ጸልሞን ~ Zalmon: ጽልመት፣ ጨለማ፣ ጥላ፣ ጠለላማለት ነው። ከዳዊት ጠባቂዎች አንዱ፥ አሆሃዊው፥ ጸልሞን ነጦፋዊው ኖኤሬ፥ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ወገን” (2 ሳሙ 23:29)

ጸዒር ~ Zair: ትንሽማለት ነው። የቦታ ስም፥ ኢዮራምም ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ጸዒር አለፈ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና ...” (2 ነገ 8:21)

ጸዕነኒም ~ Zaanannim: መጻተኞች፣ ስደተኛ፣ ተጓዥ፣ መንገደኛማለት ነው። ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ ... (ኢያ 19:33)

ጸፍናት ፐዕናህ ~ Zaphnath-paaneah: አሳሽ፣ ዳሳሽ፣ መርማሪ፣ ፈላጊ ማለት ነው። ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ” (ዘፍ 41:45)

ጹፍ ~ Zuph:ሰፈፍማለት ነው። ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜም ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፦ አባቴ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፥ እንመለስ አለው።” (1 ሳሙ 9:5)

ጺልታይ ~ Zilthai: ላዬ ሕያው ጥላ፣ ጠለላማለት ነው።

1. ብንያማዊ፥ ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች” (1 ዜና 8:20)

2. በጺቅላግ ከዳዊት ሠራዊት ጋር የተቀላቀለ፥ የምናሴ ሻለቆች ከነበሩ፥ ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት፥ ኤሊሁ፥ ጺልታይ ወደ እርሱ ከዱ። (1 ዜና 12:20)

ጺቅላግ ~ Ziklag: ጠመዝማዛ ማለት ነው። በይሁዳ ደቡባዊ ግዛት የነበረ ከተማ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ ማድማና፥ ሳንሳና፥ (ኢያ 15:31)

ጺን ~ Zin: ረባዳ፣ ጠፍጣፋ፣ ደልዳላማለት ነው። ወጡም ምድሪቱንም ጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ (ዘኊ 13:21)

ጺዖር ~ Zior: ብልጭ ትንሽ ብርሃንማለት ነው። በይሁዳ ተራራማ ክፍል የሚገኝ ከተማ፥ አፌቃ፥ ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:54)

ጺጽ ~ Ziz: ትንበያ ማለት ነው። ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ እነሆ፥ ጺጽ ዓቀበት ይወጣሉ በሸለቆውም መጨረሻ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገኙአቸዋላችሁ።” (2 ዜና 20:16)

ጻርታን ~ Zaretan: መከራ እንግልትማለት ነው። ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች የዮርዳኖስን ውኃ ሲነኩ፥ ውኃው የቆመበት ቦታ፥ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ ጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ ... ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።” (ኢያ 3:1617)

ጼላ ~ Zelah: ዛለ፣ ደከመማለት ነው። ለብንያም ነገድ የተሰጠ ቦታ፥ ሬቄም፥ ይርጵኤል፥ ተርአላ፥ ጼላ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።” (ኢያ 18:28)

ጼሌቅ ~ Zelek: ሊቅ፣ ጠሊቅ፣ ጥልቅ፣ ዘላቂ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሊቅሕ፣ ሉቃስ]

Zelek- ‘ጥልቅከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ፥ (2 ሳሙ 23:37) (1 ዜና 11:39)

ጼልጻህ ~ Zelzah: ጥላ፣ ጠለላ ማለት ነው። የብንያም አዋሳኝ የሆነ የቦታ ስም፥ ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ዳርቻ ጼልጻህ አገር ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ እርሱም፦ ... (1 ሳሙ 10:2)

ጼር ~ Zer: ጾር፣ ጣእ ጦር፣ ፈተና፣ መከራ፣ አሳር... ማለት ነው። የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት የሆነ የቦታ ስም፥ (ኢያ 19:35)

ጽሩዓ ~ Zeruah: ዘርህ፣ ዘር፣ ወገን፣ ዘመድ፣ ረዳት፣ አጋዥ፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ጽሩያ፣ ጽሩዓ፣ ጽሪ]

የናባጥ ልጅ የኢዮርብ እናት፥ (1 ነገ 11:26)

ጽሩያ ~ Zeruiah: ዘረያ፣ ዘረ ሕያው፣ የሕያው አምላክ ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የእግዚአብሔር ልጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ጼር፣ ጽሩዓ፣ ጽሪ]

Zeruiah- ዘር እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የናባጥ ልጅ የኢዮርብ እናት፥ (1 ዜና 2:16)

ጽሪ ~ Zeri: ዘሪ፣ ዘር የሚዘራ፣ የሚያመርት፣ የሚያበረክት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ጼር፣ ጽሩያ፣ ጽሩዓ]

በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ፣ የኤዶታም ልጅ፥ (1 ዜና 25:3)

ጽሮር ~ Zeror: እስር፣ ነዶማለት ነው። ቂስ የተባለ የብንያማዊ ሰው፥ የብኮራት አባት፥ ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ብንያማዊ ሰው ነበረ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ ጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበረ” (1 ሳሙ 9:1)

ጽናን ~ Zenan: ጠማማ ማለት ነው። የይሁዳ አዋሳኝ የሆነ የቦታ ስም፥ ጽናን ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ ዲልዓን፥” (ኢያ 15:37)

ጽዮን ~ Zion: ጽኑ፣ ጽኑዓን፣ ብርቱ፣ ጠንካራ፣ መከታ፣ አምባ፣ መመኪያ... ማለት ነው ኢየሩሳሌምም ጽዮን ትባላለች። [ተዛማጅ ስም- ሲዎን]

[ቃሉ አምባ ማለት ነው / መቅቃ]

. የኢየሩሳሌም ሌላ ስም፥ “...ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮን ያዘ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት:” (1 ዜና 115-7)

. በአዲስ ኪዳን ጽዮን የሚለው ስም ለቤተ ክርስቲያን እና ለሰማያዊ የእግዚአብሔር መንግሥት፥ መጠሪያ ስም ሁኖ ያገለግላል። (ዕብ 12:22) (ራእ 14:1)

ጽዳድ ~ Zedad: ገዳዳ አቀበትማለት ነው። በሐማት አጠገብ፣ በሰሜን ፍልስጥኤም የነበረ ከተማ፥ ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ታመለክታላችሁ የዳርቻውም መውጫ ጽዳድ ይሆናል (ዘኊ 34:8 ሕዝ 47:15)

ጽፋት ~ Zephath: ማማማለት ነው። የከነዓን ከተማ ጥንታዊ ስም፥ ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፥ ጽፋት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፥ ፈጽመውም አጠፉአት። የከተማይቱንም ስም ሔርማ ...” (መሣ 1:17)

ጾርዓ ~ Zareah, Zorah: ጸራ፣ ጠራ፣ ጮራ፣ ጨረር... ማለት ነው።

       ጾርዓ / Zareah: በደቡብ በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች፥ (ነህ 11:29)

       ጾርዓ / Zorah: የዳን ነገድ ርስት፥ በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ አሽና፥ ዛኖዋ” (ኢያ 15:33)

ጾርዓ ~ Zorah: ጢንዚማለት ነው። ለዳን ነገድ የተሰጠ ከተማ፥ የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ ጾርዓ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥” (ኢያ 19:41)

ጾፊም ~ Zophim: ጠባቂዎችማለት ነው። ባላቅ እስራኤላውያንን እንዲረግምለት ባላምን የወሰደበት ሜዳ፥ ወደ ጾፊም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ” (ዘኊ 23:14)

ጾፋ ~ Zophah: ሽንክ ዋርማ፣ ጽዋማለት ነው። የኤላም ልጅ፥ የወንድሙም የኤላም ልጆች ጾፋ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ። (1 ዜና 7:3536)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ