ዘሃም ~ Zaham: አበሳ፣ በደል፣ ግፍማለት ነው። የሮብዓም እና የመሐላት ልጅ፥ እርስዋም የዑስን፥ ሰማራያን፥ ዘሃም ወንዶች ልጆች ወለደችለት።” (2 ዜና 11:19)

ዘለፋ ~ Zilpah: ጠፈጠፍማለት ነው። የልያ ባሪያ፥ ላባም ለልጁ ለልያ ባሪያይቱን ዘለፋ ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት።” (ዘፍ 29:24)

ዘማራይም ~ Zemaraim: ዘማያም፣ ያማዊ፣ የማያም ወገን፣ የማያም አገር ሰው... ማለት ነው።

እና ያም ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

ከብንያም ልጆች ነገድ ከተሞች አንዱ፥ ቤትዓረባ፥ ዘማራይም ቤቴል፥ (ኢያ 18:22) (2 ዜና 13:4-20)

ዘምራን ~ Zimran: ዝማሬ፣ ዜማ፣ መዝሙር... ማለት ነው። የኬጡራ ትልቁ ልጅ፥ እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት።” (ዘፍ 25:2 1 ዜና 1:32)

ዘምዙማውያን ~ Zamzummims: ዘማውያን፣ ዝሙት የሚፈጽሙ፣ ሴሰኞች፣ ወንጀለኞችማለት ነው። ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ ራፋይምም ... ነበር አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል” (ዘዳ 2:2021)

ዘሩባቤል ~ Zerubbabel, Zorobabel: ዘረ ባቢል፡ የባቢሎን ዘር፣ በባቢሎን የተወለዱ... ማለት ነው።

ዘር እና ባቢሎን ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[የባቢሎን ዘር ማለት ነው / መቅቃ] በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የፈዳያ ልጅ፥ (1 ዜና 3:19)

2. የሰላትያል ልጅ፥ (ሐጌ 1:1)

       ዘሩባቤል / Zorobabel: ዘሩባቤል፥ ባቢሎን ዘር፥ በባቢሎን የተወለደ ማለት ነው። ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤል ወለደ፤ (ማቴ 1:1213 ሉቃ 3:27)

ዘራእያ ~ Zerahiah: ዘረ ሕያው፣ የሕያው ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ዘመድ፣ የእግዚአብሔር ልጅ... ማለት ነው።

ዘር እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የጸሐፊው የዕዝራ አያት፣ የኦዚ ልጅ፥ (1 ዜና 6:6 51)

2. በዕዝራ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ፣ የኤሊሆዔናይ አባት፣ የፋሐት ሞዓብ ልጅ፥ (ዕዝ 8:4)

ዘሬድ ~ Zared: ዘሬድ፣ ወርደ፣ የወረደ፣ ከላይ የመጣ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ያሬድ፣ ዬሬድ]

እና ወረደ (ያሬድ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። እስራኤል ከቃዴስ በርኔ ተጉዘው ያለፉበት የቦታ ስም፥ (ዘኁ 21:12)

ዘበኞቹ ~ Guard: ጋርድ፣ የሚጋርድ፣ የሚከልል፣ የሚጠብቅ... ማለት ነው።

Guard- ጋረደከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። የፈርዖን ዘበኞች፥ (ዘፍ 3736)

ዘቢና ~ Zebina: መገብየት፣ መግዛትማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የናባው ልጅ፥ ከናባው ልጆችም፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ፥ ዘቢና ያዳይ፥ ኢዮኤል፥ በናያስ። (ዕዝ 10:43)

ዘቢዳ ~ Zebudah: የተሸለመ፣ ስጦታን ያገኘማለት ነው። የንጉሥ ኢዮአቄም እናት፥ ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ዘቢዳ ትባል ነበር እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች።” (2 ነገ 23:36)

ዘባይ ~ Zabbai: ዘአብያ፣ አብ፣ አባዊ፣ አባታዊ... ማለት ነው።

እና አባ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

. በዕዝራ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፣ የቤባይ ልጅ፥ (ዕዝ 10:28)

. በነህምያ ዘመን ከተመለሱ፣ ቅጥሩን በመጠገን ከተባበሩ፥ (ነህ 3:20)

ዘብዲ ~ Zabdi: ዘውዴ፣ ስጦታዬማለት ነው።

1. የሰሜኢ ልጅ፥ ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ” (1 ዜና 8:19)

2. በዳዊት መንግሥት፥ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት ሹም የነበረ፥ በወይንም ቦታዎች ላይ ራማታዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚሆነው በወይኑ ሰብል ላይ ሸፋማዊው ዘብዲ ሹም ነበረ(1 ዜና 27:27)

3. የአሳፍ ልጅ፥ በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ ዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ ... (ነህ 11:17)

ዘብዴዎስ ~ Zebedee: ስጦታዬማለት ነው። የሐዋርያቱ የያዕቆብ እና የዮሐንስ አባት፥ አሳ አጥማጁ፥ ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች ዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ...” (ማቴ 4:2127:56)

ዘኩር ~ Zacchur, Zaccur: ዘኩር፣ ዝኩር፣ ዝክር፣ መታሰቢያ፣ ማስታዎሻ... ማለት ነው።

ዘከረ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዘካርያስ፣ ዘካይ፣ ዘኬዎስ፣ ዛኩር]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዘኩር / Zacchur: የማስማዕ ልጅ፥ ዘኩር (1 ዜና 4:26)

       ዘኩር / Zaccur:

1. ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከተላኩ፣ ከሮቤል ነገድ የሰሙኤል አባት፥ ዘኩር (ዘኁ13:4)

2. ከሜራሪ ወገን የሆነ፣ የያዝያ ልጅ፥ ዘኩር (1 ዜና 24:27)

3. የአሳፍ ልጅ፥ ዘኩር (1 ዜና 25:2 10)

4. ከግዞት ተመልሰው የከተማውን ቅጥር በመጠገን ነህምያን ከተባበሩ፣ የአምሪ ልጅ፥ ዘኩር (ነህ 3:2)

5. በነህምያ ዘመን በገንዘብ ያዥነት ከተሾሙ፣ የመታንያ ልጅ ዘኩር

(ነህ 13:13)

6. ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙ፣ (ነህ 10:12)

ዘካርያስ ~ Zachariah, Zacharias, Zechariah: ዘካሪ ያሕ፣ ዝክረ ሕያው፣ ዝክረ ዋስ፣ የጌታ ዝክር፣ የአምላክ መታሰቢያ፣ የጻድቅ ማስታዎሻ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ዘኩር፣ ዘካይ፣ ዘኬዎስ፣ ዛኩር]

ዘከረ እና ያሕ፣ ዋስ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[ትርጉሙ:- “እግዚአብሔር ያስታውሳልማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዘካርያስ / Zachariah:

1. የኢዮርብዓ ልጅ፥ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ስድስት ወር የነገሠ፥ (2 ነገ

15:8)

2. የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ልጅ የሕዝቅያስ የእናቱ አባት፥ (2 ነገ 18:2)

       ዘካርያስ / Zacharias:

1. የመጥምቁ የዮሐንስ አባት፥ (ሉቃ 1:5)

2. ጌታ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል ስለመገደሉ ጌታ የጠቀሰው፣ የራክዩ ልጅ፥ (ማቴ 23:35)

       ዘካርያስ / Zechariah:

1. የአዶ ልጅ፣ ነቢዩ ዘካርያስ፥ (ዕዝ 5:1)

2. የሮቤል ልጆች አለቃ፥ (1 ዜና 5:78)

3. የመገናኛው ድንኳን ደጅ በረኛ የነበረ፥ የሜሱላም ልጅ፥ (1 ዜና 9:21)

4. የቃል ኪዳኑን ከተከተሉ፣ ከሁለተኛው ተራ የሆነ፥ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ከነበሩ፥ (1 ዜና 15:20-24)

5. የይሺያ ልጅ፥ ከይሺያ ልጆች ዘካርያስ የሜራሪ ልጆች …” (1 ዜና

24:2526)

6. በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ዘመን የነበረ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ፥ (2 ዜና

24:20) ጌታ ኢየሱስ የጠቀሰው ይህን ዘካርያስ ነው፥ (ማቴ 23:35)

7. በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን የነበረ፥ የሌዊያዊው የቀዓት ልጅ፥ (2 ዜና

34:12)

8. በዕዝራ ዘመን ከምርኮ ከተመለሱ፥ የፋሮስ ልጅ፥ (ዕዝ 8:3)

9. ንጉሥ ዳዊትን ያገለግሉ ከነበሩ ሹማምንት በምናሴ ነገድ ክፍል አለቃ የነበረ፥ (2 ዜና 17:7) (1 ዜና 27:21)

10. የበናያስ ልጅ፥ የየሕዚኤል አባት፥ (2 ዜና 20:14)

11. የኢዮሣፍጥ ልጅ፥ (2 ዜና 21:2)

12. የንጉሥ ሕዝቅያስ የእናቱ፣ የአቡ አባት፥ (2 ዜና 29:1)

13. በሕዝቅኤል ዘመን፥ የአሳፍ ልጅ፥ (2 ዜና 29:13)

14. ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ከሰጡ፥ (2 ዜና 35:8)

15. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፣ የኤላም ልጅ፥ (ዕዝ 10:26)

16. የአማርያ ልጅ፥ (ነህ 11:4)

17. ከይሁዳና ከብንያም ልጆች በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ፥ (ነህ 11:5)

18. የፋስኮር ልጅ፥ ካህኑ፥ (ነህ 11:12)

19. መለከት ከሚነፉ ካህናት፣ የዮናታን ልጅ፥ (ነህ 12:36 41)

20. የሮቤል ነገድ አለቃ የነበረ፥ (1 ዜና 5:78)

21. ከዖቤድኤዶም ወገን የሆነ፥ የእግዚአብሔር ታቦ በረኞች ከነበሩ ካህናት፥ (1 ዜና 15:24)

22. ከካህኑ ዕዝራ ጋር ከምርኮ ከተመለሱ፥ (ዕዝ 8:16) (ነህ 8:4)

23. ከሜራሪ ወገን ከነበረው ከሖሳ ልጆች አራተኛው፥ (1 ዜና 26:11)

24. በንጉሥ ዖዝያ ዘመን የንጉ አማካሪ የነበረ፥ (2 ዜና 26:5)

ዘካይ ~ Zaccai: ዘካይ፣ ዘኬ፣ ዝክር፣ ማስታዎሻ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ዘኩር፣ ዘካርያስ፣ ዘኬዎስ፣ ዛኩር]

ዘኬከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ነህ 7:14)

ዘኬዎስ ~ Zacchaeus: ዘኬዎስ፣ ዝክር፣ ዝክረ ዋስ፣ አስታዋሽ፣ በጸሎት የሚያስብ... ማለት ነው።

ዘኬ እና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ዘኩር፣ ዘካርያስ፣ ዘካይ፣ ዘኬዎስ፣ ዛኩር]

ኢየሱስን በቤቱ ያስተናገደ፣ የቀራጮች አለቃ፥ (ሉቃ 19:2)

ዘዳግም ~ Deuteronomy: የተደገመ ሕግ፥ እንደገና የተባለ ሕግ ማለት ነው። (1:1 4:40)

ዘጸአት ~ Exodus: መውጣት፣ መፍለስ፣ መሰደድማለት ነው። እስራኤላውያን -ከአራት መቶ ሠላሳ [በግብፅ] የባርነት ዘመን በኋላ -የወጡበት ታሪክ፥ እነዚህ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው። (ዘጸ 6:27)

ዘፍጥረት ~ Genesis: መጀመሪያ፣መፈጠር፣ መወለድ ማለት ነው። መጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1:1)

ዙኤ ~ Zia: ፍርሃትማለት ነው። ገለዓዳዊው፥ የአቢካኢል ልጅ፥ የአባቶቻቸውም ቤቶች ወንድሞች ሚካኤል፥ ሜሱላም፥ ሳባ፥ ዮራይ፥ ያካን፥ ዙኤ ኦቤድ ሰባት ነበሩ።” (1 ዜና 5:13)

ዙዚም ~ Zuzims: ብኩን፣ ዕረፍት የሌለውማለት ነው። በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም ... (ዘፍ 14:5)

ዚዛ ~ Zina Ziza: ብዙ፣ የተትረፈረፈ ማለት ነው። የሰሜኢ ሁለተኛ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጆች ኢኢት፥ ዚዛ የዑስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ(1 ዜና 23:10)

       ዚዛ / Ziza: የተትረፈረፈማለት ነው።

1. የስምዖን ልጅ፥ ሺፊ ልጅ ዚዛ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ” (1 ዜና 4:37-43)

2. “እርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት (2 ዜና 11:20)

ዚፍ ~ Zif, Ziph: ወጋገንማለት ነው። የአበባ ማበቢያ ወር ስም፥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።” (1 ነገ 6:137)

       ዚፍ / Ziph: ዘአፍ፣ አፍ ማለት ነው።

1. የይሃሌልኤል ልጅ፥ (1 ዜና 4:16) ኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ

2. በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል የነበረ ከተማ፥ (ኢያ 15:24) ዚፍ ጤሌም፥ በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥

3. በይሁዳ ተራራዎች ላይ የነበረ ከተማ፥ (ኢያ 15:55) ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ ዩጣ፥ ኢይዝራኤል፥

ዚፍሮን ~ Ziphron: ጣፋጭ፣ ሽታማለት ነው። የሰሜን ፍልስጥኤም አዋሳኝ የሆነ ከተማ፥ ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል” (ዘኊ 34:9)

ዛማት ~ Zimmah: ግብ፣ ላማማለት ነው።

1. የኢኤት ልጅ፥ ከጌድሶን ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት” (1 ዜና 6:20)

2. የሰሜኢ ልጅ፥ ዓዳያ ልጅ፥ የኤታን ልጅ፥ ዛማት ልጅ፥” (1 ዜና 6:42)

3. የጌድሶን ልጅ፥ ሌዋውያኑም፥ ከቀዓት ልጆች የአማሢ ልጅ ... ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች ዛማት ልጅ ዩአክና የዩአክ ልጅ ዔድን፥” (2 ዜና 29:12)

ዛራ ~ Zerah, Zara(h): ዘርህ፣ ዘራ፣ ዘር፣ ወገን፣ ዘመድ፣ ቤተ ድ፣ ቤተሰብ... ማለት ነው።

ዘርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዔሳው ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፥ ዛራ (ዘፍ 36:13)

2. የይሁዳ ልጅ፥ ዛራ (ዘፍ 38:30 1 ዜና 2:4 ማቴ 1:3)

3. የስምዖን ልጅ፥ ዛራ (1 ዜና 4:24)

4. የያትራይ ልጅ፥ ዛራ (1 ዜና 6:21 41)

       ዛራ / Zara (h): ጮራ ማለት ነው። የይሁዳ ልጅ፥ (ዘፍ 38:30 48:12) “ከእርሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለበት ወንድሙ ወጣ ስሙም ዛራ ተባለ።

ዛቡታዮስ ~ Vajezatha: ጹሕ የተከበረ የተመሰገነማለት ነው። የሐማ ልጅ፥ በርያ፥ ሰርባካ፥ መርመሲማ፥ ሩፋዮስ፥ አርሳዮስ፥ ዛቡታዮስ የሚባሉትን፥” (አስ 9:9)

ዛባድ ~ Zabad: ስጦታማለት ነው።

1. ከዳዊት ኃያላን አንዱ፥ የአሕላይ ልጅ፥ ኬጢያዊው ኦርዮ፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ (1 ዜና 11:41)

2. የታሐት ልጅ፥ የኤፍሬም ልጆች ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ ልጁ ሽቱላ፥” (1 ዜና 7:21) 3. የሰምዓት ልጅ፥ የተማማሉበትም የአሞናዊቱ የሰምዓት ልጅ ዛባድ የሞዓባዊቱም የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ። (2 ዜና 24:2526)

4. የዛቱዕ ልጅ፥ ከዛቱዕ ልጆችም፤ ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድ ዓዚዛ።” (ዕዝ 10:27)

5. የሐሱም ልጅ፥ ከሐሱም ልጆችም፤ መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴ፥ ሰሜኢ።” (ዕዝ 10:33)

6. የናባው ልጅ፥ ከናባው ልጆችም፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ ዘቢና፥ ያዳይ፥ ኢዮኤል፥ በናያስ።” (ዕዝ 10:43)

ዛብሄል ~ Zebah: አብ፣ ዘብ፣ ዘባዊ... ማለት ነው።

ጌዴዎን የጠቀሰው ስም፥ የሱኮትንም ሰዎች። የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ሳሳድድ፥ ደክመዋልና እኔን ለተከተሉ ሕዝብ እንጀራ፥ እባካችሁ፥ ስጡ አላቸው” (መሣ 8:5-21)

ዛብሎን ~ Zebulun: ነዋሪ፣ መንደርተኛ ማለት ነው። የያዕቆብ እና የልያ ስድስተኛ ልጅ፥ ልያም። እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።” (ዘፍ 30:20)

ዛቱዕ ~ Zatthu: እንቡጥ ማለት ነው። ኤላም፥ ዛቱዕ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥” (ነህ 10:14)

ዛኖዋ ~ Zanoah: ዘኖኅ፣ ኖኅ፣ ኖሃዊ፣ የኖኅ ማለት ነው። (ውኃማ፣ ረግረግ፣ ጎርፍ ተብሎም ይተረጎማል።)

እና ኖኅ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

1. የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች፥ (ኢያ 15:34)

2. የይቁቲኤል ልጅ፥ (1 ዜና 4:18)

ዛዕዋን ~ Zaavan: ስደተኛ መጻተኛማለት ነው። የኤጽር ልጅ፥ የኤጽር ልጆችም እነዚህ ናቸው ቢልሐን፥ ዛዕዋን ዓቃን። (ዘፍ 36:27 1 ዜና 1:42)

ዛኩር ~ Zacher: ዘኪር፣ ዝክር፣ መታሰቢያ፣ ማስታዎሻ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች:- ዘኩር፣ ዘካርያስ፣ ዘካይ፣ ዘኬዎስ]

ዘከረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

የዒኤል ልጅ፥ (1 ዜና 8:31)

ዛዛ ~ Zaza: ብዙ ማለት ነው። የዮናታን ልጅ፥ የዮናታንም ልጆች ፌሌትና ዛዛ ነበሩ እነዚህ የይረሕምኤል ልጆች ነበሩ። (1 ዜና 2:33)

ዜማስ ~ Zenas: ሕያውማለት ነው። ሕግ አዋቂው በመባል የተጠራ፥ ጳውሎስ ለቲቶ ይዞት እንዲሄድ ያሳሰበው ሰው፥ ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።” (ቲቶ 3:13)

ዜቡል ~ Zebul: ነዋሪ፣ ቤተኛ መንደርተኛማለት ነው። በአቤሜሌክ እና በከነናውያን መካከል ውዝግብ በተፈጠረበት ወቅት፣ በሴኬምስ ገዥ የነበረ፥ የአቤድም ልጅ ገዓል። የምንገዛለት አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድርነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡል የእርሱ ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ” (መሣ 9:28303641)

ዜብ ~ Zeeb: ዘብ፣ አብ፣ ዘበኛ፣ የተጠበቀ፣ የተከበረ... ማለት ነው። ከምድያም መኳንንት አንዱ፥ በዜብ መጥመቂያ ላይ የተገደለ፥ (ይሁ 7:25)

ዜታር ~ Zethar: ስጡር፣ ኮከብማለት ነው። ከሰባቱ የንጉሥ አርጤስስ ጃንደረቦች አንዱ፥ ... ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርን፥ ከርከስን አዘዛቸው።” (አስ 1:10)

ዝሚራ ~ Zemira: ዘሚራ፣ ዘማሪ፣ መዘምር፣ ለጌታ የሚያዜም፣ ሌት የሚቆም... ማለት ነው።

ዘመረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። ከብንያም ወገን፣ የቤኬር ልጅ፥ (1 ዜና 7:8)

ዝባድያ ~ Zebadiah: የሕያው ስጦታማለት ነው።

1. ንጉሡን ያገለገሉት ከነበሩ ሹማምት፥ የኢዮአብ ወንድም፣ የአሣሄል ልጅ፥ ለአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያ ነበረ በእርሱም ክፍል ... (1 ዜና 27:7)

2. ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ሰደደ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ። (2 ዜና 17:78)

3. የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ፥ እነሆም፥ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያ በላያችሁ ተሾመዋል ... (2 ዜና 19:8-11)

4. ዝባድያ ዓራድ፥ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች” (1 ዜና 8:15)

5. የሜሱላም ልጅ፥ ሜሱላም ልጆች ነበሩት በኵሩ ዘካርያስ፥ ሁለተኛው ይዲኤል፥ ሦስተኛው ዮዛባት” (1 ዜና 26:2)

ዞሔሌት ~ Zoheleth: መዛ መድከም፣ መጎተት ማለት ነው። አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዓይንሮጌል አጠገብ ባለችው ዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ ... (1 ነገ 1:9)

ዞሔት ~ Zoheth: መለየትማለት ነው። የይሽዒም ልጅ፥ የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ።” (1 ዜና 4:20)

ዞሳራ ~ Zeresh: ዘራ ማለት ነው። የሐማ ሚስት፥ ሐማ ግን ታግሦ ወደ ቤቱ ሄደ ልኮም ወዳጆቹንና ሚስቱን ዞሳራ አስጠራ።” (አስ 5:1014 6:13)

ዞዓር ~ Zoar: ትንሽነትማለት ነው። ሎጥ እና ሁለቱ ልጆቹ ከሶዶም ሸሽተው የሄዱበት አገር፥ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ” (ዘፍ 19:2223)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ