ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ወልደአዴር ~
Benhadad:
ቤን ሀዳድ፣ የሀዳድ ልጅ፣ የተወደደ ልጅ፣ የአዴር ልጅ... ማለት ነው።
Benhadad- ‘ቤን’
(ልጅ) እና ‘አዳድ’
(ውድ) ከሚሉ ሁለት ቃላት የመጣ ስም ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።
የጠብሪሞን ልጅ የሶርያ ንጉሥ፥ (1 ነገ 15:18) ፣ (2 ነገ 8:7)
ወና ~
Halak:
‘እልቅ፣ ባዶ፣ ደልዳላ’ ማለት ነው። ኢያሱ ከያዛቸው ቦታዎች የደቡባዊ
ወሰን፥ “እስከ ሴይርም
ከሚያወጣው ወና ከሆነው ተራራ ጀምሮ
ከአርሞንዔም ተራራ
በታች በሊባኖስም
ሸለቆ ውስጥ
እስካለው እስከ
በኣልጋድ ድረስ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ይዞ መታቸው፥ ገደላቸውም።” (ኢያ
11:17፥ 12:7)
ወንያ ~
Vaniah:
‘ሕያው መና’ ማለት ነው። ከባኒ ልጆች አንዱ፥ “ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤልያሴብ፥ መታንያ፥” (ዕዝ 10:36)
ወንድም ~
Ahi:
አያ፣ ወንድም፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም- አኪ]
Ahi-
‘አያ’ ከሚለው ቃል የመጣ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
. የአብዲኤል ልጅ፥ “የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቃ የጉኒ ልጅ የአብዲኤል ልጅ ወንድም ነበረ” (1 ዜና 5፤15)
. የሳሜር
ልጅ፥ አኪ- (1 ዜና 7:34)
ወይን ~
Vine, Wine: ወይነ፣ ዋይን፣ ወይን ጠጅ... ማለት ነው።
‘ወይን’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
ወይን / Vine: “ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።” (ዘፍ 9:20)
ወይን / Wine:
. ወይን ከኖኅ ዘመን ጀምሮ የሚታወቅ ጥንታዊ መጠጥ ነው፥“ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።” (ዘፍ 9:20)
. የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም ያቀረበለት፥ “የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም
እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ እርሱም
የልዑል እግዚአብሔር
ካህን ነበረ።” (ዘፍ 14:18)
. “መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፥ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ
ወደ ታላቁ
ወደ እግዚአብሔር
ቍጣ መጥመቂያ
ጣለ።”
(ራእ 14:19)
ወደብ ~
Haven:
ሒዋን፣ የሕያው ቦታ፣ የዘላለማውያን መኖሪያ፣ መቅደስ... ማለት ነው። Haven- ‘ሒዋን’
ከሚለው የመጣ
ስም ነው።
የመርከብ ማረፊያ፥
(መዝ 107፡30)
ዋሻ ~
Den:
ደን፣ ጫካ፣ ዱር፣ ዋሻ... ማለት ነው።
Den-
‘ደን’ ከሚለው ቃል የተገኘ
ስም ነው።
. የአንበሳ ግልገሎች መተኛ፥“...በየዋሻቸውም ይተኛሉ” (መዝ 104፡ 22)
፣ (ዳን 6:16 ፣ 17)
. ባህታውያን መኖሪያ፥ “ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።” (ዕብ 11:38)
. ሽፍቶች የሚውሉበት፥ “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።” (ማቴ 21:13 ፣ ማር 11:17)
No comments:
Post a Comment