመሪያዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቄድማ፣ ቅዴሞት]
በአብርሃም ዘመን በፍልስጥኤም ከነበሩ ሕዝቦች፥ “ቀድሞናውያንንም ኬጢያውያንንም” (ዘፍ 15:19
፣ 20)
ቀጰዶቅያ ~ Cappadocia:
‘ጠፍር፣ ማሰሪያ’
ማለት ነው። ክርስትና አስቀድሞ ከተስፋፋባቸው ግዛቶች፥ “የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ …በኢየሱስ ክርስቶስ
ደም ይረጩ
ዘንድ ለተመረጡት
በጳንጦስና በገላትያ
በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ”
(1 ጴጥ 1:1)
ቁሚ ~
Cumi:
ቁሚ፣ ተነሺ፣ መቆም፣ መነሣት፣ መጽናት፣አለመቀመጥ፣ አለመተኛት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
‘ቆመ’ ከሚለው ግስ
የመጣ ቃል ነው።
ጌታ የሞተችዋን ልጅ ሲያስነሳ የተናገረው ቃል፥ “የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ። ጣሊታ
ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው:”
(ማር 5፡41)
ቍርባን ~
Corban:
ቁርባን፣ ቆረበ፣ ቀረበ፣ ከአምላክ ጋር ተዋሐደ፣ ኅብረት ፈጠረ፣ ወደ እግዚአብሔር ተጠጋ... ማለት ነው።
‘ቆረበ’ ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በማርቆስ
ወንጌል ‘ቁርባን’ የተባለው ፥
በማቴዎስ ወንጌል ‘መባ’ ተብሎ ተተርጉሟል፥
“እናንተ ግን ትላላችሁ።
ሰው አባቱን ወይም
እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥” (ማቴ 15:5 ፣ 11፥ ማር 7:11)
ቁአስጥሮስ ~ Quartus: አራተኛ ማለት
ነው። በሐዋርያው ጳውሎስ
ለሮማውያን ክርስቲያኖች ሰላምታ የላከ፥ “የእኔና የቤተ ክርስቲያን ሁሉ አስተናጋጅ
ጋይዮስ ሰላምታ … ቁአስጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።” (ሮሜ 16:23)
ቍጣ ~ Fury: አስፈሪ፣ አስደንጋጭ፣
ቁጡ፣ ኃይለኛ ማለት
ነው። የእግዚብሔር ቁጣ አስፈሪ፥ ቅጣቱም ከባድ መሆኑን ለመግለጽ፥ “እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።” (ሌዊ 26፡28) ፥ (ሌዊ
26:28፥ ኢዮ 20:23
፥ ኢሳ 63:3 ፥
ኤር 4:4 ፥
ሕዝ 5:13 ፥
ዳን 9:16 ፥
ዘካ 8:2)
ቂሳ ~
Kishi, Kushaiah: ካሽ ያሕ፣ ካሲ፣ ኩሺ ያሕ፣ የሚክስ፣ ይቅር የሚል፣ ይቅር ባይ አምላክ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ቂስ]
Kishi-
‘ካሰ’
ከሚለው ግስ የመጣ
ስም ነው።
Kushaiah- ‘ካሽ’ እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ ፣ ሕያው)
ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ቂሳ / Kishi:
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም
እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ በየተራቸው ያገለግሉ ከነበሩ፥ የኤታን ልጅ፥ “በግራቸውም በኩል ...
ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥” (1 ዜና 6:44)
ቂሳ / Kushaiah:
የኤታን ልጅ፥ (1
ዜና 15:17)
ቂስ ~
Kish:
ቄስ፣ ካሽ፣ የሚክስ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ቂሳ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የሜራሪ ወገን፣ የሞሖሊ ልጅ፥ (1 ዜና 23:21)
2. የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ፥ የንጉሥ ሳዖል አባት፥ ጽኑዕ ኃያል ሰው የነበረ፥ (1
ዜና 9:36)
3. በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ፣ ሌዋዊው የአብዲ ልጅ፥ (2
ዜና 29:12)
4. የአይሁዳዊው መርዶክዮስ ቅድመ አያት፥ (አስ 2:5)
5. ብንያማዊው የንጉሥ ሳኦል አባት ሆኖ፥ የአቢኤል ልጅ፥ (2
ሳሙ
21:14)
፣ (1 ሳሙ 9:1፣3፣ 10:11፣21፣ 14:51)
ቂስ ~ Cis: ቂስ፣ ቄስ፣
ኩሽ፣ ካሽ፣ ካስ፣
ካሲ... ማለት
ነው። የሳኦል አባት፥ “ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት ሰጣቸው፤”
(ሐዋ 13:21)
ቂሶን ~ Kishion, Kishon: ‘ጽኑዕ፣ ጠንካራ’ ማለት ነው።
“ወደ ረቢት፥ ወደ
ቂሶን፥
ወደ አቤጽ፥” (ኢያ 19:20)
ቂሶን
/
Kishon:
‘ጠመዝማዛ’
ማለት ነው። በመካከለኛው
ፍልስጥኤም የነበረ ወንዝ፥
“ኤልያስም። ከበኣል ነቢያት
አንድ ሰው እንዳያመልጥ
ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።” (1 ነገ 18:40)
ቂር ~ Kir: ‘ቅጥር፣
አጥር፣ ክልል’
ማለት ነው። የአሦር
ንጉሥ ሶርያውያንን ማርኮ
የወሰደበት ቦታ፥ “… በደማስቆ ላይ
ወጣባት ወሰዳትም፥ ሕዝብዋንም
ወደ ቂር አፈለሳቸው፥ ረአሶንንም ገደለ”
(2 ነገ 16:9፤ አሞ 1:5፥ 9:7)
ቂርሐራሴት ~ Kirharaseth: ‘የጡብ ምሽግ’ ማለት ነው። የቦታ ስም፥ “ከተሞችንም አፈረሱ … የሚያፈሩትንም ዛፎች ሁሉ ቈረጡ የቂርሐራሴትን ድንጋዮች ብቻ አስቀሩ ባለ ወንጭፎች ግን ከብበው መቱአት።” (2 ነገ 3:25)
ቂርያታይም ~ Kirjathaim: ቂራት፣ የታጠሩ፣ የተከበቡ፣ የተከተሙ... ማለት ነው።
1.
የንፍታሌም
መጻተኞች መናኽሪያ፥ “ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው …
ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጡ”
(1 ዜና 6:76)
2.
“… የነበሩት ነገሥታት መጡ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ”
(ዘፍ 14:5፤ ዘዳ 2:910)
ቂርያት ሐጾት ~ Kirjath-huzoth: ‘ደማቅ ቀየ፣ ደማቅ ከተማ’ ማለት ነው። የሞዓባያውያን ከተማ፥ “በለዓምም ... ወደ ቂርያት ሐጾትም መጡ።”
(ዘኊ 22:39)
ቂርያት ~
Kirjath:
ቂራት፣ የታጠሩ፣ የተከተሙ... ማለት ነው።
የብንያም ነገድ ከተሞች ተብለው ከተዘረዘሩ፥ የመጨረሻው፥ “ሬቄም፥ … የኢያቡስ ከተማ፥
ቂርያትጊብዓት
አሥራ ሦስት ከተሞችና
መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች
ርስት በየወገኖቻቸው ይህ
ነበረ።”
(ኢያ 18:28)
ቂርያትሰና ~ Kirjath-sannah:
‘የሲና ከተማ፣ የተምር ቀየ’ ማለት ነው። “ሶኮ፥ ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና”
(ኢያ 15:49)
ቂርያትአርባቅ ~ Kirjath-arba: አራት ቅጥራት፣ አራት ከተሞች፣ ብዙ ቀያት... ማለት ነው። የሔብሮን የቀድሞ ስም፥ ለካሌብ በኢያሱ የተሰጠች፥
“በቂርያትአርባቅም ሞተች እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና
ሊያለቅስላት ተነሣ።” (ዘፍ 23:2፥
35:27፤ ኢያ 15:13)
ቂርያትይዓሪም ~ Kirjath-jearim: ‘የአራም
ከተማ፣ የከተማ ዱር’
ማለት ነው። የገባዖናውያን ከተማ፥ “የእስራኤልም
ልጆች ተጕዘው …የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ”
(ኢያ 9:17)
ቂርያትጊብዓት ~ Kirjath-sepher: ቅርያት ሰፈር፣ ቅርያት መንደር፣ ቀያት፣ አካባቢ... ማለት ነው።
ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን ሲያከፋፍል፥ ከብንያም ልጆች
ነገድ ድርሻ ከተሞች፥
“...ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡስ
ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት
አሥራ ሦስት ከተሞችና
መንደሮቻቸው...”
(ኢያ 18:28) ፤
(ኢያ 15:15፣
16)
ቂርዮት ~ Kirioth: ‘ቂራት፥
ቀያት፣ ሁለት
ከተሞች’ ማለት
ነው። ነቢዩ አሞጽ
በእሳት እንደሚጠፋ ትንቢት
ከተናገረባቸው የሞዓብያን ከተሞች፥
“በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች ሞዓብም በውካታና በጩኸት
በመለከትም ድምፅ ይሞታል” (አሞ 2:2)
ቂሮስ ~ Cyrus: ‘ፀሓይ’ ማለት ነው።
የፋርስን መንግሥት የመሠረተ፥ ንጉሥ፥ “በኤርምያስም አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ
በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር
የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ …” (2 ዜና 36:22፣23፤ ዳን6:28፥ 10:1፣13)
ቂና ~
Kinah:
‘ቅኔ’
ማለት ነው። በይሁዳ ደቡባዊ ዳርቻ፥ የነበረ ከተማ፥ “ቀብስኤል፥
ዔዴር፥ ያጉር፥
ቂና፥”
(ኢያ 15:22)
ቂድሮን ~ Kitron:
‘ቋጠሮ፣ መቋጠር፣ አንድ
ላይ ማሰር’ ማለት
ነው። የዛብሎን ከተማ የነበረ፥ “ዛብሎንም የቂድሮንንና የነህሎልን ሰዎች አላወጣቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፥ …” (መሣ 1:30)
ቃላይ ~
Kallai:
ቃለያሕ፣ ቃለ ሕያው፣ የጌታ ቃል፣ ቃለ እግዚአብሔር፣ ትጉህ አገልጋይ... ማለት ነው።
‘ቃለ’
እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው)
ከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው።
ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር ከወጡ ካህናትና ሌዋውያን፥ ቃላይ፥ (ነህ 12:20)
ቃሞን ~ Camon: ‘ቆመነ፣
ቆመ፣ ተነሣ፣ ትንሣኤ’
ማለት ነው። መስፍኑ ኢያዕር የተቀበረበት
ቦታ፥ “ኢያዕርም
ሞተ፥ በቃሞንም ተቀበረ።” (መሣ 10:5)
ቃሬያ ~ Careah, Kareah:
‘ራሰ በራ’ ማለት ነው። የዮሐናን
አባት፥ “የጭፍሮቹም
አለቆች ሁሉ፥ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፥ …” (2 ነገ 25:23)
ቃሬያ /
Kareah: ‘ራሰ
በራ፣ መላጣ፣ ፀጉር
የሌለው’ ማለት ነው።
የዮሐናንና የዮናታን አባት፥ “የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ
ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ
ልጆች … ምጽጳ መጡ።” (ኤር 40:8፣13፣15፣16)
ቃና ~ Cana, Kanah: ቃና፣ ጣዕም... ማለት ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ቦታዎች አሉ።
ቃና / Cana: የጌታ እናት ከልጅዋ ጋር ለሰርግ የተገኘችበት አገር፥ “በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤” (ዮሐ 2፡1-11)
ቃና / Kanah:
1. የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው፥ (ኢያ 16:8)
2. በአሴር ርስት በስተሰሜን የሚገኝ ከተማ፥ (ኢያ 19:28)
ቃየል ~
Cain:
ቀን፣ ቀኝ፣ ቀናተኛ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ቃየን]
Cain-
‘ቀኝ’
ከሚለው ቃል የመጣ
ስም ነው።
የአዳም ልጅ የአቤል ታላቅ ወንድም ቃየል፥ “አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ...” (ዕብ 11:4)
ቃየን ~
Cain:
ቀን፣ ቀኝ፣ ቀናተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ቃየል]
Cain-
‘ቅኝ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
የአዳም ልጅ የአቤል ታላቅ ወንድም፥ “አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።” (ዘፍ
4፡1)
ቃይናን ~ Cainan, Kenan: ቃየንዓውያን፣ የቃየን ወገኖች ማለት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ቃይናን / Cainan:
1. የሄኖስ ልጅ፥ “ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፥ ቃይናንንም ወለደ”
(ዘፍ 5፡9-14)
2. በሉቃስ ወንጌል ሰለጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የአርፋክስድ ልጅ፥
(ሉቃ 3:36)
ቃይናን / Kenan: ከአዳም ሦስተኛ ትውልድ የሆነ፥ “አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ ቃይናን፥ መላልኤል”
(1 ዜና 1:2)
ቃዴስ ~ Kadesh, Kedesh:
ቅዱስ፣ ለጌታ የተለየ፥ የከበረ፣ የተባረከ፣ የተመሰገነ... ማለት ነው።
‘ቀደሰ’ ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
[ቅዱስ
ማለት ነው / መቅቃ]
በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ቦታዎች አሉ።
ቃዴስ / Kadesh:
እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ካለፋባቸው ቦታዎች፥ “መልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ...” (ዘጸ 4:7)
ቃዴስ / Kedesh:
1. በይሁዳ በስተደቡብ ድንበር፥
(ኢያ 15:23)
2. የይሳኮር ነገድ የሰፈረበት፥
(1 ዜና 6:72)
3. ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ
ከተማ፥ (ኢያ
19:37)፣ (መሣ 4:6)
ቄሬኔዎስ ~
Cyrenius:
‘ቀንደኛ፣ ተዋጊ፣ ጦረኛ...’ ማለት ነው። የሶርያ አገር ገዥ የነበረ፥ “ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ” (ሉቃ 2:2)
ቄርቂስ ~
Crescens:
‘ታዳጊ’ ማለት ነው። የጳውሎስ አገልጋይ፥ ከሰባቱ
ደቀመዛሙርት አንዱ፥ “ዴማስ
የአሁኑን ዓለም ወዶ
ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም
ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤”
(2 ጢሞ 4:10)
ቄናት ~ Kenath: ቀነት፣ የቀና፣ ቀናውያን፣ የቃና ሰዎች ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቄናዊ፣ ቄናውያን፣ ቄኔዛዊው፣ ቄኔዝ]
የኖባህ መንደር የቀድሞ ስም፥ “ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮችዋንም ወሰደ፥
በስሙም ኖባህ
ብሎ ጠራቸው” (ዘኁ 32:42)
ቄናዊ ~ Kenite, Kenites:
ቀናያት፣ ቀናውያን፣ ቅን፣ ያመኑ፣ የተገዙ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቄናት፣ ቄናውያን፣ ቄኔዛዊው፣ ቄኔዝ]
Kenite-
‘ቅኝት፣ ቀነየ፣ ገዛ...’
ከሚለው ቃል የመጣ
ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ቄናዊ / Kenite: የምድያም ካህን፣ ዮቶር ቄናዊ ተብሎ ተጠራ፥ “የቄናዊው የሙሴ አማት ልጆችም
ከይሁዳ ልጆች ጋር
ዘንባባ ካለባት ከተማ
ተነሥተው ከዓራድ በደቡብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወጡ ሄደውም ከሕዝቡ ጋር
ተቀመጡ”
(መሣ 1:16)
ቄናውያን / Kenites: የቄናት ሰዎች … ምድያማውያን፥ (ዘፍ 15:19)
ቄኔዛዊ ~
Kenezzites:
የቄኔዝ ሰዎች፣ የኬጢ ወገኖች፣ የኬጢ አገር ሰዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቄናት ፣ ቄናዊ፣ ቄናውያን፣ ቄኔዝ]
የአብርሃም
ሚስት፣ የኬጡራ ወገኖች፥
“እርሱም፦ በእውነት እግዚአብሔርን ፈጽመው ከተከተሉ ከእነዚህ ከቄኔዛዊው...” (ዘኁ 32:12) “…
ቄኔዛዊውም
የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው”
(ኢያ 14:6፣ 14)
ቄኔዝ ~
Kenaz:
‘አደን’ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቄናት ፣ ቄናዊ፣ ቄናውያን፣ ቄኔዛዊ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. ከዔሳው ልጆች አለቆች አንዱ፥ የኤልፋዝ ልጅ፥ “የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ።” (ዘፍ 36:11፣15፣ 42)
2. የካሌብ ወንድም፥ (ኢያ 15:17)
3. የካሌብ ልጅ፣ የኤላም ልጅ፥ (1 ዜና 4:15፣16)
ቄዳ ~
Clauda:
‘ስቅስቅታ፣ አንጉርጉሮ’ ማለት ነው። ጳውሎስ
ወደ ሮሜ ባደረገው
ጉዞ፥ ካለፈባቸው ቦታዎች፥
“ቄዳ በሚሉአትም ደሴት
በተተገንን ጊዜ ታንኳይቱን ለመግዛት በጭንቅ ቻልን፤”
(ሐዋ 27:16)
ቄዳር ~
Kedar:
‘ጠይም፣ ጠቋራ’ ማለት ነው። የእስማኤል ሁለተኛ ልጅ፥ “ነባዮት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥
መብሳም፥ ማስማዕ፥” (ዘፍ 25:13)
ቄድማ ~ Kedemah:
ቀዳማይ፣ ቀዳሚ፣ ቅዳሜ፣ ፊተኛ፣ የመጀመሪያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቀድሞናውያን፣ ቅዴሞት]
‘ቀደመ’ ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
የአብርሃም ልጅ፥ ከእስማኤል ልጆች፥ “ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥
ናፌስ፥ ቄድማ።”
(ዘፍ 25:15)
ቄድሮን ~
Cedron:
‘ጥቁር ጎርፍ’
ማለት ነው። በኢየሩሳሌም ምሥራቃዊ
ጠርዝ ሥር የሚወርድ
ወንዝ፥ “ኢየሱስም
ይህን ብሎ አትክልት
ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ …” (ዮሐ 18:1)
ቄድሮን ~
Kidron:
‘ውጥንቅጥ፣ ውስብስብ’
ማለት ነው። የፈፋ ስም፥
“በአገርም የነበሩት ሁሉ በታላቅ ድምፅ አለቀሱ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻገሩ፥ ንጉሡም
ደግሞ የቄድሮንን ፈፋ
ተሻገረ ሕዝቡም ሁሉ
ወደ …” (2 ሳሙ
15:23)
ቈላስይስ ~ Colosse: ‘ቅጣት፣
እርማት’
ማለት ነው። “በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና
በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና
ሰላም ይሁን።” (ቆላ 1:2፥4:13፣15፣16)
ቅላውዲያ ~ Claudia: ‘አንካሳ፣ የአካል ጉዳተኛ’
ማለት ነው። ወደ
ጢሞቴዎስ በተላከ መልእክት
የተጠቀሰች ክርስቲያን፥ “… ኤውግሎስና ጱዴስ
ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል” (2 ጢሞ 4:21)
ቅል ~
Gourd:
ጋርድ፣ መጋረጃ፣ ከለላ፣ ጥላ... ማለት ነው።
Gourd-
‘ጋረደ’
ከሚለው ግስ የተገኘ
ስም ነው።
ዮናስ በመንገድ በደከመው ጊዜ ከፀሐይ ትጋርደው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘጋጀለት
ተክል፥ “እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፥ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ
ላይ ጥላ
እንድትሆን በዮናስ ላይ
ከፍ ከፍ አደረጋት፤
ዮናስም ስለ ቅሊቱ
እጅግ ደስ አለው:” (ዮና 4፡6-10)
ቅመም ~ Bether: ‘መለየት መከፈል’ ማለት ነው። በንጉሥ ሰሎሞን መዝሙር ውስጥ የተጠቀሰ የተራራ ስም፥ “ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ በቅመም … የዋላውን እምቦሳ ምሰል" (መኃ 2:17)
ቅዒላ ~ Keilah: ቃለ ያሕ፣ ቃለ ሕያው፣ የጌታ ቃል፣ ቃለ እግዚአብሔር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቆልያ፣ ቆላያ]
‘ቃል’ ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ሆኖ የተሰጠ፥ “ንጺብ፥ ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:44)
ቅዴሞት ~ Kedemoth:
ቀደማት፣ ቀዳማያት፣ ቀዳማውያን፣ ፊተኞች የመጀመሪያዎች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቄድማ፣ ቀድሞናውያን]
‘ቀደመ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
የእስራኤልም ልጆች እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን የተሰጠ፥ “ቤትበኣልምዖን፥ ያሀጽ፥ ቅዴሞት” (ኢያ
13:18)
ቅፍርናሆም ~ Capernaum: ‘የንስሐ
መስክ፣ የዕዕረፍት ቦታ፥ የሰላም
ከተማ’
ማለት ነው። በናዝሬት
በአማረሩት ጊዜ፥ ከአይሁድ
ዘወር ለማለት ጌታ
የሄደበት አገር፥
“ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።” (ማቴ 4:13-16፤ ሉቃ 4:16-31)
ቆላያ ~
Kolaiah:
ቃለ ያሕ፣ ቃለ ሕያው፣ ቃለ ህይወት፣ ቃለ እግዚአብሔር፣ የጌታ ቃል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቅዒላ፣ ቆልያ]
‘ቃለ’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. ከግዞት ተመልሰው፥ በኢየሩሳሌም ከተቀመጡት የብንያም ወገኖች፥
(ነህ 11:7)
2. ሐሰተኛ ትንቢትን የሚናገር፣ የአካብ አባት ፥ (ነህ 29:21)
ቆልያ ~
Kelaiah:
ቃለ ያሕ፣ ቃለ ሕያው፣ የጌታ ቃል፣ ቃለ እግዚአብሔር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቅዒላ፣ ቆላያ]
‘ቃለ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣
ሕያው)
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው። የምድርን አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተው፣ ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ከሰጡ፥ “...ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፥ ፈታያ፥ ይሁዳ፥ አልዓዛር።” (ዕዝ 10:23)
ቆሳም ~
Cosam:
‘ቅስም፣ ነቢይ፣ ትንቢት ተናጋሪ’ ማለት ነው። በድንግል ማርያም እጮኛ፥ በዮሴፍ
የዘር ሐረግ፥ የኤልሞዳም
ልጅ፥ “የሚልኪ
ልጅ፥ የሐዲ ልጅ፥
የዮሳስ ልጅ፥ የቆሳም ልጅ፥ የኤልሞዳም ልጅ፥ የኤር ልጅ፥” (ሉቃ 3:28)
ቆስ ~
Coos:
‘ጫፍ’ ማለት ነው። ጳውሎስ ከጉዞው መልስ በዚህ አርፏል፥
“ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤
በቀጥታም ሄደን ወደ
ቆስ በነገውም ወደ
ሩድ ከዚያም ወደ
ጳጥራ መጣን፤” (ሐዋ 21:1)
ቆሬ ~ Korah:
ቁሪ፣ ቁር፣ ብርድ፣ ቅዝቃዜ... ማለት ነው።
1.
የዔሳው ልጅ፥ (ዘፍ
36:5፣14፣18፤ 1 ዜና 1:35)
“አህሊባማም የዑስን፥ የዕላምን፥ ቆሬን ወለደች በከነዓን ምድር የተወለዱለት
የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው።”
2.
ከኤዶም አለቆች አንዱ፥ የዓዳ ልጅ፥ (ዘፍ 36:16) “ቆሬ አለቃ፥
ጎቶም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው።”
3.
የኬብሮን ልጅ፥ (1
ዜና 2:43) “የኬብሮንም ልጆች ቆሬ፥ ተፉዋ፥
ሬቄም፥ ሽማዕ ነበሩ።”
4.
በምድረ በዳ ሙሴንና አሮንን የተቃወሙ፥ (ዘኊ 16፥ 27) “ከቆሬና ከዳታን
ከአቤሮንም ማደሪያ ከዙሪያውም
ሁሉ ፈቀቅ አሉ፤
ዳታንና አቤሮንም ሴቶቻቸውም ልጆቻቸውም ሕፃናቶቻቸውም ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ።”
ቆርኔሌዎስ ~ Cornelius: ቀርን፣ ቀንድ፣
ቀንደኛ፣ ፊተኛ፣ ዋና ማለት ነው።
የጣልያን ወታደር፥ የሮም መቶ አለቃ፥ ተቀማጭነቱ በቄሣርያ የነበረ፥ “በቂሣርያም …
ጭፍራ የመቶ አለቃ
የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት
አንድ ሰው ነበረ” (የሐዋ 10:1)
ቆሮንቶስ ~ Corinth: ‘ውብ፣
ጌጥ’
ማለት ነው። ጥንታዊ
ውብ የግሪክ ከተማ፥ “ከዚህም በኋላ ጳውሎስ ከአቴና ወጥቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ”
(የሐዋ 18:1)
ቆዓ ~ Koa: “እነርሱም
የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም
ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥
ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ …. ናቸው።” (ሕዝ 23:23)
ቆጵሮስ ~ Cyprus: ‘ሐቀኛ’ ማለት ነው።
በሜድትራንያን የሚገኝ የኤስያ
ደሴት፥ (ሐዋ 4:36) “ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም
በሐዋርያት በርናባስ ተባለ
ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ
ነው”
ቆጽ ~ Coz: ‘ቆጥ፣ ቀንድ’ ማለት ነው።
በይሁዳ የዘር ሐረግ
የተጠቀሰ፥ “ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።” (1 ዜና 4:8)
No comments:
Post a Comment