የሕማይ ~ Jahmai: ሕያው ያየው፣ አምላክ የጠበቀውማለት ነው። የይሳኮር ሰው፥ በቶላ ቤት አለቃ የነበረ፥ የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ ይብሣም፥ ሽሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው (1 ዜና 7:2)

የሕዚኤል ~ Jahaziel: ያሕዘ ኤል፣ አምላክ ያዘ፣ በአምላክ እጅ ያለ... ማለት ነው።

ያዘ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኬብሮን ሦስተኛ ልጅ፥ የሕዚኤል (1 ዜና 2319)

2. በጺቅላግ ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ የሕዚኤል (1 ዜና 12:4)

3. በዳዊት ዘመን የነበረ ካህን፥ የሕዚኤል (1 ዜና 16:6)

4. የዘካሪያስ ልጅ፥ የሕዚኤል (2 ዜና 20:14-17)

5. በዕዝራ ዘመን ከተመለሱት፣ አባት፥ የሕዚኤል (ዕዝ 8:5)

የሕዜራ ~ Jahzerah: ያሕ ዘራ፣ የሕያው ዘር፣ የአምላክ ወገን... ማለት ነው።

ያሕ’ (ያሕዌ ሕያው) እና ዘርከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ይሁዳ ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ሲማረኩ፣ ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች ከኤፍሬምና ከምናሴ ልጆች በኢየሩሳሌም የቀመጡ። የሜሱላም ልጅ፥ የዓዲኤል አባት፥ (1 ዜና 912)

የሕዝያ ~ Jahaziah: በሕያው የተያዘ፣ አምላክ ያየውማለት ነው። ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊውም ሳባታይ ረዱአቸው።” (ዕዝ 10:15)

የማአት ~ Ahimoth: አሂሞት፣ አያ ሞት፣ አያሞቴ፣ እስከሞት የሚጸና ወንድም፣ ብርቱ ወዳጅ፣ ሐቀኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪሞት] Ahimoth- አያእና ሞትከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የማታትዩ ልጅ፥ (ሉቃ 3:26)

. ከሕልቃናም ልጆች አማሢ፥ አኪሞት” (1 ዜና 625)

የምሌክ ~ Jamlech: የአምላክ፣ የእግዚአብሔር፣ የጌታ፣ የፈጣሪ... ማለት ነው።

መለከከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በስማቸው ከተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ከነበሩ፥ (1 ዜና 4:34)

የሰናዖር ካባ ~ Babylonish garment: በባቢሎናውያን የተሠራ ልብስ፣ ዋጋው ውድ የሆነ የባቢሎን ግምጃ በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ ...” (ኢያ 7:21)

የሱዊ ~ Isui: እሽ፣ ዝም፣ ጸጥ ማለ ነው። የአሴር ሦስተኛ ልጅ፥

የአሴርም ልጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ በሪዓ፥ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር፥ መልኪኤል።” (ዘፍ 46:17)

የሱዋ ~ Ishuai: እሽታ፣ ጸጥታ፣ ዝምታማለት ነው።

እሽከሚለው ድምፅ የተገኘ ስም ነው። የአሴር ልጅ፥ (1 ዜና 730) (ዘፍ 46:17)

የሱዋ ~ Jesui: ታጋማለት ነው። የአሴር ልጅ፥ የአሴር ልጆች በየወገናቸው ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ የሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን።” (ዘኊ 26:44)

የሴሞ ~ Jeshimon: ብቸኛ፣ ገለልተኛ፣ ዘዋራ፣ ሰዋራ ስፍራማለት ነው። በሙት ባሕር በስተደቡብ ያለ የተተወ ቦታ፥ እነዚያም ተነሥተው ከሳኦል በፊት ወደዚፍ ሄዱ ዳዊትና ሰዎቹ ግን የሴሞ ደቡብ በኩል በዓረባ በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።” (1 ሳሙ 23:1924)

የስለታም ሰይፍ እርሻ ~ Helkath-hazzurim: የጦርነት አውድማ... ማለት ነው። የዳዊት ሠራዊት ከሳ ሠራዊት ጋር ፍልሚያ ያደረገበት ቦታ፥ ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ ያዘ፥ ሰይፉንም በወደረኛው ጎን ሻጠ፥ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም የስለታም ሰይፍ እርሻ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም በገባዖን ነው።” (2 ሳሙ 2:16)

የስቦቅ ~ Ishbak: የሽ በቅ፣ መሄድ ማለት ነው። አብርሃም ከኬጡራ ከወለዳቸው ልጆች አንዱ፥ እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት።” (ዘፍ 25:2)

የሪያ ~ Irijah: የሕያው ብርሃን፣ አምላክ ያየውማለት ነው። የሰሌምያ ልጅ፥ ... የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ ሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበረ እርሱም፦ ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው። (ኤር 37:1314)

የርሙት ~ Jarmuth: የራማ ከፍተኛማለት ነው።

1. በይሁዳ መስክ ያለ ከተማ፥ ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም፥ የርሙት” (ኢያ 15:35)

2. “የርሙትንና መሰምርያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰምርያዋን አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።” (ኢያ 21:29)

የሼብአብ ~ Jeshebeab

የሺ አብ፣ የብዙዎች አባት... ማለት ነው።

የአራተኛው የካህናት ምድብ አለቃ፥አሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥ (1 ዜና 24:13).

የሻያ ~ Jesaiah, Jeshaiah: የሺህ ያሕ፣ የሽዎች ጌታ፣ የብዙኃን አምላክ... ማለት ነው።

የሺህ እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       የሻያ / Jesaiah: የሐናንያ ልጅ፥ (1 ዜና 321)

       የሻያ / Jeshaiah:

1. የኤዶታ ልጅ፥ (1 ዜና 25:3)

2. የአልዓዛር ልጅ፥ (1 ዜና 26:25)

3. የጎቶልያ ልጅ፥ (ዕዝ 8:7)

4. ከሜራሪ ልጆች ወገን፥ (ዕዝ 8:19)

5. የብንያም ልጅ፥ (ነህ 11:7)

የቃምያ ~ Jekamiah: ያቆም ያሕ፣ ሕያው ቋሚ፣ ለጌታ የቆመ፣ በአምላክ የጸና፣ ሕዝበ እግዚአብሔር... ማለት ነው።

ቆመእና ያሕ (ያሕዌ) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሰሎም ልጅ፥ (1 ዜና 241)

የበራክዩ ~ Jeberechiah: ይባረክ ያሕ፣ ሕያው የባረከው እግዚአብሔር የባረከማለት ነው። በአካዝ ዘመን የነበረ፣ ዘካርያስ የተባለ ሰው አባት፥ (ኢሳ 8:2)

የብኒኤል ~ Jabneel: ያብነ ኤል፣ የጌታ መሠረት፣ የእግዚአብሔር ሥራ... ማለት ነው። (በአምላክ የታነጸ ተብሎም ይተረጎማል።)

ያብ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

. የይሁዳ ልጆች ነገድ ዕጣ ድንበር፥ (ኢያ 15:11)

. (ኢያ 19:33)

የብና ~ Jabneh: የአብነህ፣ የአምላክ፣ የእግዚአብሔር ሥራ... ማለት ነው። ንጻ ማለት ነው ተብሎ ይተረጎማል። [ተዛማጅ ስም- የብኒኤል]

የአብከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። የይሁዳ ንጉሥ ዖዝያን ከያዛቸው ከተሞች፥ (2 ዜና 266)

የተረገመ ~ Anathema: ለቅጣት የተለየ ማለት ነው። ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና። (1 ቆሮ 12:3 16:22 ገላ1:9)

የቲር ~ Jattir: የተከበረ፣ ክቡር፣ ግርማዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮቶር]

ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከተሰጡ የመማፀኛ ከተሞች፥ በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር” (ኢያ 1548)

የቴት ~ Jetheth: ምጽዋት፣ መስጠትማለት ነው። ከኤዶም አለቆች፥ የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥” (ዘፍ 36:40)

የትኒኤል ~ Jathniel: ያምላክ ስጦታማለት ነው። ከቆሬያውያን በበረኝነት ከተመደቡ፥ ከሜሱላም ልጆች አራተኛው፥ አራተኛው ትኒኤል አምስተኛው ኤላም፥ ... ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ” (1 ዜና 26:2)

የአራተኛው ክፍል ገዥ ~ Tetrarch: አራተኛ ገዥ ማለት ነው።

በአራተኛ ክፍል፥ ገዥ ለነበረ የሄሮድስ መጠሪያ፥ በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ (ማቴ 14:1 ሉቃ 3:119 9:7 ሐዋ 13:1)

የዑስ ~ Jeush: ሰብሳቢ፣ አደራጅ፣ ገጣጣሚማለት ነው።

1.የዔሳው ትልቁ ልጅ፥ አህሊባማም የዑስን፥ የዕላምን፥ ቆሬን ወለደች በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች ...” (ዘፍ 36:51418)

2. ቢልሐን ልጅ፥ የይዲኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ የቢልሐንም ልጆች የዑስ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ... ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ።” (1 ዜና 7:10)

3.የሰሜኢ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጆች ኢኢት፥ ዚዛ፥ የዑስ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ። (1 ዜና 23:1011)

4. የሮብዓም ልጅ፥ እርስዋም የዑስን፥ ሰማራያን፥ ዘሃምን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።” (2 ዜና 11:19)

የኢያቢስ ~ Jabesh: ደረቅማለት ነው።

1. የሰሎም አባት፥ የእስራኤል አምስተኛ ንጉሥ፥ ኢያቤስ ልጅ ሰሎም ተማማለበት፥ በይብልዓም መትቶ ገደለው፥ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። (2 ነገ 15:10 1314)

2. “የኢያቢስ ሽማግሌዎች። ወደ እስራኤል አገር ሁሉ መልክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቆይልን ከዚያም …” (1 ሳሙ 11:3 9 10)

የኢያዕር መንደሮች ~ Havoth-jair: የሠለጠነ መንደርማለት ነው።

1. የምናሴ ልጅ ኢያዕር፥ የወረራቸውን መንደሮች ሲሰ የሰጠው ስም፥ የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው።” (ዘኊ 32:41)

2. “የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን ምድር ሁሉ ወሰደ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ።” (ዘዳ 3:41)

የኤላ ~ Joelah: የላይ፣አምላክ የረዳውማለት ነው።የጌዶርዓዊው የይሮሃም ልጅ፥ የጌዶር ሰው የይሮሃም ልጆች የኤላ ዝባድያ (1 ዜና 12:7)

የዕላ ~ Jaala: የአላ፣ የላይ ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ፥ የሰሎሞን አገልጋዮች፥ የዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥” (ነህ 7:58)

የዕሡ ~ Jaasau: ሥራዬማለት ነው። እንግዳ ሚስቶች ካገቡ፥ መትናይ፥ የዕሡ ባኒ፥ ቢንዊ፥ ሰሜኢ፥” (ዕዝ 10:37)

የዕራ ~ Jarah: ማርማለት ነው። ከሳ ወገን፥ የሚካ ልጅ፥ አካዝም የዕራ ወለደ የዕራም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ ...” (1 ዜና 9:42)

የክርስቶስ ተቃዋሚ ~ Antichrist: ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን” (1 ዮሐ 2:1822 4:3 2 የሐ 1:7)

የዳን ሰፈር ~ Mahanehdan: የዳኝነት ድንኳን፣ የፍርድ ቤትማለት ነው። እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ካረፉባቸው ስፍራዎች፥ ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ እነሆም፥ ከቂርያትይዓሪም በስተ ኋላ ነው።” (መሣ 18:12)

የድላፍ ~ Jidlaph: ት፣ ማልቀስ ማለት ነው። የናኮር ልጅ፥ ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላፍ ባቱኤል ናቸው” (ዘፍ 22:22)

ዩልያ ~ Julia, Junia: ሉጫ ጸጉር ማለት ነው። ለፍሌጎንና ዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ... ሰላምታ አቅርቡልኝ። (ሐዋ 16:15)

       ዩልያ / Junia: ወጣት ማለት ነው። በሮም የነበረች ክርስቲያን፣ ጳውሎስ በሰላምታ ደብዳቤው የጠቀሳት፥ በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፥ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ፥ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ዩልያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16:7)

ዩልዮስ ~ Julius: ሉጫ ጸጉር ማለት ነው። ጳውሎስ ታስሮ ወደ ጣሊያን በተወሰደ ጊዜ፥ የነበረው የቄሳር መቶ አለቃ፥ ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንሄድ ዘንድ በተቈረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች ከአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚሉት ለመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጡአቸው (ሐዋ 27:13)

ዩሲምኤል ~ Jesimiel: የስመ ኤል፣ የኃያል ስም፣ የአምላክ ስም ማለት ነው። የሰሚ ልጅ፥ የሲሞናውያን አለቃ፥ ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ዩሲምኤል በናያስ፥” (1 ዜና 4:36)

ዩባል ~ Jubal: ተወርዋሪ፣ ተወንጫፊ ማለት ነው። የላሜሕ ልጅ፥ ከዓዳ የወለደው፥ የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።” (ዘፍ 4:21)

ዩባብ ~ Jobab: የአባ አባ፣ የአባባ፣ የአባት፣ የአብ፣ የጌታ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ኢዮባብ፣ ዮባብ] የዮቅጣን ልጅ፥ (ዘፍ 1029)

ዩዳሄ ~ Jehoiada: ያሕ ወዴ፣ በጌታ የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ፣ የእግዚአብሔር ወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን]

ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) እና ወደደ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የበናያስ አባት፥ (2 ሳሙ 20:23) (2 ሳሙ 8:18) (1 ዜና 18:17)

2. የአሮን ቤት አለቃ፥ (1 ዜና 12:27)

3. “...በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ ዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል። (ኤር 29:25-29 2 ነገ 25:18)

4. የፋሴሐ ልጅ፥ (ነህ 3:6)

ዩጣ ~ Juttah: የወጣ የተዘረጋማለት ነው። በተራራማው የይሁዳ አገር የነበረ ከተማ፥ ዩጣ እና ቀርሜሎስ፥ ያዋስኑታል፥ (አያ 15:55) ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ ኢይዝራኤል፥

ዪምና ~ Imnah, Jimnah: ያመነ፣ የታመነ... ማለት ነው። [ተዛማች ስሞች- ያሚን፣ ይምና]

እሙንከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዪምና / Imnah: የአሴር ልጅ፥ (1 ዜና 7:30)

. ይምና- (2 ዜና 31:14)

       ዪምና / Jimnah: (ዘኁ 26:44)

       ዪምና / Jimnah: ያመነ፣ የታመነ፣ ቀኝ እጅ ማለት ነው። የአሴር ልጅ፥ የአሴርም ልጆች ዪምና የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሪዓ፥ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር፥ መልኪኤል።” (ዘፍ 46:17)

ያሐት ~ Jahath: አሐቲ፣ አንድ፣ አንድ የሆነ፣ የተዋሐደ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢኢት ኢኤት]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. የሰሎሚት ልጅ፥ (1 ዜና 24:22)

. የሰሜኢ ልጅ፥ ኢኢት (1 ዜና 2310)

. የራያ ልጅ፥ ኢኤት (1 ዜና 4:2)

. የጌድሶን ልጅ፥ ከጌድሶን ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት ልጁ ዛማት (1

ዜና 6:20)

. የሜራሪ ልጅ፥ (2 ዜና 34:12)

ያሀጽ ~ Jahaz: ጠብ፣ ክርክር ማለት ነው። በአርኖን ወንዝ በስተሰሜን፥ በሞዓብና በአሞራውያን ድንበር፥ በዮርዳኖስ ማዶ የሚገኝ፥ ሴዎን የተሸነፈበት ከተማ፥ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽ መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። (ዘኊ 21:23 ዘዳ 2:32)

ያሕልኤል ~ Jahleel: ያሕለ ኤል፣ ለሕያው አምላክ፣ ለዘላለም ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ያሕጽኤል]

ያሕ እና ኤል ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የዛብሎን ልጅ፥ (ዘፍ 46:14)

ያህ ይርኤ ~ Jehovah-jireh: ሕያው አምላክ ያያል ማለት ነው። መሪያ ተራራ፥ አብርሃም ዋዕት ያቀረበበት ቦታ፥ አብርሃምም ያንን ቦታ ይርኤ ብሎ ....ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል።” (ዘፍ 22:14)

ዳይ ~ Jahdai: ያሕ ዲያ፣ ያሕ ውድ፣ የሕያው ውድ፣ የተወደደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ያሕ (ያሕዌ ሕያው) እና ውድከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። ያሕዳይ ልጆች ሬጌም፥ ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ፥ ሸዓፍ ነበሩ።” (1 ዜና 247)

ያሕጽኤል ~ Jahleel, Jahziel: ያሕ ል፣ ለሕያው አምላክ፣ ለዘላለም ጌታ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ያሕልኤል]

Jahleel, Jahziel- ያሕ ()’ እና ኤል ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ያሕጽኤል / Jahleel: የንፍታሌም ልጅ፥ (ዘፍ 4624)

       ያሕጽኤል / Jahziel: (1 ዜና 7:13)

       ያሕጽኤል / Jahzeel: ያሕ ኤል፣ ሕያው አምላክ፣ እግዚአብሔር ጸጋ፣ በአምላክ የተሰጠማለት ነው። ከአራቱ የንፍታሌም ልጆች የመጀመሪያው፥ የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም።” (ዜና 46:24)

ያሎን ~ Jalon: ሰኛ፣ ነዋማለት ነው። ከይሁዳ ነገድ የሆነ፥ የዕዝራ አራተኛና የመጨረሻ ልጅ፥ የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ።” (1 ዜና 4:17)

ያሚን ~ Jamin: ያሚን፣ ያምን፣ ያመነ፣ የተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ሐማ፣ ሄማን፣ ንዕማን፣ አሒማን፣ አማና፣ አሜን፣ አሞን፣ አኪመን፣ ዪምና፣ ይምና]

አመነከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የስምዖን ልጅ፥ (ዘኁ 2612)

2. የራም ልጅ፥ (1 ዜና 2:27)

3. ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን ሲባር ሕዝቡን ያስተምሩ ከነበ (ነህ 8:7)

ያሱብ ~ Jashub, Shear- jashub: ያስብ፣ ቸር ያሽብ፣ ጌታ ያስብ፣ በአምላክ የታሰበ ማለት ነው።

አሰበከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

[ትርጓሜውም ቅሬታ ይመለሳልማለት ነው  / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ያሱብ / Jashub:

1. የይሳኮር ልጅ፥ (1 ዜና 71)

2. እንግዶች ሚስቶቻ ቸውን ከተው፣ የባኒ ልጅ፥ (ዕዝ 10:29)

        ያሱብ / Shear - jashub: የኢሳይያስ ልጅ፥ (ኢሳ 7:3)

ያሳር ~ Jesher: ቀጥተኛ፣ እውነተኛማለት ነው። የካሌብ ልጅ፥ የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ ልጆቹዋም ያሳር ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ” (1 ዜና 2:18)

ያሪን ~ Jarib: ተቀናቃኝ፣ ጠላት፣ ምቀኛማለት ነው።

1. የስምዖን ልጅ፥ የስምዖንም ልጆች ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪን ዛራ፥ ሳኡል” (1 ዜና 4:24)

2. ካህናቱን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጡ ዕዝራ ከላካቸው አለቆች አንዱ፥ ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሸማያ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ያሪብ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ኤልናታን ላክሁ። (ዕዝ 8:16)

3. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ካገቡ፥ ...ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ፥ መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብ ጎዶልያስ።” (ዕዝ 10:18)

ያራሕ ~ Jerah: ጨረቃማለት ነው። የዮቅጣን አራተኛ ልጅ፥ ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥” (ዘፍ 10:27 1 ዜና 1:20)

ያሬሽያ ~ Jaresiah: ርስ ያሕ፣ ሕያው ያረሰው፣ አምላክ የመገበውማለት ነው። ብንያማዊ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች (1 ዜና 8:17)

ያሬድ ~ Jared: ድ፣ ይወርድ፣ የወረደ፣ ከላይ የመጣ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዬሬድ]

ወረደከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

የመላልኤል ልጅ ሆኖ፣ የሄኖክ አባት፥ (ዘፍ 515-20)

ያሻር ~ Jasher: ጻድቅማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ስብስብ ውስጥ ያልተጨመረ፥ ነገር ግን በኢያሱ መጽሐፍ የተጠቀሰ ቅዱስ መጽሐፍ፥ ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ ያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ...” (ኢያ 10:13)

ያሾቢአም ~ Jashobeam: መንደርተኛ፣ ነዋሪማለት ነው። በጺቅላግ ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ ቆርያውያን ሕልቃና፥ ይሺያ፥ አዛርኤል፥ ዮዛር፥ ያሾቢአም” (1 ዜና 12:6)

ያቂም ~ Jakim: ያቂም፣ ያቁም፣ የቆመ፣ የጸና፣ የበረታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]

አቆመከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. በኢየሩሳሌም የተቀመጡ በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የኤልፍዓል ልጆች፥ (1 ዜና 8:19)

2. ዳዊት ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓት ከፍሎ ከመደባቸው፥ (1 ዜና 2412)

ያቆብ ~ Jacob: ያቅብ፣ ያስቀር፣ ይጠብቅ፣ ያግድ፣ ይከልክል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ያዕቆባ፣ ያዕቆብ]

አቀበከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

[ትርጉሙ ተረከዝን ይይዛልማለት ነው / መቅቃ]

. የይስሐቅ ልጅ፥ ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት ያቆብንም።” (ዘፍ 31:1)

. ያዕቆብ (ዘፍ 2526)

ያቢ ~ Vophsi: ሀብታም ማለት ነው። የናቢ አባት፥ ከንፍታሌም ነገድ ያቢ ልጅ ናቢ” (ዘኊ 13:14)

ያባል ~ Jabal: ምንጭ ወንዝ፣ ጎርፍማለት ነው። የላሜሕ እና የዓዳ ልጅ፥ ዓዳም ያባል ወለደች እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ። (ዘፍ 4:20)

ያቤጽ ~ Jabez: ዘን፣ መከራ፣ ችግር፣ ጣርማለት ነው።

1. የይሁዳ ወገን የሆነ፥ ...እናቱም። በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው።” (1 ዜና 4:910)

2. የቦታ ስም፥ ያቤጽ የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ...” (1 ዜና 2:55)

ያቦቅ ~ Jabbok: ባዶ፣ ማድረግ ማለት ነው። በአሞን ልጆች ድንበር ያለ ወንዝ፥ በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ... እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥ (ኢያ 12:25)

ያትራይ ~ Jeaterai: የሌዊያዊው፥ የጌድሶን ልጅ፥ ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ” (1 ዜና 6:21)

ያኒም ~ Janum: ማንቀላፋት፣ እንቅልፍማለት ነው። በይሁዳ ተራራዎች ላይ ያለ ከተማ፥ አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ ያኒም ቤትታጱዋ፥ (ኢያ 15:53)

ያናይ ~ Jaanai: የአምላክ መልስ የሆነ፣ የተደረገማለት ነው። ከጋድ ነገድ አለቃ፥ አንደኛው ኢዮኤል፥ ሁለተኛው ሳፋም፥ ያናይ ሳፋጥ በበሳን ተቀመጡ። (1 ዜና 5:12)

ያኖዋ ~ Janoah: የኖህ፣ ኖኃዊ፣ ዕረፍትማለት ነው። የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ወርሮ ከወሰዳቸው፥ በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምን አገር ሁሉ ወሰደ ... (2 ነገ 15:29)

ያዕቃን ~ Jaakan:መክበብ ማለት ነው። የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ በዚያም አሮን ሞተ በዚያም ተቀበረ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። “(ዘዳ 10:6)

ያዕቆባ ~ Jaakobah: ያቅባህ፣ አቃቢ፣ ጠባቂ፣ ቆጣቢ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ያቆብ፣ ያዕቆብ]

አቀበከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። በወገኖቻቸው ላይ አለቆች የነበሩ፥ (1 ዜና 436)

ያዕቆብ ~ Jacob, James: ያቆብ፣ ያቅብ፣ ያስቀር፣ ይጠብቅ፣ ያግድ፣ ይከልክል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ያቆብ፣ ያዕቆባ]

አቀበከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

[ትርጉሙ ተረከዝን ይይዛልማለት ነው / መቅቃ]

የይስሐቅ ልጅ፥ ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር:” (ዘፍ 2526)

የማርያም እጮኛ፣ የዮሴፍ አባት፥ "ያዕቆብ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።" (ማቴ 1:16)

       ያዕቆብ / James: ሐዋርያው ያዕቆብ፥ ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብ ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።” (ማቴ4:21)

1. የዘብዎስና የሰሎሜ ልጅ፥ የዮሐንስ ታላቅ ወንድም፥ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብ ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። (ማቴ 20:20 27:56)

2. የጌታ ወንድም፥ ነገር ግን ከጌታ ወንድም ያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።” (ገላ 1:1819)

ያእዛንያ ~ Jaazaniah: ያዝን ያሕ፣ አምላክ ያዘነለት፣ እግዚአብሔር ጸሎቱን የሰማው ማለት ነው።

አዘነ እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኤርምያስ ልጅ፥ (ኤር 353)

2. የሆሻያ ልጅ፥ (ኤር 421)

3. የማዕካታዊው ልጅ፥ (2 ነገ 25:23)

4. የሳፋን ልጅ፥ (ሕዝ 8:11)

5. የዓዙርን ልጅ፥ (ሕዝ 11:1)

ያኪን ~ Jachin: አበረታችማለት ነው።

1. የስዖን አራተኛ ልጅ፥ የስዖን ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል (ዘፍ 46:10)

2. የሀያ አንደኛው ምድብ፥ የካህናትአለቃ፥ ሀያኛው ለኤዜቄል፥ ሀያ አንደኛው ያኪን ሀያ ሁለተኛው ለጋሙል (1 ዜና 24:17)

3. ከግዞት ከተመለሱ ካህናት አንዱ፥ ከካህናቱም ዮዳሄ፥ ዮአሪብ፥ ያኪን” (1 ዜና 9:10)

ያካን ~ Jachan: በጥባጭ ማለት ነው። ከሰባቱ የጋድ ነገድ አለቆች አንዱ፥ የአባቶቻቸውም ቤቶች ወንድሞች ሚካኤል፥ ሜሱላም፥ ሳባ፥ ዮራይ፥ ያካን ዙኤ፥ ኦቤድ ሰባት ነበሩ።” (1 ዜና 5:13)

ያዋን ~ Javan: አታላይማለት ነው።

1. የያፌት ልጅ፥ የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።” (ዘፍ 10:24)

2. ረባውያን ከተማ፥ ዌንዳንና ያዋን ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር ከኦሴል የተሠራ ብረትና ብርጕድ ቀረፋም ሸቀጥሽ ነበረ።” (ሕዝ 27:19)

ያዚዝ ~ Jaziz: ያዝዝ፣ ራ፣ ያስሂማለት ነው። አጋራዊው ሰው፥ የዳዊት እረኞች አለቃ፥ በመንጎቹም ላይ አጋራዊው ያዚዝ ሹም ነበረ። እነዚህ ሁሉ በንጉሡ በዳዊት ሀብት ላይ ሹሞች ነበሩ (1 ዜና 27:31)

ያዝኤል ~ Jaaziel: ያዘ ኤል፣ አምላክ የጠበቀው፣ በጌታ ያለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ያዝያ]

ያዘ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው

ዳዊት በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ከተናገራቸው የሌዋውያን ኣለቆች፥ (1 ዜና 1515)

ያዝያ ~ Jaaziah: ያዘ ያሕ፣ በጌታ የተያዘ፣ አምላክ የጠበቀው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ያዝኤል]

Jaaziah- ያዘ እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሜራሪ ወገን፥ (1 ዜና 242627) (1 ዜና 15:18)

ያዱአ ~ Jaddua: ውዱ፣ የተወደደ፣ ተወዳጅ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት አለቆ አንዱ፥ (ነህ 1021)

2. የዮናታን ልጅ፥ (ነህ 112:11 22)

ያዳ ~ Jada: ውድ፣ የተወደደ፣ ተወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳይ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

የኦናም ልጅ፥ (1 ዜና 2:28)

ያዳይ ~ Jadau: ውዱ፣ የተወደደ፣ ተወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የናባው ልጅ፥ (ዕዝ 10:43)

ያዶን ~ Jadon: የዳን፣ የዳኝ፣ ይዳኝ፣ ይፈርድ፣ ይበይን... ማለት ነው።

ዳኝከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን የተባበረ፣ ሜሮኖታዊው ሰው፥ (ነህ 3:7)

ያጉር ~ Jagur: አጉር፣ አገር፣ መኖሪያ ማለት ነው። የኤዶም አዋሳኝ፥ በደቡብ ጫፍ የሚገኝ የይሁዳ ከተማ፥ ቀብስኤል፥ ዔዴር፥ ያጉር ቂና፥ (ኢያ 15:22)

ያፊዓ፣ ያፍያ ~ Japhia: ግርዊ፣ መልካምማለት ነው።

1. ያሱ ጋር ለጦርነት ከተባበሩ፥ የኪሶ ንጉሥ፥ ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ... ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ። ወደ እኔ ውጡ፥ (ኢያ 10:3)

2. የዳዊት ልጅ፥ ያፍያ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።” (2 ሳሙ 5:16)

3. በዛብሎን ደቡባዊ ድንበር የሚገኝ ከተማ፥ ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓ ደረሰ ከዚያም በምሥራቅ ... ወጣ።” (ኢያ 19:12)

ያፌት ~ Japhet: ያፈት፣ ይፍታ፣ ይፈታ፣ የተፈታ፣ የተለቀቀ፣ የተስፋፋ... ማለት ነው።

ፈታ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍታህ፣ ይፍታሕ፣ ይፍታሕኤል፣ ዮፍታሔ፣ ፈታያ]

. የኖኅ ልጅ፥ (ዘፍ 532)

.እግዚአብሔርም ያፌት ያስፋ በሴምም ድንኳን ይደር ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን” (ዘፍ 927)

ያፍሌጥ ~ Japhlet: የዳነ የተፈታ፣ የወጣማለት ነው። በበረያ በኩል፥ የአሴር ወገን፥ ሔቤርም ያፍሌጥን፥ ሳሜንር፥ ... ሶላን ወለደ። (1 ዜና 7:3233)

ዬሕድያ ~ Jehdeiah: ያሕድ ያሕ፣ በጌታ የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ፣ የተመሰገነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ውደ እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሱባኤል ልጅ፥ (1 ዜና 2420)

ዬሬድ ~ Jered: ያሬድ፣ ከላይ የወረደ፣ ከላይ የመጣ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ያሬድ]

ወረደከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

. የጌዶር አባት፥ (1 ዜና 4:18)

.ያሬድ ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ” (1 ዜና 13)

ዬቴር ~ Jether, Ithra: ዬቴር፣ የተከበረ፣ ግርማዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮቶር]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዬቴር / Ithra: የይሁዳን ሠራዊት አለቃ፣ የይስማኤላዊ የአሜሳይ አባት፥ (2 ሳሙ 17:25)

ዬቴር / Jether:

1. የጌዴዎን ልጅ፥ (መሣ 820)

2. የሙሴ አማት፥ (ዘኁ 4:18)

3. “... የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ ዬቴር ልጅ አሜሳይን፥ በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር ደሙን በራሱ ላይ ይመልሰው። (1 ነገ 2:32)

4. የያዳ ልጅ፥ (1 ዜና 2:32)

5. የዕዝራ ልጅ፥ (1 ዜና 4:17)

6. የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ከተመረጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች፥ ከመኳንንቱ አለቆች፥ (1 ዜና 7:38)

ዬዳይ ~ Jahdo: ያሕዶ፣ ይሆዳ፣ ውህድ፣ ተዋሃደ፣ አንድ የሆነ... ማለት ነው።

ውህድከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የኢዬሳይ አባት፣ የቡዝ ልጅ፥ (1 ዜና 514)

ዬጽር ~ Jezer: ጾር፣ ጦር፣ ፈተና... ማለት ነው። የንፍታሌም ልጅ፥ (ዘፍ 4624)

ይሃሌልኤል ~ Jehalelel: ያሃልለ ኤል፣ ለሕያው አምላክ እልል፣ ሌሉያ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሃሌሉያ፣ ሂሌል፣ ማህለህ፣ ማህለት]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዓዛርያስ አባት፥ (2 ዜና 29:12)

2. የይሁዳ ወገን፥ (1 ዜና 416)

ይሑባ ~ Jehubbah: የተጠበቀማለት ነው። የአሴር ወገን፥ የሳሜር ልጅ፥ የሳሜርም ልጆች አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሑባ አራም ነበሩ።” (1 ዜና 7:34)

ይሁዲ ~ Jehudi: ይሁዲ፣ አይሁዳዊ፣ ውህድ፣ ተዋሃደ፣ አንድ የሆነ፣ ያይሁድ ወገን ማለት ነው።

ይሁዳከሚለው ስም የመጣ ስም ነው።

የናታንያ ልጅ፥ ወደ ባሮክ የተላከ፥ (ኤር 361421)

ይሁዳ ~ Juda, Judah, Judas, Jude, Judea: ዩዳ፣ ይሁዳ፣ ውህድ፣ ተዋሃደ፣ አንድ የሆነ፣ አይሁዳዊ... ማለት ነው። (ውድ፣ የተወደደ፣ የተመሰገነ፣የቀረበ ተብሎም ይተረጎ ማል)

ዋሐደከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ይሁዳ / Juda:

1. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የዮሴፍ ልጅ፥ (ሉቃ 3:30)

2. በጌታ የዘር ሐረግ፥ የያዕቆብ ልጅ፥ (ሉቃ 3:3334) የአይሁድ ዘር፥ ጌታችን ይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ …” (ዕብ 7:14) (ራእ 5:5 7:5)

3. የጌታ ወንድም በመባል የሚታወቀው፥ ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም ይሁዳ የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ ...” (ማር 6:3)

       ይሁዳ / Judah:

1. ከሊያ የተወለደው፣ የያዕቆብ ልጅ፥ ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው...” (ዘፍ 29:35)

2. “ይሁዳ ባያት ጊዜ ጋለሞታን መሰለችው ፊትዋን ተሸፍና ነበርና።” (ዘፍ 3815)

       ይሁዳ / Judas:

1. የያዕቆብ ልጅ፥ ይሁዳ (ማቴ 1:2 3)

2. ጌታን አሳልፎ የሰጠው፣ የስምዖን ልጅ የአስቆሮቱ፥ ይሁዳ (ዮሐ

6:71 13:2 26) (ሥራ 1:25)

3. ይሁዳ ወገን፥ (ሥራ 9:11)

4. ሐዋርያው በርስያን፥ (ሥራ 15:22 27 32)

       ይሁዳ / Jude: ሐዋርያው፥ የያዕቆብ ወንድም፥ ይሁዳ (ይሁ 1:1)

       ይሁዳ / Judea: በዮርዳኖስ በስተምዕራብ የፍልስጥኤም ምድር፣ ጌታ የተወለደበት ቦታ፥ (ማቴ 2:1 5)

ይሁዳ ካለች ከበኣል ~ Baale of Judah: ባለ ይሁዳ፣ በዓለ ይሁዳ፣ የአይሁድ በዓል፣ የይሁዳ ጌታ... ማለት ነው።

Baale of Judah- ባለ እና ይሁዳ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የእግዚአብሔር ታቦት ተቀምጦበት የነበረ፣ የቦታ ስም፥ (2 ሳሙ 62)

ይሁድ ~ Jehud: ማለት ነው። ከዳን ነገድ ከተሞች አንዱ፥ (ኢያ 19:45)

ይሒኤል ~ Jehiel: ያሕ ኤል፣ ሕያው አምላክ፣ ሕያው ኃይል፣ ዘላለማዊ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ይዑኤል፣ ይዒኤል]

ያሕ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ በዳዊት ከተሾሙ ሌዋውያን፥ (1 ዜና 15:18 20)

2. የኢዮሣፍጥ ልጅ፥ (2 ዜና 21:2)

3. በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን፥ ከእግዚአብሔር ቤት አለቆች አንዱ፥ (2 ዜና 35:8)

4. የለአዳን ልጅ፥ (1 ዜና 23:8)

5. የሐክሞኒ ልጅ፥ (1 ዜና 27:32)

6. የአብድዩ አባት፥ የኢዮአብ ልጅ፥ (ዕዝ 8:9)

7. የኤላም ልጅ፥ (ዕዝ 10:2) (ዕዝ 10:26)

8. የካሪም ልጅ፥ (ዕዝ 10:21)

. የንጉሥ ሕዝቅያስ መንግሥትን ለመመለስ ከተባበሩ አንዱ፣ ሌዊያዊው፥ ይዒኤል- (2 ዜና 29:14)

ይሒዝቅያ ~ Jehizkiah: ያሕ ሕዝቂያ፣ የአምላክ ኃይል፥ የሕያው ብርታት፣ የሕያው አምላክ ቃል... ማለት ነው።

ሕዝቅ እና ያሕ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሰሎም ልጅ፥ (2 ዜና 2812)

ይህዌህ ንሲ ~ Jehovah-nissi: ያሕ ነሥአ፣ አምላክ አነሣ፣ ሕያው ተሸከመ... ማለት ነው። ሙሴ፥ እስራኤል ከአማሌቃውያን ጋር ሲዋጉ፥ እጁን ዘርግቶ ኃይልን ባገኙበት ኮረብታ፥ ላቆመው መቅደስ የሰጠው ስም፥ ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም ይህዌህ ንሲ ብሎ ጠራው” (ዘጸ 17:15)

ይሆሐናን ~ Johanan, Jehohanan: የሐናን፣ የጌታ የሆነ፣ እግዚአብሔር የማረው፣ ያው ስጦታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮሐናን] ያሕ’ (ያሕዌ) እና አናን’ (ሐና) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ጸጋ ሰጭ ነው ማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የቤባይ ልጅ፥ (ዕዝ 10:28)

2. የጦብያ ልጅ፥ (ነህ 6:18)

3. በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ (ነህ 12:14)

4. “ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን ...” (ነህ 12:42)

. የሜሱላም ልጅ፥ ሰባተኛው ኤሊኤል፥ ስምንተኛው ዮሐናን (1 ዜና 12:12)

       ይሆሐናን / Jehohanan: አምላክ የሰጠውማለት ነው።

1. የመቅደሱ በር ጠባቂ የነበረ፥ አራተኛው የትኒኤል፥ አምስተኛው ኤላም፥ ስድስተኛው ይሆሐናን ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ። (1 ዜና 26:3)

2. የኢዮሣፍጥ ሹማምንት አንዱ፥ ከእርሱም በኋላ አለቃው ይሆሐናን ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ” (2 ዜና 17:15)

3. የይስማኤል አባት፥ በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ ይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ... ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። (2 ዜና 23:1)

4. እንግዳ ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ ከታዘዙ፥ ከቤባይ ልጆችም፤ ይሆሐናን ሐናንያ፥ ዘባይ፥ አጥላይ” (ዕዝ 10:28)

5. ካህን፥ ከአማርያ ይሆሐናን ከመሉኪ ዮናታን፥” (ነህ 12:14)

6. የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን ከተባበሩ ካህናት፥ (ነህ 12:42) “ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን መልክያ፥ ኤላም፥ ... አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ። (ነህ 12:14)

ይሆዓዳ ~ Jehoadah: ያሕ ዓድ፣ ሕያው ውድ፣ በጌታ የተወደደ፣ የአምላክ ወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬሕድያ፣ ዬዳይ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ያሕ (ሕያው) እና ውድ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የአካዝ ልጅ፥ (1 ዜና 836)

ይሙኤል ~ Jemuel: የአምላክ ቀንማለት ነው። የስሞዖን ትልቁ ልጅ፥ የስሞዖን ልጆች ይሙኤል ያሚን፥ ... ልጅ ሳኡል።” (ዘፍ 46:10 ዘጸ 6:15)

ይሚማ ~ Jemima: የዋህ፣ ሰላማዊማለት ነው። ከመከራው በኋላ ለኢዮብ ከተወለዱለት ሦስት ሴቶች፥ ትልቋ ልጅ፥ የመጀመሪያይቱንም ስም ይሚማ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ... ብሎ ሰየማቸው። (ኢዮ 42:14)

ይምራ ~ Imrah: ይምር፣ ይቅር ይልማለት ነው። ከአሴር ነገድ፥ የጾፋ ቤተሰብ፥ ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ፥ ይትራን፥ ብኤራ ነበሩ።” (1 ዜና 7:36)

ይምና ~ Imnah: ያመነ፣ የታመነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዪምና፣ ያሚን፣ ይምና]

Imnah- እሙንከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:- 1. የኤላ ልጅ፥ (1 ዜና 7: 5)

2. “የሌዋዊውም ይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና ...” (2 ዜና 31:14)

3. የአሴር ልጅ፥ (1 ዜና 7:30)

ይሳኮር ~ Issachar: ስጦታ፣ ካሳ ማለት ነው። የያዕቆብ ዘጠነኛ ልጅ፥ ልያም ባሪያዬን ለባሌ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ አለች ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው” (ዘፍ 30:18).

ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ፣ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን መግለጥ... ማለት ነው።

ሳቀከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። [ትርጉሙ ይስቃልማለት ነው /  መቅቃ]

የአብርሃም እና ሣራ ልጅ አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።” (ዘፍ 211-3) ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች። (ዘፍ 216)

ይስማኤላዊ ~ Israelite: እስማኤላውያን፣ የእስራኤል ወገን፣ የያቆብ ወገኖች፣ የአብርሃም ልጆች... ማለት ነው።

እስማኤልከሚለው ስም የመጣ የነገድ ስም ነው። የእስማኤል ወገን፥ (2 ሳሙ 1725) (1 ዜና 2:17)

ይስዓር ~ Izehar: ግልጽነት ማለት ነው። የቀዓት ልጅ፥ የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው እንበረም፥ ይስዓር ኬብሮን፥ ዑዝኤል።” (ዘኊ 3:19) ይረሕምኤል ~ Jerahmeel: ይምሕረ ኤል፣ መሓሪ አምላክማለት ነው።

1. የካሌብ ወንድም፥ የሔዝሮን ልጅ፥ ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች ይረሕምኤል አራም፥ ካልብ ነበሩ” (1 ዜና 2:92526)

2. የሌዋዊው፥ የቂስ ልጅ፥ ከቂስ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል የሙሲም ልጆች ሞሖሊ፥ ዔዳር፥ ኢያሪሙት” (1 ዜና 24:29)

3. “ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው” (ኤር 36:26)

ይሩበኣል ~ Jerubbaal: አየረ በዓልማለት ነው። ዎን የተጠራበት ስም፥ (መሣ 6:32 7:1 8:29 1 ሳሙ 12:11) ስለዚህም በዚያ ቀን፦ መሠዊያውን አፍርሶአልና በኣል ከእርሱ ጋር ይምዋገት ብሎ ጌዴዎንን፦ ይሩበኣል ብሎ ጠራው

ይሩኤል ~ Jeruel: አየረ ኤል፣ ታላቅ ገዥ፣ ታላቅ አምላክ፣ የሰማዩ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ይሪኤል]

አየረ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው።

የቦታ ስም፥ “... በሸለቆውም መጨረሻ ይሩኤል ምድረ በዳ ...” (2 ዜና 2016 20)

ይሪኤል ~ Jeriel: አየረ ኤል፣ ታላቅ ገዥ፣ ታላቅ አምላክ፣ የሰማዩ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ይሩኤል]

አየረ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። የቶላ ልጅ፥ (1 ዜና 7:2)

ይሪዖት ~ Jerioth: ከካሌብ ሚስቶች አንዷ፥ የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ይሪዖት ልጆች ወለደ ልጆቹዋም ... ነበሩ። (1 ዜና 2:18)

ይሬማይ ~ Jeremai: የራማዊ፣ የላይ ቤት፣ ሰማያዊማለት ነው። ከምርኮ ሲመለሱ፥ እንግዳ ሴቶችን አግብተው ከነበሩ እና ከፈቷቸው፥ የሐሱም ልጅ፥ ከሐሱም ልጆችም፤ መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ ምናሴ፥ ሰሜኢ።” (ዕዝ 10:33)

ይሬምት ~ Jeremoth: ያረ ሞት፣ አየረ ሞት፣ ታላቅ ሞት፣ ከፍተኛ... ሞት ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢያሪሙት፣ ይሬሞት]

አየረ እና ሞት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

. በሪዓ ልጅ፥ አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት (1 ዜና 8:14)

. የቤላ ልጅ፥ ኢያሪሙት- (1 ዜና 7:7)

የቤኬርም ልጅ፥ ኢያሪሙት- (1 ዜና 7:8)

የኤማን ልጅ፥ ኢያሪሙት - (1 ዜና 25:4)

የሙሲ ልጅ፥ ኢያሪሙት- (1 ዜና 23:23)

የሔማን ልጅ፥ ኢያሪሙት- (1 ዜና 25:22)

ይሬሞት ~ Jeremoth: የረ ሞት፣ አየረ ሞት፣ ታላቅ ሞት፣ ከፍተኛ ሞት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢያሪሙት፣ ይሬምት]

አየረ እና ሞት ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኤላ ልጅ፥ (ዕዝ 10:26 27)

2. የዛቱዕ ልጅ፥ (ዕዝ 10:27)

ይርጵኤል ~ Irpeel: የአምላክ ውስማለት ነው። ከብንያም ከተሞች አንዱ። ሬቄም፥ ይርጵኤል ተርአላ፥ ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡስ

ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ” (ኢያ 18:27)

ይሺያ ~ Ishiah, Ishijah, Isshiab, Jesiah: የሺህ ያሕ፣ ሺህ ሕያው፣ የብዙዎች ጌታ፣ የሽዎች አምላክ... ማለት ነው።

ሺህ እና ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች: -

       ይሺያ / Ishiah: የይዝረሕያ ልጅ፥ (1 ዜና 73)

       ይሺያ / Ishijah: በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን እንዲፈቱ ከተደረጉት፥ (ዕዝ 1031)

       ይሺያ / Isshiah:

1. የረዓብያ ልጅ፥ (1 ዜና 24:21-22)

2. የሚካ ወንድም፥ (1 ዜና 24:26)

       ይሺያ / Jesiah: የዑዝኤል ልጅ፥ የዑዝኤል ልጆች አለቃው ሚካ፥ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ” (1 ዜና 23:20)

1. የዳዊትን ሠራዊት በጺቅላግ ከተቀላቀሉ፥ ቆርያውያን ሕልቃና፥ ይሺያ አዛርኤል፥ ዮዛር፥ ያሾቢአም” (1 ዜና 12:6)

2. የዑዝኤል ልጅ፥ የዑዝኤል ልጆች አለቃው ሚካ፥ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።” (1 ዜና 23:20)

ይሽማ ~ Ishma: ይሽማ፣ እሽም፣ ስም፣ ዝና... ማለት ነው።

ስምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በይሁዳ የዘር ሐረግ፣ የኤጣ አባት ልጅ፥ (1 ዜና 43)

ይሽማያ ~ Ishmaiah: ሰማ ያሕ፣ አምላክ ሰማ፣ ሕያው ሰማ... ማለት ነው።

ሰማእና ያሕ’ (ያሕዌ ዋስ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በዳዊት ዘመን በዛብሎን አለቃ የነበረ፣ የአብድዩ ልጅ፥ (1 ዜና 27: 19)

ይሽምራይ ~ Ishmerai: የሺህ መሪ፣ የሽዎች መሪ፣ የብዙዎች መሪ፣ የሺህ አለቃ፣ የሽዎች ጠባቂ... ማለት ነው።

የበሪዓ ልጅ፥ (1 ዜና 8:18)

ይሽቢብኖብ ~ Ishbi-benob: በኔቦ የተቀመጠማለት ነው። ከራፋይ ወገን የሆነ፥ ሦስት መቶ ሰቅል ናስ የጦር መሣሪያ የታጠቀ፥ ከራፋይም ወገን የነበረው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ይገድል ዘንድ አሰበ ...አዲስም የጦር መሣሪያ ታጥቆ ነበር።” (2 ሳሙ 21:1617)

ይሽባ ~ Ishbah: የሺህ አባ፣ የሺህ አባት፣ የብዙዎች ጌታ፣ ታላቅ አባት፣ የተከበረ... ማለት ነው።

የኤሽትምዓ አባት፣ የዬቴር ልጅ፥ (1 ዜና 417)

ይሽዒ ~ Ishi: የሺህ፣ የሺ፣ ሺህ፣ ብዙ ሀብት ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የሶሳን አባት፣ የአፋይም ልጅ፥ (1 ዜና 2:31)

2. የዞሔት አባት፥ (1 ዜና 4:20)

3. ከስምዖን ልጆች አለቆች፥ (1 ዜና 4:42)

4. ከምናሴ ነገድ አለቆች፥ (1 ዜና 5:24)

ይሽጳ ~ Ispah: በራማለት ነው። ከብንያም ወገን፥ የበሪዓውያን አለቃ፥ ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች (1 ዜና 8:16)

ይቀብጽኤል ~ Jekabzeel: ያቅብ ዘኤል፣ በአምላክ የተጠበቀ፣ ለእግዚአብሔር የተለየ... ማለትነው።

Jekabzeel- ያቅብ እና ኤል ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ነው። በይሁዳ በስተደቡብ የነበረ ከተማ፥ (ነህ 1125)

ይቁቲኤል ~ Jekuthiel: ያምላክ ተስፈኞችማለት ነው። በይሁዳ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤል ወለደች ... (1 ዜና 4:18)

ይቃምያ ~ Jecamiah: ያቆም ያሕ፣ በሕያው የቆመ፣ በእግዚአብሔር የተመሠረተ... ማለት ነው።

ያቆመእና ያሕ (ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የምርኮኛው የኢኮንያን ልጅ፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።” (1 ዜና 3:8)

ይቅምዓም ~ Jakamean: ያቀመን፣ ያቆም፣ ያስነሳ፣ ያጸና... ማለት ነው። የኬብሮን ልጅ፥ (1 ዜና 23:19)

ይብለዓም ~ Ibleam: የብሉይ ሰዎች፣ የጥንት ሰዎች ማለት ነው። የምናሴ ከተማና የመንደሩ ሰዎች፥ ምናሴም የቤትሳንንና የመንደሮችዋን፥ የታዕናክንና የመንደሮችዋን፥ የዶርንና የመንደሮችዋን፥ ይብለዓምንና የመንደሮችዋን፥ የመጊዶንና የመንደሮችዋን ሰዎች አላወጣቸውም ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ።” (መሣ 1:27)

ይብሣም ~ Jibsam: አስደሳችማለት ነው። የይሳኮር ወገን፥ የቶላ ልጅ፥ የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም ሽሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሀያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ። (1 ዜና 7:2)

ይትላ ~ Jethlah: ቆጥ ሰገነት ማለት ነው። በዳን ግዛት ዳርቻ የነበረ ከተማ፥ ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ ኤሎን፥ ተምና፥” (ኢያ 19:42)

ይትማ ~ Ithmah: ጽኑ ማለት ነው። ከዳዊት ኃያላን አንዱ፥ መሐዋዊው ኤሊኤል፥ ይሪባይ፥ ዮሻዊያ፥ የኤልናዓም ልጆች፥ ሞዓባዊው ይትማ” (1 ዜና 11:46)

ይትረኃም ~ Ithream: ብዙ ሕዝብ የተትረፈረፈማለት ነው። ስድስተኛው፥ የዳዊት ልጆች፥ በኬብሮን ከተወለዱ፥ ስድስተኛውም የዳዊት ልጅ ሚስት የዔግላ ልጅ ይትረኃም ነበረ ...” (2 ሳሙ 3:5 1 ዜና 3:3)

ይትራን ~ Ithran: የተከበረ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮቶር] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የዲሶን ልጅ፥ (ዘፍ 3626) (1 ዜና 1:41)

2. ከአሴር ነገድ፣ የጾፋ ልጅ፥ (1 ዜና 7:30-40)

ይዑኤል ~ Jeiel, Jeuel: የኤል፣ የአምላክ፣ የጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ይሒኤል፣ ይዒኤል]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ይዑኤል / Jeiel: የአዶኒቃ ልጅ፥ (ዕዝ 8:13)

       ይዑኤል / Jeuel: የዛራ ልጅ፥ (1 ዜና 96)

ይዒኤል ~ Jehiel: ያሕ ኤል፣ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ይሒኤል፣ ይዑኤል]

ያሕ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል (1 ዜና 935)

2. የአሮኤራዊው የኮታ ልጅ፥ (1 ዜና 11:44)

3. የኤሊጸፋን ልጅ፥ (2 ዜና 29:14)

4. ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆን ካቀረቡ፥ (2 ዜና 35:8 9)

ይዓሪም ~ Jearim: ጫካ ማለት ነው። በይሁዳ ድንበር ላይ ያለ ተራራ፥ ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ ወደ ቤትሳሚስ ...” (ኢያ 15:10)

ይኮልያ ~ Jecholiah, Jecoliah: የቃለ ያሕ፣ የአምላክ ቃል፣ ቃለ ይወት፣ ሕገ እግዚአብሔር ማለትነው።

የቃለ እና ያሕ’(ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

       ይኮልያ / Jecholiah: የንጉሡ የዖዝያ እናት፥ (2 ነገ 15:2)

       ይኮልያ / Jecoliah: (2 ዜና 263)

ይዝረሕያ ~ Izrahiah, Jezrahiah: እዝር ያሕ፣ የሕያው ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ቤተሰብ... ማለት ነው።

ዘረ እና ያሕ’(ሕያው ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ይዝረሕያ / Izrahiah: የኦዚ ልጅ፥ (1 ዜና 73)

       ይዝረሕያ / Jezrahiah: በነህምያ ዘመን፣ የመዘምራኑ አለቃ፥ (ነህ 1242)

ይዝረሕያ ~ Jezrahiah: የዘረ ያሕ፣ የሕያው ዘር ማለት ነው። በነህምያ ዘመን ለኢየሩሳሌም ቅጥር ጥገና በተረገ ክብረ በዓል ከዘመሩ፥ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ ... ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ።” (ነህ 12:42)

ይዝራዊ ~ Izrahite: ዝራያት፣ ዘራውያን፣ የዕዝራ ወገኖች... ማለት ነው። ለአምስተኛው ወር አምስተኛው አለቃ ይዝራዊ ሸምሁት ነበረ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። (1 ዜና 278)

ይዝኤል ~ Jeziel: እዝ ኤል፣ የአምላክ እዝ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የጌታ ታዛዥ... ማለት ነው።

ያዝእና ኤልከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የዳዊትን ሠራዊት የተቀላቀለ፣ የሸማዓ ልጅ፥ (1 ዜና 123)

ይዝያ ~ Jeziah: ያዚ ያሕ፣ የሕያው ዘር ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ፥ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የፋሮስ ልጅ፥ ከእስራኤልም ከፋሮስ ልጆች፤ ራምያ፥ ይዝያ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያ፥ በናያስ” (ዕዝ 10:25)

ይዲኤል ~ Jediael: በአምላክ የታወቀማለት ነው።

1. የብንያም ልጅ፥ ያባቶች ቤት አለቃ፥ የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይዲኤል ሦስት ነበሩ።” (1 ዜና 7:611)

2. የሌዋዊው፥ የሜሱላም ሁለተኛ ልጅ፣ ሜሱላም ልጆች ነበሩት በኵሩ ዘካርያስ፥ ሁለተኛው ይዲኤል ሦስተኛው ዮዛባት (1 ዜና 26:12)

3. ከዳዊት ኃያላን አንዱ፥ የሽምሪ ልጅ፥ ይድኤል፥ የሽምሪ ልጅ ይድኤል ወንድሙም ይድኤል፥ ወንድሙም ቲዳዊው ዮሐ፥” (1 ዜና 11:45)

4. “ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል ሚካኤል፥ ... እርሱ ከዱ። (1 ዜና 12:20)

ይዲዳ ~ Jedidah: የውድ፣ የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬሕድያ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ይወድድከሚል ቃል የተገኘ ስም ነው። የኢዮስያስ እናት፣ የአዳያ ልጅ፥ (2 ነገ 22:1)

ይዲድያ ~ Jedidiah: ያሕ ውድ፣ የሕያው ወዳጅ፣ በጌታ የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ይወድድ እና ያሕ’(ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

እግዚአብሔር የንጉሥ ዳዊትን ልጅ፣ ሰሎሞንን፣ የጠራበት ስም፥ ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው። (2 ሳሙ 12 25)

ይዳላ ~ Idalah: ‘ዕድለ ያሕ፣ የአምላክ መታሰቢያማለት ነው። ከዛብሎን ከተሞች አንዱ፥ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ ቤተ ልሔም አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 19:15)

ይዳያ ~ Jedaiah: ያሕ፣ ሕያውን ወደድ፣ አምላክን ማመስገንማለት ነው።

1. የስምዖንውያን አለቃ፥ የሺምሪ ልጅ፥ የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ ይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ (1 ዜና 4:37)

2. ከባቢሎን ምርኮ መልስ፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን ከተባበሩ፥ በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አንጻር ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ አደሰ።” (ነህ 3:10)

3. ከካህናቱ ምድብ፥ የአንዱ አለቃ፥ ዮዳኤ፥ መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ዮዳኤ” (1 ዜና 24:7)

4. ዮዳሄ ከካህናቱም ዮዳሄ ዮአሪብ፥ ያኪን (1 ዜና 9:10)

ይድባሽ ~ Idbash: ጀግና ማለት ነው። ከይሁዳ ወገን፥ የኤጣም ልጅ፥ እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ።” (1 ዜና 4:3)

ይጋር ሠሀዱታ ~ Jegar-sahadutha: የቃል ኪዳን ምልክት፣ የምስክር ሐውልትማለት ነው። የያቆብ አማት፥ ላባ በእሱና በያዕቆብ መካከል ለተደረገ ቃልኪዳን፥ መታሰቢያ እንዲሆን ያስቀመጠው የድንጋይ ክምር፥ ላባም ይጋር ሠሀዱታ ብሎ ጠራት ያዕቆብም ገለዓድ አላት። (ዘፍ 31:47)

ይግአል ~ Igal: መርገም፥ አምላካዊ ቅጣትማለት ነው።

1. የይሳኮር ወገን የሆነ፥ ከሰላዮች አንዱ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል” (ዘኊ 13:7)

2. “የሱባ ሰው የናታን ልጅ ይግዓል ጋዳዊው” (2 ሳሙ 23:36)

ይግኣል ~ Igeal: በቀል፣ ቅጣትማለት ነው። ከይሁዳ ንጉሣዊ ወገን፥ የነህምያ ልጅ፥ የሴኬንያም ልጅ ሸማያ ነበረ። የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግኣል ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ።” (1 ዜና 3:22)

ይጽሐር ~ Jezoar: የሔላ ልጅ፥ ከአሴር ሚስቶች አንዷ፥ የሔላም ልጆች ዴሬት፥ ይጽሐር ኤትናን ናቸው።” (1 ዜና 4:7)

ይጽሪ ~ Izri: ይዝሬ፣ ዘሬ፣ ወገኔ... ማለት ነው።

በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ከነበሩ፥ (1 ዜና 2511)

ይፍታሕ ~ Jiphtah: ይፍታ የተፈታ፣ ያልታሰረ፣ የተለቀቀ፣ የተስፋፋ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍታህ፣ ያፌት፣ ይፍታሕኤል፣ ዮፍታሔ፣ ፈታያ] ከይሁዳ ነገድ ከተሞች፥ የቦታ ስም፥ (ኢያ 1543)

ይፍታሕኤል ~ Jiphthahel: ይፍታህ ኤል፣ በጌታ የተፈታ፣ በአምላክ ነጻ የወጣ፣ እግዚአብሔር የማረው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍታህ፣ ያፌት፣ ይፍታሕ፣ ዮፍታሔ፣ ፈታያ]

ይፍታህእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የቦታ ስም ነው። ዛብሎን እና የአሴር ልጆች በየወገኖቻቸው የርስታቸው ድንበር፥ (ኢያ 1914)

ይፍዴያ ~ Iphedeiah: ሕያው የፈታው፣ አምላክ ነጻ ያወጣው ማለት ነው። ከብንያም ነገድ፥ ከሻሻቅ ልጆች አንዱ፥ ሐናን፥ ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ ይፍዴያ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች” (1 ዜና 8:25)

ዮሐ ~ Joha: ዬሃ፣ የሕያው፣ የዘለለም፣ አምላካዊ... ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የብንያማዊው የበሪዓ ልጅ፥ (1 ዜና 8:16)

2. ከዳዊት ወታደሮች አንዱ፥ (1 ዜና 11:45)

ዮሐና ~ Joanna: የሐና፣ ጸጋ፣ ለጌታ የሆነ፣ ለአምላክ የተሰጠ፣ እግዚአብሔር የማረው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- የዮና]

የሐናከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።

. የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት፥ ዮሐና (ሉቃ 8:3) (ሉቃ 24:10)

. በጌታ የዘር ሐረግ፣ የሬስ ልጅ የዮናን (ሉቃ 327)

ዮሐናን ~ Johanan: የሐናን፣ ያሕ አናን፣ የጌታ የሆነ፣ የሕያው በረከት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ይሆሐናን]

ያሕ (ያሕዌ) እና ሐናን (አናን) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ጸጋ ሰጭ ነውማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች ዳዊት ወደነበረባት ወደ አምባይቱ ከመጡ፣ የሜሱላም ልጅ፥ (1 ዜና 12:12)

2. የዓዛርያስ ልጅ፥ የዓዛርያስ አባት፥ (1 ዜና 6:9 10) (2 ዜና 28:12)

3. የኤልዮዔናይ ልጅ፥ (1 ዜና 3:24)

4. የቃሬያ ልጅ፥ (ኤር 41:11-16)

5. የኢዮስያስ ልጅ፥ (1 ዜና 3:15)

6. ዳዊት ከሳ ሸሽቶ ወደ ነበረባት ወደ አምባይቱ ከመጡ፥ (1 ዜና 12:4)

7. ከኤፍሬም ልጆች አለቆች፥ (2 ዜና 28:12)

8. ከዕዝራ ጋር ከግዞት ከተመለሱ፣ የሃቃጣን ልጅ፥ (ዕዝ 8:12)

9. ከሌዋያን አለቆች አንዱ፣ የኤልያሴብ ልጅ፥ (ነህ 12:23)

. ይሆሐናን- (ነህ 6:18)

ዮሐንስ ~ John: የሕያዋን ዋስ፣ የሕያዋን ሕያው ዋስ፣ ዘላለማዊ አዳኝ... ማለት ነው።

ሕያውእና ዋስከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. መጥምቁ ዮሐንስ፥ (ማቴ 3:1-2)

2. የዘብዴዎስ ልጅ የያዕቆብ ወንድም፣ ሐዋርያው ዮሐንስ፥ (ማር 1:19)

3. “በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስ እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ” (ሥራ 4:6) (ሥራ 6:6)

4.የሐዋርያው የማርቆስ ሌላ ስም፥ “...ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ። (ሥራ 12:12 25 13:5 13 15:37)

ዮሲፍያ ~ Josiphiah: ያሰፍ ያሕ፣ ሕያው ያስፋ፣ አምላክ ያስፋፋው፣ እግዚአብሔር ያበዛውማለት ነው።

ያስፋ እና ያሕ (ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ከዕዝራ ጋር ከግዞት ከተመለሱ፣ የሰሎሚት ልጅ፥ (ዕዝ 8:10)

ዮሳ ~ Joses: የሺህ፣ ብዙ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮሴዕ]

. የጌታ ወንድም ተብሎ የተጠራ፥ ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?” (ማቴ 13:55 ማር 6:3)

. ዮሴዕ - (ሉቃ 3:29)

ዮሳቤት ~ Jehosheba: ሳባ፣ ያሕ ሰብ፣ የጌታ ሰው፣ ያው ሰው፣ የቃል ኪዳን ልጅማለት ነው።

Jehosheba- ያሕ (ሕያው) እና ሳባ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

የንጉሡ የኢዮራም ልጅ፥ የአካዝያስ እኅት ዮሳቤት (2 ነገ 112)

ዮሴዕ ~ Jose: የሺህ፣ የብዙ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮሳ]

. በጌታ የዘር የተጠቀሰ፥ የኤልዓዘር ልጅ ዮሴዕ (ሉቃ 3:29)

. ዮሳ - (ማቴ 13:55 ማር 6:3)

ዮሴፍ ~ Joses, Joseph: ያስፋ፣ ዘርን ያብዛ፣ ወገንን ያበርክት፣ ይስፋፋማለት ነው።

ሰፋከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

[ትርጉሙ ይጨምርማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዮሴፍ / Joses: ትውልዱ የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ፥ ባርናባስ በመባል የሚታወቀው፥ (ሥራ 4:36)

       ዮሴፍ / Joseph:

1. የያቆብ ልጅ፥ ስሙንም። እግዚአብሔር ሁለተኛ ወንድ ልጅን ይጨምርልኝ ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራችው (ዘፍ 30:23 24)

2. ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ ከላካቸው የይግአል ልጅ፥ (ዘኁ 13:7)

3. እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው ከነበሩ፥ (ዕዝ 10: 4142)

4. በነህምያ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ፥ (ነህ 12:1415)

5. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ (ሉቃ 3:30)

6. ሌላ በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የዮዳ ልጅ፥ (ሉቃ 3:26)

7. ሌላ በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የማታትዩ ልጅ፥ (ሉቃ 3:25)

8. የማርያም እጮኛ፥ (ሉቃ 3:23)

9. ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ የለመነ እና የቀበረ፥ (ሉቃ 23:50)

10. በርስያን የተባለው፥ (ሥራ 1:23)

ዮስካ ~ Iscah: ቀጣይ፣ የወደፊቱን የሚያይ አስተዋይማለት ነው። የአብርሃም ወንድም፣ የናኮር ልጅ፥ የሚልካ እኅት አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት ሐራንም የሚልካና ዮስካ አባት ነው።” (ዘፍ 11:29)

ዮራ ~ Jorah: የበልግ ዝናብ ማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ የዩራ ልጆች ይገኙበታል፥ ዮራ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት (ዕዝ 2:18)

ዮራም ~ Jorim: የራማ ከፍተኛ፣ የተከበረ ማለት ነው። በጌታ የዘር ሐረግ፥ የማጣት ልጅ፥ የዮሴዕ ልጅ፥ የኤልዓዘር ልጅ ዮራም ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥” (ሉቃ 3:29)

ዮርማሮዴቅ ~ Evil-merodach: መርዶ፣ መጥፎ ዜናማለት ነው። የንጉሥ ናቡከደነፆር ልጅና አልጋ ወራሽ፥ እንዲህም ... የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪንን ከወህኒ አወጣው” (2 ነገ 25:27 ኤር 52:3134)

ዮርዳኖስ ~ Jordan: ይወርድ ዳኝ፣ የወርደነ ዋስ፣ ከላይ የወረደ ዋስ፣ ከላይ የመጣ አዳኝ፣ ከላይ የመጣ ዳኛ ማለት ነው።

ወረደከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

[ወራጅ ማለት ነው /  መቅቃ]

. የፍኤም አገር ወንዝ፥ (ዘፍ 13:10)

.ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ ዮርዳኖስ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር” (ማቴ 3:5)

ዮሻብሒሴድ ~ Jushabhesed: መኖሪያ ቦታማለት ነው። የዘሩባቤል ልጅ፥ ሐሹባ፥ ኦሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ፥ ዮሻብሒሴድ አምስት ናቸው” (1 ዜና 3:20)

ዮሻዊያ ~ Joshaviah: ህይወት ሰጪማለት ነው። ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ መሐዋዊው ኤሊኤል፥ ይሪባይ፥ ዮሻዊያ የኤልናዓም ልጆች፥ ሞዓባዊው ይትማ፥” (1 ዜና 11:46)

ዮቂም ~ Jokim: ያሕ ቁም፣ አምላክ ያቆመው፣ በጌታ የጸና፣ ብርቱ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮአቂም]

ቆመከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

ከይሁዳ ነገድ፣ ከአሽቤዓ ቤት የሴሎ ልጅ፥ (1 ዜና 4:22)

ዮቅምዓም ~ Jokmeam: ዮቂም፣ ቁም፣ ያቆመው፣ የጸና፣ ብርቱ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮቂም]

የቆመከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በተራራማው በኤፍሬም አገር ካሉት የመማፀኛ ከተሞች፥ (1 ዜና 6:68)

ዮቅሳን ~ Jokshan: አብርሃም ከኬጡራ ከወለዳቸው ልጆች አንዱ፥ እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት። (ዘፍ 25:23 1 ዜና 1:32)

ዮቅንዓም ~ Jokneam: ያቀንያም፣ አምላክ ያቀናው፣ አምላክ ያቆመው፣ በጌታ የተሠራማለት ነው።

የቀናከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ከወጣ የርስታቸው ድንበር፥ (ኢያ 19:11)

ዮቅድዓም ~ Jokdeam: ያቀድም፣ የቀደመ ቀዳማዊ፣ ጥንታዊማለት ነው። በይሁዳ ተራሮች ላይ የነበረ ከተማ፥ ዮቅድዓም ዛኖዋሕ፥ ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና አሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:57)

ዮቅጣን ~ Joktan: ቅንጣት፣ ትንሽ፣ ቀጭንማለት ነው። ከዔቦር ሁለት ልጆች አንዱ፥ ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ... የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው (ዘፍ 10:25 1 ዜና 1:19)

ዮብ ~ Job: ያብ፣ ብ፣ የአብ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአምላክ የሆነ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢዮብ፣ ያሱብ ሺምሮ]

አብከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

. የይሳኮር ልጅ፥ የይሳኮርም ልጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ ዮብ ሺምሮን (ዘፍ 4613)

. ኢዮብ- (ሕዝ 14:14 20) ያሱብ ሺምሮ- (1 ዜና 7:1)

ዮቶር ~ Jether, Jethro: ክቡር፣ ግርማዊማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዬቴር] የሙሴ አማት ካህኑ ዮቶር ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር ተመለሰ...” (ዘጸ 4:18 18:1)

ዮና ~ Jona: ዋና፣ ዋኖስ፣ ርግብ፣ ትሑት፣ ቅን ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮናስ]

[ትርጉሙ ርግብማለት ነው / መቅቃ]

የስምዖን አባት፥ ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ። አንተ ዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው።(ዮሐ 1:42 43)

ዮና ልጅ ~ Bar-jona: በር ዮና፣ የዮና ልጅ፣ የየዋሁ ልጅ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዮና፣ ዮናስ]

Bar-jona- በር (ቤት ልጅ) እና ዮና ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

. ሐዋርያው ጴጥሮስ፥ (ማቴ 1617)

.ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ። አንተ ዮና ልጅ ስምዖን ነህ...” (ዮሐ 1:42)

ዮና ~ Janna: ፍካትማለት ነው። በጌታ የዘር ሐረግ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ የመልኪ አባት፥ ዮና ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ የማታትዩ ልጅ፥ የአሞጽ ልጅ፥ የናሆም ልጅ፥ የኤሲሊም ልጅ” (ሉቃ 3:25)

ዮናስ ~ Jonah, Jonas: ዋኖስ፣ ርግብ፣ የዋህ፣ ትሑት፣ ቅን ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮና]

[ትርጉሙ ርግብማለት ነው / መቅቃ]

       ዮናስ / Jonah: የአማቴ ልጅ፥ ነቢዩ ወደ ዮናስ (2 ነገ 14:25-27) (ዮናስ 1:1)

       ዮናስ / Jonas: ነቢዩ ዮናስ (ማቴ 12:39 40 41...)

ዮናታን ~ Jehonathan, Jonathan: ያሕ ናታን፣ ዮናታን፣ የአምላክ ስጦታ፣ የሕያው ሀብትማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮናትን] ያሕ’(ያሕዌ) እና ናታንከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[ትርጉሙ እግዚአብሔር ሰጥቷልማለት ነው / መቅቃ]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዮናታን / Jehonathan:

. በንጉሥ ዳዊት ልዩ ልዩ መዝገቦች ላይ የተሾመ፣ የዖዝያ ልጅ፥ (1 ዜና

2725)

. በዮአቂም ዘመን ከአባቶች ቤቶች አለቆች፣ ካህን፥ ፈልጣይ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን” (ነህ 12:18)

       ዮናታን / Jonathan:

1. ከሙሴ ወገን፣ የጌርሳም ልጅ፥ (መሣ 18:30)

2. የአብያታር ልጅ ዮናታን (2 ሳሙ1:23) (2 ሳሙ15:36 17:15-

21) (1 ነገ 1:42 43)

3. የዳዊት ወታደር፣ የአሳን ልጅ፥ (2 ሳሙ 23:3233)

4. የሻጌ ልጅ፥ (1 ዜና 11:34)

5. ከዓዲ ልጅ፥ (ዕዝ 8:6)

6. በዕዝራ ዘመን የነበረ ካህን፣ የአሣሄል ልጅ፥ (ዕዝ 10:15)

7. በዮአቂም ዘመን ከአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ከመሉኪ ወገን፥ (ነህ

12:14)

8. የቃሬያ ልጅ፥ (ኤር 40:8)

9. የዮአዳ ልጅ፥ (ነህ 12:11 22 23)

10. በቅጥሩ የእድሳት በዓል ላይ ጥሩንባ የሚነፋ፣ የሸማያ ልጅ፥ (ነህ

12:35)

ዮናትን ~ Jehonathan: ያሕ ናታን፣ ዮናታን፣ ያምላክ ስጦታ፣ የሕያው ሀብትማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮናታን]

ያሕ’(ያሕዌ) እና ናታን ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበሩ፥ (2 ዜና 17:8)

ዮናን ~ Joanna, Jonan: ያሐናን፣ ጸጋ ከጌታ የሆነ፣ ከአምላክ የተሰጠ፣ እግዚአብሔር የማረው ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮሐና]

የሐናከሚለው ቃል የተገኘ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

       ዮናን / Joanna: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የሬስ ልጅ፥ (ሉቃ 3 27)

. የኩዛ ሚስት፥ ዮሐና- (ሉቃ 8:3) ዮሐና- (ሉቃ 24:10)

      ዮናን / Jonan: (ሉቃ 3:30 31)

ዮአስ ~ Joah: አያ፣ የወንድምማለት ነው።

1. የአሳፍ ልጅ፥ የኤልያቄም መዝገብ ቤት ላፊ፥ የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ” (ኢሳ 36:31122)

2. ዮአክ ልጁ ዮአክ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ።” (1 ዜና 6:21)

3. ዖቤድኤዶም ልጅ፥ ኢዮአስ፥ እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት። በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥” (1 ዜና 26:4)

4. የዛማት ልጅ፥ ዩአክ፥ ሌዋውያኑም፥ ከቀዓት ልጆች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፥ ከሜራሪም ልጆች የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች የዛማት ልጅ ዩአክና ዩአክ ልጅ ዔድን፥” (2 ዜና 29:12)

5. የኢዮአካዝ ልጅ፥ ኢዮአክ፥ “... የኤዜልያስ ልጅ ሳፋን፥ የከተማይቱም አለቃ መዕሤያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የኢዮአካዝ ልጅ ኢዮአክ የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ ዘንድ ሰደዳቸው።” (2 ዜና 34:8)

ዮአሪብ ~ Jehoiarib: አምላክ የጠበቀውማለት ነው። ከሃያ አራቱ የካህናት ምድብ፥ የመጀመሪያው አለቃ፥ መጀመሪያውም ዕጣ ዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ” (1 ዜና 24:7)

ዮአቂም ~ Joiakim: ያሕ ቁም፣ ሕያው ያቆመው፣ አምላክ ያቆመው፣ በጌታ የጸና... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም]

ያሕ (ሕያው) እና ቆመ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የኢያሱ ልጅ፥ ሊቀ ካህኑ ዮአቂም (ነህ 12:10 12 እና 26)

ዮአኪን ~ Jehoiachin: ያሕ አቅን፣ ጌታ ያቃናው፣ የአምላክ ሥራ፣ በእግዚአብሔር የተሾመ፣ ሕያው ያከናወነው... ማለት ነው።

[ትርጉሙ እግዚአብሔር ያቆማልማለት ነው / መቅቃ]

በአባቱ እግር ተተክቶ ለመቶ ቀን በኢየሩሳሌም የነገሠ፣ የኢዮአቄም ልጅ፥ (2 ዜና 369)

ዮአዳ ~ Joaada: የወዳ፣ በሕያው የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬሕድያ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮዓዳን፣ ዮዳሄ]

ከኤልያሴብ ልጅ፣ ሊቀ ካህኑ ዮአዳ (ነህ 13:28)

ዮዓዳን ~ Jehoaddan: ያሕ ወደን፣ በጌታ የተወደደ፣ ለአምላክ የቀረበ፣ የሕያው ወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬሕድያ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዳሄ]

የዮአኪን ልጅ፣ የንጉሥ አሜስያስ እናት፥ (2 ነገ 142)

ዮእድ ~ Joed: እድ፣ የእጅ፣ ምስክርማለት ነው። ድያ ልጅ፥ የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ ዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። (ነህ 11:7)

ዮካል ~ Jucal: የቃ ማለት ነው። የሰሌምያ ልጅ፥ (ኤር 381) (ኤር 37:3)

ዮካልን ~ Jehucal: ያሕ ቃል፣ ሕያው ቃልማለት ነው። ሴዴቅያስ ወደ አምላኩ እንዲጸልይለት ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ከላካቸው ሁለት ሰዎች አንዱ፥ የሴለምያ ልጅ፥ ንጉሡም ሴዴቅያስ። ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልን ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።” (ኤር 37:3)

ዮካብድ ~ Jochebed: ያከብድ፣ ከፍ ያደርግ፣ ከባድ፣ የተከበረ... ማለት ነው።

[ትርጉሙ እግዚአብሔር ክብርማለት ነው  / መቅቃ]

የነቢዩ ሙሴ እናት፣ የሌዊ ልጅ፥ የእንበረም ሚስት፥ ዮካብድ (ዘኁ 2659)

ዮዘካር ~ Jozachar: የዝክር፣ የተዘከረ፣ የታሰበ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮዛባት]

ያሕ’(ያሕዌ ሕያው) እና ዝክር ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሰምዓት ልጅ፥ (2 ነገ 12:21)

ዮዛባት ~ Zabad: ጦታማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዮዘካር] የሞዓባዊቱ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት (2 ዜና 24:26)

ዮዛር ~ Joezer: የዘር፣ ወገን፣ ረዳትማለት ነው። ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ ቆርያዊው፥ ቆርያውያን ሕልቃና፥ ይሺያ፥ አዛርኤል፥ ዮዛር ያሾቢአም” (1 ዜና 12:6)

ዮዛባት ~ Jehozabad, Josabad, Jozabad, Jozabad:

የአምላክ ስጦታ፣ ጸጋ፣ ጥሎሽ፣ ማጫ ካሳ... ማለት ነው።

1. ከከሌዊያውያን በር ጠባቂዎች አንዱ፥ የዖቤኤዶም ልጅ፥ እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት ሦስተኛው ኢዮአስ፥ ... አምስተኛው ናትናኤል (1 ዜና 26:4)

2. የሰምዓት ልጅ፥ ባሪያዎቹም የሰምዓት ልጅ ዮዘካር የሾሜር ልጅ ዮዛባት መቱት፥ ሞተም በዳዊትም ከተማ ... ነገሠ (2 ነገ 12:21)

3. “ከእርሱም በኋላ ዮዛባት ከእርሱም ጋር ለሰልፍ የተዘጋጁ መቶ ሰማኒያ ሺህ ሰዎች ነበሩ።” (2 ዜና 17:18)

       ዮዛባት / Josabad: ጥሎሽ፣ ስጦታ፣ ሽልማት ማግኘትማለት ነው። ከብንያም ጦረኞች አንዱ፥ ከዳዊት ሠራዊት የተቀላቀለ፥ (1 ዜና 12:5) “ገድሮታዊው ዮዛባት ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ በዓልያ፥ ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥

       ዮዛባት / Jozabad: አምላክ ያበለጸገውማለት ነው።

1. ከጊልቦ ውጊያ በፊት፥ ወደ ዳዊት ከተቀላቀሉ የምናሴ ሠራዊት፥ የሺህ አለቃ፥ ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት ይዲኤል፥ ... ወደ እርሱ ከዱ (1 ዜና 12:20)

2. ሌላ፥ ከጊልቦ ውጊያ በፊት፥ ወደ ዳዊት ከተቀላቀሉ የምናሴ ሠራዊት፥ የሺህ አለቃ፥ ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት ኤሊሁ፥ ... ከዱ።” (1 ዜና 12:20)

3. በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን የነበረ፥ በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ ... ዮዛባት ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ። (2 ዜና 31:13)

4. የሌዋውያን አለቃ የነበረ፥ የሌዋውያኑም አለቆች ...ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ።” (2 ዜና 35:9)

5. በዕዝራ ዘመን የነበረ፥ የኢያሱ ልጅ፥ በአራተኛውም ቀን ... ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባት የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። (ዕዝ 8:33)

6. በግዞት እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ ካህናት፥ ፋስኩር ልጅ፥ ከፋስኩር ልጆችም፤ ኤልዮዔናይ፥ መዕሤያ፥ ይስማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባት ኤልዓሣ” (ዕዝ 10:22)

7. ሌላ፥ በግዞት እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ... ዮዛባት ሐናን፥ ፌልያ፥ ሌዋውያኑም ሕጉን ያስተውሉ ዘንድ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር ሕዝቡም በየስፍራቸው ቆመው ነበር።” (ነህ 8:7)

ዮያሪብ ~ Joiarib: ራባ መርባት፣ መራባት፣ ባዛትማለት ነው።

1. ከካህናት ምድብ ራቾች አንዱ፥ ከካህናቱ ዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፥ ያኪን” (ነህ 11:10)

2. የዘካርያስ ልጅ፥ የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ ዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።” (ነህ 11:5)

3. “መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማያ፥ ዮያሪብ ዮዳኤ፥” (ነህ 12:6)

4. “ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ... ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብ ወደ ኤልናታን ላክሁ። (ዕዝ 8:16)

ዮዲት ~ Judith: ዲት፣ ይሁዲት፣ ድ፣ ተዋደ፣ አንድ የሆነ፣ አይሁዳዊት... ማለት ነው። (ውዲት፣ ውድ፣ የተወደደች፣ የተፈቀረች ተብሎም ይተረጎማል።)

ይሁዲትከሚለው የመጣ ስም ነው። የኬጢያዊው የብኤሪ ልጅ፥ (ዘፍ 26:34)

ዮዳሄ ~ Jehoiada: እግዚአብሔር ያወቀው፣ የሕያው ወዳጅ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዩዳሄ፣ ዮዳሄ፣ ያሕዳይ፣ ያዱአ፣ ያዳ፣ ያዳይ፣ ዬሕድያ፣ ዬዳይ፣ ይሆዓዳ፣ ይዲዳ፣ ይዲድያ፣ ዮአዳ፣ ዮዓዳን]

ከዳዊት ወታደሮች፣ የበናያስ አባት፥ ዮዳሄ ልጅ በናያስ ...” (2 ሳሙ 8:18) (1 ዜና 18:17)

ዮግሊ ~ Jogli: መሰደድማለት ነው። የዳናውያን አለቃ፥ የቡቂ አባት፥

ከዳን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ዮግሊ ልጅ ቡቂ (ዘኊ 34:22)

ዮግብሃ ~ Jogbehah: ተኛ ታላቅ፣ የተከበረማለት ነው። በጋድ ነገድ የተገነባና የተመሸገ፥ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኝ ከተማ፥ ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃ” (ዘኊ 32:35)

ዮፍታሔ ~ Jephthae, Jephthah: የፌት፣ የፈታ፣ የተለቀቀ፣ ያልታሰረ፣ ፍት የተሰጠው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍታህ፣ ያፌት ይፍታሕ፣ ይፍታሕኤል፣ ፈታያ]

ይፍታ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የቃሉ ምንጭ ፈታ የሚለው ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ይከፍታልማለት ነው / መቅቃ]

       ዮፍታሔ / Jephthae: ሐዋርያው ጳውሎስ ለአይሁዳውያን በላከው ደብዳቤ የጠቀሰው፣ የገለዓድ ልጅ፥ ዮፍታሔ (ዕብ 1132)

       ዮፍታሔ / Jephthah: የገለዓድ ልጅ፥ (መሣ 111-33)

ዮፎኒ ~ Jephunneh: መንገዱ የቀናማለት ነው።

1. የኢያሱ ተባባሪ የነበረው፥ የካሌብ አባት፥ ከይሁዳ ነገድ ዮፎኒ ልጅ ካሌብ” (ዘኊ 13:6)

2. የዬቴር ልጅ፥ ዮሮኒ፥ የዬቴር ልጆች ዮሮኒ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ።” (1 ዜና 7:38)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ