ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
አሐስባይ ~
Ahasbai:
አያ አሳቢ፣ አሳቢ ወንድም፣ ተቆርቋሪ ወዳጅ... ማለት ነው።
‘አያ’ እና ‘አሳቢ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የማዕካታዊው
ኤሌፋላት አባት፥
(2 ሳሙ 23:34)
አሐራ ~
Aharah:
‘እንደ ወንድም፣ ቀሪ ወንድም...’ ማለት ነው። የብንያም ሦስተኛ ልጅ፥ “ሦስተኛውንም አሐራን፥ አራተኛውንም ኖሐን፥ ... ራፋን ወለደ።” (1 ዜና 8:1)
አሐርሔል ~ Aharhel: አያ
ራሔል፣ የራሔል
ወንድም...
ማለት ነው።
የይሁዳ ወገን፥
የሃሩምንም ልጅ፥
“ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥
የሃሩምንም ልጅ
የአሐርሔልን ወገኖች
ወለደ።”
(1 ዜና 4:8)
አሐሽታሪን ~ Haahashtari: ‘መልእክተኛ’ ማለት ነው። የአሴር ወገን፥ “ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። ...” (1 ዜና 4:6)
አሑማይ ~ Ahumai: አያ ማይ፣ አያ ማዕይ፣ አያ ውኃ፣ ወንድም ውኃ፣ ውኃ ወዳጅ... ማለት ነው።
‘አያ’ እና ‘ማይ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የይሁዳ ወገን፥ የኢኤት ልጅ፥ (1 ዜና 4:2)
አሑዛም ~ Ahuzam: ‘ያዥ፣ ተያዥ፣ የተያዘ’
ማለት ነው። የነዕራ ልጅ፥ “ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። ...”
(1 ዜና 4:6)
አሒሑድ ~ Ahihud: አያ ውሕድ፣ ተባባሪ ወንድም፣ ማኅበርተኛ፣ የአንድነት ወዳጅ፣ ረዳት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
አሒሁድ]
‘አያ’ እና ‘ውሕድ’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አሒሑድ / Ahihud:
የኤሁድ ልጅ፥ (1
ዜና 8፡7)
አሒሁድ / Ahihud: ከአሴር ነገድ፣ የሴሌሚ ልጅ፥ (ዘኁ 34:27)
አሒሉድ ~
Ahilud:
አያ ውልድ፣ ልጅ ወንድም፣ የወንድም ልጅ... ማለት ነው።
1. የታሪክ ጸሐፊው፥ የኢዮሣፍጥ አባት፥ (2
ሳሙ 8:16፥ 20:24፤ 1
ነገ 4:3፤ 1 ዜባ18:15) “የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ የአሒሉድም ልጅ
ኢዮሣፍጥ ታሪክ
ጸሐፊ ነበረ”
2. በሰሎሞን ቤተሰብ ቀለብ ከሚሰፍሩ አሥራ ሁለት ሹማምንት አንዱ የሆነው የባዓና
አባት፥ (1 ነገ 4:12) “ከቤትሳን ጀምሮ
እስከ አቤልምሖላና
እስከ ዮቅምዓም ማዶ ድረስ በታዕናክና በመጊዶ በጸርታንም አጠገብ በኢይዝራኤል በታች ባለው በቤትሳን ሁሉ የአሒሉድ ልጅ በዓና ነበረ”
አሒማን ~ Ahiman: አያ አምን፣ የታመነ ወንድም፣ ሰላማዊ ጓደኛ፣ መልካም ወዳጅ፣ታማኝ ወንድም... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:-
ሐማ፣ ሄማን፣ አማና፣ አሜን፣ አሞን፣ አኪመን፣ ያሚን]
‘አያ’ እና ‘አመነ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል፣ የቤተ መቅደስ ጠባቂ የነበረ፥ (1 ዜና
9:17)
2. የዔናቅ ልጅ፥ (ዘኁ 13፡22)
አሂሳሚክ ~ Ahisamach: ‘አያ ኃያል፣ ብርቱ ወንድም’ ማለት ነው።ከመገናኛው ድንኳን
እና ከቃል
ኪዳኑ አገልጋዮች፥
ከዳን ነገድ፥
የኤልያብ አባት፥
“እኔም እነሆ ከእርሱ
ጋር ከዳን
ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ ...” (ዘጸ 31:6፤ 35:34፤ 38:23)
አሒሳር ~ Ahishar:
‘የዘማሪ ወንድም’
ማለት ነው።
በንጉሥ ሰሎሞን
ቤተመንግሥት ደጅ
አሳላፊ የነበረ፥
“አሒሳርም የቤት
አዛዥ፥ የዓብዳም
ልጅ አዶኒራም
አስገባሪ ነበረ።” (1 ነገ 4:6)
አሒናዳብ ~ Ahinadab: ‘አያ የተከበረ፣
ታላቅ ወንድም...’
ማለት ነው።
ለሰሎሞን ቤተመንግሥት ቀለብ ከሚሰፍሩ አሥራ ሁለት ሹማምንት አንዱ፥ የዒዶ ልጅ፥
“በመሃናይም የዒዶ ልጅ
አሒናዳብ”
(1 ነገ 4:14)
አሒዔዝር ~
Ahiezer:
አያ ዘር፣ ወንድም ወገን፣ ረዳት ወንድም፣ አጋዥ፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪዔዘር]
‘አያ’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. በጺቅላግ ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ አለቃቸው
አሒዔዝር ፥
(1 ዜና 12:3)
2. ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የወጡ፥ ከየነገዱ አንድ ሰው፥ ከዳን ነገድ፣ የአሚሳዳይ ልጅ፥
(ዘኁ 2:25፤10:25)
አሒያ ~ Ahian: አያ
ወይን፣ ወይን
ወዳጅ፣ ባለ ወይን... ማለት
ነው። የሸሚዳ
ልጅ፥ “የሸሚዳም ልጆች አሒያን፥
ሴኬም፥ ሊቅሒ፥
አኒዓም ነበሩ።” (1 ዜና7:19)
አሒዮ ~
Ahio:
አሒዮ፣ አያዋ፣ ወንድሜ፣ ወዳጀ፣ ጓደኛዬ፣ አለኝታዬ... ማለት ነው።
‘አያዋ’ ከሚለው ቃል የመጣ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. ከዳዊትጋር በይሁዳ ካለች ከበኣል ተነሥተው በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ
በእግዚአብሔር ስም
የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ካመጡ፥ የአሚናዳብ ልጅ፥ (1 ዜና 13:7) ፥ (2
ሳሙ 6:3፣ 4)
2. የበሪዓ ልጅ፥ “አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥” (1 ዜና 8:14)
3. የይዒኤል ልጅ፥ (1 ዜና 8:31፥ 9:37)
አህሊባማ ~
Aholibamah:
‘የአብ ታላቅ ማደሪያ’ ማለት ነው። ከሦስቱ የዔሳው
ሚስቶች አንዷ፥
“ዔሳው ከከነዓን ልጆች
ሚስቶችን አገባ
የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን አህሊባማን፥” (ዘፍ
36:2፣26)
አሕላብ ~
Ahlab:
‘እልብ’ ማለት ነው። የአሴር ከተማ፥ነገር
ግን ቀደም
ብለው በዚያ
የነበሩ ከነናውያን
አልተፈናቀሉም፥ “አሴርም የዓኮንና
የሲዶንን የአሕላብንም የአክዚብንም የሒልባንም የአፌቅንም
የረአብንም ሰዎች
አላወጣቸውም።”
(መሣ 1:31)
አሕላይ ~ Ahlai: ‘ጌጣጌጥ’
ማለት ነው።
ከዳዊት ኃያላን
አንዱ፥ የሶሳን
ልጅ፥ “አፋይምም ልጅ ይሽዒ ... የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ።” (1 ዜና 2:31፣35)
አሕምታ ~
Achmetha:
አያሞት፣ የሞት ወንድም... ማለት ነው። በሜዶን አውራጃ
የሚገኝ የከተማ
ስም፥ “በሜዶን አውራጃ
ባለው አሕምታ በሚባል ከተማ በንጉሡ ቤት ውስጥ አንድ ጥቅልል ተገኘ፥ ... ለመታሰቢያ ተጽፎ ነበር” (ዕዝ 6:2)
አሕሻዊሮስ ~ Ahasuerus:
‘አያ የሽ ራስ፣ አያ መስፍን፣ አያ አለቃ’
ማለት ነው።
የዳርዮስ አባት፥
የሜዶን ንጉሥ፥
“በከለዳውያን መንግሥት ላይ
በነገሠ፥ ከሜዶን
ዘር በነበረ
በአሕሻዊሮስ ልጅ በዳርዮስ በመጀመሪያ ዓመት፥” (ዳን 9:1)
አኅዋ ~ Ahava: ውኃ
ማለት ነው።
የቦታ ስም፥
ከባቢሎን ምርኮ
ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ፥
ዕዝራ ሕዝቡን
ያሰባሰበበት የወንዝ
ዳርቻ፥ “ወደ አኅዋም
ወደሚፈስስ ወንዝ
ሰበሰብኋቸው፥ በዚያም
ሦስት ቀን
ሰፈርን ...” (ዕዝ 8:15)
አሖዋ ~
Ahoah:
ወዳጅ፣ ወንድም... ማለት ነው። የብንያም ወገን፥ ፥ “ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም።” (1 ዜና 8:4)
አላሔ ~ Halah: የአሦር
ንጉሥ እስራኤላውያንን ማርኮ
ያፈለሰበት ከተማ፥
“በሆሴዕ በዘጠኝኛው ዓመት
... በአላሔና በአቦር
በጎዛንም ወንዝ
በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።”
(2 ነገ 17:6፥ 18:11፤ 1 ዜና 5:26)
አላሜሌክ ~
Alammelech:
አላመሌክ፣ ዓለመ መልአክ፣ የዓለም መልአክ፣ የዓለም ጌታ፣ የሁሉ ገዥ... ማለት ነው።
‘ዓለም’ እና ‘መልአክ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። የአሴር ልጆች ነገድ ድንበር፥ አላሜሌክ፥ (ኢያ 19፡26)
አልሞን ~ Almon: ‘ስውር’
ማለት ነው።
ከብንያም የተቀደሱ
ከተሞች አንዱ፥
“አናቶትንና መሰምርያዋን፥ አልሞንንና
መሰምርያዋን ...” (ኢያ 21:18)
አልንጦን ~ Olympas: ‘ሰማያዊ፣ ምድረ ገነት’ ማለት ነው። በሮም
የነበረ ክርስቲያን፥ “ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ከእነርሱ ጋር ላሉ ቅዱሳን
ሁሉ ሰላምታ
አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:15)
አልዓዛር ~ Eleazar: ኤል አዛር፣ የጌታ ወገን፣ የተባረከ፣ የተቀደሰ፣ የአምላክ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ዓዛርኤል፣ አዛርኤል፣ ዓዛርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤሊዔዘር፣ ኤልዓዘር፣ ኤዝርኤል]
‘ኤል’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር
ረዳቴ ነው
ማለት ነው
/ መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አልዓዛር / Eleazar:
1. የነቢዩ ሙሴ ወንድም፣ የአሮን ልጅ፥ (ዘጸ 6፡23)፣ (ዘኁ 3:4)፣ (ዘኁ 26:3)
2. በኮረብታው ላይ የነበረው የአሚናዳብ ልጅ፥ (1 ሳሙ 7:1)
3. ከዳዊት ኃያላን ሠራዊት አንዱ፣ የዱዲ ልጅ፥ (2 ሳሙ 23:9፣ 1 ዜና
11:12)
4. የሜራሪ ወገን፣ የሞሖሊና ልጅ፥ (1
ዜና 23:21 ፣ 22)
፣ (ሩት 24:28)
5. በነህምያ ዘመን የነበረ ካህን፥ (ነህ 12:42)
6. በባቢሎን በግዞት ዘመን፥ እንግዶች ሚስቶችን ካገቡ፥ (ዕዝ 10:25)
7. የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፥
(ዕዝ 8:33)
8. በጌታ የዘር ሐረግ የተገለጸው፣ የኤልዩድ ልጅ፥ (ማቴ 1:15)
አልዓዛር / Eliezar:
1. የብንያም ወገን የቤኬር ልጅ፥ (1 ዜና 7:8)
2. የነቢዩ ሙሴ ሁለተኛ ልጅ፥ (ዘጸ 18:4፣ 1 ዜና 23:15 ፣ 17፣
26:25)
3. ዳዊት፥ የእስራኤል ሽማግሌዎችና፥
የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ካመጡ ካህናት፥ (1 ዜና 15:24)
4. በእስራኤልም ነገዶች ላይ አለቃ የነበረ፥ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፥ (1 ዜና 27:16)
5. የመሪሳ ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር፥ (2 ዜና 20:37)
6. በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች
አለቆች፥ (ዕዝ 8:16)
7. በዕዝራ ዘመን ከባቢሎን ሲወጡ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የኢያሱ ልጅ፥ (ዕዝ 10:18 ፣ 23፣ 31)
8. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰው፣ የዮራም ልጅ፥ (ሉቃ 3:29)
በአብርሃም ቤት አገልጋይ የነበረ የደማስቆ ሰው፥ “አብራምም፦ ...
የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ።” (ዘፍ 15፡2፣3)
አልዓዛር / Lazarus: ለዘር
1. በሞተ በሦስተኛው ቀን ጌታ ያስነሣው፥ የማርያምና የማርታ ወንድም፥ (ኢያ 11:1)
2. በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት መሆኑን ጌታ ሲያስተምራቸው የጠቀሰው፥
(ሉቃ 16:19-31)
አልፋ ~
Alpha:
አልፋ፣ አላፊ፣ ቀዳማዊ፣ ጥንታዊ፣ ፊተኛ፣ አንደኛ፣ መጀመሪያ... ማለት ነው። [የግሪክ ቋንቋ የመጀመሪያ ፊደል ስም / መቅቃ]
ከጌታ ኢየሱስ
መጠሪያ ስሞች
አንዱ፥ “ያለውና የነበረው
የሚመጣውም ሁሉንም
የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” (ራእ 1:8
፣ 11 ፣ 21:6 ፣ 22፣ 13) ፣ እግዚአብሔር አምላክ እራሱን ያሳወቀበት ስም፥ “ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛው በኋላኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ” (ኢሳ 41:4፣ 44:6)
አሎን ~ Allon: ‘ኃያል፣ ጠንካራ’ ማለት ነው። የይዳያ ልጅ፥ “የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ”
(1 ዘፍ 4:37)
አሎንባኩት ~ Allon-bachuth:
‘የማልቀሻ ዛፍ፣ኮምበል ዛፍ’ ማለት ነው። የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ የተቀበረችበት ቦታ፥ “የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከአድባር ዛፍ በታች ተቀበረች ስሙም አሎንባኩት ተብሎ ተጠራ” (ዘፍ 35:8)
አሚ ~ Ami: ‘ሕዝቤ’ ማለት ነው። ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ፥ “የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ ... የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።”
(ዕዝ 2:57)
አሚሳዳይ ~ Ammishaddai: አሚ ሻዳይ፣ ኃያል ሕዝብ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር... ማለት ነው።
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴ እስራኤልን ሲመድብ የተጠቀሰ፥ ከዳን ነገድ የአኪዔዘር
አባት፥ (ዘኁ 1:12)
አሚናዳብ ~ Abinadab (Amminadab, aminadab):
የተከበረ፣ አንቱ የተባለ... ማለት ነው።
1. ታቦቱ ለሀያ ዓመት የቆየበት፥ የቂርያትይዓሪው ሰው፥ ሌዋዊው፥ አሚናዳብ፥ “የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ፥ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት የእግዚአብሔርም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት” (1 ሳሙ 7:1፣2፤ 1 ዜና 13:7)
2. የእሴይ ሁለተኛ ልጅ፥ “እሴይም አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት አሳለፈው እርሱም፦ ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም አለ” (1 ሳሙ 16:8፤ 17:13)
3. በጊልቦዓ ተራራ ላይ፥ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሲዋጉ ከወደቁ አንዱ፥ የሳኦል ልጅ፥ “ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው
ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን
ልጆች ዮናታንንና
አሚናዳብን ሜልኪሳንም
ገደሉ።”
(1 ሳሙ 31:2)
4. ከሰሎሞን አለቆች፥ የአንደኛው አባት፥ “በዶር አገር ዳርቻ ሁሉ የአሚናዳብ ልጅ፥ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈትን አግብቶ ነበር” (1 ነገ 4:11)
አሚጣል ~ Hamutal: ‘የወላፈን መከላከያ፣ ጥላ’ ማለት ነው። የልብና
ሰው የኤርሚያስ ልጅ፥ የንጉሥ ኢዮአክስ እናት፥ “ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት
ዓመት ጕልማሳ
ነበረ በኢየሩሳሌምም
ሦስት ወር
ነገሠ። እናቱም
አሚጣል ትባል ነበር፥ ... (2
ነገ 23:31፥ 24:18፤ ኤር 52:1)
አማሌቅ ~ Amalek, Amalekites: አምላእክ፣ አምላኪ፣ የሚያመልክ፣ አምልኮት ያለው... ማለት ነው።
‘መለከ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አማሌቅ / Amalek:
1. የኤልፋዝ ልጅ፥ (1 ዜና 1:36)
2. የዓዳ ልጅ፥ (ዘፍ 36:16)
አማሌቅ አገር / Amalekites:
አማሌቅ አውያን
1. “ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴሶን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ።”
(ዘፍ 14፡7)
2. “በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል ...” (ዘኁ 13:29፣ 1
ሳሙ 15:7)
አማልቶያስ ቂራስ ~ Keren-happuch: ‘ሙዳይ፣ መሶበ ወርቅ’ ማለት ነው። የኢዮብ ሴት ልጅ፥ “የመጀመሪያይቱንም ስም ይሚማ፥ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ስም አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው”
(ኢዮ 42:14)
አማሢ ~
Amasai, Amzi: ዐማጺ፣ ያመፀ፣ የሸፈተ፣ አልታዘዝም ያለ፣ ትዕቢተኛ፣ ትምክህተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ አሜስያስ፣ አሞጽ]
‘ዐመፀ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አማሢ / Amasai:
1. የሕልቃና ልጅ፥ “የሕልቃናም ልጆች አማሢ፥ አኪሞት።” (1 ዜና 6፡ 25፣35)
2. የመሐት አባት፥ (2 ዜና 29:12)
. አማሳይ ፥ (1 ዜና 12:18)
. ዓማሣይ፥ (1 ዜና 15:24)
አማሲ / Amzi:
1. የዘካርያስ ልጅ፣ ካህኑ አማሲ፥ (ነህ 11:12)
2. ከሜራሪ ወገን የሆነ፣ ሌዋዊው አማሲ፥ (1 ዜና 6:46)
አማሳይ ~
Amasai:
ዐማፂ፣ ያመፀ፣ የሸፈተ፣ አልታዘዝም ያለ፣ ትዕቢተኛ፣ ትምክትኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አማሢ፣ አማሲ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ አሜስያስ፣ አሞጽ]
‘ዐመፀ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አማሳይ / Amasai: ዳዊት ወደ ነበረባት ወደ አምባይቱ ከብንያምና ከይሁዳ ወገን ከመጡ፥ (1
ዜና 12:18)
ዓማሣይ / Amasai:
በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ከነበሩ ካህናት አንዱ፥ (1
ዜና 15:24)
አማስያ ~ Amashai: አማሽ፣ ዐማፂ፣ የሚያምስ፣ የሸፈተ፣ አልታዘዝም ያለ፣ ትዕቢተኛ፣ ትምክህትኛ፣ በጥባጭ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አማሢ፣ አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ አሜስያስ፣ አሞጽ]
‘አማሽ’
ከሚለው ቃል
የተገኝ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አማስያ / Amashai:
በኢየሩሳሌም ከተቀመጡት የአገሩ አለቆች፥ የቤቱንም ሥራ ከሠሩ፥ የኤዝርኤል ልጅ፥ (ነህ 11:13)
ዓማስያ / Amashai:
በኢዮሣፍጥ መንግሥት
ዘመን በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ የዝክሪ ልጅ፥ (2
ዜና 17:16)
አማርያ ~
Amariah:
አማረ ያሕ፣ የተማረ፣ አምላክ ይቅር ያለው፣ ምሕረት ያገኘ፣ መሐሪ አምላክ ማለት ነው።
‘ማረ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የሌዊ ልጆች፥ የአኪጦብ አባት፥ “መራዮት አማርያን ወለደ” (1 ዜና 6፡ 7፣52)
2. የእግዚአብሔር ሰው ከሙሴ ልጆች ከሌዊ ነገድ፥ (1 ዜና 23:19፣24:23)
3. የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ከሌዋውያንና ከካህናት ከእስራኤልም የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ በእግዚአብሔር ስም ፍርድን እንዲፈርዱ ክርክርንም እንዲቈርጡ
በኢየሩሳሌም የሾመው፥
(2 ዜና 19:11)
4. የዘካርያስ ልጅ፥ (2 ዜና 31:15)
5. የነቢዩ ሶፎንያስ ቅድመ
አያት፣ የሕዝቅያስ
ልጅ፥ (ሶፎ 1:1)
6. ከፋሬስ ወገን የሆነ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፥ (ነህ 11:4.)
7. ከባቢሎን ከተመለሱ ካህኑ አማርያ፥ (ነህ 10:3)
8. በዕዝራ ዘመን ከተመለሱ የባኒ ልጅ፥ (ዕዝ 10:41፣ 42)
አማኑኤል ~ Emmanuel, Immanuel:
አማኑ ኤል፣ አማነ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው።
‘አማን’ እና ’ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው / መቅቃ]
አማኑኤል / Emmanuel:
በአዲስ ኪዳን የትንቢቱን መፈጸም ሲያበስር፥“እነሆ፥ ድንግል
ትፀንሳለች ልጅም
ትወልዳለች፥ ስሙንም
አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ
ጋር የሚል
ነው”
(ማቴ 1፡23)
አማኑኤል / Immanuel:
በነብዮ ኢሳይያስ በተነገረው ትንቢት የተጠራ፥ “…እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች”
(ኢሳ 7፡14)
አማና ~ Amana: አማነ፣ አመነ፣ ሰላማዊ ሆነ፣ የታመነ ወዳጅ፣ እውነተኛ ጓደኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ሐማ፣ ሄማን፣ አሒማን፣ አሜን፣ አሞን፣ አኪመን፣ ያሚን]
በጠቢቡ ሰሎሞን ቃል ውስጥ የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ (መክ 4፡8)
አሜሳይ ~ Amasa: አመሳ፣ ዐመፃ፣ የሚያምስ፣ የሚረብሽ፣ ተቃዋሚ፣ የማይታዘዝ፣ የማይገዛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አማሢ፣ አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ ዓሜሳይ፣ አሜስያስ፣ አሞጽ]
‘ዐመፀ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
. አሜሳይ / Amasa:
የእስማኤላዊው የዬቴር ከአቢግያ የወለደው፥ (1
ዜና 2፡17)
. ዓሜሳይ / Amasa:
የሐድላይ ልጅ፥ (2 ዜና 28:12)
አሜስያስ ~
Amaziah:
አማሲ ያሕ፣ አማጸ ሕያው፣ በጌታ እልከኛ፣ ሕግ የጣሰ፣ አሻፈረኝ ያለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አማሢ፣ አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ ዓሜሳይ፣ አሞጽ]
‘ዐመፀ’ እና ‘ያሕ’
(ያሕዊ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
1. ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ከተሰጡ፣ የሌዊ ወገን የሆነ፥ (1
ዜና 6፡45)
2. የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ፥ (2 ነገ 14:1-4) ፣ በዳዊት ላይ ያመፀ፥
(2
ዜና 25፡27)
3. የቤቴል ካህን፥ (አሞ 7:10-17)
4. የአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየወገኖቻቸው ላይ አለቆች ከነበሩ፣ የኢዮስያ አባት፥ (1 ዜና 4:34)
አሜን ~ Amen: አምን፣ የታመነ፣ እውነት ነው ብዬ አምናልሁ፣ እርቅና ሰላም እቀበላለሁ፣ አንድነት እፈልጋለሁ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:-
ሐማ፣ ሄማን፣ አሒማን፣ አማና፣ አሞን፣ አኪመን፣ ያሚን]
‘አመነ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው። [የተረጋገጠና የታመነ ከሚል የዕብራይስጥ ቃል የወጣ ነው፥ እንደ አንቀጹ ትርጉሙ ይሁን፣
በእውነት ኪወክ /
አ]
[መልካም ማለት ነው / መቅቃ]
ጌታ ኢየሱስ
በዮሐንስ ራእይ
‘አሜን’ ተብሎ ተጠርቷል፥ “..አሜን የሆነው፥
የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ
ይላል”
(ራእ 3፡14)
አምራፌል ~ Amraphel: ‘ምራፈ ኤል፣ የአማልክት ጠባቂ’ ማለት
ነው። የሰናዖር
ንጉሥ፥ “በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥
በአሕዛብ ንጉሥ
በቲድዓል ዘመን
እንዲህ ሆነ” (ዘፍ
14:1፣4)
አምና ~
Ahiam:
አሂ እመ፣ አያ እማ፣ የእማ ወንድም፣ የእናት ወንድም፣ አጐት... ማለት ነው።
‘እኁ’ እና ‘እም’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የአሮዳዊው የአራር ልጅ፥ አምና፥ (2 ሳሙ 23፡33)
፣ (1 ዜና 11:35)
አምኖን ~
Amnon:
አምነን፣ አምነ፣ የታመነ፣ በእምነቱ የጸና... ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የሺሞን ልጅ፥ (1 ዜና 4፡20)
2. ለዳዊት በኬብሮን ከተወለዱለት
በኵሩ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው፣
(2 ሳሙ 13:28
፣ 29)
አሞራውያን ~
Amorites:
አሞራያት፣ አሞራውያን፣ የአሞን አገር ስዎች... ማለት ነው።
“ተመልሰውም ቃዴስ
ወደ ተባለች
ወደ ዓይንሚስፓጥ
መጡ የአማሌቅን
አገር ሁሉና
ደግሞ በሐሴሶን
ታማር የነበረውን
አሞራውያንን መቱ።” (ዘፍ
14፡7)
አሞናውያን ~ Ammonite:
አሞናያን፣ አማነያት፣
አማናውያን፣ የአሞን
ወገኖች፣ የአሞን
አገር ሰዎች... ማለት ነው።
. የሎጥ
ልጅ ወገኖች፥
(ዘፍ 19፡38)
. “ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ በመስጴጦምያ ካለው ከፋቱራ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግምህ ዘንድ አምጥተውብሃልና አሞናዊና ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ
አይግባ እስከ
አሥር ትውልድ
ድረስ ለዘላለም
ወደ እግዚአብሔር
ጉባኤ አይግባ።” (ዘዳ 23:4)
አሞን ~ Ammon, Amon: አሞን፣ አምን፣ የታመነ፣ በምነቱ የጸና… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:-
ሐማ፣ ሄማን፣ አሒማን፣ አማና፣ አሜን፣ አኪመን፣ ያሚን]
‘አመነ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አሞን / Ammon: የሎጥ ልጅ፥ “ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም፦ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው” (ዘፍ 19፡38)
አሞን / Amon: “የእስራኤልም ንጉሥ።
ሚክያስን ውሰዱ፥ ወደ ከተማይቱም አለቃ ወደ አሞን፥ ወደ ንጉሡም ልጅ ወደ ኢዮአስ መልሳችሁ።” (2 ዜና
18:25) ፣ (1
ነገ 22፡26)
አሞጽ ~ Amos, Amoz: ዐመፅ፣ ዐመጻ፣ በደል፣ ግፍ፣ ተቃውሞ፣ ውንብድና… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አማሢ፣ አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ ዓሜሳይ፣ አሜስያስ]
‘ዐመፀ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አሞጽ / Amos:
በይሁዳ ንጉሥ
በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን የነበረ ነቢይ፥ (አሞ 1፡1)
አሞጽ /
Amoz: የነብዮ ኢሳይያስ አባት፥ (2 ነገ 19፡2፣20)፥ (2
ነገ 19:2፣ 20 ፣ 20:1፥ ኢሳ 1:1፣ 2:1)
አሱብ ~
Hashub:
ሀሹብ፣ ሐሳብ፣ ሒሳብ፣ ዓላማ፣ ምኞት… ማለት ነው።
‘አሰበ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
1. የኢየሩሳሌምን ቅጥር ያደሰ የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ ፥ (ነህ 3:11)
2. ኢየሩሳሌምን ቅጥር ያደሰ፥ ሌላው አሱብ፥ (ነህ 3:23)
3. ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት፥ (ነህ 10:23)
4. ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ፥ (ነህ
11:15)
አሲማት ~
Ashima:
‘አስማት፣ ድግምት፣ ምትሐት’ ማለት ነው። የሐማት ሰዎች
አምላክ፥ (2 ነገ 17:31) “የሐማትም ሰዎች
አሲማትን ሠሩ
አዋውያንም ኤልባዝርንና
ተርታቅን ሠሩ
የሴፈርዋይም ሰዎችም
ለሴፈርዋይም አማልክት
ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር”
አሳ~ Asa: ‘መድኃኒት ዐዋቂ፣ ፈዋሽ’ ማለት
ነው። የአቢያ
ልጅ፥ የይሁዳ
ሦስተኛ ንጉሥ፥ “አብያምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም
አሳ በፋንታው
ነገሠ።”
(1 ነገ 15:8-14)
አሣሄል ~
Asahel:
አሣህ ኤል፣ ጌታ ሠራ፣ አምላክ አከናወነ፣ አምላክ የሠራው… ማለት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.የንጉሥ ዳዊት እኅት የጽሩያ ልጅ፥ (2 ሳሙ2፡18፣19)
2. ንጉሡ
ኢዮሣፍጥን ከሚያገለግሉ፥
(2 ዜና 17:8)
3. በንጉሡ ሕዝቅያስ በቤተ መቅደስ የንዋየ ቅዱሳቱ ሐላፊ የነበረ፥ (2
ዜና
31:13)
4. በዕዝራ ዘመን የነበር፣ የዮናታን አባት፥ ካህኑ አሣሄል፥ (ዕዝ 10:15)
አሳም ~ Ozem: ‘ብርቱ፣ ፈጣን፣ ጉጉ’ ማለት ነው።
የዳዊት ወንድም፥
የእሴይ ስድስተኛ ልጅ፥
“አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም
አሳምን፥ ሰባተኛውንም
ዳዊትን ወለደ” (1 ዜና
2:15)
አሣርኤል ~
Asareel: እሥረ ኤል፣ እሥረ አምላክ፣ ግዝት፣ መሐላ፣ የጌታ ምርኮ…
ማለት ነው።
‘አሰረ’ እና ’ኤል’
ከሚሉ ሁሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው ። ክይሁዳ ነገድ፣ የይሃሌልኤል ልጅ፥ አሣርኤል፥ (1 ዜና 4፡16)
አሳብያ ~
Hashabiah:
ሐሻበ ያሕ፣ ሐሳበ ሕያው፣ አምላክ ያሰበው፣ እግዚአብሔር
የረዳው… ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሐሸብያ፣
ሐሸቢያ]
‘አሳብ’ እና ‘ያሕ’(ሕያው)
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
የቃሉ ምንጭ
ደግሞ ‘አሰበ’
የሚለው ግስ ነው።
ከሌዋውያን ወገን፣ የዓዝሪቃ ልጅ፥ (1 ዜና 9:14) ፣ (ነህ 11:15)
አሳን ~ Hashem: ሐሽም፣ ሽም፣ ስም…
ማለት ነው።
የንጉሥ ዳዊት
ዘበኛ፥ “ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፥ የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፥ የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥” (1 ዜና 11:34)
አሳፍ ~
Asaph:
አሰፍ፣ አሰፋ፣ አበዛ፣ ተራባ፣ ቁጥሩና ግዛቱ ጨመረ… ማለት ነው።
‘ሰፋ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም
ነው። የበራክያ ልጅ፥ (1 ዜና 6፡39፣ (ነህ 2:8)
አሴል ~ Eshek: ‘ተጽዕኖ’
ማለት ነው።
ከሳዖል ትውልድ
የሆነ፥ “የወንድሙም የአሴል ልጆች በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት።” (1 ዜና 8:39)
አሴር ~
Aser, Asher, Assir: አሳር፣ እሥር፣ ግዝት፣ ምርኮ… ማለት ነው።
‘አሠረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው። [ትርጉሙ ደስተኛ ማለት
ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
I. አሴር / Aser: “ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች...”
(ሉቃ 2:36)
አሴር / Asher: ልያ ለያቆብ የወለደችለት ልጅ፥ (ዘፍ 30:13)
አሴር / Assir:
1. የቆሬ ልጅ፥ (ዘጸ 6:24)
2. የአቢሳፍ ልጅ፥ (1 ዜና 6:24)
አሴር ~ Asher, Assir: ደስታ
ማለት ነው።
የያዕቆብ ስምንተኛ ልጅ፥ ከልያ አገልጋይ፣ ከዘለፋ የተወለደ፥ (ዘፍ 30:13) “ልያም። ደስታ ሆነልኝ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።”
አሴር / Assir:
‘እስር፣ ግዝት፣ እግድ’ ማለት ነው።
1. የቆሬ ልጅ፥ (ዘጸ 6:24፤ 1 ዜና 6:22) “የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕልቃና፥ አብያሳፍ ናቸው፥ እነዚህ የቆሬ ልጆች ወገኖች ናቸው።”
2. የቀዓት ልጅ፥ (1 ዜና 6:23፣37)
“ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ሕልቃና”
3. የኢኮንያ መጠሪያ፥ (1 ዜና 3:17) “የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ መልኪራም፥”
አሥሪኤል ~ Asriel: አሥራ ኤል፣ የአምላክ ሥራ፣ ግብረኤል፣ የአብ ሥራ… ማለት ነው።
የገለዓድ ልጅ፥ “ከአሥሪኤል የአሥሪኤላውያን ወገን፥” (ዘኁ 26:31)
አሥርከተማ~ Decapolis: አሥር ከተሞች ማለት ነው። በምሥራቅና በደቡባዊ ምሥራቅ የገሊላን ባሕር የከበቡ አሥር የግሪክ ከተምች፥ “ሄዶም ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት አሥር ከተማ በሚባል አገር ይሰብክ ጀመር፥ ሁሉም
ተደነቁ።”
(ማር 5:20፥ 7:31)
አስሮን፣ ኤስሮ ~ Hezron: አጥር፣ ዙሪያ፣ የታጠረ፣ የተከለለ… ማለት ነው።
1. የሮቤል ልጅ፥ “የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ።” (ዘፍ46:9፤
ዘጸ 6:14)
2.
የፋሬስ ልጅ፥
ኤስሮ፥ “የይሁዳም ልጆች
ዔር፥ አውናን፥
ሴሎም፥ ፋሬስ፥
ዛራ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።” (ዘፍ
46:12፤ ሩት 4:18)
አስቀሪጦን ~ Asyncritus: ‘ተወዳዳሪ የማይገኝለት’ ማለት ነው። ጳውሎስ ሰላምታ ያቀረበለት ሮሜያዊ ክርስቲያን፥ “ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ” (ሮሜ 16:14)
አስቄዋ ~ Sceva: ‘ዝግጁ’
ማለት ነው።
የካህናትም አለቃ
የነበረ፥ “የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች
ነበሩት።”
(ሐዋ 19:14-16)
አስቆሮቱ ~ Iscariot:
‘የቆሮት ሰው’ ማለት
ነው። ጌታን
አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ የተጠራበት አገር ስም፥ “ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው
የአስቆሮቱ ይሁዳ” (ማቴ 10:4)
አስባኣል ~
Eshbaal:
የሽባዓል፣ የሺህ በዓል፣ የሺህ ጌታ፣ የብዙኃን ገዥ፣ የብዙዎች አለቃ… ማለት ነው።
የንጉሥ ሳኦል
ልጅ፥ (1 ዜና 8፡33)
አስቤል ~ Ashbel: አሰበ
ኤል፣ አምላክ
ያሰበው… ማለት
ነው። የብንያም
ልጅ፥ “የብንያምም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ፥ ናዕማን፥ አኪ፥ ሮስ፥
ማንፌን፥ ሑፊም
ጌራም አርድን
ወለደ።”
(ዘፍ 46:21፤ ዘኊ
26:38፤ 1
ዜና 8:1)
አስታሮት ~ Ashtaroth: ‘መንጋ፣ ክምችት’ ማለት ነው። የንጉሥ ዐግ ግዛት፥ የባሳን ከተማ፤ የጣዖት ስም፥ “በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ሙሴ፥ በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ
ሴዎንን፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀምጦ የነበረውን
የባሳንን ንጉሥ
ዐግን ከመታ
በኋላ፥ እግዚአብሔር
ስለ እነርሱ
ያዘዘውን ሁሉ
ለእስራኤል ልጆች
ነገራቸው።” (ዘዳ 1:4፤ ኢያ 12:4፣ 13:12፣ 9:10)
አስቴር ~ Esther: አስቴረ፣
አስተር፣ አሰጠረ፣
ሰተር፣ ሰጠረ፣
ደበቀ፣ ምሥጢር
አደረገ… ማለት
ነው። [በፋርስ ቋንቋ
ኮከብ ማለት
ነው / መቅቃ]
በመጽሐፈ አስቴር፣ የሀደሳ ሌላ ስም፥ “አባትና እናትም አልነበራትምና የአጎቱ ልጅ ሀደሳ የተባለችውን አስቴርን አሳድጎ ነበር ...” (አስ 2፡7)
አስናት ~ Asenath:
‘አዘናት፣ ሐዘንተኛ፣ እደለ ቢስ፣ መከረኛ’
ማለት ነው።
የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ፥ በግብፅ የዮሴፍ ሚስት፥ “ፈርዖንም የዮሴፍን ስም
ጸፍናት ፐዕናህ
ብሎ ጠራው
የሄልዮቱ ከተማ
ካህን የጶጥፌራ
ልጅ የምትሆን
አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ” (ዘፍ 41:45)
አስናፈር ~ Asnapper: ‘ፈጣን’
ማለት ነው።
በሰማርያ ከተማ
ነዋሪ የሆነ፥ “ታላቁና ኃይለኛው አስናፈር ያፈለሳቸው በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው የቀሩትም
አሕዛብ ደብዳቤውን
ጻፉ።”
(ዕዝ 4:10)
አስከናዝ ~
Ashkenaz:
‘ሰደድ እሳት’ ማለት ነው። ከጋሜር ሦስት ልጆች አንዱ፥
“የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥
ሪፋት፥ ቴርጋማ
ናቸው።”
(ዘፍ 10:3)
አስጢ ~ Vashti: ‘ውብ’
ማለት ነው።
የንጉሡ አርጤክስስ
ሚስት፥ “ነገር ግን
ንግሥቲቱ አስጢን
በጃንደረቦቹ እጅ
በላከው በንጉሡ
ትእዛዝ ትመጣ
ዘንድ እንቢ
አለች ንጉሡም
እጅግ ተቈጣ፥
በቍጣውም ተናደደ።” (አስ
1:10-12)
አሦር ~
Asshur:
አሱር፣ እሥር፣ ግዝት፣ ምርኮ…
ማለት ነው።
የኖኅ ልጅ የሴም ሁለተኛ ልጅ፥ “የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም
ናቸው:”
(ዘፍ 10፡22)
፣ (1 ዜና 1:17)
አሶን ~ Assos: አሰሳ፣
ፍተሻ፣ ዳሰሳ…
ማለት ነው።
የሮሜ የወደብ
ከተማ፥ “እኛ ግን
ጳውሎስን ከዚያ
እንቀበለው ዘንድ
ስላለን ወደ
መርከብ ቀድመን
ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና።” (ሐዋ
20:13፣14)
አረማዊ ~
Barbarian:
በር በሪያ፣ የበሪያ ልጅ፣ አገልጋይ፣ ታዛዥ፣ ነጻ ያልወጡ… ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች-
እንግዳ፣ ላልተማሩ]
Barbarian- ‘በር’
፣‘በረ’ እና ‘ያሕ’ን ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
. መላጥያ በምትባል ደሴት የሚኖሩ ሰዎችን ጳውሎስ የጠራበት ስም፥ “አረማውያንም የሚያስገርም
ቸርነት አደረጉልን፤
...” (ሥራ 28:1
፣ 2 ፣ 4)፣ (ሥራ
28:1 ፣ 2
፣ 4)
. እንግዳ ፥ (1 ቆሮ 14:11)
. ላልተማሩም ፥ (ሮሜ 1:14)
አሩማ ~ Arumah: ከፍተኛ
ማለት ነው።
የንጉሥ አቤሜሌክ መቀመጫ
የነበረ፥ የሴኬም አጎራባች አገር፥ “አቤሜሌክም በአሩማ ተቀመጠ ዜቡልም ገዓልንና ወንድሞቹን
በሴኬም እንዳይኖሩ
አሳደዳቸው።”
(መሣ 9:41)
አሪሶት ~ Harosheth: ‘አራሾች፣ ሠራተኞች’ ማለት
ነው። “እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተቀመጠው ሲሣራ ነበረ።” (መሣ 4:2)
አራ ~
Ara:
‘አንበሳ’
ማለት ነው። “የዬቴር ልጆች ዮሮኒ፥ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ።” (1 ዜና 7:38)
አራም ~
Aram, Ram: አራማ፣ ራማ፣ ከፍተኛ፣ ታላቅ… ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የኖኅ ልጅ፣ የሴም ልጅ፥ (ዘፍ 10:22)
2. የቀሙኤል ልጅ፥ (ዘፍ 22:21)
3. የኤስሮም ልጅ፥ (ሩት 4:19)
4. የአሮኒ ልጅ፥ (ሉቃ 3:33)
አራም ~ Ram: ራም፣ ራማ፣ ከፍተኛ… ማለት ነው።
1. የኤስሮም ልጅ፥ “ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን
ወለደ፥”
(ሩት 4:19)
2. የይረሕምኤል ልጅ፥ ራም፥
(1 ዜና 2:25፣27) “የኤስሮምም የበኵር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኵሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ።”
3. ራም፥ “ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቍጣ ነደደ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።”
(ኢዮብ 32:2)
አራራት ~
Ararat:
አራራት፣ ተራራት፣ ተራሮች፣ ከፍተኛ ቦታ… ማለት ነው።
. የኖኅ መርከብ ያረፈችበት ቦታ፥ “መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች” (ዘፍ 8:4)
. የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የሸሸበት ቦታ፥ “...ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም
አስራዶን በእርሱ
ፋንታ ነገሠ” (2 ነገ
19:37) ፣ (ኢሳ 37:38)
አራር ~ Sharar: ‘ብርቱ፣ ጠንካራ’ ማለት
ነው። የአምናን
አባት፥ “የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥ የማዕካታዊው ልጅ የአሐስባይ ልጅ ኤሌፋላት፥ የጊሎናዊው
የአኪጦፌል ልጅ
ኤልያብ፥”
(2 ሳሙ 23:34)
አራብ ~
Arab:
አረብ፣ የረባ፣ የተራባ፣ የተዋለደ፣ የተባዛ፣ የዓረብ አገር፣ ምድረ
በዓዳ… ማለት ነው።
‘ረባ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
በደቡብ በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች
ነገድ ከተሞች፥
(ኢያ 15:52)
አራን ~ Aran: ‘የሜዳ ፍየል’ ማለት
ነው። የዲሳን
ልጅ፥ ከሴይር
ልጆች አለቆች፥
“የዲሳን ልጆችም እነዚህ
ናቸው ዑፅ፥
አራን።”
(ዘፍ 36:28)
አርማትያስ ~ Arimathea: ‘ከፍተኛ’
ማለት ነው።
የይሁዳ ከተማ፥
“በመሸም ጊዜ ዮሴፍ
የተባለው ባለ
ጠጋ ሰው
ከአርማትያስ መጣ፥
እርሱም ደግሞ
የኢየሱስ ደቀ
መዝሙር ነበረ፤” (ማቴ
27:57፤ ሉቃ 23:51፤ ዮሐ
19:38)
አርማጌዶን ~ Armageddon: የጌዶን
ተራራ ማለት
ነው። ዮሐንስ
ባየው ራእይ፥
ለሰባቱ መላእክት
በተነገረው ድምፅ፥ ከስድስተኛው
ጋር በተገናኝ
የተነገረ፥ “በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው”
(ራእይ 16:16)
አርሞንዔም ~ Hermon:
‘ቁንጮ’ ማለት
ነው። በሰሜን
ፍልስጥኤም የሚገኝ
ተራራ፥ “የእስራኤልም ልጆች
የመቱአቸው፥ ከአርኖንም
ሸለቆ ጀምሮ
እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ...” (ዘዳ 3:8፤ ኢያ 12:1)
አርስጣባሉ ~ Aristobulus: ‘የተከበረ፥ የተመሰገነ
አማካሪ’
ማለት ነው።
በሮሜ ነዋሪ
ከሆኑ፥ ጳውሎስ
በመልእክቱ ሰላምታ
ካቀረበላቸው ቤተሰቦች፥
“በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ
ለተመሰገነው ለኤጤሌን
ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ከአርስጣባሉ ቤተ
ሰዎች ላሉት
ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ
16:10)
አርስጥሮኮስ ~ Aristarchus: ‘የተመሰገነ መሪ’ ማለትነው። የተሰሎንቄ ነዋሪ የሆነ፥
“የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ
ከተሰሎንቄ ሰዎችም
አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ
የደርቤኑም ጋይዮስና
ጢሞቴዎስ የእስያ
ሰዎችም ቲኪቆስ
ጥሮፊሞስም ነበሩ፤” (ሐዋ
20:4)፤ የጳውሎስ ደቀ
መዝሙር የነበረ፥
(ሐዋ 19:29፣ 27:2) ፤ ከጳውሎስ ጋርም በሮም የታሰረ፥ (ቆላ 4:10; ፊሊ 1:24)
አርስጦስዮስ ~ Aretas: ‘ከባድ፣ ጽኑ፣
አስቸጋሪ፣ ፈታኝ’ ማለት
ነው። በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን የነበረ የሦርያ ንጉሥ፥ ጳውሎስን ለማሰር ይከታተለው ነበር፥
በቅጥሩም ባለ
መስኮት በቅርጫት
አወረዱትና ከእጁ
አመለጠ፥ “በደማስቆ አርስጦስዮስ ከተባለ ንጉሥ በታች
የሆነ የሕዝብ
ገዥ ሊይዘኝ
እየወደደ የደማስቆ
ሰዎችን ከተማ
ያስጠብቅ ነበር” (2 ቆሮ 11:32)
አርቄስዮስ ~ Carshena:
‘ታዋቂ’ ማለት ነው። ከሰባቱ
የፋርስና የሜዶን
መሳፍንት አንዱ፥
“በመንግሥቱም ቀዳሚዎች ሆነው
የሚቀመጡ የንጉሡ
ባለምዋሎች ሰባቱ
የፋርስና የሜዶን
መሳፍንት አርቄስዮስ፥
ሼታር፥ አድማታ፥
ተርሺሽ፥ ሜሬስ፥ ማሌሴዓር፥ ምሙካን በአጠገቡ ሳሉ።” (አስ 1:14)
አርባቅ ~
Arba, Arbah: አረባዓ፣ ዓረብ፣ ምድረ በዓዳ፣ ማድረበዳ ማለት ነው።
Arba-
‘አረባ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
አርባቅ / Arba: የኬብሮን የአቀድሞ ስም፥ “የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያትአርባቅ ትባል ነበር ይህም አርባቅ ...” (ኢያ 14፡15)
አርባቅ / Arbah: “ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች
ሆነው ወደ
ተቀመጡባት ወደ
መምሬ ወደ
ቂርያት አርባቅ እርስዋም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ”
(ዘፍ 35፡27)
አርኤሊ ~
Areli:
አየረ ኤሊ፣ ሰማያዊ፣ አምላካዊ፣ ታላቅ ጌታ፣ ታላቅ ኃይል… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አርኤል፣ አርያ]
. የያቆብ ልጅ፣ የጋድ ልጅ፥ አርኤሊ፥ (ዘፍ 46፡16)
. ነገዱም በዚሁ
ስም ተጠራ፥
“ከአሮድ የአሮዳውያን ወገን፥ ከአርኤሊ የአርኤላውያን ወገን።” (ዘኁ 26:17)
አርኤል ~
Ariel:
ኤሪ ኤል፣ አየረ ኤል፣ ሰማያዊ፣ አምላካዊ፣ ታላቅ ኃይል… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አርኤሊ፣ አርያ]
[የእግዚአብሔር ምድጃ
ማለት ነው/ መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን የወጡ፥ መቅደሱን እንዲጠብቁ መልእክት ከተቀበሉት አንዱ፥ (ዕዝ 8:16)
2. የከተማ ስም፥ “ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! …” (ኢሳ
29:1፣ 2፣ 7) ፣ (ሕዝ 43:15፣ 16)
አርካድ ~ Accad: ‘እንደ ማዲጋ፣
ማሰሮ፣ ቶፋ
ያለ፥ ለውኃ
መቅጃነት የሚውል’ ማለት
ነው። የእንግሊዝኛ
‘አካድ (Accad)’
ሲሆን፥ የአማርኛው
ደግሞ ‘አርካድ’
ተብሎ ይጠራል።
በሰናዖር ምደር
የነበረ ከተማ፥
“የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው” (ዘፍ 10:10)
አርኬላዎስ ~
Archelaus:
‘የሕዝብ ገዥ’ ማለት ነው። የሄሮድስ ልጅ፥ በይሁዳ የነገሠ፥ “በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥
ወደዚያ መሄድን
ፈራ፤ በሕልምም
ተረድቶ ወደ
ገሊላ አገር
ሄደ”
(ማቴ 2:22)
አርያ ~
Arieh:
አረያ፣ አርያሕ፣ አምላካዊ፣ ምሳሌያዊ፣ ታላቅ፣ ሰማይ፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ያለ… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አርኤሊ፣ አርኤል]
‘አሮን’ ከሚለው ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም አለው።
በይሁዳ ንጉሥ በዓዛርያስ በአምሳኛው ዓመት የምናሔም ልጅ ፋቂስያስ በእስራኤል ላይ በሰማርያ በነገሠ ጊዜ የተገደለ፥ (2 ነገ 15፡25)
አርዮስፋጎስ ~ Areopagus: ‘የማርስ ኮረብቶች’ ማለት
ነው። ጳውሎስ ለግሪክ
ሰዎች ወንጌልን
የሰበከበት ተራራማ
ቦታ፥ “ይዘውም። ይህ
የምትናገረው አዲስ
ትምህርት ምን
እንደሆነ እናውቅ
ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን
እንግዳ ነገር
ታሰማናለህና፤ እንግዲህ
ይህ ነገር
ምን እንደሆነ
እናውቅ ዘንድ
እንፈቅዳለን ብለው
አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።” (ሐዋ 17:19)
አርዮክ ~ Arioch:
‘የተከበረ፣ የተመሰገነ፣ የተደነቀ’ ማለት ነው።
1.
የእላሳር ንጉሥ፥
“በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥
በእላሳር ንጉሥ
በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቲድዓል ዘመን እንዲህ ሆነ” (ዘፍ
14:1)
2.
የባቢሎን ንጉሡ
የዘበኞቹ አለቃ፥
“የዚያን ጊዜም ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን ይገድል ዘንድ የወጣውን የንጉሡን የዘበኞቹ አለቃ አርዮክን በፈሊጥና በማስተዋል
ተናገረው”
(ዳን 2:14)
አርድ ~ Ard: አርድ፣
ያርድ፣ ይወርድ፣
አያት፣ ቅድመ
አያት፣ ሲወርድ
ሲዋረድ የመጣ፣ ትልቅ፣ ከፍተኛ፣ ጥንታዊ…
ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አርዶን] የብንያም ልጅ፣ የቤላ ልጅ፥ (ዘኁ 26፡38-40)
አርዶን ~
Ardon:
አርደን፣ የበላይ ፈራጅ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ከበላይ የታዘዘ… ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አርድ]
የካሌብ ልጅ፥ “የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ።” (1 ዜና 2:18)
አርጎብ ~ Argob: ‘ድንጋያማ’ ማለት ነው። በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ፥ “በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ... በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ፥ ስድሳ ከተሞችን ወሰድን።” (ዘዳ 3:4፣13፣14)
አርጢሞን ~ Artemas: የጳውሎስ ደቀመዝሙር የነበረ፥ “አርጢሞንን
ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም
ቈርጬአለሁና”
(ቲቶ 3:12)
አርጤምስ ~ Diana: ‘ፍጽምት፥ አንጸባራቂ’ ማለት
ነው። የጣዖት
ከተማ ስም፥
“… የኤፌሶን ከተማ
ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ
የመቅደስ ጠባቂ
መሆንዋን የማያውቅ
ሰው ማን
ነው?”
(ሐዋ 19:35)
አርጤክስስ ~ Artaxerxes:
‘ብርቱ ጦረኛ፣ ኃያል
ተዋጊ’
ማለት ነው።
1. የፋርስ ንጉሥ፥ “በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ ደብዳቤውም በሶርያ ፊደልና በሶርያ ቋንቋ
ተጽፎ ነበር።” (ዕዝ 4:7)
2. “በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ
ጠጁን አንሥቼ
ለንጉሡ ሰጠሁት።
ቀድሞ ግን
በፊቱ ያለ
ሐዘን እኖር ነበር።” (ነህ 2:1)\
አርፋክስድ ~ Arphaxad:
‘ፈዋሽ፣ አዳኝ፣ አካሚ’ ማለት
ነው። ከጥፋት
ውኃ በኋላ
የተወለደ፥ የሴም
ልጅ፥ “… ሴም
የመቶ ዓመት
ሰው ነበረ፥
አርፋክስድንም ከጥፋት
ውኃ በኋላ
በሁለተኛው ዓመት
ወለደ።”
(ዘፍ 11:10- 13፤ 1 ዜና 1:17፣18፤ ሉቃ 3:36)
አርፋድ ~ Arpad: ‘ብርቱ ከተማ’ ማለት
ነው። ከደማስቆ
ወጣ ሲሉ
የሚገኝ፥ “የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን
ከእጄ አድነዋታልን?” (ኢሳ 36:19፣37:13)
አሮን ~ Aaron, Aaronites: አሮን፣ አረያን፣
አረያነ፣ አርአያ፣
ተምሳሌ፣ አብነት፣ መንገድ መሪ፣ ብርሃን አብሪ፣ መምህር ፥ አሮን ቤት፣ አሮናውያን፣ ቤተ አሮን፣ የአሮን ወገኖች፣ የአሮን አገር ሰዎች…
ማለት ነው።
የስሙ ምንጭ
‘አረያ’ የሚለው ቃል ነው።
አሮን / Aaron:
የሙሴ ወንድም
ሆኖ እናቱ
ያቆቢድ ፤ አባቱ አምራም ፤ እኅቱ ደግሞ ማርያም ይባላሉ። (ዘጸ 4:14)
አሮንቤት / Aaronites:
ዮዳሄ አለቃ
የሆነበት፥ (1
ዜና 12:27)
አሮኖን ~ Arnon: የሚያጎራ፣
የሚያገሳ፣ የሚጮህ…
ማለት ነው።
በሞዓብ በስተሰሜን የሚገኝ፥ የሞዓብዓውያንን እና የአሞራውያንን ምድር የሚከፍል ወንዝ። “ከዚያም ተጕዘው
ከአሞራውያን ዳርቻ
በሚወጣው ምድረ
በዳ ውስጥ
በአሮኖን ማዶ
ሰፈሩ አሮኖን
በሞዓብና …” (ዘኊ 21:13፣14፣24፣26፤ መሣ11:22)
አሮዔር ~ Aroer: ‘ጥራጊ፣ ውዳቂ፣ ዐጽም’
ማለት ነው።
1. በአርኖን ወንዝ ዳር
የሚገኝ ከተማ፥
“በአርኖን ወንዝ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ
እስከ ሲዎን
ተራራ እስከ
አርሞንዔም ድረስ” (ዘዳ
4:48፤ መሣ 11:26፤ 2 ነገ 10:33)
2. በጋድ ነገድ ከተገነቡ
ከተሞች አንዱ፥
አሮዔር፥ “የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥
አሮዔርን፥”
(ዘኁ 32:34)
3. በይሁዳ በስተደቡብ ያለ ከተማ፥ አሮዔር፥ “በየቲር ለነበሩ፥ በአሮዔር ለነበሩ፥ በሢፍሞት
ለነበሩ፥ በኤሽትሞዓ
ለነበሩ፥”
(1 ሳሙ 30:26፣28)
አሽሑር ~ Ashur: ‘ጥቁር’
ማለት ነው።
የኤስሮም ልጅ፥
ከአቢያ የወለደው፥ የቴቁሔን አባት፥ “ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት
አቢያ የቴቁሔን
አባት አሽሑርን
ወለደችለት።”
(1 ዜና 2:24፣ 4:5)
አሽና ~ Ashnah: ‘ለውጥ’
ማለት ነው።
በይሁዳ ቆላማ
ምድር የሚገኝ
ከተማ፥ “በቈላው ኤሽታኦል፥
ጾርዓ፥ አሽና፥
ዛኖዋ፥”
(ኢያ 15:33)
አሽንክታብ ~ Phylacteries: ‘ልዩ
ልብስ፣ ጌጣ
ጌጥ’
ማለት ነው።
“ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም
ያስረዝማሉ፥”
(ማቴ 23:5)
አቂላ ~
Aquila:
‘ንስር’ ማለት ነው። የጵርስቅላ ባል፥ ከኢጣሊያ የመጣ ከጳውሎስ
ጋር የተገናኘ
ክርስቲያን፥ “በወገኑም የጳንጦስ
ሰው የሚሆን
አቂላ የሚሉትን
አንድ አይሁዳዊ
አገኘ ...” (ሐዋ 18:2)
አቃሮን ~
Ekron:
‘ተፈናቃይ’ ማለት ነው። ከአምስቱ የፍልስጥኤም አለቆች ከተሞች፥
የሩቁ ሰሜናዊ
ከተማ፥ “... የከነዓናውያን
ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ
አቃሮን ዳርቻ
ድረስ፥ የጋዛ፥
የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥
የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥” (ኢያ 13:3)
አቅረቢም ~ Akrabbim: አቅራቢያ፣
አካባቢም፣ የቅርብ
ርቀት… ማለት
ነው። ‘ቀረበ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው። በሙት ባሕርና በጺን መካከል ያለ መተላለፊያ፥ የይሁዳ ደቡባዊ ዳርቻ የሆነ ጉልህ ቦታ፥ “ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ...” (ኢያ 15:3)
አቆስ ~
Hakkoz:
‘እሾህ፣ ቀንድ’
ማለት ነው። መቅደሱን ለማገልገል፥ በዳዊት ከተሾሙት፥
በሰባት ተራ
ከሚያገለግሉት፥ ከካህናቱ
አንዱ፥ “ስድስተኛው ለሚያሚን፥
ሰባተኛው ለአቆስ፥” (1 ዜና 24:10)
አበኔር ~ Abner: አብ ኔር፣ የብርሃን አባት፣ ታላቅ ብርሃን... ማለት ነው። የሳኦል
አጎት የኔር
ልጅ፥ የሳኦል ሠራዊት አለቃ የነበረ፥ “የሳኦልም ሚስት ስም ...ነበረ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበረ” (1 ሳሙ 14:50፤ 17:55፤ 20:25)
አቡ ~
Abi:
አበ፣ አብዬ፣ አባ፣ ትልቅ... ማለት ነው።
የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ልጅ የሕዝቅያስ እናት ስትሆን፣ የዘካርያስ ልጅ፥ (2
ነገ 18፡ 2)፣ (2 ዜና 29:1)
አቢማኤል ~
Abimael:
አቢ መኤል፣ አበ አምላክ፣ አበ ኃያል፣ ትልቅ አምላክ፣ በጣም ኃይለኛ... ማለት ነው።
የኖኅ የልጅ ልጅ፣ የዮቅጣን ልጅ፥ “ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም” (ዘፍ
10:28)
አቢሜሌክ ~ Abimelech, Ahimelech:
አባ መላክ፣ ታላቅ መላክ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቤሜሌክ]
‘አበ’ እና ‘መለከ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
‘አቤሜሌክ’ የሚለውን ጨምሮ ‘አቢሜሌክ’ በሚለው ስም የሚታወቁ አምስት ሰዎች አሉ።
አቢሜሌክ / Abimelech:
1. የጌራራ ንጉሥ፥ “አብርሃምም ሚስቱን ሣራን፦ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት”
(ዘፍ 20፡1-18)
2. የፍልስጥኤም ንጉሥ፥ ... ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤምም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ
ጌራራ ሄደ” (ዘፍ 26:1)
3. የጌዴዎን ልጅ፥ (መሣ 8:31)
አቢሜሌክ / Ahimelech:
የአብያታር አባት፣ ካህኑ አቤሜሌክ፥ “የአኪጦብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአቤሜሌክም ልጅ አብያታር ...።” (1 ዜና 18:16) ፣ (1 ሳሙ 22፡20-23)
አቢሱ ~ Abishua: አቢሻ፣ አበሻ፣ አብ ሽዋ፣ አበ ሺህ፣ የሽዎች አባት፣ ባለብዙ ሃብት፣ ታላቅ ባለጸጋ፣ ባለ ብዙ ንብረት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
አቢሳ] Abishua- ‘አበ’ እና ‘ሽዋ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
1. የብንያም ወገን፣ የቤላ ልጅ፥ (1 ዜና 8፡4)
2. የፊንሐስ ልጅ፥ (1 ዜና 6:4፣ 5፣ 50፣ 51)
፣ (ዕዝ 7:4፣5)
አቢሱር ~ Abishur: አበ
ቸር፣ ቅን
አባት... ማለት ነው።
ከይሁዳ ወገን
ከሆነ፥ ከሸማይ ልጆች አንዱ፥ “የኦናምም ልጆች ሸማይና ያዳ ነበሩ። የሸማይ ልጆች ናዳብና
አቢሱር ነበሩ።” (1 ዜና 2:28፣29)
አቢሳ ~
Abishag, Abishai: አቢ ሸግ፣ አብ ሸጋ፣ ትልቅ ሸጋ፣ በጣም ቆንጆ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢሱ]
Abishag- ‘አብ’
እና ‘ሸጋ’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አቢሳ / Abishag: የንጉሥ ዳዊት የመጨረሻ ሚስት፥ (1
ነገ 1:3)
አቢሳ / Abishai: ከዳዊት ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ የወረደ፥ የንጉሥ ዳዊት እኅት የጹርያ ልጅ፥ (1
ሳሙ 26:6)
አቢሳፍ ~
Ebiasaph:
አብያሳፍ፣ አባ ሰፊ፣ በጣም ትልቅ፣ ሰፊ ሕዝብ፣ ታላቅ አገር፣ የብዙዎች አባት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
አብያሳፍ]
‘አባ’ እና ‘አሰፋ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የቆሬ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፥ (1 ዜና 6፡23፣ 37)
አቢብ ~ Abib:
አበባ፣ ውብ፣ ቆንጆ... ማለት ነው።
‘አበበ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው።
. አምላክ እግዚአብሔር በሌሊት ከግብፅ እስራኤልን ያወጣበት፣ የወር ስም፥ “እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል።” (ዘጸ 13:4)
. ለእስራኤል ከተማ የመጠሪያ ስም ተጨማሪ ሆኖ ያገለግላል፥
“በቴልአቢብም ወዳሉ በኮቦርም ወንዝ አጠገብ ወደ ተቀመጡ ምርኮኞች መጣሁ...”
(ሕዝ 3:15)
አቢኒኤም ~
Abinoam:
አቢ ናኦም፣ የናዖም አባት፣ በጣም ትሑት... ማለት ነው።
‘አብ’
እና ‘ናኦም’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
የባርቅ አባት፥ “ልካም ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠርታ...”
(መሣ 4:6)
አቢዓልቦ ~ Abi-albon: አበ ልብ፣ ልባም፣ ልበ ትልቅ፣ አስተዋይ አባት... ማለት ነው። ከዳዊት ኃያላን ዘበኞች አንዱ፥ “ሂዳይ፥ ዓረባዊው አቢዓልቦን፥ በርሑማዊው”
(2 ሳሙ 23:31)
አቢኤል ~ Abiel: አቢ ኤል፣ አቤል፣ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ታላቅ አምላክ፣ ታላቅ ጌታ፣ ታላቅ ገዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አቤል፣ ኤልያብ] ‘አብ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በዚህ
ስም የሚታወቁ
ሰዎች:
-
1. ቢኒያማዊው የቂስ አባት፥
(1 ሳሙ 14፡51)
2. ንጉሥ ዳዊት በዘበኞቹ ላይ የሾመው፥ (1 ዜና 11:32 ፣ 33)
አቢዔዜር ~
Abiezer:
አባቴ ወገኔ፣ ታላቅ ረዳት፣ ከፍተኛ መመኪያ፣ ትልቅ ዘመድ፣ ዘሬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢዔዝር]
‘አበ’
እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
አቢዔዜር / Abiezer:
ከብንያማውያን የነበረው ዓናቶታዊው፥ የንጉሥ ዳዊት ዘበኛ፥ (2 ሳሙ 23:27 ፣ 28) ፣ (1
ዜና 11:28 ፥ 27:12)
. አቢዔዝር- (1 ዜና 7:18)
አቢዔዝራዊ ~ Abiezrite: አቢዘራት፣ አቢዘራውያን፣ የአቢዘር ወገኖች፣ የአቢዘር አገር ሰዎች... ማለት ነው።
የኢዮአስ አገር፥
(መሣ 6፡11
፣ 24)
አቢዔዝር ~
Abiezer:
አባቴ ወገኔ፣ታላቅ ረዳት፣ ከፍተኛ መመኪያ፣ ትልቅ ዘመድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢዔዜር]
‘አበ’
እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
ከምናሴ ወገን የሆነ፥ አቢዔዝር፥ (ኢያ 17:2) ፣ (1 ዜና 7:18)
አቢካኢል ~
Abihail:
አባ ኃይል፣ ጉልበተኛ፣ ታላቅ ኃያል... ማለት ነው።
‘አብ’ እና ‘ኃይል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ አምስት ሲሆኑ፥ ሦስት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ናቸው።
1. የሜራሪ ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ፥ የሱሪኤል አባት፥ (ዘኁ 3፡35)
2. የአቢሱር ሚስት፥ (1 ዜና 2:29)
3. ከጋድ ነገድ የሆነ፣ የዑሪ ልጅ፥ (1
ዜና 5:14)
4. የዳዊት ወንድም፥ የኤልያብ
ልጅ፥ (2 ዜና 11:18)
5. የመርዶክዮስ አጎት፣ የአስቴር አባት፥ (አስ 2:15)
አቢያ ~
Abia:
አብያ፣ አባዬ፣ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ሕያው አምላክ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አብያ]
‘አብ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
1. የኤስሮም ሚስት፥ (1 ዜና 2:24)
2. የሰሎሞን ልጅ፣ የሮብዓ ልጅ፥ (1
ዜና 3:10) ፣ (ማቴ 1:7)
አቢዳን ~
Abidan:
አበ ዳኘ፣ አብ ዳኛ፣ ታላቅ ዳኛ፣ ከፍተኛ ዳኛ፣ ታላቅ ፈራጅ... ማለት ነው።
‘አብ’ እና ‘ዳኝ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የብንያም ልጆች አለቃ፣ የጋዴዮን ልጅ፥ (ዘኁ 1:11፣ 2:22 ፥ 7:60 ፣ 65፥ 10:24)
አቢግያ ~ Abigail: አቢጌል፣
አብ ገላ፣
ታላቅ ገላ፣
በጣም ቆንጆ፣
ታላቅ ውበት፣
በጣም ውብ... ማለት ነው።
Abigail- ‘አብ’
እና ‘ገላ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የእሴይ ልጅ፣ የዳዊት እኅት ፥ (1 ዜና 2:16 ፣ 17)
2. የናባል ሚስት፥ ናባል ሲሞት ንጉሥ ዳዊት አገባት፥ (1 ሳሙ 25:3)
አቢጣል ~ Abital: አቢ
ጣል፣ አባ
ጥላ፣ ትልቅ
ጥላ፣ ትልቅ
ከለላ፣ መጠለያ... ማለት ነው።
‘አብ’ እና ‘ጥላ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የንጉሥ ዳዊት
አምስተኛ ሚስት፣
የሰፋጥያስ እናት፥
(2 ሳሙ 3:4)፣ (1 ዜና 3:3)
አባ ~
Abba:
አብ፣ ወላጅ (ፈጣሪ) ፣ ትልቅ (በልሥጣን፥በኃይል)
፣ አዛውንት (በዕድሜ፥በልምድ)...
ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም- አባት]
. ጌታ ኢየሱስ አባቱን የጠራበት ስም፥ “አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ” (ማር 14፡36)
. ሐዋርያው ጳውሎስ
እግዚአብሔር አምላክን፥ ለሮማውያን የገለጸበት ስም፥ “አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት
የባርነትን መንፈስ
አልተቀበላችሁምና።”
(ሮሜ 8:15)
. ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር አምላክን፥ ለገላትያ ሰዎች የገለጸበት ስም፥ “ልጆችም ስለ
ሆናችሁ እግዚአብሔር
አባ አባት ብሎ
የሚጮኽ የልጁን
መንፈስ በልባችሁ
ውስጥ ላከ።” (ገላ 4:6)
አባት ~ Father: አባት፣ ባ ዘር፣ አባ ዘር፣ አብ ዘር፣ አብ ቤት፣ የአብ ወገን... ማለት ነው።
. አባ እና እማ ማለት ሳያውቅ የልጅነት ምልክት፥ “እግዚአብሔርም፦ ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ።” (ኢሳ 8:4)
. ወላጅ አባት፥ “መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ
ናት”
(ኤፌ 6:2)
. የሥላሴ ምሳሌ ሲሆን፣ ውኃው የእግዚአብሔር አብ ምሳሌ ነው፥ “የሚመሰክሩት መንፈሱና
ውኃው ደሙም
ሦስት ናቸውና፤
ሦስቱም በአንድ
ይስማማሉ።”
(1 ዮሐ 5:7፣ 8)
. ሽማግሌ፥ “ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ
ወንድሞች፥ የሸመገሉትን
ሴቶች እንደ
እናቶች፥ ቆነጃጅቱን
እንደ እኅቶች
በፍጹም ንጽሕና
ለምናቸው።”
(1 ጢሞ 5:1)
. አምላካችን፥ “ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን
ፈቃድ ስለ
ኃጢአታችን ራሱን
ሰጠ። (ገላ 1:4) “በእናንተ የሚናገር
የአባታችሁ መንፈስ
ነው እንጂ፥
የምትናገሩ እናንተ
አይደላችሁምና”
(ማቴ 10:20፣ 29)
. እግዚአብሔር አምላክ፥“የሰጠኝ አባቴ
ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ
ሊነጥቃቸው ማንም
አይችልም”
(ዮሐ 10:29)
. “እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት።” (ዮሐ 8:41)
አባቶችአለቃ ~ Patriarch: ቀዳማዊ፣
ጥንታዊ፣ የሩቅ
አባት፣ አያት፣ ቅድመ
አያት... ማለት ነው።
. ዳዊት በዚህ ማዕረግ ተጠርቷል፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም ...” (ሥራ 2:29)
. አብርሃም የአባቶች አለቃ ተባለ፥ (ዕብ 7:4)
አባና ~ Abana: እብን፣
ድንጋያማ፣ ዓለታማ፣ የጸና... ማለት
ነው። ትልቁ
የደማስቆ ወንዝ፥
“የደማስቆ ወንዞች አባናና
ፋርፋ ከእስራኤል
ውኆች ሁሉ
አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ...” (2 ነገ 5:12)
አቤል ~ Abel: አበ
ኤል፣ አቤል፣
አባቴ አምላኬ፣
ጌታዬ አምላኬ፣
ታላቅ አምላክ፣
ታላቅ ጌታ፣
ታላቅ ገዥ... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢኤል፣ ኤልያብ] ‘አብ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
አንድ ሰውና አንድ አገር በዚህ ስም ይጠሩ እንደ ነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ ይገኛል፥
. የአዳምና ሒዋን ሁለተኛ ልጅ፥ (ዘፍ 4፡2)
. የቦታ ስም፥ “እርሱ ግን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል፥ ወደ ቤትመዓካ፥ ወደ ቤሪም ሁሉ አለፈ ሰዎችም ደግሞ ተሰብስበው ተከተሉት” (2 ሳሙ
20:14)፣ (2
ሳሙ 20:15)
አቤሜሌክ ~ Ebedmelech, Elimelech: አብደ መላክ፣ አብዴ መላክ፣ አገልጋይ መልእከተኛ፥ ኤል መላክ፣ መልአከ ኤል፣ ያምላክ መልእክተኛ፣ ታላቅ መላክተኛ... ማለት ነው። (የንጉሥ አባት ተብሎም ይተረጎማል። ኪወክ / አ)
[ተዛማጅ ስም - አቢሜሌክ]
Ebedmelech-
‘አብደ’
እና ‘መላክ’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። Elimelech- ‘ኤል’
እና ‘መላክ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [የንጉሥ አገልጋይ
ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:
-
አቤሜሌክ / Ebedmelech:
1. የጌዴዎን ልጅ፥ (መሣ 8:31)
2. በንጉሡ ሴዴቅያስ ዘመን የነበረ፥ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ፥ “በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ
እንዳኖሩት ሰማ...” (ኤር 38፡7-13)
አቤሜሌክ / Elimelech:
የሩት አማት፥ (ሩት 1፡2)
አቤሴሎም ~ Abishalom, Absalom:
አበ ሰላም፣ ታላቅ ሰላም፣ ታላቅ ዕረፍት፣ ረጅም ጸጥታ፣ መረጋጋት የሰፈነበት... ማለት ነው።
‘አብ’ እና ‘ሰላም’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አቤሴሎም / Abishalom:
የመዓካ አባት፥ (1 ነገ 15፡2) ፣
(2
ዜና 11:20፣ 2)
አቤሴሎም / Absalom:
የዳዊት ልጅ፥ (2
ሳሙ 3፡3)
አቤር ~
Heber:
አብር፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዔቦር፣ ሔቤር፣ ዔብሪ፣ ዔቤር፣ ዕብራዊ፣ ኦቦር]
‘አበረ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን፥ ‘ኅብር’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
. በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ (ሉቃ 3:35)
. ከአሴር ነገድ፣ የበሪዓ ልጅ፥ ሔቤር - (ዘፍ 46፡17)
. የሦኮን አባት፥
ሔቤር-
(1 ዜና 4:18)
. ብንያማዊ፥ ሔቤር- (1
ዜና 8:17፣18)
. ሌላ ብንያማዊ፥
ሔቤር-
(መሣ 4:21፣ 22)
. ዔቤር - (1 ዜና 8:22፣23)
አቤሮን ~
Abiram:
አብረን፣ አበርን፣ ተባበርን፣ ኅብረት መፍጠር ማለት ሲሆን፥ ‘አባ ራም፣ ከፍተኛ አባት ማለት ነው፥’ ተብሎም ይተረጎማል።
1. በቆሬ ሙሴን እና
አሮንን ተቃውመው
ከተነሡት፥ ከኤልያብ ልጆች አንዱ፥ “የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከሮቤልም ልጆች የኤልያብ ልጆች
ዳታንና አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን
በሙሴ ላይ
ተነሡ።”
(ዘኍ 16:1)
2. የኢያሪኮን ግንብ መሠረት ሲያበጅ የሞተው፥ የቤቴል ሰው፥ የአኪኤል ትልቁ ልጅ፥
(1 ነገ 16:34) ፤ በነቢዩ በኢያሱ
የተነገረውም ትንቢት
በርሱ ተፈጽሟል።
(ኢያ 6:26)
አቤንኤዘር ~
Ebenezer:
አበነ ዘር፣ አባቴ ወገኔ፣ አባቴ ረዳቴ፣ የአባቶቸ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አቢዔዜር፣ አቢዔዝር]
‘አብነ’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው።
እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጉ የወጡበት
ቦታ፥ “ሳሙኤልም አንድ
ድንጋይ ወስዶ
በምጽጳና በሼን
መካከል አኖረው
ስሙንም። እስከ
አሁን ድረስ
እግዚአብሔር ረድቶናል
ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።”
(1 ሳሙ7፡7-12)
አቤድ ~
Ebed:
አቤድ፣ አብደ፣ አብዲ፣ አገልጋይ፣ ሠራተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አብዲ፣ ዓብዳ]
‘አብደ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
አቤሜሌክን የሰደበ የገዓል አባት፥ (መሣ 9:26 ፣ 30
፣ 31...)
አቤጽ ~
Abez:
ያበጠ፣ ከፍተኛ፣ ጅንን፣ ኩሩ... ማለት ነው። በረቢት እና በቂሶን መካከል የሚገኝ የይሳኮር ድርሻ የሆነ የቦታ ስም፥ “ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥”
(ኢያ 19:20)
አብራም ~
Abram:
አብ ራም፣ አባ ራም፣ ከፍተኛ አባት ማለት ነው።
‘አብ’ እና ‘ራማ’
ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
[ታላቅ አባት ማለት ነው። / መቅቃ]
የታራ ልጅ፣
የእስማኤል አባት፥
የአብርሃም የቀድሞ
ስም፥ (ዘፍ 11:27)
አብርሃም ~
Abraham:
አብ ራሃም፣ ታላቅ አባት፣ ከፍተኛ አባት፣ የብዙዎች
አባት... ማለት ነው።
እስማኤልን ከወለደ
በኋላ፥ ይስሐቅን
ከመውለዱ በፊት
ስሙ ከአብራም
ወደ አብርሃምነት ተቀየረ፥ “ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና:”
(ዘፍ 17:5)
አብዩድ ~
Abihu, Abiud: አቢሁድ፣ አብ ውድ፣ የተወደደ አባት፣ በጣም ተወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አቢሁድ፣ አብዮድ]
‘አቢ’
እና ‘ውድ’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:
-
አብዩድ / Abihu: የአሮን ልጅ፥ ከሙሴና አሮን ጋር ወደ እግዚአብሔር እንዲወጡ ከተመረጡ፥ (ዘጸ 24:1) ፣ አብዮድ- (ዘጸ 6፡23)
አብዩድ / Abiud: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ የዘሩባቤል ልጅ፥ (ማቴ
1:13) ፣ (1
ዜና 8:3)
አብያ ~
Abiah, Abijah, Abijam:
አባ ያሕ፣ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊ ጌታ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
አቢያ]
‘አብ’ እና ያሕ’(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አብያ / Abiah:
1. የነብዮ ሳሙኤል ልጅ፥
(1 ሳሙ 8:2)
2. ከብንያም ወገን፣ የቤኬር ልጅ፥ (1
ዜና 7፡8)
አብያ / Abijah:
1. ከአልዓዛር ወገን፥ “ስምንተኛው ለአብያ፥ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥” (1 ዜና 24፡11)
2. የሮብዓም ልጅ፥ (2 ዜና 12:16) ፣ (1
ነገ 4:21)
3. የኢዮርብዓም ልጅ የመጀመሪያው፥
(1 ነገ 14:1)
4. የኢዮርብዓም ልጅ፥ (ነህ 12:4 ፣ 17) ፣ (1 ዜና 24:10) ፣ (2
ዜና
8:14)
5. በነህምያ ዘመን የነበረ
ካህን፥ (ነህ 10:7)
አብያ /
Abijam:
‘ባሕረኛ፣ መርከበኛ’ ማለት ነው። የሮብዓም ልጅ ሲሆን፥ ስሙ በይሁዳ ነገሥታት ስም ቅጥያ ሆኖ ይሰጣል፥ “የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያም በይሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ።” (1 ነገ 15:1፣7፣8)
አብያሳፍ ~ Abiasaph: አባ
አሰፋ፣ አባ
አስፍቸው፣ ሰፊ
ሕዝብ፣ ታላቅ
አገር፣ የብዙዎች አባት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢሳፍ]
‘አባ’ እና ‘አሰፋ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የቆሬ ልጅ፥
(ዘጸ 6፡24)
አብያታር ~
Abiathar:
አብ ዘር፣ የአባት ወገን፣ ታላቅ ዘር፣ ታላቅ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አቢዔዜር፣ አቢዔዝር]
‘አብ’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ካህኑ የአቢሜሌክ
ልጅ፣ ካህኑ
አብያታር፥ (1 ሳሙ 22፡20)
፣ ከኤሊ
በመቀጠል አራተኛ የሆነ ታላቅ ካህን ነው። ዳዊት ከሳኦል ፊት በተሰደደ ጊዜ አብሮት ተሰዷል። (1 ሳሙ 23:9፥ 30:7 ፥ 2 ሳሙ2:1፥ 5:19)
አብዮድ ~
Abihu:
አበ ውድ፣ አቢዮ፣ አባዬ፣ አባቴ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
አብዩድ]
Abihu-
‘አብዬ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
የሙሴ ወንድም፥ የአሮን ልጅ፥ (ዘጸ 6፡23)
፣ አብዩድ - (ዘጸ 24:1)
አብደናጎ ~
Abednego:
አብዲ ኔጎ፣ አብዲ ነጋ፣ የንጋት አገልጋይ፣ የብርሃን ታዛዥ፣ የብርሃን አገልጋይ ማለት ነው።
‘አብደ’ እና ‘ነጋ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
የባቢሎን ንጉሥ
ናቡከደነፆር ወደ
ኢየሩሳሌም መጥቶ
ከወረረ በኋላ፥
ለተማረኩ እስራኤላውያን የጃንደረቦች አለቃ አስፋኔዝ ለአዛርያ የሰጠው ስም፥ “የጃንደረቦቹም አለቃ
ስም አወጣላቸው
ዳንኤልን ብልጣሶር፥
አናንያንም ሲድራቅ፥
ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።” (ዳን 1:7) ፣ (ዳን 2:49)
አብዲ ~
Abdi:
አገልጋዬ፣ ተላላኪዬ፣ ታዛዤ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓብዳ፣ አቤድ]
‘አብዴ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የቂስ አባት፥ (1 ዜና 6:44)
2. በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ፥ የቂስ አባት፥ (2 ዜና 29:12)
3. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፣ የኤላም ልጅ፥ (ዕዝ 10:26)
አብዲኤል ~ Abdiel: አብደ ኤል፣ የአምላክ አገልጋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አብድያ፣ አብድያስ፣ ዓብድኤል]
‘አብደ’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የጉኒ
ልጅ፥ (1 ዜና 5:15)
አብድዩ ~
Obadiah:
አብደ ያሕ፣ የሕያው አገልጋይ፣ የአምላክ አገልጋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አብዲኤል፣ ዓብዳ ፣ አብድያስ]
Obadiah- ‘አብዲ’
እና ‘ያሕ’ (ያህዌ)
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት
ወስዶ አምሳ
አምሳውን በዋሻ
ውስጥ ሸሽጎ
እንጀራና ውኃ
ይመግባቸው ነበር፥
(1 ነገ 18:3)
2. የይዝረሕያ ልጅ፥ (1 ዜና 7:3)
3. የኤሴል ልጅ፥ (1 ዜና 8:38)
4. የይሒኤል ልጅ፥ (ዕዝ 8:9)
5. ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት በአራተኛ ደረጃ የሆነው፣ ነቢዩ አብድዩ፥ (አብድዩ 1:1)
6. በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥
(1
ዜና 12:9)
7. የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ካተሙት ካህናት፥ “ሜሪሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥
ጌንቶን፥ ባሮክ” (ነህ 10:5፣6)
8. በዛብሎን ላይ አለቃ የነበረ፥ የይሽማያ አባት፥ (1 ዜና 27:19)
9. የኢየሩሳሌም ንጉሥ ኢዮስያስ፣
የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ ዘንድ ካዘዛቸው፥ የሜራሪ ልጅ፥ (2 ዜና 34:12)
10. በዕዝራ ዘመን ከግዞት ከተመለሱት፣ የይሒኤል ልጅ፥ (ዕዝ 8:9)
11. “የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች” (1 ዜና 3:21)
12. የሰሙስ ልጅ፥ (1 ዜና 9:16፣ ነህ 12:25)
. የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሣፍጥ፥ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ካዘዛቸው፣ አብድያስ፥ (2 ዜና 17:7)
አታያ ~
Athaiah:
እጣ ያሕ፣ የሕያው እጣ፣ ያምላክ ሥራ... ማለት ነው። ከባቢሎን
ምርኮ በኢየሩሳሌም
ከተቀመጡ፥ ከይሁዳ
ወገን የሆነ
የዖዝያ ልጅ፥
“ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ
አታያ”
(ነህ 11:4)
አነሜሌክ ~
Anammelech:
አነ መላክ፣ ሐና መላክ፣ መልአከ ሐና... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ሐኒኤል]
አሕዛብ ልጆቻቸውን
ይሠውላቸው ከነበሩ
ጣዖታት፥ “... የሴፈርዋይም ሰዎችም
ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር” (2 ነገ 17:31)
አኒዓም ~ Aniam: ‘የሕዝብ እስትንፋስ’ ማለት ነው። የሸሚዳ ልጅ፥ “የሸሚዳም ልጆች አሒያን፥ ሴኬም፥ ሊቅሒ፥ አኒዓም ነበሩ።”
(1 ዜና 7:19)
አኒኤል ~
Hanniel:
ሐና ኤል፣ የሐና አምላክ፣ እግዚብሔር የሰጠው፣ ይቅር የተባለ... ማለት ነው።
‘ሐና’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው።
ምድሪቱን ርስት አድርገው ለሚከፍሉላችሁ ሰዎች የምናሴ ነገድ ልጆች አለቃ፥ የሱፊድ
ልጅ፥አኒኤል፥ (ዘኁ 34:23)
የአሴር ነገድ አለቃ፣ የዑላ ልጅ፥ ሐኒኤል- (1 ዜና 7:39)
አናሐራት ~ Anaharath:
‘ቃጠሎ’ ማለት ነው። በይሳኮር ድንበር የነበረ ቦታ፥ “ወደ ከስሎት፥ ወደ ሱነም፥ ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺኦን፥ ወደ አናሐራት፥”
(ኢያ 19:19)
አናምኤል ~
Hanameel:
‘የአምላክ በረከት’ ማለት ነው። የሰሎም ልጅ፥ የኤርምያስ
ዘመድ፥ “እነሆ፥ የአጐትህ
የሰሎም ልጅ
አናምኤል ወደ
አንተ መጥቶ።
ትገዛው ዘንድ
መቤዠቱ የአንተ
ነውና በዓናቶት
ያለውን... ” (ኤር 32:7፣8፣9፣12)
አናሲሞስ ~ Onesimus: ‘ጠቃሚ’
ውጤታማ ማለት
ነው። የጳውሎስ
አገልጋይና ተከታይ
የነበረ፥ “ወሬያችንን እንድታውቁና
ልባችሁን እንዲያጽናና፥
ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው። ...” (ቆላ 4:9)
አናኒ ~
Hanani:
ሐናኒ፣ እግዚአብሔር የሰጠው፣ ይቅር የተባለ፣ ጸሎቱ የተሰማ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ዓናኒ፣ ሐናኒ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. ነቢዩ አናኒ፥ “በዚያን ጊዜም
ባለ ራእዩ
አናኒ ...” (2 ዜና 16:1-10)
2. ካህኑ አናኒ፥ “ከኢሜር ልጆችም፤ አናኒና ዝባድያ።” (ዕዝ 10:20)
3. የኢየሩሳሌም ገዥ የነበረው፥
(ነህ 1:2)
4. በመጽሐፈ ነህምያ የተጠቀሰ አናኒ፥ (ነህ 12:36)
. የኤልዮዔናይ ልጅ፥
ዓናኒ፥ (1 ዜና 25:4፣25)
. የሒማን ልጅ
ሐናኒ፥ (1 ዜና 25:4፣25)
አናንያ ~
Hananiah:
ሐናኒ ያሕ፣ ጸጋ እግዚአብሔር፣ ጌታ የሰጠው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ሐናንያ]
‘ሐና’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ
፣ ሕያው) ከሚሉ
ሁለት ቃላት
የተመሠረተ ነው።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም፣ ከወረረ በኋላ ወደ ባቢሎን ከተወሰዱ፥
(ዳን 1:6፣7)
አንቲጳስ ~
Antipas:
‘እንደ አባት ያለ’ ማለት ነው። የሰማዕት ስም፥ “... የሰይጣን
ዙፋን ባለበት
የምትኖርበትን አውቃለሁ፤
ስሜንም ትጠብቃለህ፥
ሰይጣንም በሚኖርበት፥
በእናንተ ዘንድ
የተገደለው የታመነው
ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ
ሃይማኖቴን አልካድህም።” (ራእይ
2:13)
አንቲጳጥሪስ ~ Antipatris: ‘ለአባቱ’
ማለት ነው።
ወታደሮች ጳውሎስን
አስረው የወሰዱበት
ከተማ፥ “ወታደሮቹም እንደ
ታዘዙት ጳውሎስን
ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ አደረሱት” (ሐዋ 23:31)
አንኩስ ~
Achish:
ንዴት፣ ብስጭት... ማለት ነው። በእንግሊዝኛ ‘አኪሽ’ ሲሆን በአማርኛ አንኩስ ነው።
1. የጌት ንጉሥ፥ ዳዊት ሳኦልን ሸሽቶ የሄደበት፥ “ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ሳኦልን ፈርቶ ሸሸ፥ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ።” (1 ሳሙ 21:10-15)
2. ከሳሚ ባሪያዎች ሁለቱ የኮበለሉበት፥ ሌላ የጌት ንጉሥ፥ “ከሦስት ዓመትም በኋላ ከሳሚ ባሪያዎች ሁለቱ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አንኩስ ኰበለሉ ሳሚንም። እነሆ፥ ባሪያዎችህ በጌት ...” (1 ነገ 2:39-46)
አንዲራኒቆ ~ Andronicus: ‘አርበኛ፣ አሸናፊ፣ ገዥ’
ማለት ነው።
የሐዋርያው ጳውሎስ ተከታይ የነበረ አይሁዳዊ ክርስቲያን፥ “በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፥
ደግሞም ክርስቶስን
በማመን ለቀደሙኝ፥
አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን
ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16:7)
አንጋይ ~
Aiath:
የቦታ ስም፥ “ወደ አንጋይ መጥቶአል በመጌዶን በኩል አልፎአል በማክማስ ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል”
(ኢሳ 10:28)
አንጾኪያ ~
Antioch:
ያገር ስም፥ “ከእነርሱ ግን የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የነበሩት
አንዳንዶቹ ወደ
አንጾኪያ መጥተው
የጌታን የኢየሱስን
ወንጌል እየሰበኩ
ለግሪክ ሰዎች
ተናገሩ።”
(ሐዋ 11:20፣21)
አኪ ~
Ahi, Ehi: አያ፣ ወንድም፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም- ወንድም]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አኪ / Ahi: የሳሜርም ልጅ፥ “የሳሜርም ልጆች አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሑባ፥ አራም
ነበሩ፥”
(1 ዜና 7:34)
አኪ / Ehi: ከብንያም ነገድ የቤላ ልጅ፥ (ዘፍ 46፡21)
. ወንድም - (1 ዜና 5፤15)
አኪመን ~
Ahiman:
አያ አምን፣ የታመነ ወንድም፣ ሰላማዊ ጓደኛ፣ መልካም ወዳጅ፣ ታማኝ ወንድም... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:- ሐማ፣ ሄማን፣ አሒማን፣ አማና፣ አሜን፣ አሞን፣ ያሚን]
Ahiman- ‘አያ’
እና ‘አመነ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. የዔናቅ ልጅ፥ “...በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ...” (ዘኁ 13፡22)
. አሒማን-(1ዜና 9:17)
አኪማአስ ~ Ahimaaz: አያ ዐመፅ፣ ዐማፂ ወንድም...
ማለት ነው።
1.
በንጉሥ ዳዊት
ጊዜ የነበረ፥
የሊቀ ካህኑ
የሳዶቅ ልጅ፥
“ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፦ እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማአስ የአብያታርም ልጅ ዮናታን ሁለቱ ልጆቻችሁ
በደኅና ወደ
ከተማ ተመለሱ” (2 ሳሙ 15:24-37; 17:15-22)
2. የሳኦል ሚስት፣ የአኪናሆም
አባት፥ “የሳኦልም ሚስት
ስም የአኪማአስ ልጅ አኪናሆም ነበረ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት ...” (1
ሳሙ 14:50)
3.
የንጉሥ ሰሎሞን
ልጅ፣ የባስማት
ባል፥ “በንፍታሌም አኪማአስ ነበረ፥ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶ ነበር” (1 ነገ 4:15)
አኪም ~
Achim:
አቂም፣ ቂም፣ ማቄም፣ በደልን ማሰብ... ማለት ነው። በጌታ የዘር
ሐረግ የተጠቀሰ፥
የሳዶቅ ልጅ፥
“አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤
ሳዶቅም አኪምን
ወለደ፤ አኪምም
ኤልዩድን ወለደ” (ማቴ 1:14)
አኪሞት ~
Ahimoth:
አሂሞት፣ አያ ሞት፣ አያሞቴ፣ እስከሞት የሚጸና ወንድም፣ ብርቱ ወዳጅ፣ ሐቀኛ ወንድም... ማለት ነው። (‘አያ መአት’ ሲሆን ታላቅ ወንድምና ብዙነህ
ተብሎ ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስም-
የማአት]
‘አያ’ እና ‘ሞት’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. የሕልቃና ልጅ፥ “የሕልቃናም ልጆች አማሢ፥ አኪሞት።” (1 ዜና 6፡ 25)
. የማአት - (ሉቃ 3:26)
አኪሳአር ~
Ahishahar:
‘የንጋት ልጅ’ ማለት ነው። የቢልሐን ልጅ፥ “የይዲኤልም ልጅ
ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም
ልጆች የዑስ፥
ብንያም፥ ኤሁድ፥
ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ።” (1 ዜና 7:12)
አኪራ ~ Ahiram: ታላቅ፣
የተከበረ ወንድም... ማለት
ነው። የብንያም
ልጅ፥ የአኪራናውያን ወገን፥ “የብንያም ልጆች በየወገናቸው ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ ከሶፋን የሶፋናውያን ወገን” (ዘኊ 26:38)
አኪሬ ~ Ahira: ‘ቂመኛ ወንድም’
ማለት ነው። ከንፍታሌም ወገን፥ የዔናን ልጅ፥ “ከንፍታሌም የዔናን ልጅ አኪሬ” (ዘኊ 1:15፤ 2:29፤ 7:78፣83፤ 10:27)
አኪቃም ~ Ahikam: አያ ቁም፣ ቋሚ ወንድም፣ ብርቱ ወንድም፣ ጽኑ ወዳጅ፣ ቋሚ መከታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
Ahikam- ‘አያ’
እና ‘ቆመ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የጸሐፊው የሳፋን ልጅ፥ (2 ነገ 22፡12-14፣ 2
ዜና 34:20)
አኪናሆም ~
Ahinoam:
አሂ ናዖም፣ አያ ናዖሚ፣ የናዖሚ ወንድም፣ ቅን ወንድም፣ ትሑት ጓደኛ... ማለት ነው።
Ahinoam- ‘አያ’
እና ‘ናሆም’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የአኪማአስ ልጅ የሳኦል ሚስት፥ አኪናሆም ፥ (1 ሳሙ 14፡50)
2. ኢይዝራኤላዊቱ የዳዊት ሚስት፥
(1 ሳሙ 25:43፣ 27:3)
አኪኤል ~
Hiel:
አያኤል፣ ኃይል፣ ኃያል፣ ብርቱ፣ ጠንካራ... ማለት ነው። ኢያሪኮን የሠራ የቤቴል ሰው፥ (1 ነገ 16፡34)
አኪዔዘር ~
Ahiezer:
አያ ዘር፣ ወንድም ወገን፣ ረዳት ወንድም፣ አጋዥ፣ ተባባሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አሒዔዝር]
Ahiezer- ‘አያ’
እና ‘ዘር’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የወጡ ከዳን የአሚሳዳይ ልጅ፥ (ዘኁ 1፡12)፣ (ዘኁ 2:25፤10:25)
. አሒዔዝር- (1 ዜና 12:3)
አኪያ ~
Ahiah, Ahijah: አያያ፣ አያ’ያሕ፣ አያ ሕያው፣ የጌታ ወንድም፣ የሕያው ወዳጅ፣ የጌታ ተባባሪ... ማለት ነው።
Ahiah, Ahijah- ‘አያ’
እና ‘ያሕ’
(ያሕዌ ፣
ሕያው)
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረቱ ስሞች ናቸው። [እግዚአብሔር ወንሜ ነው ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
አኪያ / Ahiah:
1. የኢካቦድ ወንድም፣ የአኪጦብ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ፣ የዔሊ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን፥
(1 ሳሙ 14:3 18)
2. የኤሁድ ልጆች በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ወደ መናሐትም ከተማረኩ፥
(1 ዜና 8፡7)
3. በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን የነበረ ጸሐፊ፣ የሴባ ልጅ፥ (1 ነገ 4:3)
አኪያ / Ahijah:
1. ነቢዩ አኪያ፥ (1 ነገ 14:2)
2. ከይሳኮር ቤት የባኦስ አባት፥ (1 ነገ 15:27 ፣ 33)
3. የይረሕምኤል ልጅ፥ (1 ዜና 2:25)
4. የዳዊት ወታደር፣ ፍሎናዊው አኪያ፥ (1 ዜና 11:36 ፣37)
5. በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ
የተሾመ፥ (1 ዜና 26:20)
6.
በነህምያ ዘመን ቃልኪዳኑን ካተሙት ከሌዋውያኑ ወገን፥ (ነህ 10:26)
አኪጦብ ~
Ahitub:
አያ ጡብ፣ አያ ዕጹብ፣ ጥሩ ወንድም፣ መልካም ወዳጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች:-
ጦብያ፣ ጦብ፣ ጦባዶንያ]
Ahitub- ‘አያ’
እና ‘ጹብ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የፊንሐስ ልጅ፥ (1 ሳሙ 14:3)
2. የአማርያ ልጅ፣ የሳዶቅ አባት፥ “አማርያም አኪጦብን ወለደ አኪጦብም ሳዶቅን
ወለደ ሳዶቅም
አኪማአስን ወለደ፥” (1 ዜና
6:7፣ 8) ፣ (2
ሳሙ 8:17)
አኪጦፌል ~ Ahithophel: አያ ጥፈ ኤል፣ የጥፋት ኃይል ወንድም... ማለት ነው። የዳዊት
መካር የነበረ
የጊሎ ሰው፥
“በዚያም ወራት የመከራት
የአኪጦፌል ምክር የእግዚአብሔርን ቃል
እንደ መጠየቅ
ነበረች የአኪጦፌልም
ምክር ሁሉ
ከዳዊትና ከአቤሴሎም
ጋር እንዲህ
ነበረች።”
(2 ሳሙ 16:23)
አካ ~ Achan: ‘ጠብአጫሪ፣ ተንኮለኛ፣
ነውጠኛ፣ በጥባጭ’ ማለት
ነው። እርም
የሆነ ነገር
የተገኘበት ሰው፥
የእግዚአብሔርን ቃል
ኪዳን አፍርሶና፥
በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት የተቃጠለ፥ የዛራ ልጅ፥
“ዘንበሪም ተለየ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።” (ኢያ 7:19-26)
አካዝ ~
Ahaz:
አያዘ፣ አያ ያዝ፣ ያዘ፣ ደገፈ፣ ተቆጣጠረ... ማለት ነው። የኢዮአታም ልጅ፥ የይሁዳ ንጉሥ አካዝ ፥ (2 ነገ 16 ፣ ኢሳ 79-9)
የሚካ ልጅ፥
(1 ዜና 8፡35)
አካዝ ~ Achaz: ያዥ፣
ወሳጅ፣ ተረካቢ፣
ተቀባይ...
ማለት ነው።
በጌታ የዘር ሐረግ
የተጠቀሰ፥ የሕዝቅያስ
አባት፥ “አካዝም ሕዝቅያስን
ወለደ፤ ሕዝቅያስም
ምናሴን ወለደ፤
ምናሴም አሞፅን ወለደ፤” (ማቴ1:9)
አካዝያስ ~
Ahaziah:
አያዝ ያሕ፣ ያዘ ያሕ፣ በጌታ የተያዘ፣ አምላክ የጠበቀው፣ በጌታ እጅ ያለ፣ አምላክን ያመነ... ማለት ነው።
Ahaziah- ‘አሃዘ’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ)
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የአክዓብ ልጅ፥ ንጉሡ አካዝያስ፥ (1 ነገ 22:40) ፣ (2 ዜና 20፡35)
2. የኢዮራም ልጅ ፥ (2 ነገ 8:24-29 ፣ 9:29) ፣ (2
ዜና 21:17፥
25:23) ፣ (2
ዜና 22:6)
አካዝያስ ~
Jehoahaz:
ያሕ ያዝ፣ በአምላክ የተያዘ፣ የሕያው ታዛዥ... ማለት ነው።
1. የይሁዳ ንሱሥ፥ የኢዮራም ትንሹ ልጅ፥ “ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ... ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አልቀረለትም።” (2 ዜና
21:17፥ 22:1፣6፣8፣9)
2. በኢዩ የተተካ የእስራኤል ንጉሥ፥ ኢዮአካዝ፥ “ኢዩም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ ... ። በፋንታውም ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ።” (2 ነገ 10:35)
3. በአባቱ የተተካ፣ ለሦስት ወር የነገሠ፥ የይሁዳ ንጉሥ፥ አካዝያስ፥ “ልጁ አሳ፥
... ልጁ ኢዮራም፥
ልጁ አካዝያስ፥
ልጁ ኢዮአስ፥” (1 ዜና
3:11)
አካይቆስ ~
Achaicus:
‘የጣር፣ የመከራ ልጅ፥ የአካይ ሰው’ ማለት ነው። ወደ ፓውሎስ
ከመጡ ሦስት
ክርስቲያኖች አንዱ፥
“በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም መምጣት ደስ ይለኛል፥ ...” (1 ቆሮ 16:17)
አካይያ ~ Achaia: ‘ጠብአጫሪ፣ ጭንቅ ፈጣሪ፣ መከራ፥
ሥቃይ’
ማለት ነው።
አይሁድ ጳውሎስን
በተቃወሙበት ጊዜ፥
በመቄዶንያ አዋሳኝ
የጋልዮስ ግዛት
የነበረ አገር፥
ከአቴንስ ግሪክ
በስተምዕራብ የሚገኝ፥
“ጋልዮስም በአካይያ አገረ
ገዥ በነበረ
ጊዜ፥ አይሁድ
በአንድ ልብ
ሆነው በጳውሎስ
ላይ ተነሡ፥
ወደ ፍርድ
ወንበርም አምጥተው።”
(ሐዋ 18:12፣19:21፥ ሮሜ 15:26፥ 16:5፤ 1 ቆሮ 16:15፤ 2
ቆሮ 7:5፥ 9:2፤ 11:10፤ 1 ተሰ 1:7፣8)
አኬልዳማ ~
Aceldama:
አካለ ደም፣ የደም ክፍል፣ ቀይ መሬት፣ ደም መሬት... ማለት ነው።
‘አካል’ እና ‘ደም’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ የቦታ ስም ነው።
[የደም መሬት
ማለት ነው።
/ መቅቃ]
ይሁዳ በዐመፅ ገንዘብ የገዛው
መሬት፣ በዚያም
ተደፍቶ ሞተ፥
“በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው።” (ሥራ 1፡19)
አክሞናዊ ~ Hachmoni: ‘አኪም፣ ጠቢብ ሰው’
ማለት ነው።
ያሾብአም አባት፥
“የዳዊትም ኃያላን ቍጥር
ይህ ነበረ
የሠላሳው አለቃ
የአክሞናዊው ልጅ
ያሾብአም ነበረ
እርሱ ጦሩን
አንሥቶ ሦስት
መቶ ሰው
በአንድ ጊዜ
ገደለ።”
(1 ዜና 11:11)
አክሪጳ ~
Archippus:
ፈረሰኛ ማለት ነው። በቆላሲያ የክርስትና መምህር የነበረ፥ “ለአክሪጳም። በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ።”
(ቆላ 4:17)
አክራትዮስ ~ Hatach:
‘በእውነት’
ማለት ነው።
ከንጉሥ አርጤክስስ
ጃንደረባዎች አንዱ፥ “አስቴርም ያገለግላት ዘንድ ንጉሡ ያቆመውን አክራትዮስን ጠራች እርሱም ከጃንደረቦች አንዱ ነበረ፥ ....” (አስ 4:5፣6፣9፣10)
አክርጳ ~ Carpus: ‘ፍሬያት፣ ፍሬያማ’ ማለት
ነው። በጢሮአዳ
የነበረ ክርስቲያን፥
“ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ... በብራና ... አምጣልኝ” (2 ጢሞ 4:13)
አክዓብ ~
Ahab:
አያ አብ፣ የአባት ወንድም፣ አጎት... ማለት ነው።
Ahab- ‘አያ’
እና ‘አብ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[የአባት ወንድም
ማለት ነው /
መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የዘንበሪ ልጅ፣ በእስራኤል ላይ በአባቱ ፋንታ የነገሠ አክዓብ፥ (1 ነገ 16፡28)
2.
የቆላያ ልጅ፣ አሰተኛ ነቢይ፥ (ኤር 29:21)
አክዚብ ~ Achzib:
‘ቅጥፈት፣ ስሕተት፣ ክህደት፣ ውሸት’ ማለት ነው።
1. በይሁዳ ግዛት ያለ
የከተማ ስም፥
“ንጺብ፥ ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ
15:44፤ ሚክ 1:14)
2. የአሦር ግዛት የሆነ
ከተማ፥ “ድንበሩም ወደ
ራማ፥ ወደ
... ዞረ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ” (ኢያ 19:29)
አክዚብ ~ Nezib: ‘ዘብ፣ ምሰሶ፣
ዋልታ’
ማለት ነው።
የይሁዳ ከተማ፥
“ንጺብ፥ ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።” (ኢያ 15:44)
አኮር ~
Achor: ‘ጭንቅ፣ መከራ’ ማለት ነው። በኢያሪኮ ያለ ሸለቆ፥ “ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ... ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ
አመጡአቸው።”
(ኢያ 7:24፣26)
አኮዘት ~
Ahuzzath:
አያ ያዘት፣ ያዥ ወንድም፣ ደጋፊ ወንድም... ማለት ነው።
Ahuzzath-
‘አያ’ እና ‘ይዘት’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
ከጌራራ በአቢሜሌክ አስተዳደር ውስጥ አማካሪ የነበረ፥ የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት፥ (ዘፍ 26:26)
አዋና ~
Ava:
ሂዋ፣ ህያዋ፣ ሕያው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ሄልዮ፣ አዌን]
በሰማርያ ከተሞች
ከሰፈሩ፥ “የአሦርም ንጉሥ
ከባቢሎንና ከኩታ
ከአዋና ከሐማት
ከሴፈርዋይም
ሰዎችን አመጣ፥
በእስራኤልም ልጆች
ፋንታ በሰማርያ
ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት በከተሞችዋም ተቀመጡ።” (2 ነገ 17፡24) ፣ (2 ነገ
18:34 ፣ 19:13
፣ ኢሳ 37:1)
አዌን ~
Aven:
ሒዋን፣ ሕያዋን፣ ዘላለማውያን፣ ጻድቃን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሄልዮ፣ አዋና]
‘ሓይወ’ ከሚለው ቃል የተገኘ
ስም ነው።
. እስራኤላዊያን የጣዖት አምልኮ ይፈጽሙባቸው ከነበሩ ቦታዎች፥ (1 ነገ 12:28)
. የሶርያ ሕዝብ የነበረበት አገር፥ “የደማስቆንም መወርወሪያ እሰብራለሁ፥ ተቀማጮችንም ከአዌን ሸለቆ አጠፋለሁ፥ በትር የያዘውንም ከዔደን ቤት
አጠፋለሁ፥ የሶርያም ሕዝብ ወደ ቂር ይማረካል፥ ይላል እግዚአብሔር፦” (አሞ
1:5)
. ሌላ የቦታ
ስም፥ የሄልዮ- (ሕዝ 30፡17)
አውሴ ~
Oshea:
ዋስትና፣ ድኅነት፣ ነጻነት’ ማለት
ነው። ‘ዋሴ’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። የነዌ ልጅ፥
“ከኤፍሬም ነገድ የነዌ
ልጅ አውሴ” (ዘኊ 13:8) ፤ “ምድሪቱን ይሰልሉ
ዘንድ ሙሴ
የላካቸው ሰዎች
ስም ይህ
ነው። ሙሴም
የነዌን ልጅ
አውሴን ኢያሱ
ብሎ ጠራው” (ዘኊ 13:16)
አውናም ~ Onam: ‘ብርቱ ጠንካራ’ ማለት ነው።
1. የሦባል ልጅ፥ “የሦባል ልጆችም እነዚህ ናቸው ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥
አውናም።”
(ዘፍ 36:23፤ 1 ዜና 1:40)
2.
የይረሕምኤል ከዓጣራ የወለደው ልጅ፥ ኦናም፥ “ለይረሕምኤልም ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው እርስዋም የኦናም እናት ነበረች።” (1 ዜና 2:26፣28)
አውዛል ~
Uzal:
‘ከርታታ፣ ዘላን’ ማለት ነው። የዮቅጣን ልጅ፥ “ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥
አውዛልንም፥”
(ዘፍ 10:27፤ 1 ዜና 1:21)
አውግስጦስ ~
Augustus:
ጠቅላይ፣ ትልቅ፣ ጉልህ፣ ታዋቂ... ማለት ነው። ጌታ ሲወለድ በፍልስጥኤም ንጉሥ የነበረ፥ “በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።”
(ሉቃ 2:1)
አውጤኪስ ~ Eutychus: ‘በዕድሉ’
ማለት ነው።
በመስኮት ላይ
ተቀምጦ የጳውሎስን
ትምህርት ሲያዳምጥ፥
እንቅልፍ ወሰደውና
ተንከባሎ ወድቅ
ሞተ፥ በታምር
ግን ነፍስ
ዘርቶ ተነሣ፥
“አውጤኪስ የሚሉትም አንድ
ጎበዝ በመስኮት
ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት” (ሐዋ 20:9)
አዚፍ ~
Achshaph:
ስሜት፣ ፍላጎት፣ ጉጉት ማለት... ነው። በአሴር ግዛት የሆነ
የከተማ ስም፥
“ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥
ቤጤን፥ አዚፍ” (ኢያ
19:25) ፤ ቀደም ብሎ የከነናውያን ነገሥታት መቀመጫ ነበር፥ (ኢያ 11:1፤ 12:20)
አዛሄል ~
Hazael:
‘አምላክ ያየው’ ማለት ነው። አምላክ ኤልያስን፥ በሶርያ ቀብቶ
እንዲያነግሠው፥ ያዘዘው፥
“እግዚአብሔርም አለው፦ ሂድ፥
... ከዚያም በደረስህ
ጊዜ በሶርያ
ላይ ንጉሥ
ይሆን ዘንድ
አዛሄልን ቅባው” (1 ነገ
19:15)
አዛር ~ Azor: ዘር፣
ወገን፣ ረዳት... ማለት
ነው። በጌታ
የዘር ሐረግ፥
የኤልያቄም ልጅ፥
“ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤
አብዩድም ኤልያቄምን
ወለደ፤ ኤልያቄምም
አዛርን ወለደ፤” (ማቴ 1:13፣14)
አዛርኤል ~ Azareel: አዛረ ኤል፣ ዘረ ኤል፣ የአምላክ ዘር፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አልዓዛር፣ አዛርያ፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል]
‘ዘር’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. “ቆርያውያን ሕልቃና፥ ይሺያ፥ አዛርኤል፥ ዮዛር፥ ያሾቢአም” (1 ዜና
12:6)
2. የይሮሐም ልጅ፥ (1 ዜና 27:22)
. በሽሽቱ ዘመን ከዳዊት ጋር የተቀላቀለ፥ ኤዝርኤል- (ነህ 12፡36)
. ኤዝርኤል- (ዕዝ 10:41)
አዛርያ ~
Azariah:
ዘረያሕ፣ ዘረ ሕያው፣ ሕያው ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የአምላክ ቤተሰብ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - አልዓዛር፣ ዓዛሪያስ፣ ዓዛርያስ፣ ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዛሪያስ፣ ዔዛርያስ፣ ዓዝርኤል፣ ኤሊሱር፣ ኤሊዔዘር፣ አልዓዛር፣ ኤልዓዘር፣ አዛርኤል፣ አዛርኤል]
‘ዘር’ እና ‘ያሕ’
(ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የኤታን ልጅ፥ “የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ” (1 ዜና 2:8)
2. የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ
ኢየሩሳሌም መጥቶ
ማርኮ ከወሰዳቸው፥
(ዳን 1:6፣ 7 ፣ 11 ፣ 16)
አዛንያ ~
Azaniah:
አዝነ ያሕ፣ እዘነ ያሕ፣ አምላክ የሰማው፣ ጌታ የሰማው፣ ጌታ ያዘነለት፣ ጸሎቱ የተሰማ... ማለት ነው።
‘እዝን’ እና ‘ያሕ’ (ያህዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የኢያሱ
አባት፥ ሌዋውያኑ
አዛንያ፥ (ነህ 10፡9)
አዛጦን ~ Ashdod: ‘ጽኑ፣ ብርቱ ምሽግ’
ማለት ነው።
“አዛጦንና የተመሸጉና
ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።” (ኢያ 15:47፤ ሐዋ 8:40)
አዛጦን ~ Azotus: ‘ብርቱ ምሽግ’ ማለት
ነው። “አዛጦንና የተመሸጉና
ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።” (ኢያ 15:47፤ ሐዋ 8:40)
አያ፣ ኢዮሄል ~ Aiah: ‘ጥሪ፣ ይግባኝ’ ማለት ነው።
1. የዘቢዮን ሚስት፥ “የሦባል ልጆች ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም።
የጽብዖንም ልጆች
አያ፥ ዓና።”
(1 ዜና 1:40)
2. የሳኦል ቁባት፥ የሪጽፋ አባት፥ “ለሳኦልም የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው
ኢያቡስቴም አበኔርን፦
ወደ አባቴ
ቁባት ለምን ገባህ?
አለው።”
(2 ሳሙ 3:7፥ 21:8፣10፣11)
አይሁዳዊቱ ~ Jehudijah, Jewess:
ይሁድ ያሕ፣ ያይሁድ አምላክ፣ አምላከ እስራኤል፣ ያቆብአዊ፣ ይሁዳዊ... ማለት ነው።
Jehudijah- ‘ይሁዲ’ እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
አይሁዳዊቱ / Jehudijah:
ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ ቢትያ፥(1ዜና 4፡18)
አይሁዳዊቱ / Jewess:
የጢሞቴዎስ እናት፥ (ሥራ 16፡1)
አይሁድ ~Jew, Jewish: ይሁዳ፣ ውህዲ፣ ይሁዲ፣ አይሁዳዊ... ማለት ነው።
አይሁድ / Jew: “በዚያም ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን ኤላትን ወደ ሶርያ መለሰ፥ አይሁድንም ከኤላት አሳደደ ...” (2 ነገ 16:6)
አይሁድ / Jewish:
እስራኤላውያን፥ “ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ
ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ
የሚሉትን ሰዎች
ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥
በሃይማኖት ጤናሞች
እንዲሆኑ በብርቱ
ውቀሳቸው።”
(ቲቶ 1፡14)
አደራሜሌክ ~
Adrammelech:
አድራ ማሌክ፣ የአደራ መላክ፣ ጠባቂ መልአክ፣ ረዳት
መልአክ፣ ታላቅ
መልእክተኛ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም-
አድራሜሌክ]
‘አደራ’ እና ‘መላክ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. የአሦር ንጉሥ የሰናክሬ ልጅ፥ (2 ነገ 19:37) ፣ የአሦር ንጉሥ የሰናክሬ ልጅ፥ (ኢሳ 37:38)
. አድራሜሌክ- (2 ነገ 17፡31)
አዱሚም ~
Adummim:
ደማም፣ ደም የመሰለ፣ ቀይ አፈር፣ ቀይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አዱሚም፣ አዳሚ፣ አዳማ፣ አዳም]
‘ደማም’
ከሚልው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያቸው ያለ ድንበር፥ (ኢያ 15፡7)
አዱሚም ~ Adummim: ደማደም፣ ቀይ፣ አፈርማ... ማለት ነው። “ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በወንዙ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ተመለከተ ...”
(ኢያ 15:7)
አዳሚ ~
Adami:
አዳሜ፣ አደሜ፣ ወገኔ፣ ዘመዴ፣ ደማዊ፣ ቀይ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አዱሚም፣ አዳማ፣ አዳም]
‘ደሜ’ ከሚለው ቃል የመጣ ቦታ ስም ነው።
የንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ርስት የተሰጠ ድንበር፥ “ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም
ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ...” (ኢያ 19፡33)
አዳማ ~ Adamah, Admah: አደማ፣ አደም፣ ቀይ፣ አፈራማ ፥ ደማዊ፣ ወገን፣ ዘመድ፣ ተወላጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አዱሚም፣ አዳሚ፣ አዳም]
‘አደም’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታዎች:-
አዳማ / Adamah,
Admah: በጢባሮስ ወንዝ በስተምዕራብ የንፍታሌም ድንበር፥ (ኢያ 19:36)
አዳማ /
Admah: የከነዓን ድንበር፥ (ዘፍ 10፡19)
አዳም ~
Adam:
አደመ፣ አደም፣ አዳም፣ ደማም፣ ቀይ፣ ደማዊ፣ እስትንፋስ ያለው፣ ሕያው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አዱሚም፣ አዳሚ፣ አዳማ]
‘ደም’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም
ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ሰዎች አሉ።
. እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው የመጀመሪያው ሰው፥ (ዘፍ 2፡19)
. የሰው ዘር ሁሉ አዳም ተብሎ ይጠራል፥ “የአዳም ... እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው” (ዘፍ 5፡1)
. አዳም የሚለው መጠሪያ ሔዋንንም ያጠቃላላል፥ “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም።
ስማቸውንም በፈጠረበት
ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው”
(ዘፍ 5:2)
አዳር ~ Adar, Tebeth: ‘ከፍታ፣ ልዕልና’ ማለት ነው፥ በይሁዳ
ደቡባዊ ድንበር ያለ ቦታ፥ “ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥
በቃዴስ በርኔ
ወደ ደቡብ
በኩል ወጣ፥
በሐጽሮንም በኩል
አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥” (ኢያ 15:3)
አዳር / Tebeth:
እጹባት፣ እጹባት፣ ውቦች፣ መልካሞች ማለት ነው። የአይሁድ
የወር ስም፥
“አርጤክስስም በነገሠ በሰባተኛው
ዓመት አዳር በሚባለው በአሥራ ሁለተኛው ወር አስቴር ወደ ንጉሡ ቤት ተወሰደች” (አስ 2:16)
አዳን ~ Addan, Addon: አዳን፣ የዳን፣ ኤደን፣ ደን... ማለት ነው።
‘ደን’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
አዳን / Addan:
ከሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፥ (ዕዝ 2፡59)
አዳን / Addon:
(ነህ 7:61)
አዳያ ~Adaiah: በሕያው የተወደደ ማለት ነው። ‘ውድ’
እና ‘ያሕ’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
1.
በኢየሩሳሌም የነገሠ፣
የኢዮስያስ የእናቱ
አባት፥ “ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ከባሱሮት የሆነ የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች” (2 ነገ 22:1)
2.
የአሳፍ ቅድመ
አያት፥ “የዓዳያ ልጅ፥
የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥”
(1 ዜና 6:42)
3.
ብንያማዊው፥ የሰሜኢ ልጅ፥ “ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ፥
ሺምራት፥ የሰሜኢ
ልጆች”
(1 ዜና 8:21)
4.
ካህኑ፥ “የመልኪያ ልጅ የጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ
የሜሱላም ልጅ
የየሕዜራ ልጅ
የዓዲኤል ልጅ
መዕሣይ”
(1 ዜና 9:12፤ ነህ 11:12)
5.
የመዕሤያ አባት፥ “በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን
ልጅ ዓዛርያስን፥
... የዓዳያንም ልጅ
መዕሤያን፥ የዝክሪንም
ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።” (2 ዜና 23:1)
6.
ከግዞት ከተመለሰኡ፣ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የባኒ ልጅ፥ “ከባኒ ልጆችም፤ ሜሱላም፥
መሉክ፥ ዓዳያ፥
ያሱብ፥ ሸዓል፥
ራሞት።”
(ዕዝ 10:29)
7.
ከግዞት ከተመለሰኡ፣ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የባኒ ልጅ፥ “ሰሌምያ፥ ናታን፥
ዓዳያ፥ መክነድባይ” (ዕዝ 10:39)
8.
የይሁዳ ወገን፥ የፋሬስ ልጅ፥ “የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ
የዓዳያ ልጅ
የዖዛያ ልጅ
...የባሮክ ልጅ
መዕሤያ።”
(ነህ 11:5)
አድማታ ~ Admatha: ‘ከጌታ የተሰጠ’ ማለት ነው። ከሰባቱ
የፋርስ ካህናት
አንዱ፥ “በመንግሥቱም ቀዳሚዎች
ሆነው የሚቀመጡ
የንጉሡ ባለምዋሎች
ሰባቱ የፋርስና የሜዶን መሳፍንት አርቄስዮስ፥ ሼታር፥ አድማታ ... ሳሉ” (አስ 1:14)
አድራሚጢስ ~ Adramyttium: ‘የሞት ችሎት’ ማለት
ነው። ሐዋርያው
ጳውሎስ በጉዞው
ካለፈባቸው የእስያ
አገሮች፥ የቦታ
ስም፥ “በእስያም ዳርቻ ወዳሉ ስፍራዎች ይሄድ ዘንድ ባለው በአድራሚጢስ መርከብ ገብተን ተነሣን፤ የመቄዶንያም
ሰው የሆነ
የተሰሎንቄው አርስጥሮኮስ
ከእኛ ጋር ነበረ።”
(ሐዋ 27:2)
አድራሜሌክ ~ Adrammelech: አድራ
ማሌክ፣ የአደራ
መልአክ፣ ጠባቂ
መልአክ፣ ረዳት
መላክ፣ የተከበረ
መልእተኛ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም-
አደራሜሌክ]
‘አደራ’ እና ‘መላክ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. ከአሕዛብ አማልክት
አንዱ፥ “...ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር” (2 ነገ 17፡31)
. የአሦር ንጉሥ የሰናክሬም ልጅ፥ አደራሜሌክ- (2 ነገ 19:37 ፣ ኢሳ
37:38)
አድርአዛር ~ Hadadezer, Hadarezer: የተወደደ ዘር፣ ወገን... ማለት ነው። የረአብን ልጅ የሱባ ንጉሥ፥ (2 ሳሙ 8:3-12፤ 1 ነገ 11:23)
“ዳዊትም ደግሞ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ የረአብን ልጅ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን መታ።”
አዶራም ~ Jehoram: ‘አምላክ ያከበረው’ ማለት ነው።
1.
አባቱ የደስታ መግለጫ ወደ ዳዊት የላከው፥ የሐማት ንጉሥ፥ የቶዑ ልጅ፥ “ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ድል ስለ መታ ቶዑ ልጁን አዶራምን ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ፥ ....” (2 ሳሙ 8:10)
2.
“ወንድሞቹም ከአልዓዛር ልጁ ረዓብያ፥ ልጁም የሻያ፥ ልጁም ኢዮራም፥ ልጁም ዝክሪ፥ ልጁም ሰሎሚት መጡ።” (1 ዜና 26:25)
3.
“ኤልያስም እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሞተ። ልጅም አልነበረውምና በይሁዳ ንጉሥ በኢዮሣፍጥ ልጅ በኢዮራም በሁለተኛው ዓመት ወንድሙ ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ” (2 ነገ 1:17፥ 3:1)
4.
የአካብ ልጅ፥ “ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ...” (2 ዜና 21:5፣20፤ 2 ነገ 8:16)
አዶኒራም ~ Adoniram, Adoram: አዳኒ ራም፣ ታላቅ አዳኝ... ማለት ነው።
‘አዳነ’ እና ‘ራማ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
አዶኒራም / Adoniram:
በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ፣ የዓብዳ ልጅ፥ (1 ነገ 4:6)
አዶኒራም / Adoram:
(2 ሳሙ 20፡24)
፣ (1 ነገ 12:18)
አዶኒቃም ~
Adonikam:
አዳኒ ቋሚ፣ ቋሚ አዳኝ፣ ቋሚ ተጠሪ፣ ጌታ ያጸናው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
‘አዳነ’
እና ‘ቆመ’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ
ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች አባት፥ (ዕዝ 2፡13)
አዶኒቤዜቅ ~ Adoni-bezek:
አዶናይ በዚቅ፣ ኃያል አዳኝ፣ የብርሃን ጌታ፣ የነጸብራቅ አምላክ... ማለት ነው።
‘አዳነ’ እና ‘በዚቅ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
ኢያሱ ከሞተ በኋላ ይሁዳ እግዚአብሔር ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ከሰጣቸው፥ የከነዓውያን ከተማ፥ (መሣ 1፡4-7)
አዶኒጼዴቅ ~ Adoni-zedek:
አዶናይ ዛዲቅ፣ አዳኝ ጻድቅ፣ እውነተኛ አዳኝ፣ እውነትኛ መሓሪ፣ ፍቱን መድኃኒት... ማለት ነው።
‘አዳነ’ እና ‘ጻድቅ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ “እንዲህም ሆነ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ ...” (ኢያ 10፡1)
አዶንያስ ~
Adonijah:
አዳኝ ዋስ፣ አዶና ያሕ፣ ሕያው አዳኝ፣ ዘላለማዊ መድኃኒት፣ ዘላቂ መፍትሄ፣ ሕያው አዳኝ... ማለት ነው።
Adonijah-
‘አዳኒ’ እና ‘ያሕ’
(ያሕዌ)
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከአጊት የተወለደው፣ የንጉሥ ዳዊት ልጅ፥ (2 ሳሙ 3፡4)
2.
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ከላካቸው፥ (2 ዜና 17:8)
3.
የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተሙት፥ ከሌዋውያን፥ (ነህ 10:16)
አገልጋይ ~
Minister:
ቤተኛ፣ ውስጥ ዐዋቂ፣ ምሥጢረኛ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም- ሎሌ]
Minister- ሚኒስትር፣ ምሥጥረኛ፣ ለጌታው የቀረበ፣ ውስጥ ዐዋቂ፣ መልእክተኛ፣ አገልጋይ፣
ሎሌ ማለት ነው።
. ሹማምንት፥ “ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር” (2 ሳሙ 22:8)
. ረዳት፥ “ሙሴና ሎሌው ኢያሱ ተነሡ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ” (ዘጸ
24:13) ፣ “እንዲህም ሆነ
የእግዚአብሔር ባሪያ
ሙሴ ከሞተ
በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን ... ተናገረው” (ኢያ 1:1)
. “በካሲፍያ ስፍራ ወደ ነበረው ወደ አለቃው ወደ አዶ ላክኋቸው ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን ያመጡልን ዘንድ ...” (ዕዝ 8:17 ፣ ነህ 10:36 ፣
ኢሳ 61:6 ፣ ሕዝ 44:11፣ ኢዮ 1:9 ፣ 13)
. ካህናት፥ “ነገር ግን አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት
ሊሆኑ፥ ለእግዚአብሔር
ወንጌል እንደ
ካህን እያገለገልሁ፥
ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ...” (ዕብ 15:16)፣ (ሮማ 13:6)፣ “እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን
አገልጋይ ነው፥
እርስዋም በሰው
ሳይሆን በጌታ
የተተከለች ናት:” (ዕብ 8:2)
. ተላላኪ፥ “መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ …”
(ሉቃ 4:20)
. ሎሌ-
(2 ነገ 4:43)
. ሎሌ-
(1 ነገ 10:5 ፣ 2 ዜና 22:8)
አጉር ~
Agur:
አጉር፣ አጎረ፣ አጉራ፣ አጓሪ፣ ሰበሰበ፣ አጠራቀመ... ማለት ነው።
‘አጎረ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም
ነው። የማሣ አገር ሰው የያቄ ልጅ፥ (ምሳ 30፡1)
አጊት ~
Haggith:
ሕገያት፣ ሕጋውያን፣ አጋውያን፣ የአጋ አገር ሰዎች፣ የጌታን ሕግ የተከተሉ... ማለት ነው።
የአዶንያስ እናት ሆና የንጉሥ ዳዊት ሚስት፥ (2 ሳሙ 3፡4)
አጋራውያን ~ Hagarites:
አጋራያን፣ አጋራይት፣ አጋዦች፣ የአጋር ወገኖች... ማለት ነው።
በሳኦል ዘመን እስራኤላውያን ከተዋጓቸው፥ (1 ዜና 5፡10፣ 18-20) ፣ (1 ዜና
11:38)
አጋር ~ Hagar, Agar:
አጋር፣ አጋዥ፣ ረዳት፣ ተባባሪ... ማለት ነው። የአብራም ሚስት የሦራ አገልጋይና የእስማኤል እናት፥ (ዘፍ 16፡1)
አጋር / Agar: እግር፣ እግረኛ፣ መንገደኛ፣ እንግዳ... ማለት ነው። እስማኤልን ለአብርሃም የወለደች፥ የሳራ አገልጋይ፥ “ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ
ሲና ናት፤
አሁንም ያለችውን
ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥
ከልጆችዋ ጋር
በባርነት ናትና።” (ገላ 4:25)
አጋብ ~
Hagab:
‘የአንበጣ መንጋ’ ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ፥ የአጋብ ልጆች ይገኙበታል፥ “የአጋባ ልጆች፥
የዓቁብ ልጆች፥
የአጋብ ልጆች፥
የሰምላይ ልጆች፥
የሐናን ልጆች፥” (ዕዝ 2:46)
አጋቦስ ~ Agabus: ‘የፌስታ፣ የፍስሐ፣ የደስታ
አባት’
ማለት ነው።
በሐዋርያት ዘመን የነበረ
ነቢይ፥ በዓለም
ሁሉ ታላቅ
ራብ እንደሚሆን
የተናገረ፥ “ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው
በመንፈስ አመለከተ፤
ይህም በቀላውዴዎስ
... ሆነ”
(ሐዋ 11:28)
አጋግ ~ Agag: ‘ነበልባል’
ማለት ነው።
የቢዖር ልጅ
በለዓም በተናገረው
ምሳሌ የተጠቀሰ፥ “ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል።” (ዘኊ 24:7)
አጌ ~
Agee:
‘ተሳዳጅ፣ ስደተኛ’ ማለት ነው። ከሦስቱ የዳዊት ኃያላን አንዱ፥ የሣማ
አባት፥ “ከእርሱም በኋላ
የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበረ።
... ሆነው ተከማችተው
ነበር ሕዝቡም
ከፍልስጥኤማውያን ፊት
ሸሹ።”
(2 ሳሙ 23:11)
አግሪጳ ~
Agrippa:
‘የጣር ልጅ፣ የጭንቅ ልጅ፥ በከባድ ምጥ የተወለደ’ ማለት ነው። “ከጥቂት ቀንም
በኋላ ንጉሡ
አግሪጳ በርኒቄም
ለፊስጦስ ...” (ሐዋ 25:13)
አጣልያ ~
Attalia:
(ሐዋ 14:25) “በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ”
አጣሮት ~ Ataroth: ‘ዘውድ’ ማለት ነው።
1.
በገለዓድ አቅራቢያ፥
በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኝ ከተማ፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል
ማኅበር ፊት
የመታው ምድር፥
አጣሮት፥ ዲቦን፥
ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ... ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።” (ዘኊ 32:3)
2. በኤፍሬም እና በብንያም ድንበር ላይ የሚገኝ ከተማ፥ “ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ፥” (ኢያ 16:2፣7)
3.
የሰልሞን ልጅ፥ የኢዮብ ቤት፥ “የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥
ዓጣሮትቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን
... ነበሩ።”
(1 ዜና 2:54)
አጣድ ~ Atad: ‘እሾህ’
ማለት ነው።
በዮርዳኖስ እና
በኢያሪኮ መካከል
የሚገኝ አገር፥
“በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው
ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ
ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት ለአባቱም ሰባት ቀን ...” (ዘፍ 50:10፣11)
አጤር ~ Ater: አጥር፣
ዝግ...
ማለት ነው።
1.
ከምርኮ ከተመለሱ፥ የበረኞች ልጆች፥ “የበረኞች ልጆች የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ
መቶ ሠላሳ
ዘጠኝ።”
(ዕዝ 2:42)
2.
ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የአጤር ልጆች ይገኙበታል፥ “ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።” (ዕዝ 2:16)
አጤኔጦ ~
Epenetus:
‘ምስጉን’ ማለት ነው። በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ጳውሎስ
በመልእክቱ ሰላምታ
ያቀረበለት፥ “በቤታቸውም ላለች
ቤተ ክርስቲያን
ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ከእስያ ለክርስቶስ
በኵራት ለሆነው
ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:5)
አጥላይ ~ Athlai:
አታላይ፣ አጭበርባሪ፣
ከአምላክ የተጣላ፣
እግዚአብሔር የጠላው... ማለት ነው። የቤባይ ልጅ፥ “ከቤባይ ልጆችም፤ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይ፥ አጥላይ”
(ዕዝ 10:28)
አጥቢያ ኮከብ ~ Lucifer: ‘መብራት ተሸካሚ’ ማለት ነው። (የንጋት ልጅ ተብሎ ይጠራል።) "አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ!
አሕዛብንም ያዋረድህ
አንተ ሆይ፥
... ምድር ድረስ
ተቈረጥህ!”
(ኢሳ 14:12)
አጵሎስ ~ Apollos: ‘አጥፊ፣ ደምሳሽ’ ማለት
ነው። “በወገኑም የእስክንድርያ
ሰው የሆነ
ነገር አዋቂ
የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ
ሰው ወደ
ኤፌሶን ወረደ፤
እርሱም በመጻሕፍት
እውቀት የበረታ
ነበረ”
(ሐዋ 18:24)
አጶልዮን ~ Apollyon: ‘አጥፊ፣ ደምሳሽ፣ መልአከ ሞት’ ማለት
ነው። ስሙም
በዕብራይስጥ አብዶን የተባለው መልአክ፥ “በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ
መልአክ ነው፥
ስሙም በዕብራይስጥ
አብዶን በግሪክም
አጶልዮን ይባላል” (ራእይ 9:11)
አፋይም ~
Appaim:
አፋም፣ በአፍ በኩል፣ በፊት ለፊት... ማለት ነው። ከይሁዳ ነገድ፥ የይሽዒ ልጅ፥ “የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም
ልጅ አሕላይ
ነበረ።”
(1 ዜና 2:30፣31)
አፌቅ ~
Aphiah, Aphek: አፍ ያሕ፣ አፈ ሕያው፣ ቃለ ህይወት፣ ንግግር፣ የጌታ ቃል፣ ቃለ እግዚአብሔር... ማለት ነው።
Aphiah- ‘አፈ’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ...
ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ከመቱአቸው የምድር ነገሥታት፥ (ኢያ 12፡17)
. ቂስ ለተባለ የአንድ ብንያማዊ ሰው ወገን፣ የንጉሥ ሳዖል ቅድመ አያት፥ (1 ሳሙ 9፡1)
አፌቅ ~ Aphek: ‘ጥንካሬ’ ማለት ነው።
1.
ኢያሱ ካጠፋቸው የከነናውያን ንጉሥ ከተማ፥ “የታጱዋ ንጉሥ፥ የኦፌር ንጉሥ፥ የአፌቅ ንጉሥ፥” (ኢያ 12:18)
2.
ሌላ የከተማ
ስም፥ “ዑማ፥ አፌቅ፥
ረአብ ደግሞ
ነበሩ ሀያ ሁለት ከተሞችና
መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 19:30)
3.
እስራኤልም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ሲወጡ ያረፋበት ቦታ፥ “እስራኤልም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ወጡ፥ በአቤንኤዘር አጠገብ ሰፈሩ ፍልስጥኤማውያን በአፌቅ ሰፈሩ።”
(1 ሳሙ 4:1)
4.
ፍልስጥኤማውያን ለውጊያ
ሲወጡ የሰፈሩበት፥ “ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ
ወደ አፌቅ
ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል
ባለው ውኃ
ምንጭ አጠገብ
ሰፈሩ።”
(1 ሳሙ 29:1)
5.
“በሚመጣውም ዓመት ወልደ አዴር ሶርያውያንን አሰለፈ፥ ከእስራኤልም ጋር
ይዋጋ ዘንድ
ወደ አፌቅ ወጣ።” (1 ነገ 20:26)
አፌዝ ~ Uphaz: ‘ንጹሕ ወርቅ’
ማለት ነው።
“የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ
ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው።” (ኤር 10:9)
አፍለሶንጳ ~ Phlegon: ‘ነበልባል፣ ቃጠሎ’
ማለት ነው።
በሮም የነበረ
ክርስቲያን፥ ጳውሎስ በሰላምታ ደብዳቤው የጠቀሰው፥ “ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ለጳጥሮባም
ለሄርማንም ... ወንድሞች
ሰላምታ አቅርቡልኝ” (ሮሜ
16:14)
አፍሮዲጡ ~ Epaphroditus: ‘ቅን’
ማለት ነው።
ጳውሎስ በመልእክቱ የጠቀሰው፥ “ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛ ወታደርም የሚሆነውን፥ የእናንተ
ግን መልእክተኛ
የሆነውና የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን አፍሮዲጡን እንድልክላችሁ
በግድ አስባለሁ፤” (ፊልጵ
2:25-30፥ 4:10-18)
አፍብያ ~ Apphia:
‘ፍሬያማ፣ ውጤታማ’
ማለት ነው።
“ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም
ጋር አብሮ
ወታደር ለሆነ
ለአርክጳ፥ በቤትህም
ላለች ቤተ ክርስቲያን፤”
(ፊል 1:2)
ኡላም ~ Ulam: ‘በረንዳ’ ማለት ነው።
1.
የገለዓድ ወገን፥ የምናሴ የልጅ ልጅ፥ “የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ” (1 ዜና 7:17)
2.
የሳኦል ልጅ፣ የአሴል ልጅ፥ “የወንድሙም የአሴል ልጆች በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም
ኢያስ፥ ሦስተኛውም
ኤሊፋላት።”
(1 ዜና 8:39፣40)
ኡሩኤል ~
Uriel:
ኡር ኤል፣ የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም-
ኡርኤል]
‘ኡር’
እና ’ኤል’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ዳዊት፣ ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ቤት ካቆማቸው የመዘምራን
አለቆች፥ (1 ዜና 6:24)
2.
የቀዓት ልጅ፥
ኡርኤል-
(1 ዜና 15:5፣ 11)
3.
የሚካያ አባት፥
ኡርኤል-
(2 ዜና 13:2)
ኡሪ ~
Uri:
ኡሪ፣ ኡሬ፣ የፀሓይ መውጫ፣ ብርሃናማ፣ ምሥራቃዊ የኡር አገር ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዑር]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የባስልኤል አባት ሆኖ፥ የሆር ልጅ፥ (ዘጸ 31:2)
2.
በዐግ አገር
ላይ ብቻውን
ሹም የነበረ፥
የጌበር አባት፥
(1 ነገ 4:19)
3.
በዕዝራ ዘመን፣ ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ከሰጡ፥ የቤተ መቅደስ ጠባቂ
የነበረ፥ “...ከበረኞችም፤ ሰሎም፥
ጤሌም፥ ኡሪ።” (ዕዝ
10:24)
ኡሪም ~ Urim: ብርሃን፣
ነበልባል፣ ጮራ፣ ፀሓይ፣ ምሥራቅ... ማለት
ነው። “በፍርዱ በደረት
ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ
ይሆናሉ አሮንም
በእግዚአብሔር ፊት
ሁልጊዜ ... ይሸከማል” (ዘፍ
28:30)
ኡርኤል ~ Uriel: የብርሃን
ጌታ፣ የአምላክ
ብርሃን... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም-
ኡሩኤል]
‘ኡር’
እና ’ኤል’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የቀዓት ልጅ፥
(1 ዜና 15:5፣ 11)
2.
የሚካያ አባት፥
(2 ዜና 13:2)
. ኡሩኤል-
(1 ዜና 6:24)
ኡቢያ ~
Obil:
‘ሐዘን፣ ልቅሶ’ ማለት ነው። የንጉሥ ዳዊት የግመሎች ጠባቂ የነበር፥
እስማኤላዊ፥ “በግመሎችም ላይ
እስማኤላዊው ኡቢያስ
ሹም ነበረ
በአህዮቹም ላይ ሜሮኖታዊው ይሕድያ ሹም ነበረ” (1 ዜና 27:30)
ኡባል ~ Ulai: ‘ንጹሕ ውኃ’
ማለት ነው።
ዳንኤል ራእዩን
ያየበት ቦታ፥
አጠገብ ያለ
ወንዝ፥ “በራእዩም አየሁ፤ ባየሁም
ጊዜ በኤላም
አውራጃ ባለው
በሱሳ ግንብ
ነበርሁ፤ በራእዩም አየሁ
በኡባል ወንዝም
አጠገብ ነበርሁ።” (ዳን
8:2፣16)
ኡኤል ~
Uel:
ውል፣ የአምላክ ፈቃድ... ማለት ነው። ከግዞት ከተመለሱ፥ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ “ኡኤል፥ በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ” (ዕዝ 10:35)
ኡካል ~
Ucal:
‘ኃይል’ ማለት ነው። “የማሣ አገር ሰው የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ሰውየው ለኢቲኤልና ለኡካል እንደዚህ ይናገራል።” (ምሳ 30:1)
ኡዛይ ~ Uzai: ‘ጠንካራ’
ማለት ነው።
የፋላል ልጅ፥
የከተማውን ቅጥር
በመጠገን ከነህምያ ጋር የተባበረ፥ “የኡዛይ ልጅ ፋላል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች ... ግንብ ሠራ። ከእርሱም በኋላ የፋሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።” (ነህ 3:25)
ኡዜንሼራ ~ Uzzen-sherah: ‘መጠበስ፣ መቃጠል’ ማለት ነው። በኤፍሬም ሴት
ልጅ ሥራ፥ በሲአራ
የተሰየመ፥ “ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የሠራች ሲአራ
ነበረች።”
(1 ዜና 7:24)
ኢሊዮ ~
Elihu:
ኤልሁ፣ አምላኬ፣ ጌታዬ፣ ፈጣሪዬ፣ ኃይሌ፣ መመኪያዬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤሊሁ፣ ኤልሁ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
. ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ወገን፥ የቶሑ ልጅ፥ (1 ሳሙ 1:1)
. ኤሊሁ-
(1 ዜና 27:18)
. ከዳዊት ጽኑዓን ኃያላን፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ፥ ኤሊሁ- (1 ዜና
12:20)
. በዳዊት ዘመን የነበረ፣ የሸማያ ልጅ፥ ኤልሁ- (1 ዜና 26:7)
ኢልያሴብ ~ Eliashib:
ኤል ያስብ፣ አምላክ ያሰበው፣ እግዚአብሔር የረዳው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤልያሴብ]
‘ኤል’ እና ‘አሰበ’ ከሚሉት ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
. እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው ከነበሩ፥ የዛቱዕ ልጅ፥ (ዕዝ 10:27)
. ኤልያሴብ- (ዕዝ 10:36) ፣ (1 ዜና 24:12) ፣ (1 ዜና 3:24) ፣ (ነህ 3:1፣20፣21)
፣ (ዕዝ 10:24)
ኢሜር ~ Immer:
ይማር፣ ይቅር ይበል... ማለት ነው።
1.
የአሥራ ስድስተኛው የካህናት ምድብ አለቃ፥ “አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥
አሥራ ስድስተኛው
ለኢሜር”
(1 ዜና 24:14)
2.
በእግዚአብሔር ቤት የተሾመ የካህኑ የጳስኮር አባት፥ “በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው
አለቃ የካህኑ
የኢሜር ልጅ
ጳስኮር ኤርምያስ
በዚህ ነገር
ትንቢት ሲናገር
ሰማ።”
(ኤር 20:1)
3.
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱ፣ የኢሜር
ልጆች ይገኙበታል፥ “የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት” (ዕዝ 2:37፤ ነህ 7:40)
4.
ሌላ፥ ከምርኮ ከተመለሱ፥ “ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ። ነገር
ግን የአባቶቻቸውን
ቤቶችና ዘራቸውን
ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም” (ዕዝ 2:59፤ ነህ 7:61)
5.
የሳዶቅ አባት፥ “ከዚያ በኋላ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አንጻር አደሰ። ከእርሱም በኋላ
የምሥራቁን በር
ጠባቂ የሴኬንያ
ልጅ ሸማያ
አደሰ።”
(ነህ 3:29)
ኢሱድ ~ Ishod: ‘ግርማዊ’
ማለት ነው።
ከምናሴ ነገድ፥
በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ
ከሰፈሩ፥ የመለኬት
ልጅ፥ “እኅቱ መለኬት
ኢሱድን፥ አቢዔዝርን፥
መሕላን ወለደች።” (1 ዜና 7:18)
ኢሳይያስ ~
Esaias, Isaiah: እሽ ያስ፣ የሺዋስ፣ የሺህ ዋስ፣ የብዙኃን አዳኝ... ማለት ነው።
[እግዚአብሔር ደኅንነት ነው፤ ማለት ነው። / መቅቃ]
ኢሳይያስ / Esaias:
የአሞጽ ልጅ ነቢዩ፥ ኢሳይያስ፥” (ማቴ 3፡3)
ኢሳይያስ / Isaiah:
(ኢሳ 1፡1)
ኢሩባኖ ~
Urbane:
‘ከተሜ’ ማለት ነው። ጳውሎስ ወደ ሮሜ በላከው የሰላምታ
ደብዳቤ የተጠቀሰ፥
“በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ
ለኢሩባኖን ለምወደውም
ለስንጣክን ሰላምታ
አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:9)
ኢቆንዮንም ~ Iconium: አይከን፣
ትንሽ ምስል... ማለት
ነው። በታናሽቱ
እስያ የነበረ
ከተማ፥ “በኢቆንዮንም እንደ
ቀድሞ ወደ
አይሁድ ምኵራብ
ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ... ተናገሩ።” (ሐዋ 14:1፣3፣21፣22፥ 16:1፣2፥ 18:23)
ኢብጻን ~
Ibzan:
‘ዕውቅ’ ማለት ነው። ከዮፍታሔ በኋላ፥ በእስራኤል ላይ ሰባት
ዓመት የፈረደ፥
የቤተልሔም ሰው፥
“ከእርሱም በኋላ የቤተ
ልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ ፈራጅ
ሆነ።”
(መሣ 12:8፣10)
ኢቲኤል ~ Ithiel: ያምላክ እጣ፣ ምልክት፣ መምጫ... ማለት ነው።
1.
የብንያም ወገን፥ የየሻያ፥ “የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።” (ነህ 11:7)
2.
“የማሣ አገር ሰው የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ሰውየው ለኢቲኤልና ለኡካል እንደዚህ ይናገራል።” (ምሳ 30:1)
ኢታምር~ Ithamar: የተምር ዛፍ፣ ተምር... ማለት ነው። ሦስተኛውና ትንሹ የአሮን ልጅ፥ “የእንበረምም ልጆች አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች ናዳብ፥
አብዮድ፥ አልዓዛር፥
ኢታምር።”
(1 ዜና 6:3)
ኢትዮጵያ ~ Ethiopia, Cushan: ኢትዮጵያ፣ ጦቢያ፣ ጹብያ፣ ጹብ ያሕ፣ የሕያው ቅዱስ፣ ምድራዊ ገነት፣ መንፈሳዊ ዓለም... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ኩሽ፣ ሳባ፣ አዜብ፣ ኬጢ፣ ምድያም፣ የዓለም ዳርቻ]
ኢትዮጵያ / Ethiopia:
ኢትዮጵያ የግዮን ወንዝ መገኛ፥ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው። እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ዘፍ 2፡13)
ኢትዮጵያ / Cushan:
የአብርሃም ልጅ፥ የምድያም አገር፣ “የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ” (ዕንባ 3፡7)
ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ~ Ethiopian eunuch, the: እጩ መኮንን፣ አልጋ ወራሽ ማለት... ነው።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር... ማለት ነው።
የንግሥት ህንደኬ
አዛዥና ጃንደረባ፣
ኢትዮጵያዊው፥ “ተነሥቶም ሄደ።
እነሆም፥ ህንደኬ
የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት
አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ
የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር” (ሥራ 8፡
27)
ኢትዮጵያዊት ~ Ethiopian woman: ጦቢያዊት፣ ጹባዊት፣ ኢትዮጵያዊት፣ ሳባዊት፣ ምድያማዊት... ማለት ነው።
[የቃሉ ትርጉም ጥቁር
ማለት ነው
/ መቅቃ]
የነቢዩ ሙሴ ሚስት፥ ሲፖራ፥ “ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ...” (ዘኁ
12፡1)
ኢኢት ~
Jahath:
ያሐድ፣ አሐት፣ አሐድ፣ አንድ የሆነ፣ የተዋሐደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ያሐት፣ ኢኤት]
. የሰሜኢ
ልጅ፥ (1 ዜና 23፡10)
. የሰሎሚት
ልጅ፥ ያሐት- (1 ዜና 24:22)
ኢኤት ~
Jahath:
ያሐት፣ አሐት፣ አሐድ፣ አንድ የሆነ፣ የተዋሐደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢኢት፣ ያሐት]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የሜራሪ ልጅ፥
(2 ዜና 34:12) `
2.
የራያ ልጅ
ኢኤት፥ (1 ዜና 4:2)
3.
የጌድሶ ልጅ፥ “ከጌድሶን ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥” (1 ዜና 6:20)
ኢዔዝር ~
Jeezer:
የዘር፣ የወገን፣ የረዳት... ማለት ነው። ከምናሴ ነገድ፥ የኢዔዝራውያን ወገን አባት፥ “የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው። ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን”
(ዘኊ 26:30)
ኢካቦድ ~
Ichabod:
‘ክብሩን ያጣ’ ማለት ነው።
የዔሊ የልጅ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ “እርስዋም የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከች ስለአማትዋና ስለ ባልዋም። ክብር ከእስራኤል ለቀቀ ስትል የሕፃኑን ስም። ኢካቦድ ብላ ጠራችው”
(1 ሳሙ 4:21)
ኢኮንያ ~
Coniah:
ቅነ ያሕ፣ የሕያው ብርታት... ማለት ነው። “እኔ ሕያው ነኝና
የይሁዳ ንጉሥ
የኢዮአቄም ልጅ
ኢኮንያን የቀኝ
እጄ ማኅተም
ቢሆን ኖሮ
እንኳ፥ ከዚያ እነቅልህ ነበር፥ ይላል እግዚአብሔር” (ኤር 22:24)
ኢኮንያን ~ Jeconiah:
ያቅነ ያሕ፣ በሕያው
የታነጸ፥ አምላክ
የመሠረተው... ማለት ነው። “የኢዮአቄምም ልጆች
ልጁ ኢኮንያን፥
ልጁ ሴዴቅያስ።” (1 ዜና
3:16)
ኢየሩሳ ~ Jerusha: ‘የራስ የሆነ፣
የተያዘ፣ የተወረሰ’ ማለት ነው። የሳዶቅ
ልጅ፥ የይሁዳ
ንጉሥ የኢዮአታም
እናት፥ “መንገሥ በጀመረ
ጊዜ የሀያ
አምስት ዓመት
ጕልማሳ ነበረ፥
በኢየሩሳሌምም አሥራ
ስድስት ዓመት
ነገሠ እናቱ
የሳዶቅ ልጅ
ኢየሩሳ ነበረች” (2 ነገ 15:33)
ኢየሩሳሌም ~
Jerusalem:
የሩሰላም፣ አየረ ሰላም፣ የሰላም አየር፣ ሰላም የሰፈነበት አገር... ማለት ነው።
‘አየረ’ እና ‘ሰላም’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[የሰላም ከተማ
ማለት ነው
/ መቅቃ]
. የሳሌም ሌላ ስም፥ “የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ:” (ዘፍ 14:18)
. ከእስራኤል ነገሥታት በፊት ኢየሩሳሌም በራሷ ነገሥታት ተዳድራለች፥ “እንዲህም ሆነ
የኢየሩሳሌም ንጉሥ
አዶኒጼዴቅ ኢያሱ
ጋይን እንደ
ያዘ ፈጽሞም
እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና
በንጉሥዋም ያደረገውን
እንዲሁ በጋይና
በንጉሥዋ እንዳደረገ፥
የገባዖንም ሰዎች
ከእስራኤል ጋር
ሰላም እንዳደረጉ
በመካከላቸውም እንደ
ሆኑ በሰማ
ጊዜ፥”
(ኢያ 10፡1)
ኢየድኤል ~
Jahdiel:
ያሃዲ ኤል፣ የውደ ኤል፣ አምላከ የወደደው፣ በጌታ የተወደደ... ማለት ነው።
‘ውደ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
የምናሴ ነገድ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ከነበሩ ፥ (1 ዜና 5፡24)
ኢዩ ~ Jehu: ‘ያሕ፣ ሕያው’
ማለት ነው።
1.
የዖቤድ ልጅ፥ የአዛርያ አባት፥ “ኢዩም ዓዛርያስን ወለደ” (1 ዜና
2:38)
2.
“አለቃቸው አሒዔዝር
ነበረ፥ ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ፥ የጊብዓዊው
የሸማዓ ልጆች
ይዝኤል፥ ፋሌጥ፥
የዓዝሞት ልጆች
በራኪያ፥ ዓናቶታዊው
ኢዩ” (1 ዜና 12:3)
3.
“እግዚአብሔርም ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ።” (1 ነገ 16:1፣7፤ 2 ዜና 19:2፥ 20:34)
4.
“በዚያም ... የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ ገብተህም
ከወንድሞቹ መካከል
አስነሣው፥ ወደ
ጓዳም አግባው።” (2 ነገ
9:2)
ኢዩኤል ~ Joel: የኤል፣
የአምላክ፣ የጌታ፣
የእግዚአብሔር ሰው... ማለት
ነው። [ተዛማጅ ስም-
ኢዮኤል]
‘ኤል’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ ሌዊያዊ፣ የይሒኤሊ ልጅ፥ (1
ዜና
26:22)
2.
በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ፣ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አለቃ፣ የፈዳያ ልጅ፥ (1 ዜና 27:20)
3. የባቱኤል ልጅ፣ ነቢዩ ኢዩኤል፥ (ኢዮ 1:1)
ኢያሱ ~ Hoshea, Jehoshua, Jeshua, Jesus, Joshua:
የሺሕ፣ ያሕ ሽዋ፣ የሽዋስ፣ የሽዎች ጌታ፣ የብዙኃን አምላክ፣ የሽዎች አዳኝ፣ የብዙዎች ነጻነት ሰጭ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሆሴዕ፣ ኢየሱስ]
‘የሺህ’ እና ’ዋስ’
ከሚሉት ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [እግዚአብሔር ያድናል
፥ አዳኝ
ማለት ነው
/ መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በዚህ
ስም የሚታወቁ
ሰዎች:-
ኢያሱ
/ Hoshea:
1.
የነዌ ልጅ፥
(ዘዳ 32፡44)
2.
የዓዛዝያ ልጅ፥
ሆሴዕ-
(1 ዜና 27:20)
3.
ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተመ፥ ሆሴዕ- (ነህ 10:23)
ኢያሱ / Jehoshua: ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ የነዌ ልጅ፥ “ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ
ሙሴ የላካቸው
ሰዎች ስም
ይህ ነው።
ሙሴም የነዌን
ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው”
(ዘኁ 13፡16)
፣ (1 ዜና 7:27)
ኢያሱ / Jeshua:
1.
ለዘጠነኛው ሊቀ ካህናት የነበረ፥ ኢያሱ፥ (ዕዝ 2:36) ፣ (1
ዜና
24:11).
2.
በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ፥ በካህናቱ
ከተሞች በየሰሞናቸው
ክፍላቸውን በእምነት
ይሰጡ ከተመደቡ፥
(2 ዜና
31:15)
3.
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2:6፥ ዕዝ 7:11)
4.
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ
ይሁዳ ወደ
እየከተማቸው ከተመለሱት
የአገር ልጆች፥
(ዕዝ 2:40፥ ነህ 7:43)
5.
ሌዊያዊ፥ (ዕዝ 8:33)
6.
ከባቢሎን መልስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ካደሱ፥ (ነህ 3:19)
7.
ዕዝራ የእግዚአብሔር
ማወቅ ሲያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ካነበቡ፥
(ነህ 8:7፥ 9:4፣5)
8.
የይሁዳ ከተማ፥
“በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል”
(ነህ 11:26)
9.
የቀድምኤልም ልጅ፥ (ነህ 12:24)
ኢያሱ / Jesus:
1.
ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በጉዞው ላይ የነበረ፥ (ቆላ 4:11)
2.
ከሙሴ በመቀጠል ሕዝበ እስራኤልን ወደ ቃልኪዳን አገራቸው የመራ፥ “ኢያሱ አሳርፎአቸው
ኖሮ ቢሆንስ፥
ከዚያ በኋላ
ስለ ሌላ
ቀን ባልተናገረ
ነበር”
(ዕብ 4:8)
ኢያሱ / Joshua:
1.
የነዌ ልጅ፥
አውሴ- (ዘጸ 17:9)
2.
(ሐጌ 1:1፣12፥ 2:2፣4፥ ዘካ 3:1፣3፣6፣8፣9)
ኢያስ ~
Jehush:
ፈጥኖ ደራሽ፣ አዳኝ፣ ዋስ... ማለት ነው። የአሴል ልጅ፥ “የወንድሙም የአሴል ልጆች በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት።”
(1
ዜና 8:39)
ኢያሶ ~ Jason: የዋስ፣ አዳኝ፣ ፈዋሽ... ማለት
ነው። በተሰሎንቄ፥
ጳውሎስንና ሲላስን
ተቀብሎ ያስተናገደ፥
“አይሁድ ግን ቀንተው
ከሥራ ፈቶች
ክፉ ሰዎችን
አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ ... ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ” (ሐዋ 17:5-9)
ኢያሪ ~
Jareb:
‘ቂመኛ፣ በቀለኛ’ ማለት ነው። “ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን
ላከ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም” (ሆሴ
5:13፥ 10:6)
ኢያሪሙት ~
Jeremoth:
የረ ሞት፣ አየረ ሞት፣ ታላቅ ሞት፣ ከፍተኛ ሞት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ይሬምት፣ ይሬሞት]
‘አየረ’ እና ‘ሞት’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ
በዚህ ስም
የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የሙሲ ልጅ፥
(1 ዜና 23:23)
2.
የኤማን ልጅ፥
ኢያሪሙት፥ (1 ዜና 25:22)
. የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ይሬምት- (1
ዜና 8:14)
. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የኤላ ልጅ፥ ይሬሞት- (ዕዝ 10:26)
. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የዛቱዕ ልጅ፥ ይሬሞት- (ዕዝ 10: 27)
ኢያሪሙት፣ ይሬሞት ~ Jerimoth: አየረ ሞት፣ ከፍተኛ ሞት፣ ታላቅ ሞት...
ማለት ነው።
1.
የቤላ ልጅ፥ “የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሪሙት፥ ዒሪ፥ አምስት ነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ በትውልድ የተቈጠሩ ሀያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።” (1 ዜና 7:7)
2.
የሜራሪ ወገን፥ የሙሲም ልጅ፥ “ከቂስ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል የሙሲም ልጆች ሞሖሊ፥ ዔዳር፥ ኢያሪሙት።” (1 ዜና 24:30)
3.
በጺቅላግ ከዳዊት
ሠራዊት ጋር የተቀላቀለ፥ ብንያማዊ፥ “ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ በዓልያ፥ ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥” (1 ዜና 12:5)
4.
የኤማን ልጅ፥ “ከኤማን የኤማን ልጆች ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥
መሎቲ፥ ሆቲር፥
መሐዝዮት”
(1 ዜና 25:4)
5.
የንፍታሌም ገዥ፥ (1
ዜና 27:19) “በዛብሎን ላይ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ በንፍታሌም ላይ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት”
6.
የዳዊት ልጅ፥
(2 ዜና 11:18)
“ሮብዓምም መሐላትን አገባ፤ አባትዋ የዳዊት
ልጅ ኢያሪሙት ነበረ እናትዋም የእሴይ
ልጅ የኤልያብ
ልጅ አቢካኢል ነበረች።”
7.
ዐሥራት ተቆጣጣሪው፥ ሌዋዊው፥ ይሬሞት፥ “በንጉሡም
በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር
ቤት አለቃ
በዓዛርያስ ትእዛዝ
ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥
... ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ... ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።” (2 ዜና 31:13)
ኢያሪኮ ~ Jericho: ‘የሽቶ አገር’ ማለት
ነው። ከጥንታዊ
ከተሞች አንዱ፥
“ከላይ የሚወርደው ውኃ
ቆመ በጻርታን
አጠገብ ባለችው
አዳም በምትባል
ከተማ በሩቅ
ቆሞ በአንድ
ክምር ተነሣ
ወደ ዓረባ
ባሕር ወደ
ጨው ባሕር
የሚወርደው ውኃ
ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም
በኢያሪኮ ፊት
ለፊት ተሻገሩ።” (ኢያ
3:16)
ኢያራ ከተማ ~ Hierapolis: አየረ ከተማ፣ ከፍተኛ ከተማ፣ ቅድስት ከተማ... ማለት
ነው። “ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ እንዲቀና እመሰክርለታለሁና።”
(ቆላ 4:13)
ኢያሬምኤል ~ Jeroham: ‘ከፍተኛ’
ማለት ነው።
የሕልቃና አባት፥
የነቢዩ ሳሙኤል
አያት፥ “... ስሙ
ሕልቃና የተባለ
ኤፍሬማዊ ሰው
ነበረ። እርሱም የኢያሬምኤል ልጅ
የኢሊዮ ልጅ
የቶሑ ልጅ
የናሲብ ልጅ
ነበረ”
(1 ሳሙ 1:1)
ኢያቡሳዊ ~ Jebus: የኢየሩሳሌም ሌላ ስም፥
“ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ
ፊት ለፊት
በምዕራብ ወገን
ወዳለው ተራራ
ራስ ላይ
ወጣ”
(ኢያ 15:8፥ 18:16፣28፤ መሣ
19:10፣11፤ 1
ዜና 11:4፣5)
ኢያቡሳዊው ~ Jebusi: ‘ኢያቡሳዊ’
ማለት ነው።
የኢየሩሳሌም ነዋሪ፥
“ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ
ደቡብ ወገን
ወጣ ድንበሩም
በራፋይም ...” (ኢያ 15:8፥ 18:16፣28)
ኢያቡስቴ ~ Ishbosheth:
‘ወራዳ’ ማለት ነው። የሳኦል
ልጅ፥ በእስራኤል ላይ
ሁለት ዓመት
የነገሠ፥ “የሳኦል ልጅ
ኢያቡስቴም በእስራኤል
ላይ መንገሥ
በጀመረ ጊዜ
የአርባ ዓመት
ሰው ነበረ። ሁለት
ዓመትም ነገሠ፤ ነገር
ግን የይሁዳ
ቤት ዳዊትን ተከተለ” (2 ሳሙ 3:10)
ኢያቢስ ~ Jabin: ‘አስተዋይ፣ ጠቢብ’
ማለት ነው።
1.
የአሶር ንጉሥ፥
የሰሜንን ነገሥታት አስተባብሮ እስራኤልን ለመውጋት የተነሣ፥ “እንዲህም ሆነ የአሶር ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማዶን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ሺምሮንም ንጉሥ፥ ወደ ...” (ኢያ 11:1-3)
2.
በአሶር የነገሠው
የከነዓን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው ...” (መሣ 4:2፣13)
ኢያቤሐር ~ Ibhar: ‘አባሪ፣ ተባባሪ፣ የተመረጠ’ ማለት ነው። የንጉሥ ዳዊት ልጅ፥ “ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥” (2 ሳሙ 5:15፤ 1 ዜና 3:6፥ 14:6)
ኢያንበሬስ ~ Jambres: ሙሴን
በግብፅ ከተቃወሙት፥
“ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ ... አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም
የተጣሉ ሰዎች
ሆነው፥ እውነትን
ይቃወማሉ።”
(2 ጢሞ 3:8)
ኢያዔል ~ Jael: የኃያል፣ ያይል፣ የበላይ... ማለት ነው።
የቄናዊው፥ የሔቤር
ሚስት፥ “የቄናዊው የሔቤር
ሚስት ኢያዔል ከሴቶች ይልቅ የተባረከች
ትሁን፤ በድንኳን
ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን” (መሣ 5:24)
ኢያዕር ~ Ira, Jair: ‘የከተማ ጠባቂ’ ማለት ነው።
1.
ከዳዊት ሹማምንት አንዱ፥ “የኢያዕር ሰውም ዒራስ ለዳዊት አማካሪ ነበረ።”
(2 ሳሙ 20:26)
2.
ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ ዒራስ፥ “ነሃራይ፥ ይትራዊው ዒራስ፥ ይትራዊው”
(2 ሳሙ 23:38፤ 1 ዜና 11:40)
3.
ሌላም የዳዊት ዘበኛ፥ ዒራስ፥ “የዒስካ ልጅ ዒራስ፥ ዓናቶታዊው”
(2 ሳሙ 23:27፤ 1 ዜና 11:28)
ኢያዕር / Jair:
‘ብርሃኔ’ ማለት ነው።
1.
“ጌሹርና አራምም
የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።” (1 ዜና 2:22)
2.
የገለዓድ ሰው፥ በእስራኤል ላይ ለሀያ ሁለት ዓመት ፈራጅ የሆነ፥ “ከእርሱም በኋላ
ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፥ በእስራኤልም ላይ
ሀያ ሁለት
ዓመት ፈረደ።” (መሣ 10:3-5)
3.
የሰሜኢ ልጅ፥ የመርዶክዮስ አባት፥ “አንድ አይሁዳዊ የቂስ ልጅ የሰሜኢ ልጅ
የኢያዕር ልጅ
መርዶክዮስ የሚባል
ብንያማዊ በሱሳ
ግንብ ነበረ።” (አስ 2:5)
4.
የጎልያድን ወንድም
ለሕሚን የገደለ፥ ያዒር፥ “ደግሞም
ከፍልስጥኤማውያን ጋር
ሰልፍ ነበረ
የያዒርም ልጅ
ኤልያናን የጦሩ
የቦ እንደ
ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ” (1 ዜና 20: 5)
ኢያዜር ~ Jazer: የዘር፣
ወገን፣ ረዳት... ማለት
ነው። “የሮቤልና የጋድ
ልጆችም እጅግ
ብዙ እንስሶች
ነበሩአቸው። እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥” (ዘኊ 32:1)
ኢይዝራኤል ~
Jezreel:
የዘረ ኤል፣ የአምላክ ዘር፣ የእግዚአብሔር ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ አዛርኤል]
‘ዘር’
እና ’ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። [እግዚአብሔር ይዘራል
ማለት ነው
/ መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ለይሳኮር ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው የወጣ፥ (ኢያ 19፡18)
2.
የኤጣም አባት
ልጅ፣ (1 ዜና 4:3)
ኢዮሳፍጥ ~ Jehoshaphat, Josaphat, Joshaphat: ያሕ ሸፍት፣ ያሕ ሳፍት፣ ያሕ መሳፍንት፣ ሕያው መስፍንት፣ ሕያው ገዥ፣ የጌታ ሹማምንት... ማለት ነው። ‘ያሕ’ እና ‘ስፍነት’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኢዮሳፍጥ / Jehoshaphat:
1.
የንጉሥ አሳ ልጅ፥ በፋንታው የነገሠ ኢዮሣፍጥ፥ (1 ነገ 15፡24)
2.
የአሒሉድ ልጅ፥
(2 ሳሙ
8:16) ፣ (1 ነገ 4:3)
3.
በእግዚአብሔር ታቦይ
ፊት መለከት
ይነፉ ነበር
ካህናት፥ (1 ዜና
15:21)
4.
የፋሩዋ ልጅ፥
(1 ነገ 4:17)
5.
የናሜሲን ልጅ፥
(2 ነገ 9:2
፣ 14)
ኢዮሣፍጥ / Josaphat: በጌታ የዘር ሐረግ፥ የአሣፍ ልጅ፥ (ማቴ 1:8)
ኢዮሣፍጥ / Joshaphat:
ከንጉሥ ዳዊት ዘበኞች፥ ሚትናዊው፥ (1
ዜና 11:43)
ኢዮሴዴቅ ~ Jehozadak, Jozadak:
ያሕ ጻድቅ፣ ሕያው ጻድቅ፣ እውነተኛ አምላክ፣ ዘላለማዊ ጌታ... ማለት ነው።
‘ያሕ’(ያሕዌ) እና ‘ጽድቅ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኢዮሴዴቅ / Jehozadak: የታላቁ ካህን፥ የሠራያ ልጅ፥ (1
ዜና
6፡14፣15)
ኢዮሴዴቅ / Jozadak: የታላቁ ካህን የኢያሱ አባት፥ (ሐጌ 1፡14-
15) ፣ (ነህ 12:26) ፣ (ዕዝ 3:2፣ 8፣ 5:2፣ 10:18፣ ነህ 12:26)
ኢዮስያ ~ Joshah: የሻ፣ የተፈቀደ፣ መሻት፣ መመኘት... ማለት ነው። ከስምዖን ወገን፥ የአሜስያስ ልጅ፥ ኢዮስያ፥ (1 ዜና 4:34፣ 38-41)
ኢዮስያስ ~Josiah: የሽ ያሕ፣ የሺህ ያሕ፣ የሕያው ሺህ... ማለት ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ይደግፋል ማለት ነው። /
መቅቃ]
የአሞጽ ልጅ፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ “ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት
ልጅ ነበረ...” (2 ነገ 22:1፣ 2
ዜና.
34:1)
ኢዮስጦስ ~ Justus: ‘ፍቱን፣ ትክክለኛ፣ እውነተኛ’ ማለት ነው።
1.
ባርናባስ ለተባለው፥
የዮሴፍ መጠሪያ፣ “ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።” (ሐዋ 1:23)
2.
ጳውሎስ ያረፈበት፥
የቆሮንቶስ ክርስቲያን፥ “ከዚያም ወጥቶ ኢዮስጦስ ወደሚባል
እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ
ሰው ቤት
ገባ ቤቱም
በምኩራብ አጠገብ
ነበረ።”
(ሐዋ 18:7)
3.
ኢያሱ የተባለው፣ የጳውሎስ ወዳጅ፥ ቅጽል ስም፥ “ከተገረዙት ወገን ያሉት፥
አብሮ ከእኔ
ጋር የታሰረ
አርስጥሮኮስ የበርናባስም
የወንድሙ ልጅ
ማርቆስ ኢዮስጦስም
የተባለ ኢያሱ
ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ...” (ቆላ
4:11)
ኢዮራም ~ Joram:
‘የራማ፣ ከፍታ፣ ከፍ
ያለ፣ የተከበረ’ ማለት
ነው።
1.
የእስራኤል ንጉሥ፥
የአክዓብ ልጅ፥ “በእስራኤልም ንጉሥ በአክዓብ ልጅ በኢዮራም በአምስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም
ነገሠ።”
(2 ነገ 8:16፣25፣28፣29፥ 9:14፣17፣21-23፣29)
2.
የይሁዳ ንጉሥ፥ የኢዮሳፍጥ ልጅ፥ “ኢዮራምም ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ጸዒር ...” (2 ነገ 8:21፣23፣24፤ 1 ዜና 3:11፤ 2
ዜና 22:5፣7፤ ማቴ1:8)
3.
በኢዮሳፍጥ ዘመን የነበረ ካህን፥ “ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ... ጦብያን፥
ጦባዶንያን ሰደደ፤ ከእነርሱም
ጋር ካህናቱን
ኤሊሳማንና ኢዮራምን
ሰደደ።”
(2 ዜና 17:8)
4.
በንጉሥ ዳዊት
ዘመን የነበረ፥
“ወንድሞቹም ከአልዓዛር ልጁ ረዓብያ፥ ልጁም የሻያ፥ ልጁም ኢዮራም ... ሰሎሚት መጡ።” (1 ዜና 26:25)
5.
የንጉሥ ቶዑ ልጅ፥ አዶራም፥ “ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና
ዳዊት አድርአዛርን
ድል ስለ
መታ ቶዑ
ልጁን አዶራምን
ደኅንነቱን ይጠይቅ
ዘንድ፥ ይመርቀውም
ዘንድ ወደ
ንጉሥ ዳዊት
ላከው እርሱም
የብርና የወርቅ
የናስም ዕቃ
ይዞ መጣ።” (2 ሳሙ 8:10)
ኢዮርብዓም ~ Jeroboam: ‘የታላቅ ሕዝብ ጌታ’
ማለት ነው።
1.
የተከፈለው የእስራኤል
መንግሥት፥ ንጉሥ፥ (1 ነገ 11:28) “ኢዮርብዓምም ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበረ። ሰሎሞንም ጕልማሳው በሥራ የተመሰገነ መሆኑን ባየ ጊዜ በዮሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው”
2.
ሁለተኛው ኢዮርብዓም፥
(2 ነገ 14:28) “የቀረውም የኢዮርብዓም
ነገር፥ ያደረገውም
ሁሉ፥ ጭከናውም፥
እንደ ተዋጋም፥
የይሁዳ የነበረውን ደማስቆንና ሐማትን ለእስራኤል እንደ መለሰ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ
መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?”
ኢዮባብ ~
Jobab:
የአባ አባ፣ የአባባ፣ የአባት፣ የጌታ፣ አባታዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ኢዮብ፣ ዩባብ፣ ዮባብ]
. በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር ከነገሡ፥ የባሶራው የዛራ ልጅ፥ (ዘፍ 36:33) ፣ (1
ዜና 1:44፣ 45)
. የዮቅጣን ልጅ፥
ዩባብ-
(ዘፍ 10፡29)
. የማዶን ንጉሥ፥
ዮባብ-
(ኢያ 11:1)
. የሸሐራይም ልጅ፥
ዮባብ-
(1 ዜና 8:9)
ኢዮቤድ፣ ዖቤድ ~ Obed: ማገልገል፣ መታዘዝ... ማለት ነው።
1.
የቡዝ እና የሩት ልጅ፥ (ሩት 4:21፣22) “ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።”
2.
የኤፍላል ልጅ፥ ዖቤድ፥ (1
ዜና 2:34-38) “ዛባድም ኤፍላልን ወለደ ኤፍላልም ዖቤድን ወለደ ዖቤድም ኢዩን ወለደ”
3.
የሸማያ ልጅ፥ ዖቤድ፥ (1 ዜና 26:7) “ለሸማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም ኃያላን የነበሩ ኤልዛባድ፥ ኤልሁ፥ ሰማክያ።”
4.
የዓዛርያስን አባት፥ ዖቤድ፥ (2 ዜና 23:1) “በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ
አለቆቹንም፥ የይሮሐምን
ልጅ ዓዛርያስን፥
የይሆሐናንንም ልጅ
ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛርያስን፥ የዓዳያንም
ልጅ መዕሤያን፥
የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።”
ኢዮብ ~
Job:
ኢዬአብ፣ የአብ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአምላክ የሆነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኢዮባብ፣ ኢዮአብ፣ ዮብ፣ ያሱብ፣ ዩባብ፣ ዮባብ]
‘አበ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
. በዖፅ አገር የነበረ ጻድቅ ሰው፥ (ኢዮብ 1:1)
. “እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” (ሕዝ 14:14፣ 20)
. የይሳኮር ልጅ፥ ዮብ- (ዘፍ 46፡13)፣ ያሱብ-
(1 ዜና 7:1)
ኢዮናዳብ ~ Jehonadab, Jonadab: ‘የሕያው ልገሳ፣ ያምላክ ስጦታ’
ማለት ነው።
1.
የሳምዓ ልጅ፥ የዳዊት ወንድም፥ “ለአምኖንም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ የሚባል ወዳጅ ነበረው ኢዮናዳብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ”
(2 ሳሙ 13:3-6)
2.
የሬካብ ልጅ፥ (ኤር 35:6-19) “እነርሱ ግን እንዲህ አሉ። የወይኑን ጠጅ
አንጠጣም፥ አባታችን
የሬካብ ልጅ
ኢዮናዳብ እንዲህ
ብሎ አዝዞናልና። እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ።”
ኢዮናዳብ / Jonadab: ‘ለጋስ’
ማለት ነው።
1.
የሬካብ ልጅ፥ (2
ነገ 10:15፤ ኤር 35:6፣10) “ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ
ኢዮናዳብን ተገናኘው
ደኅንነቱንም ጠይቆ።
ልቤ ከልብህ
ጋር እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን? አለው ኢዮናዳብም። እንዲሁ ነው አለው።
ኢዩም። እንዲሁ
እንደ ሆነስ
እጅህን ስጠኝ
አለ። እጁንም
ሰጠው ወደ ሰረገላውም አውጥቶ
ከእርሱ ጋር አስቀመጠውና።”
2.
የዳዊት ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፥ (2
ሳሙ 13:3) “ለአምኖንም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ የሚባል ወዳጅ ነበረው ኢዮናዳብም እጅግ ብልህ
ሰው ነበረ።”
ኢዮአስ ~ Jehoash: ‘ከሕያው የተገኘ ከአምላክ የተሰጠ’ ማለት ነው።
1.
ስምንተኛው የይሁዳ ንጉሥ፥” ኢዮአስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሰባት ዓመት
ልጅ ነበረ።” ልጅ፥
(2 ነገ 11:21፣ 12:1፣2፣4፣6፣7፣18፥ 14:13)
2.
በሰማርያ ለአሥራስድስት ዓመት የነገሠ፥ ዮአስ፥ “...የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል
ላይ በሰማርያ
ነገሠ አሥራ
ስድስትም ዓመት
ነገሠ።”
(2 ነገ 13:10፣25፥ 14:8፣9፣11፣13፣15፣16፣17)
ኢዮአስ ~ Joash: ‘ሕያው የረዳው፣ ጌታ የደረሰለት’ ማለት ነው።
1.
የጌዴዎን አባት፥
“የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው
ለኢዮአስ በነበረችው
በአድባሩ ዛፍ
በታች ተቀመጠ
ልጁም ጌዴዎን
ከምድያማውያን ለመሸሸግ
…” (መሣ 6:11፣29፥ 8:13፣29፣32)
2.
የዳዊትን ሠራዊት
በጺቅላግ ከተቀላቀሉ፥ “ካህኑ ዮዳሄም ያስተምረው በነበረ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ።” (1 ዜና 12:3)
3.
የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ “የእስራኤልም ንጉሥ። ሚክያስን ውሰዱ፥ ወደ
ከተማይቱም ሹም
ወደ አሞን
ወደ ንጉሡም
ልጅ ወደ
ኢዮአስ መልሳችሁ።
ንጉሡ እንዲህ
ይላል።”
(1 ነገ 22:26)
4.
የይሁዳ ንጉሥ፥ “የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት ዮሳቤት የአካዝያስን
ልጅ ኢዮአስን
ወስዳ ከተገደሉት
ከንጉሥ ልጆች
መካከል ሰረቀችው እርሱንና ሞግዚቱንም ወደ እልፍኝ ፥…” (2 ነገ 11:2፥12:19፣20)
5.
የእስራኤል ንጉሥ፥ “በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት
የኢዮአካዝ ልጅ
ዮአስ በእስራኤል
ላይ በሰማርያ
ነገሠ አሥራ
ስድስትም ዓመት
ነገሠ።”
(2 ነገ 13:10፣12፣13፣25)
6.
“የቤኬርም ልጆች ዝሚራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ … እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።” (1 ዜና 7:8)
7.
በዘይቱ ቤቶች ሹም የነበረ፥ “በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ በዘይቱም ቤቶች ላይ
ኢዮአስ ሹም
ነበረ”
(1 ዜና 27:28)
ኢዮአቄም ~
Jehoiakim:
ያሕ አቆም፣ የሕያው ቋሚ፣ አምላክ ያቆመው፣ ጌታ ያጸናው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ዓዝሪቃም፣ ኤልያቄም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
‘ያሕ’ እና ‘ቆመ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው / መቅቃ]
. የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄም፥ “...
ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው”
(2 ነገ 23:34)
. “በእርሱም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነዖር ወጣ፥ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ተገዛለት ከዚያም በኋላ ዘወር አለና ዐመፀበት።”
(2 ነገ 24፡1)
ኢዮአብ ~ Joab: ኢዬአብ፣ የአብ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአምላክ የሆነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኢዮባብ፣ ኢዮብ፣ ዮብ፣ ያሱብ፣ ዩባብ፣ ዮባብ] ‘አብ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው / መቅቃ]
የንጉሥ ዳዊት እኅት የጽሩያ ልጅ፥ (2
ሳሙ 2:13፣ 10:7፣ 11:1፣ 1 ነገ 11:15)
ኢዮአታም ~ Joatham, Jotham: ‘እውነተኛ፣ ፍጹም ጌታ፣ እንከን አልባ’ ማለት ነው።
የዖዝያን ልጅ፥ (ማቴ 1:9) “ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤”
ኢዮአታም ~ Jotham:
1.
የይሩበኣል ልጅ፥ “ወደ አባቱም ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፤ ሰባእ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው። ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ።” (መሣ 9:5)
2.
የያሕዳይ ልጅ፥ ኢዮታም፥ “ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። የያሕዳይም ልጆች
ሬጌም፥ ኢዮታም፥
ጌሻን፥ ፋሌጥ፥
ሔፋ፥ ሸዓፍ
ነበሩ።”
(1 ዜና 2:47)
ኢዮአካዝ ~ Joahaz: ‘መያዝ’
ማለት ነው።
የዮአስ አባት፥
“...የኤዜልያስ ልጅ
ሳፋን፥ የከተማይቱም
አለቃ መዕሤያ፥
ታሪክ ጸሐፊም
የኢዮአካዝ ልጅ
ኢዮአክ የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ
ዘንድ ሰደዳቸው።” (2 ዜና
34:8)
ኢዮኤል ~
Joel, Vashni: የኤል፣ የአምላክ፣ የጌታ፣ የእግዚአብሔር ሰው... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም- ኢዩኤል]
‘ኤል’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የነቢዩ ሳሙኤል
ልጅ፥ (1 ሳሙ 8:2)
2.
የአሜስያስ ልጅ፥
(1 ዜና 4:35)
3.
የሸማያ አባት፥ “የኢዮኤል ልጆች ልጁ ሸማያ፥” (1 ዜና 5:4)
4.
የጋድ ልጅ፥
(1 ዜና 5:12)
5.
የይዝረሕያ ልጅ፥
(1 ዜና 7:3)
6.
የናታን ወንድም፥
(1 ዜና 11:38)
7.
የጌድሶን ልጅ፥
(1 ዜና 15:7፣ 11)
8.
የለአዳን ልጅ፥
(1 ዜና 23:8፣ 26:22)
9.
የዓዛርያስ ልጅ፥
(2 ዜና 29:12)
10.
የናባው ልጅ፥
(ዕዝ 10:43)
11.
የዝክሪ ልጅ፥
(ነህ 11:9)
ኢዮኤል / Vashni:
‘ኃያል፣ ጠንካራ’ ማለት ነው። የሳሙኤል ልጅ፥ (1 ዜና 6:28)
“የሳሙኤልም ልጆች በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ።”
ኢዮጴ ~ Japho, Joppa: ‘ጹብ፣ ውበት፣ ቁንጅና’
ማለት ነው። “ይሁድ፥ ብኔብረቅ፥ ጋትሪሞን፥ ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።”
(ኢያ 19:46)
ኢዮጴ / Joppa: በደቡብምዕራብ
የፍልስጥኤም ዳርቻ የነበረ ከተማ፥ “ይሁድ፥ ብኔብረቅ፥ ጋትሪሞን፥ ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።” (ኢያ 19:46)
ኢጡር ~
Jetur:
ያጥር፣ አጠር፣ የተከለለ፣ የተከበበ... ማለት ነው። “ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ።” (ዘፍ 25:15)
ኢጣልያ ~
Italy:
‘ባለብዙ ከብት’ ማለት ነው። ጣሊያን አገር፥ ዋና ከተማው ሮማ የሆነ፥ (ሐዋ 18:2፥ 27:1፤ ዕብ 13:24)
ኣልፐራሲም ~ Baal-perazim: ‘የክፍፍል ጌታ፣
የመለያየት ባለቤት’ ማለት
ነው። ዳዊት
በፍልስጥኤማውያን ላይ
ድልን የተቀዳጀበት
ቦታ፥ “ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲም መጣ፥
በዚያም መታቸውና።
ውኃ እንዲያፈርስ
እግዚአብሔር ጠላቶቼን
በፊቴ አፈረሳቸው
አለ። ስለዚህም
የዚያን ስፍራ
ስም በኣልፐራሲም ብሎ
ጠራው።”
(2 ሳሙ 5:20፤ 1 ዜና 14:11)
ኤሁድ ~ Ehud: ኤሁድ፣ እሑድ፣ ውሕድ፣ የተዋሐደ፣ አንድ የሆነ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስም-
ናዖድ]
. የቢልሐ
ልጅ፥ (1 ዜና 7፡10)
. የጌራ
ልጅ፥ ናዖድ- (መሣ 3:15)
ኤሉል ~ Elul: እልል፣
እልልታ... ማለት ነው።
የወር ስም፥
“ቅጥሩም በኤሉል ወር
በሀያ አምስተኛው
ቀን በአምሳ
ሁለት ቀን
ውስጥ ተጨረሰ” (ነህ
6:15)
ኤሉስ ~
Alush:
‘ጋጋታ፣ ግርግር’ ማለት ነው። እስራኤላውያን ወደ ቃል ኪዳን አገር ባደረጉት
ጉዞ፥ ካረፋባቸው
ቦታዎች፥ “ከራፋቃም ተጕዘው
በኤሉስ ሰፈሩ።” (ዘኊ
33:13፣14)
ኤሉዛይ ~ Eluzai: ‘የአምላክ ኃይል፥
የጌታ ብርታት’ ማለት
ነው። ወደ ዳዊት ከተቀላቀሉ ብንያማውያን ጦረኞች አንዱ፥ “ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ በዓልያ፥ ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥” (1 ዜና 12:5)
ኤሊ ~
Eli:
ኤልይ፣ ኢላይ፣ ኃይሌ፣ የእግዚአብሔር ኃይል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ዔሊ፣ ኤላ]
የቃሉ ምንጭ
‘ኃይል’ የሚለው ቃል ነው።
1.
በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፣ የማቲ ልጅ፥ (ሉቃ 3:23)
2.
ካህኑ፥ ኤሊ፥
(1 ሳሙ 1፡9)
ኤሊ ~
Heli:
እላይ፣ ላይ፣ ወደ ሰማይ... ማለት ነው። የድንግል ማርያም እጮኛ፣ የዮሴፍ አባት፥ (ሉቃ 3:23) “ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር፤ እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥”
ኤሊሆዔናይ ~ Elioena, Elioenai: ኤል ዓየን፣ ኢሌኒ፣ የጌታ ዓይን፣ አምላክ ያየው ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤሊዔናይ፣ ዔሊዮዔናይ፣ ኤልዮዔናይ]
Elioena, Elioenai-
‘ኤል’
እና ‘ዓይን’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኤሊሆዔናይ / Elioena:
የዘራእያ ልጅ፥ (ዕዝ 8:4)
ኤሊሆዔናይ / Elioenai:
የሜሱላ ልጅ፥ (1
ዜና 26:3)
ኤሊም ~ Elim: ‘ጠንካራ ዛፎች’ ማለት
ነው። እራስኤላውያን የኤርትራን
ባሕር ከተሻገሩ በኋላ ካረፉባቸው ቦታዎች፥ “እነርሱም ወደ ኤሊም መጡ፥ በዚያም አሥራ
ሁለት የውኃ
ምንጮችና ሰባ
የዘንባባ ዛፎች
ነበሩባት በዚያም
በውኃው አጠገብ
ሰፈሩ።”
(ዘጽ 15:27፤ ዘኊ 33:9)
ኤሊሱር ~ Elizur: ኤሊ ዘር፣ ኤልአዛር፣ የጌታ ወገን፣ የተባረከ ዘር፣ የተቀደሰ ዘር፣ የአምላክ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አልዓዛር፣ ኤሊዔዘር፣ አልዓዛር፣ ኤልዓዘር]
Elizur-
‘ኤል’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ነው። የሰዲዮር
ልጅ፥ (ዘኁ 1፡5፣6)
ኤሊሱዔ ~
Elishua:
ኤል ሽዋ፣ የብዙዎች አምላክ፣ የሽዎች ጌታ፣ የአምላክ ሃብት... ማለት ነው።
Elishua- ‘ኤል’
እና ’ሸዋ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ለዳዊት
በኢየሩሳሌም ከተወለዱለት፥
(2 ሳሙ 5፡15)
ኤሊሳ ~Elishah: ኤልሻ፣ ኤል ሺህ፣ የሽዎች ጌታ፣ የአምላክ ሃብት፣ የብዙዎች አዳኝ... ማለት ነው።
Elishah- ‘ኤል’
እና ‘ሺህ’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ነው። የያዋን
ልጅ፥ (ዘፍ 10፡4)
ኤሊሳማ ~
Elishama:
ኤል ሰማ፣ ሰማ ኤል፣ አምላክ የሰማው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሙኤል፣ እስማኤል]
‘ኤል’ እና ‘ሰማ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከኤፍሬም ነገድ፥ የዓሚሁድ ልጅ፥ (ዘኁ 1፡10)
2.
የንጉሥ ዳዊት ልጅ፥ (1
ዜና 3:8
፣ 14:7) ፣ (1
ሳሙ 5:16) ፣ (1 ዜና
3:6)
3.
ከይሁዳ ወገን፣
የቃምያ ልጅ፥
(1 ዜና 2:41)
4.
ጎዶልያስንና ከእርሱ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንን እስኪሞቱ ድረስ ከመቱ፥ የናታን አባት፥ (2 ነገ 25:25) ፣ (ኤር 41:1)
5.
የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ ባሰማ ጊዜ፥ የንጉሥ ኢዮአቄም ጸሐፊ የነበረ፥ (ኤር 36:12፣ 20፣ 21)
6.
በንጉሥ ኢዮሣፍጥ ትእዛዝ የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበሩ፥ (2 ዜና 17:8)
ኤሊሳፋጥ ~ Elishaphat:
ኤል ስፍነት፣ የአምላክ መስፍን፣ የእግዚአብሔር ዳኛ፣ የአምላክ ዳኛ... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ‘ሰፋት’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የዝክሪ
ልጅ፥ (2 ዜና 23፡1)
ኤሊሳፍ ~
Eliasaph:
ኤል ሰፋ፣ አምላክ ያሰፋው፣ እግዚአብሔር ያበረከተው፣ የአምላክ በረከት... ማለት ነው።
‘ኤል እና ‘ሰፋ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከጋድ ወገን፥
የራጉኤል ልጅ፥
(ዘኁ 1፡14)
2.
የዳኤል ልጅ፥
(ዘኁ 3:24)
ኤሊቃ ~
Elika:
አለቃ፣ ኤል ላቅ፣ አምላክ ያላቀው፣ ጌታ አለቃ ያደረገው፣ እግዜአብሔር
ከፍ ከፍ
ያደረገው... ማለት ነው።
ከሥላሳዎች የዳዊት
ኃያላን አንዱ።
“ልጅ ኤልያናን፥ አሮዳዊው
ሣማ፥ ሒሮዳዊው
ኤሊቃ፥”
(2 ሳሙ 23:25)
ኤሊኤል ~ Eliel: ኤል ኤል፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ጌታ ጌታዬ፣ አምላኬ አምላኬ፣ የኃያላን ኃያል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤልኤል]
‘ኤል’ን ደጋግሞ
በመጥራት የተመሠረተ
ቃል ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የምናሴ ነገድ፥ ከአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ (1 ዜና 5:24)
2.
ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ
ፊት እያዜሙ
ያገለግሉ፥ የነቢዩ
ሳሙኤል ቅድመ
አያት፥ (1 ዜና 6:34)
3.
በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ
በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ፥ የብንያም ነገድ አለቃ፣ የኤልፍዓል ልጅ፥ (1 ዜና 8:20)
4.
በኢየሩሳሌም የተቀመጡ
በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የሰሜኢ ልጅ፥ (1 ዜና 8:22 ፣ 23)
5.
መሐዋዊው የንጉሥ ዳዊት ወታደር፥ (1 ዜና 11:46)
6.
በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ፥
(1
ዜና 12:11)
7.
የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ በንጉሥ ዳዊት ከታዘዙ፥
(1 ዜና 15:9፣ 11)
8.
በንጉሡ በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ከነበሩ፥ (2
ዜና 31:13)
. ኤልኤል-
(1 ዜና 11:47)
ኤሊዔናይ ~
Elienai:
ኤል ዓይነ፣ አምላክ ያየው፣ ጌታን ያየ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኤሊሆዔናይ፣ ዔሊዮዔናይ፣ ኤልዮዔናይ]
በኢየሩሳሌም የተቀመጡ፥ በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች
ከነበሩ፥ (1 ዜና 8፡20)
ኤሊዔዘር ~
Eliezar:
ኤል ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የተቀደሰ ዘር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አልዓዛር፣ ኤሊሱር፣ አልዓዛር፣ ኤልዓዘር፣]
‘ኤል’ እና ‘ዘር’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ ‘እግዚአብሔር እረዳቴ ነው’ ማለት ነው / መቅቃ]
. የአብራም አገልጋይ፣ የደማስቆ ሰው፥ (ዘፍ 15፡2፣3)
. አልዓዛር- (ዘጸ 18:4 ፣ 1 ዜና 23:15፣ 17 ፣ 26:25)፣ (1
ዜና
7:8)
፣ (1
ዜና 15:24)፣ (1
ዜና 27:16)፣ (2 ዜና 20:37)፣ (ዕዝ 8:16)፣ (ዕዝ
10:18 ፣ 23
፣ 31)
. ኤልዓዘር- (ሉቃ 3:29)
ኤሊያሕባ ~
Eliahba:
ኤል አባ፣ አምላክ አባቴ፣ ጌታዬ ፈጣሪዬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤልአብ፣ አብኤል፣ አቤል]
‘ኤል’ እና ‘አባ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ከዳዊት ክብር ዘበኞች አንዱ፣ ሸዓልቦናዊው፥ (2 ሳሙ 23:32)
ኤሊዳሄ ~ Beeliada, Eliada: በዓለ አዳ፣ የዕድል አምላክ... ማለት ነው። በኢየሩሳሌም ከተወለዱ፥ ዘጠኝ የዳዊት ልጆች አንዱ፥ “ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።” (1 ዜና 14:7)
ኤሊዳሄ ~
Eliada:
1.
ዳዊት መንግሥቱን በኢየሩሳሌም ካጸና በኋላ ከወለዳቸው ልጆች አንዱ፥ “ናፌቅ፥ ያፍያ፥ ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።”
(2 ሳሙ 5:16)
2.
ከብንያም ወገን የሆነ፥ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ “ከብንያምም ጽኑዕ ኃያል የነበረው ኤሊዳሄ፥ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ...” (2 ዜና 17:17)
3.
ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለ፣ የሬዞን አባት፥ “እግዚአብሔርም ደግሞ
ከጌታው ከሱባ
ንጉሥ ከአድርአዛር
የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ጠላት አድርጎ አስነሣበት።” (1 ነገ 11:23)
ኤሊፋላት ~ Eliphalet, Elpalet: ‘አምላክ ያድናል’ ማለት ነው። በኢየሩሳሌም ለዳዊት ከተወለዱለት ሦስት ልጆች፥ የመጨረሻው፥ “ናፌቅ፥ ያፍያ፥ ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።”
(2 ሳሙ 5:16፤ 1
ዜና 14:7)
ኤሊፋላት / Elpalet: በኢየሩሳሌም ለዳዊት ከተወለዱለት ሦስት ልጆች፥ የመጨረሻው፥ “ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥” (1 ዜና 14:5)
ኤሊፋል / Eliphal: የአምላክ ታምራት ማለት ነው። ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ የኡር ልጅ፥ “የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ ሚኬራታዊው ኦፌር፥” (1 ዜና 11:36)
ኤላ ~ Elah:
ኤልይ፣ ላይ፣ ታላቅ፣ ኃያል፣ የእግዚአብሔር ኃይል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ዔሊ፣ ኤሊ]
የቃሉ ምንጭ
‘ኃይል’ የሚለው ቃል ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
በእስራኤል ላይ በቴርሳ ሁለት ዓመት የነገሠ፣ የባኦስ ልጅ፥ (1 ነገ 16፡8-10)
2.
የሆሴዕ አባት፥
(2 ነገ 15:30
፣ 17:1)
3.
የካሌብ ልጅ፥
(1 ዜና 4:15)
ኤላም ~
Elam, Helam: ‘እስከ ዘለዓለም’
ማለት ነው። የሴም ልጅ፥ “የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው።” (ዘፍ 10:22)
ኤላም / Helam: ‘ገዥ፣ ጠንካራ
ምሽግ’
ማለት ነው።
በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ በኤፍራጥስ ምዕራብ፥ ሶርያውያን በአድርአዛር አማካኝነት ተሰባስበው ዳዊትን የገጠሙበት ስፍራ፥ “አድርአዛርም ልኮ በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን፥ አመጣ
ወደ ኤላምም
መጡ፥ የአድርአዛርም
ሠራዊት ...” (2 ሳሙ 10:16፣17)
ኤላም
/
Helem: ህልም ማለት ነው።
(‘በረንዳ፣ ደጀሰላም’
ማለት ነው።
ኪወክ / አ)
1.
የአሴር ወገን፥ “የወንድሙም የኤላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ”
(1 ዜና 7:35)
2.
ሔሌም፥ “አክሊሎችም ለሔሌምና ለጦብያ ለዮዳኤም ለሶፎንያስም ልጅ ለሔን በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ ለመታሰቢያ ይሆናሉ።” (ዘካ 6:14)
ኤላት ~
Elath:
ኃያላት፣ ጠንካራ፣ ዓለት... ማለት ነው። የከተማ ስም፥ “ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ፥ ኤላትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለሳት” (2 ነገ 14:22)
ኤሌፍ ~
Eleph:
‘የተማረ’ ማለት ነው። የብንያም ድርሻ፥ ከተማ፥ “ሬቄም፥ ይርጵኤል፥
ተርአላ፥ ጼላ፥
ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም
የምትባል የኢያቡስ
ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት
አሥራ ሦስት
ከተሞችና ...” (ኢያ 18:28)
ኤልማስ ~ Elymas: ‘አዋቂ፣ ጠቢብ፣
ጠንቋይ’
ማለት ነው።
“ጠንቋዩ
ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው።” (ሐዋ 13:8)
ኤልሞዳም ~ Elmodam:
‘የአምላክ ሚዛን’
ማለት ነው።
በዮሴፍ የዘር
ሐረግ፥ የኤር
ልጅ፥ “የሚልኪ ልጅ፥
የሐዲ ልጅ፥
የዮሳስ ልጅ፥
የቆሳም ልጅ፥
የኤልሞዳም ልጅ፥
የኤር ልጅ፥” (ሉቃ 3:28)
ኤልሳቤጥ ~ Elisabeth, Elisheba:
ኤል ሳባ ቤት፣ ኤል ሳቤት፣ ኤል ሰባት፣ የአምላክ ቤተሰብ፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው።
‘ኤል’፣ ‘ሳባ’ እና ‘ቤት’
ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኤልሳቤጥ / Elisabeth:
ከአሮን ወገን
ስትሆን የዘካርያስ ሚስት፣ የመጥምቁ የዮሐንስ እናት፥ የጌታ እናት የማርያም አክስት፥ (ሉቃ 1፡5)
ኤልሳቤጥ / Elisheba:
የአሮን ሚስት፥ (ዘጸ 6፡23)
ኤልሳዕ ~
Elisha:
ኤል ሺህ፣ የሽዎች ጌታ፣ የብዙዎች አዳኝ፣ የሽዎች አምላክ... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ’ሺህ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር
ደኅንነት ነው
ማለት ነው
/ መቅቃ] የአቤልምሖላን ሰው፥ የሣፋጥ ልጅ፥ (1 ነገ 19፡16-19)
ኤልሻዳይ ~ God,
the Almighty: ኤል ሻዳይ፣ ሁሉን ቻይ፣ ምንም የማይሳነው... ማለት ነው።
እግዚአብሔር ለአብራም የገለጠለት ስም፥ “...እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም
ሁን።”
(ዘፍ 17፡1)
ኤልሻዳይ ~ God, the Almighty: ሁሉን ማድረግ
የሚቻለው፣ ምንም ነገር የማይሳነው... ማለት ነው። የጌታ ስም፥ “አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው
በሆነ ጊዜ
እግዚአብሔር ለአብራም
ተገለጠለትና፥ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥
ፍጹምም ሁን” (ዘጸ
34፡6፣ 7)
ኤልቆሻዊ ~
Elkoshite:
ኤል ኩሽ፣ የኩሽ አምላክ፣ የኩሽዓውያን ጌታ፣ የሰንበት ጌታ... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ’ኩሻይት’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የነቢዩ
ናሆም አገር፥
(ናሆ 1፡1)
ኤልባዝር ~ Nibhaz:
‘ትንቢት፣ ነቢይ’
ማለት ነው።
የጣዖት ስም፥
“የሐማትም ሰዎች አሲማትን
ሠሩ፤ አዋውያንም ኤልባዝርንና
ተርታቅን ሠሩ፤ የሴፈርዋይም ሰዎችም ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን
በእሳት ያቃጥሉ
ነበር”
(2 ነገ 17:31)
ኤልቤቴል ~
Elbethel:
ኤል ቤተ ኤል፣ የአምላክ-ቤተመቅደስ፣ የጌታ ወገን ቤት፣ የኃያሉ አምላክ ቤት... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ‘ቤቴል’
ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ያቆብ ከዔሳው በሸሸው
ጊዜ እግዚአብሔር
የተገለጠለት የቦታ፥
“በዚያም መሰውያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም ኤልቤቴል ብሎ ጠራው እርሱ ከወንድሙ ፊት
በሸሸበት ጊዜ
እግዚአብሔር በዚያ
ተገልጦለት ነበርና።” (ዘፍ
35፡7)
ኤልብሪት ~
Baal-berith:
ባለ በር፣ ባለ በራት፣ ባለቤት... ማለት ነው። (ባለቃልኪዳን ተብሎም
ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስም-
በኣልብሪት]
. በሴኬም ጌዴዎን ከሞት በኋላ፥ “በሴኬምም ግንብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ኤልብሪት ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ።” (መሣ
9:46)
. በኣልብሪት- (መሣ 8፡33፣ 9:4)
ኤልብሪት ~
Berith:
በራት፣ በሮች፣ መተላለፊያ... ማለት ነው። ቃል ኪዳን ወይም
ውል ተብሎ
ይተረጎማል። “በሴኬምም ግንብ
ውስጥ የነበሩ
ሰዎች ሁሉ
ይህን በሰሙ
ጊዜ ወደ
ኤልብሪት ቤት
ወደ ምሽጉ
ውስጥ ገቡ።” (መሣ
9:46)
ኤልተቄን ~ Eltekeh: ‘አምላክን የሚፈራ’ ማለት
ነው። የነገደ
ዳን ከተማ፥
“ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና
መሰምርያዋን፥ ገባቶንንና
መሰምርያዋን፥ ኤሎንንና
መሰምርያዋን፥”
(ኢያ 21:23)
ኤልቶላድ ~
Eltolad:
ኤል ትውልድ፥ የአምላክ ዘር... ማለት ነው። በይሁዳ በስተደቡብ ያለ ከተማ፥ “በኣላ፥ ዒዪም፥ ዓጼም፥ ኤልቶላድ” (ኢያ
15:30)
ኤልናታን ~
Elnathan: ኤል ናታን፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠ፣ የጌታ ሀብት፣ የጌታ ስጦታ፣ የአምላክ ችሮታ... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ‘ናታን’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ንጉሡ ኢዮአቄም ወደ ግብፅ ከላካቸው፥ የዓክቦር ልጅ፥ (ኤር 26:22፣
36:12
፣ 25)
2.
“ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ... የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።”
(2 ነገ 24፡8)
3.
በዕዝራ ዘመን የነበሩ ሦስት ሰዎች “ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሸማያ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ
ሜሱላም፥ ደግሞም
ወደ አዋቂዎቹ
ወደ ዮያሪብና
ወደ ኤልናታን ላክሁ።” (ዕዝ 8:16)
ኤልናዓም ~
Elnaam:
‘አምላክ ደስታዬ’ ማለት ነው። የሁለቱ የዳዊት ዘበኞች፥
የይሪባይና የዮሻዊያ
አባት፥ “መሐዋዊው ኤሊኤል፥
ይሪባይ፥ ዮሻዊያ፥
የኤልናዓም ልጆች፥
ሞዓባዊው ይትማ፥” (1 ዜና 11:46)
ኤልዓሣ ~ Elasah: አምላካዊ ማለት ነው።
1.
በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሴቶችን ካገቡ ካህናት፥ “ከፋስኩር ልጆችም፤ ኤልዮዔናይ፥ ... ናትናኤል፥ ዮዛባት፥ ኤልዓሣ።” (ዕዝ 10:22)
2.
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከላካቸው ሁለት ሰዎች፥ የሳፋን ልጅ፥ “ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን ... ላከው።”
(ኤር 29:3)
ኤልዓዘር ~ Eliezar: ኤል ዘር፣ የጌታ ወገን፣ የተቀደሰ ዘር፣የአምላክ ልጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አልዓዛር፣ አቢዔዜር፣ አቢዔዝር፣ ኤሊሱር፣ ኤሊዔዘር፣ አልዓዛር]
‘ኤል’ እና ‘ዘር’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር እረዳቴ ነው ማለት ነው / መቅቃ]
በጌታ የዘር
ሐረግ የተጠቀሰ፣
የዮሴዕ ልጅ፥
ኤልዓዘር ፥
(ሉቃ 3:29)
ኤልዓድ ~
Elead:
‘ያምላክ ምስክር’ ማለት ነው። የኤፍሬም ወገን፥ “የአገሩም ተወላጆች
የጌት ሰዎች
ከብቶቻቸውን ሊወስዱ
ወርደው ነበርና
የገደሉአቸው ልጆቹ ኤድርና ኤልዓድ ነበሩ።” (1 ዜና 7:21)
ኤልኤል ~
Eliel:
ኤል ኤል፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ጌታ ጌታዬ፣ አምላኬ አምላኬ፣ የኃያላን ኃያል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ኤሊኤል]
‘ኤል’ን በድጋሚ
በመጥራት የተመሠረተ
ስም ነው።
ከዳዊት ዘበኞች፣ የኤልናዓ ልጅ፥ ኤልኤል፥ (1 ዜና 11:46፣ 47)
፣ (1 ዜና 5:24) ፣ (1 ዜና 6:34)
፣ (1
ዜና 8:20)
፣ (1
ዜና 8:22 ፣ 23) ፣ (1
ዜና 11:46)
፣ (1
ዜና11:47)
፣ (1
ዜና 12:11) ፣ (1 ዜና 15:9 ፣ 11) ፣ (2 ዜና 31:13)
ኤልዛባድ ~ Elzabad:
አምላክ የሰጠው ማለት ነው።
1.
ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዳዊት ከተቀላቀሉ ኃይለኞች፥ “ዘጠነኛው ኤልዛባድ፥
አሥረኛው ኤርምያስ፥
አሥራ አንደኛው
መክበናይ።”
(1 ዜና 12:12)
2.
“ለሸማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም ኃያላን የነበሩ ኤልዛባድ፥
ኤልሁ፥ ሰማክያ።” (1 ዜና 26:7)
ኤልዛቤል ~ Jezebel: የ ዘ በዓል፣ በዓለ ኤል፣ በዓል አምላኩ... ማለት ነው። የእስራኤል
ንጉሥ፥ የአክዓብ ሚስት፥ የኤትበኣልን ልጅ፥ “... የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፥ ሄዶም በኣልን አመለከ ሰገደለትም” (1 ነገ 16:31)
ኤልዩድ ~
Eliud:
ኤል ሁድ፣ ኤል ውድ፣ በአምላክ የተወደደ... ማለት ነው። (ከጌታ የተዋሐደ፣ የአምላክ አንድነት ተብሎም ይተረጎማል።)
በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የአኪም ልጅ፥ ኤልዩድ፥ (ማቴ 1:15)
ኤልያሊ ~
Elealeh:
ዔል ላይ፣ ታላቅ አምላክ፣ የላይኛው ጌታ፣ የበላይ አምላክ... ማለት ነው።
የሮቤል ልጅ ርስት ሁኖ የተሰጠ፥ የቦ ታ ስም፥ (ዘኁ 32:37) ፣ (ዘኁ 32:3 ፣ 37) ፣ (ኢሳ 15:4 ፣ 16:9፣ ኤር
48:34)
ኤልያሴብ ~ Eliashib: ኤል ያስብ፣ አምላክ ያሰበው፣ እግዚአብሔር የረዳው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኢልያሴብ]
‘ኤል’ እና ‘ያስብ’
ከሚሉት ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
ከይሁዳ ወገን፣ የኤልዮዔናይ ልጅ፥ (1
ዜና 3:24)
2.
አልዓዛርና ከኢታምር
ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች ለአገልግሎት፥ በዕጣ ከተመደቡ፥ (1 ዜና 24፡12)
3.
በነህምያ ዘመን፣ ከምርኮ ሲመለሱ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ከጠገኑ፥ (ነህ 3:1 ፣ 20 ፣ 21)
4.
በዕዝራ ዘመን፣ ከምርኮ ሲመለሱ እንግዳ ሚስቶችን አግብተው ከነበሩ፥ (ዕዝ 10:24)
5.
እንግዶች ሚስቶች ካገቡ፣ የባኒ ልጅ፥ (ዕዝ 10:36)
. እንግዶች ሚስቶች ከአገቡ፥ የዛቱዕ ልጅ፥ ኢልያሴብ፥ (ዕዝ 10:27)
ኤልያስ ~
Eliah, Elijah: ኤል ዋስ፣ ኤል ያሕ፣ ሕያው ጌታ፣ ኃያል አምላክ፣ ሕያው አምላክ... ማለት ነው።
Eliah,
Elijah- ‘ኤል’ እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኤልያስ / Eliah:
1.
ብንያማዊው የነገዱ
አለቃ፥ (1 ዜና 8፡27)
2.
በዕዝራ ዘመን እንግዶች ሚስቶችን ካገቡ፣ ከካሪም ልጅ፥ (ዕዝ 10: 21፣
26)
ኤልያስ / Elijah: የሞተን ልጅ ያስነሣ፣ ዝናም ለሁለት ዓመት እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ፣ ነቢዩ ኤልያስ ፥ (1 ነገ 17፡1)
[ትርጉሙ ‘እግዚአብሔር አምላክ ነው’ ማለት ነው / መቅቃ]
[...ፍችው፥ ኃይለ እግዚአብሔር። አ / ኪወክ]
ኤልያስ ~
Elias:
ኤል ዋስ፥ ኃያል አዳኝ፥ኃይለ እግዚአብሔር... ማለት ነው። “ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።”
(ማቴ11:14)
ኤልያቄም ~ Eliakim: ኤል ያቆም፣ ኤል አቆመ፣ በአምላክ የጸና፣ እግዚአብሔር ያነሣው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ቀሙኤል፣ ቁሚ፣ አኪቃም፣ አዶኒቃም፣ ኢዮአቄም፣ ዓዝሪቃም፣ ያቂም፣ ዮቂም፣ ዮአቂም]
‘ኤል’
እና ‘ቆመ’
ከሚሉት ሁለት
የተመሠረተ ስም
ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር
ያስነሳል ማለት
ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የኬልቅያስ ልጅ፥ (2 ነገ 18፡18) ፥ (ኢሳ 36:3)
፥ (2 ነገ 18:18 ፣ 26
፣ 37)
2.
በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ የዮናን ልጅ፥ (ሉቃ 3፡30 ፣31)፣ (ማቴ
1:13)
3.
የኢዮስያስ ልጅ የኢዮአክስ ወንድም፥ የኢዮአቄም የቀድሞ ስም፥
(2
ዜና 36:4)፣ (2 ነገ 23:34)
4.
በነህምያ ዘመን የነበረ ካህን፣ የኢየሩሳሌም ግንብ በማደስ የተባበረ፥ (ነህ 12:41)
ኤልያብ ~
Eliab, Aholiab, Eliam: ኤል አብ፣ የአባቴ አምላክ፣ አባቴ አምላኬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
አቤል፣ አቢኤል]
‘ኤል’ እና ‘አብ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የአሂሳሚክ ልጅ፥
(ዘጸ 31:6)
2.
የሮቤል ልጅ፣ የዳታንና አቤሮን አባት፥ (ዘኁ 16፡1፣12)
3.
የኬሎን ልጅ፥ (ዘኁ 1:9 ፣ 2:7
፣ 7:24 ፣ 29
፣ 10:16)
4.
የዳዊት ወንድም፣ የእሴ ልጅ፥ (1 ሳሙ 16:6 ፣ 17:13 ፣ 28 ፥ 1
ዜና
2:13)
5.
በዳዊት ዘመን የነበረ መዘምር፥ (1 ዜና 15:18 ፣ 20
፣ 16:5)
6.
ከጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች፥ (1
ዜና 12:10)
7.
የሕልቃና ልጅ፥
(1 ዜና 6:27)
ኤልያብ
~
Aholiab: ኃያል አባት፣ የአብ ድንኳን፣ ያባት ርስት... ማለት
ነው። ለቤተመቅደሱ
ንዋየ ቅዱሳትን
እንዲያዘጋጁ ከተመረጡ፥
ከዳን ነገድ የሆነ፥
የአሂሳሚክ ልጅ፥ “እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ጥበብን አኖርሁ።” (ዘጸ 31:6፤ 35:34፤ 36:1፣2፤ 38:23)
ኤልያብ ~
Eliam:
ዓለም፥ የአምላክ ፍጥረት፥ በጠቅላላው... ማለት ነው።
1.
የንጉሥ ዳዊት
የሚስቱ አባት፥
“ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ አንድ
ሰውም። ይህች
የኤልያብ ልጅ
የኬጢያዊው የኦርዮ
ሚስት ቤርሳቤህ
አይደለችምን?
አለ።”
(2 ሳሙ 11:3)
2.
ከሠላሳዎቹ የዳዊት ኃያላን አንዱ፥ “የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥ የማዕካታዊው ልጅ የአሐስባይ ልጅ ኤሌፋላት፥ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ
ኤልያብ፥”
(2 ሳሙ 23:34)
ኤልያታ ~ Eliathah: ‘ኃያል አንተ፣ አምላክን ያገኘ’ ማለት
ነው። በዳዊት
ጊዜ፥ በቤተ
መቅደስ፥ ይዘምሩ
ከነበሩ፥ “ከኤማን የኤማን
ልጆች ቡቅያ፥
መታንያ፥ ዓዛርዔል፥
ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥
ሆቲር፥ መሐዝዮት” (1 ዜና 25:4፥27)
ኤልያና ~
Elhanan:
ኤል ሐናን፣ የእግዚአብሔር ቡሩክ፣ የአምላክ ጸጋ፣ ትሑት፣ አምላከ ሐናን... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ‘ሐናን’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
በዳዊት ጭፍሮች ዘንድ ከነበሩት ኃያል፥ የየዓሬ ኦርጊ ልጅ፥ (2
ሳሙ
21፡19)
2.
በዳዊት ጭፍሮች ዘንድ ከነበሩት ኃያል፥ የዱዲ ልጅ፥ (2 ሳሙ 23:24፣
25)፣ (1
ዜና 11:26)
ኤልያፍ ~ Elihoreph: ‘የአምላክ ሽልማት’ ማለት
ነው። ከሰሎሞን ጸሐፍት አንዱ፥
“ጸሐፊዎቹም የሴባ ልጆች
ኤልያፍና አኪያ፥
ታሪክ ጸሐፊም
የአሒሉድ ልጅ
ኢዮሣፍጥ፥”
(1 ነገ 4:3)
ኤልዮዔናይ ~
Elioenai:
ኤል አየን፣ ኢሌኒ፣ ጌታ አየነ፣ አምላክ ያየው፣ የአምላክ ዓይኖች... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤሊሆዔናይ፣ ኤሊዔናይ፣ ዔሊዮዔናይ]
‘ኤል’ እና ‘ዓይን’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ
በዚህ ስም
የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የነዓርያ ልጅ፥
(1 ዜና 3:23
፣ 24)
2.
የዓሢኤል ልጅ፥
(1 ዜና 4:36)
3.
የቤኬር ልጅ፥
(1 ዜና 7:8)
4.
የሜሱላም ልጅ፥
(1 ዜና 26:3)
5.
የፋስኩር ልጅ፥
(ዕዝ 10:22)
. የዛቱዕ ልጅ፥ ዔሊዮዔናይ- (ዕዝ 10:27)
ኤልዳዓ ~
Eldaah:
የአምላክ ጥበብ ማለት ነው። የኬጡራ ልጅ፣ የምድያም ልጅ፥ “የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።” (ዘፍ 25:4፥ 1
ዜና 1:3)
ኤልዳድ ~ Eldad, Elidad:
ኤልዳድ፣ ኤልወደድ፣ አምላክ የወደደው፣ በጌታ የተወደደ... ማለት ነው።
‘ኤል’ እና ‘ውድ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ኤልዳድ / Eldad:
ሙሴ ከመረጣቸው፥ ከሰባው ሽማግሌዎች፣ ነቢዩ ኤልዳድ፥ (ዘኁ 11:26)
ኤልዳድ / Elidad:
ምድሪቱንም ርስት
አድርገው ይከፍሉ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ሙሴን እንደነገረው፥ የኪስሎን ልጅ፥ (ዘኁ 34:21)
ኤልዳፋ ~ Elzaphan: ‘አምላክ የጠበቀው’ ማለት ነው። የዑዝኤል ሁለተኛ ልጅ፥ “የዑዝኤል ልጆች ሚሳኤል፥ ኤልዳፋን፥ ሥትሪ ናቸው” (ዘጸ 6:22)
ኤልፋዝ ~ Eliphaz: ‘አምላክ ያበረታው’ ማለት ነው።
1.
ዓዳ ለዔሳው
የወለደችለት፥ የተመን
አባት፥ “ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች” (ዘፍ 36:4፤ 1 ዜና 1:35፥36)
2.
“ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው
ሶፋር ነበሩ።
...” (ኢዮ 2:11፥15:12-16)
ኤልፍዓል ~ Elpaal: ‘የአምላክ ሥራ’ ማለት ነው። የብንያማዊው፥” ሸሐራይ ልጅ፥ የአቢጡብ ወንድም፥ “ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ” (1 ዜና 8:11)
ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ~ Eli, Eli, lama
sabachthani: አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኽኝ…
ጌታ በጸሎቱ ከተጠቀመባቸው ቃላት፥ “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ፤ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን
ተውኸኝ፤ ማለት
ነው።”
(ማቴ 27፡46)
ኤሎን፣ ኤሎም ~ Ajalon: ‘ሰንሰለት’ ማለት ነው።
1.
ለነገደ ዳን
የተሰጠ፥ ከተማና
ሸለቆ፥ “አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በኤሎን በሸዓልቢምም
በመቀመጥ ጸኑ። ነገር
ግን የዮሴፍ
ቤት እጅ
ከበደች፥ አስገበረቻቸውም።” (መሣ 1:35)
2.
በኤሎም የተሰየመ፥ የዛብሎን ነገድ ከተማ፥ ኤሎም፥ “ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፥
በዛብሎንም ምድር
ባለችው በኤሎም
ተቀበረ።”
(መሣ 12:12)
ኤሎን ~ Elon: ‘ዝግባ’
የዛፍ ዓይነት ነው።
1.
የዳን ከተማ፥ “ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥ ተምና፥” (ኢያ
19:43)
2.
የዔሳው ሚስት፣ የቤሴሞት አባት፥ “ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች
አድርጎ አገባ” (ዘፍ 26:34)
3.
የዛብሎን ልጅ፥ “የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ፥ ኤሎን፥ ያሕልኤል”
(ዘፍ 46:14)
4.
በእስራኤል ላይ ፈራጅ ከነበሩ፥ ከአሥራ ሁለቱ አሥራ አንደኛው፥ “ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፥ በዛብሎንም ምድር ባለችው በኤሎም ተቀበረ” (መሣ
12:11፣12)
ኤሚም ~
Emims:
እመም፣ ሕመም፣ በሽታ... ማለት ነው። በአብርሃም ዘመን በዮርዳኖስ
በስተምሥራቅ፥ በኋላም
በሞዓባውያን ምድር
ይኖሩ የነበሩ
ሰዎች፥ “በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ” (ዘፍ
14:5፤ ዘዳ 2:10)
ኤማሁስ ~
Emmaus:
‘ፍል ውኃ፣ መታጠቢያ፣ መዋኛ’ ማለት ነው። በትንሣኤው ዕለት፥ ጌታ ከገበያተኞች
ጋር ይሄድበት
የነበረ መንደር፥
“እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ
በዚያ ቀን
ከኢየሩሳሌም ስድሳ
ምዕራፍ ያሕል
ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ
ነበር”
(ሉቃ 24:13)
ኤማን ~
Heman:
አማን፣ ሃማን፣ ያመነ፣ የታመነ፣ ሰላም ያገኘ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ሄማን፣ አማን፣ አሜን]
‘አማን’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የቀዓት ልጅ፥ ዘማሪው ኤማን፥ (1 ዜና 6:33)
2.
የኢዮኤል ልጅ፥
(1 ዜና 15:17)
. የማሖል
ልጅ፥ ሄማን- (1
ነገ 4፡31)
. የዛራ ልጅ፥ ሄማን- (1 ዜና2:6)
ኤሞር ~ Emmor, Hamor: ‘ውርንጭላ፣ተሸካሚ፣ አገልጋይ፣ የጭነት እንስሳ፣ አህያ’ ማለት ነው።
የሴኬም አባት፥
“ወደ ሴኬምም አፍልሰው
አብርሃም ከሴኬም
አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው
መቃብር ቀበሩአቸው።” (ሐዋ 7:16)
ኤሞር / Hamor: “ድንኳኑን ተክሎበት
የነበረውንም የእርሻውን
ክፍል ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው” (ዘፍ 33:19፥ 34:2፣4፣
6፣8፣13፣18፣20፣24፣26)
ኤሲሊ ~ Esli: ‘አቅራቢያ’
ማለት ነው።
በጌታ የዘር
ሐረግ፥ የነጌ
ልጅ፥ “የዮና ልጅ፥
የዮሴፍ ልጅ፥
... ልጅ፥ የናሆም
ልጅ፥ የኤሲሊም ልጅ”
(ሉቃ 3:25)
ኤስሮም ~ Esrom: ‘እስር፣ እጥር፣ ክልል’
ማለት ነው።
“ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና
ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤” (ማቴ 1:3፤ ሉቃ 3:33)
ኤስቦን፣ ኤሴቦን ~ Ezbon: አገልግሎት ማለት ነው።
1.
የጋድ ልጅ፥ “የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤስቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥
አርኤሊ።”
(ዘፍ 46:16፤ ዘኊ 26:16)
2.
የቤላ ልጅ፥ “የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ... ሀያ ሁለት ሺህ
ሠላሳ አራት
ነበሩ።”
(1 ዜና 7:7)
ኤስና ~
Ozni:
ኦዝን፣ ዕዝን፣ ጆሮ፣ አዳማጭ፣ ሰሚ፣ አዛኝ... ማለት ነው።
‘አዘነ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው። የጋድ ልጅ፥
(ዘኁ 26:16)
ኤስኮል ~ Eshcol: ‘የወይን ዘለላ’ ማለት
ነው። አብርሃም
ሎጥን ከምርኮ
ለማስመለስ ባደረገው ጥረት ተባባሪ የነበረ፥ “አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም
ነገረው፤ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም
... ጋር ቃል
ኪዳን ገብተው
ነበር።”
(ዘፍ 14:13፣24)
ኤስድሪኤል ~ Adriel: ‘የአምላክ ሕዝብ’ ማለት
ነው። ለዳዊት
ታጭታ የነበርን
የሳኦል ልጅ፣
ሜሮብን ያገባ፥
የቤርዜሊ ልጅ፥
“ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜሮብ ዳዊትን የምታገባበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤስድሪኤል ተዳረች” (1 ሳሙ 18:19)
ኤራ ~
Arah:
ኤራ፣ ኤረያ፣ ሰማያዊ፣ ከምድር የራቀ... ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የዑላ ልጅ፥
(1 ዜና 7፡39)
2.
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2:5) ፣ (ነህ 7:10)
3. “ጦብያም
የኤራ ልጅ
የሴኬንያ አማች
ስለ ነበረ፥
...” (ነህ 6:18)
ኤራስ ~
Hirah:
‘ራስ፣ የንጉሥ ወገን፣ ክቡር ዘር፣ ወራሽ’ ማለት ነው። የይሁዳ ወዳጅ፥ “በዚያም ወራት እንዲህ
ሆነ ይሁዳ
ከወንድሞቹ ተለይቶ
ወረደ፥ ስሙን
ኤራስ ወደሚሉት
ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው
ገባ።”
(ዘፍ 38:1፣12)
ኤሬስ ~
Heresh:
‘አናጢ’ ማለት ነው። ከመቅደስ አገልግሎት ጋር ቅርበት የነበረ
ሌዊያዊ፥ “በቅበቃር፥ ኤሬስ፥
ጋላል፥ የኣሳፍ
ልጅ የዝክሪ
ልጅ የሚካ
ልጅ መታንያ” (1 ዜና 9:15)
ኤርማፍ ~
Harumaph:
‘ሰልካካ አፍንጫ’ ማለት ነው። የይዲያ አያት፥ “በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ
አንጻር ያለውን
አደሰ። በአጠገቡም
የአሰበንያ ልጅ
ሐጡስ አደሰ” (ነህ 3:10)
ኤርምያ ~
Jeremiah:
የራመ ያሕ፣ ራማ ያሕ፣ ታላቅ አምላክ፣ የሰማዩ ጌታ፣ የላይኛው ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ኤርምያስ]
ከምናሴ ነገድ፥ በዮርዳኖስ በስተምሥራቅ፣ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ (1 ዜና 5:24)
ኤርምያስ ~ Jeremiah, Jeremias:
የራመ ያሕ፣ የራመ ዋስ፣ ታላቅ አምላክ፣ የሰማዩ ጌታ፣ የላይኛው አዳኝ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤርምያ] [ትርጉሙ እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው / መቅቃ]
‘ራማ’ እና ‘ያሕ፣ ዋስ’ (ያሕዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኤርምያስ /
Jeremiah:
1.
ዳዊት ከምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአንባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ ጋሻና ጦር የሚይዙ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ሰልፈኞች፥ ወደ እርሱ ከተጠጉ፥ (1 ዜና
12፡11)
2.
ዳዊት ከምድረ
በዳ ውስጥ
ባለችው በአንባይቱ
ሳለ ከጋድ
ወገን የሆኑ
እነዚህ ጋሻና ጦር የሚይዙ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ሰልፈኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፥ (1 ዜና
12:13)
3.
በጺቅላግ ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ፥ (1
ዜና 12:4)
4.
የምናሴ የነገድ እኵሌታ ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ (1 ዜና
5:24)
5.
የንጉሥ ኢዮአክስ
አያት፥ (2 ነገ 23:31)
6.
ነቢዩ፣ የኬልቅያስ
ልጅ፥ (ኤር 1:1) ፣ (ኤር 32:6)
ኤርምያስ / Jeremias:
“እርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት” (ማቴ 16:14)
ኤርስጦስ ~ Erastus: ተወዳጅ፣ ተፈቃሪ ማለት ነው።
1.
የቆሮንጦስ ከተማ
ሹም፥ “... የከተማው መጋቢ ኤርስጦስ ወንድማችንም ቁአስጥሮስ
ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።” (ሮሜ 16:23)
2.
ከጢሞቴዎስ ጋር ወደ ሜቅዶኒያ የተለከ የጳውሎስ አገልጋይ፥ “ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፥ ጥሮፊሞስን ... በሚሊጢን ተውሁት።”
(ሐዋ 19:22)
ኤርጌል ሳራስር ~ Nergal-sharezer: ‘የጀግና ዘር’ ማለት ነው። የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን
በወረረ ጊዜ፥
አብረውት ከነበሩ
አለቆች፥ “የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ... ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች
ሁሉ ጋር
ገብተው በመካከለኛው
በር ውስጥ
ተቀመጡ።”
(ኤር 39:3፣13)
ኤርጌል
~ Nergal:
‘ታላቅ፣ ክቡር’
ማለት ነው።
ከታዋቂ የአሲርያ
አማልክት አንዱ፥
“የባቢሎንም ሰዎች ሱኮትበኖትን
ሠሩ የኩታም
ሰዎች ኤርጌልን
ሠሩ”
(2 ነገ 17: 30)
ኤሽታኦል~
Eshtaol: ‘ሺሕ ታውል፣ ጠንካራ ሴት’ ማለት ነው። ለዳን ነገድ የተሰጠ፥ የይሁዳ የታችኛው አገር፥ “በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ ዛኖዋ”
(ኢያ 15:33)
ኤሽትሞዓ ~ Eshtemoa: እሽታም፥ ፈቃደኛ፥ ታዛዥ ማለት ነው። በይሁዳ ተራራማ ክፍል የነበረ ከተማ፥ “የቲርንና መሰምርያዋን፥ ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥” (ኢያ 21:14፤ 1 ዜና 6:57)
ኤሽዓን ~
Eshean:
‘አቀበት፥ ቁልቁለት’
ማለት ነው። ከይሁዳ ከተሞች አንዱ፥ (ኢያ 15:52) “አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ ያኒም፥ ቤትታጱዋ፥”
ኤብያ ~ Habaiah: ‘አምላክ የጋረደው’ ማለት
ነው። ከባቢሎን
ምርኮ ከተመለሱ፥ የኤብያ ልጆች፥ ይገኙበታል፥ “ከካህናቱም ልጆች የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥
ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ
ልጆች ሚስት
ያገባ፥ ...” (ዕዝ 2:61፤ ነህ 7:63)
ኤታም ~ Etham: ‘ደሴት’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን ከግብፅ
ከወጡ በኋላ
ካረፉባቸው ቦታዎች፥
“ከሱኮትም ተጓዙ፥ በምድረ
በዳውም ዳር
በኤታም ሰፈሩ።” (ዘጽ
13:20፤ ዘኊ33:6፣7)
ኤታኒም ~ Ethanim: ‘ብርቱ’
ማለት ነው።
የወር ስም፥
ወርሃ ጽጌ፥
“የእስራኤልም ሰዎች ኤታኒም በሚባል በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ
ሰሎሞን ተከማቹ።” (1 ነገ 8:2)
ኤታን ~ Ethan: ‘ዘላቂ’ ማለት ነው።
1.
ጠቢብነቱ ከንጉሥ ሰሎሞን ጋር የተነጻጸረ፥ ከአራቱ የማሖል ልጆች አንዱ፥ “ከሰውም ሁሉ
ይልቅ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች
ከሄማንና ከከልቀድ
ከደራልም ይልቅ
ጥበበኛ ነበረ።
በዙሪያውም ባሉ
አሕዛብ ሁሉ
ዝናው ወጣ።” (1 ነገ
4:31፤ 1
ዜና 2:6)
2.
በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ፥ የሜራሪ ወገን፥ የቂሳ ልጅ፥ “በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ” (1 ዜና 6:44)
3.
ንጉሥ ሰሎሞን
የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ
ድንኳን ማደሪያ
ፊት እያዜሙ
ያገለግሉ ከነበሩ፥ “የዓዳያ ልጅ፥
የኤታን ልጅ፥
የዛማት ልጅ፥” (1 ዜና 6:42)
ኤታይ ~ Ithai: ‘ከጌታ ጋር’ ማለት
ነው። የብንያም
ወገን፥ ግብዓያዊው
የሪባይ ልጅ፥
“ከብንያም ወገን ከግብዓ
የሪባይ ልጅ
ኤታይ፥”
(1 ዜና 11:31)
ኤትበኣል ~
Ethbaal:
የት በዓል፥ ወደ በዓል... ማለት ነው። የሰዶን ንጉሥ፥ የኤልዛቤል
አባት፥ ... የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ
ኤልዛቤልን አገባ፥
ሄዶም በኣልን
አመለከ ሰገደለትም” (1 ነገ 16:31)
ኤትኒ ~
Ethni:
‘ጠንካራ’
ማለት ነው። የመልክያ ልጅ፥ “የመልክያ ልጅ፥ የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥”
(1 ዜና 6:41)
ኤትና ~ Ethnan: ‘ቅጥር’
ማለት ነው።
ከሔላም ልጆች
አንዷ፥ የአሱር
ሚስት፥ “የሔላም ልጆች
ዴሬት፥ ይጽሐር፥
ኤትናን ናቸው።” (1 ዜና
4:7)
ኤንሐዳድ ~ Henadad: የመወደድ
ጸጋ ማለት
ነው። የሌዊ
ወገን፥ በመቅደሱ
ጥገና ከፍተኛ
ተሳትፎ ካደረጉት
አንዱ፥ “ኢያሱም ልጆቹም
ወንድሞቹም፥ የይሁዳም
ልጆች ቀድምኤልና
ልጆቹ፥ የኤንሐዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ያሠሩ ዘንድ
በአንድነት ቆሙ።” (ዕዝ 3:9)
ኤንያ ~ Aeneas: ‘ምስጉን፣ ተመስጋኝ’ ማለት
ነው። ጴጥሮስ
የፈወሰው አካለ ስንኩል ሰው፥ “በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ።” (ሐዋ 9:33፣34)
ኤኬላ ~ Hachilah: የተራራ
ስም፥ “የዚፍ ሰዎችም
ወደ ሳኦል
ወደ ጊብዓ መጥተው። እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ደቡብ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በጥሻ ውስጥ ባሉት አምባዎች በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን?” (1 ሳሙ 23:19)
ኤክራን ~ Ocran:
‘ጭንቀት፣ መከራ፣ ችግረኛ’
ማለት ነው።
የፋግኤል አባት፥
“ከአሴር የኤክራን ልጅ ፋግኤል፥” (ዘኊ 1:13፥ 2:27፥7:72፣77፥ 10:26)
ኤዊ ~
Evi:
ኤዊ፣ ሕያው፣ ሒዋን፣ ሒዋዊ... ማለት ነው። (መጎምጀት፣ መሳሳት፣ መመኘት ማለት ነው፥ ተብሎም ይተረጎማል)
‘ሕያው’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
እግዚአብሔር ሙሴን
እንዳዘዘ ከምድያም
ጋር ተዋጉ፥
ወንዶችንም ሁሉ
ገደሉ፥ ከተገደሉት፥
የምድያም ነገሥታት
አንዱ ኤዊ፥
(ዘኁ 31፡8)፣ (ኢያ 13:21)
ኤዊያውያን ~
Hivites:
‘ሕያውያን፣ ኗሪዎች፣ መንደርተኛ’ ማለት ነው። የካም ልጅ፣ የከነዓን ስድስተኛ
ልጅ፥ “ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም”
ኤዋው፣ አዋው ~ Avim: ‘ቅን፣ ፈቃደኛ፣ መልካም ሰው’ ማለት ነው።
1.
ቀደም ብለው በፍልስጥኤም ከሰፈሩ፥ “እስከ ጋዛም ድረስ በመንደሮች ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም
ተቀመጡ”
(ዘዳ 2:23)
2.
በአሲሪያ ንጉሥ ተባረው፥ በእስራኤል ከተሞ ች እንደገና ከሰፈሩ፥ “የሐማትም ሰዎች
አሲማትን ሠሩ፤ አዋውያንም
ኤልባዝርንና ተርታቅን
ሠሩ፤ የሴፈርዋይም ሰዎችም ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን
በእሳት ያቃጥሉ
ነበር።” (2 ነገ 17:31)
ኤውላጥ ~ Havilah: ‘ክብ’ ማለት ነው።
1.
የኩሽ ልጅ፥ “የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው።” (ዘፍ 10:7)
2.
የዮቅጣን ልጅ፥
“ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ እነዚህ
ሁሉ የዮቅጣን
ልጆች ናቸው።” (ዘፍ 10:29)
ኤውንቄ ~ Eunice: ‘አሸናፊ፣ ድልነሳ፣
ድልነሽ፣ አሸናፊ’ ማለት
ነው። ግሪካዊ
ኢአማኒ ያገባች
አይሁዳዊት ሴት፥
የጢሞቴዎስ እናት፥
“...
ይህም እምነት
ቀድሞ በአያትህ
በሎይድ በእናትህም
በኤውንቄ ነበረባቸው፥
...” (ጢሞ 1:5)
ኤውግሎስ ~ Eubulus:
‘መልካም መካር’
ማለት ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ
በመልክቱ የጠቀሰው፥
በሮም የነበረ
ክርስቲያን፥ “ከክረምት በፊት
እንድትመጣ ትጋ።
ኤውግሎስና ጱዴስ
ሊኖስም ቅላውዲያም
ወንድሞችም ሁሉ
ሰላምታ ያቀርቡልሃል።” (2 ጢሞ 4:21)
ኤዎድያን ~ Euodias: ‘የተወደደ፣ የተመረጠ እጣን’ ማለት
ነው። በፊልጵስዩስ
የነበረች ክርስቲያን፥ “በአንድ አሳብ በጌታ እንዲስማሙ ኤዎድያንን እመክራለሁ ሲንጤኪንንም
እመክራለሁ።”
(ፊልጵ 4:2)
ኤዜል ~
Ezel:
‘እዘ ኃያል፣ ታዛዥ፣ አገልጋይ፣ መልእክተኛ’ ማለት ነው። በሳኦል ቤት አቅራቢያ የሚገኝ፥ ታዋቂ ድንጋይ፥ “... ከዚህም በኋላ ፈጥነህ ውረድ፥ ነገሩም በተደረገበት ቀን ወደ ተሸሸግህበት ስፍራ
ሂድ፥ በኤዜል ድንጋይም አጠገብ ቆይ።” (1 ሳሙ
20:19)
ኤዜልያስ ~ Azaliah: አዝ
ለ ያሕ
(ዋስ) ፣ እዘለ ያሕ፣
ለሕያው የተያዘ፣
ለጌታ የተጠበቀ፣ ለአምላክ የተሰጠ፣ በአምላክ የተያዘ ማለት ነው።
በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን ጸሐፊ የነበር፣ የሳፋን ልጅ፣ የሜሶላም ልጅ፥ (2 ነገ 22፡3
፣ 2 ዜና 34:8)
ኤዜቄል ~
Jehezekel:
የእዝቅ ኤል፣ የሕያው ኃይል፣ ኃይለ እግዚአብሔር... ማለት ነው።
በዳዊት ዘመን በእግዚአብሔር የሚያገለግል ካህን፥ (1 ዜና 24፡16)
፣ (2 ዜና 28:12)
ኤዝርኤል ~
Azarael, Azareel: አዛረ ኤል፣ ዘረ ኤል፣ የአምላክ ዘር፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዓዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ ዓዛርኤል]
‘ዘር’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኤዝርኤል / Azarael:
በዳዊት ዘመን፥ ከአመስጋኞች ተርታ በእግዚአብሔር ቤት የቆሙ፥ (ነህ 12፡36)
ኤዝርኤል / Azareel:
1.
እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው ከነበሩ፥ (ዕዝ 10:41)
2.
የአሕዛይ ልጅ፥
(ነህ 11:13)
. ከሳዖል
በሸሸ ጊዜ፥
ከዳዊት ሠራዊት
ጋር የተቀለቀለ፥
አዛርኤል-
(1 ዜና
12፡6)
. በዳዊት ዘመን፣ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ
ከነበሩ፥ ዓዛርኤል- (1
ዜና 25:18)
. በእስራኤል ልጆች ነገዶች አለቆች ከነበሩ፣ የይሮሐም ልጅ፥ ዓዛርኤል- (1 ዜና 27:22)
ኤዝባይ ~
Ezbai:
እዝ ባይ፣ እዘ አብ፣ እዝብ፣ ሕዝብ፣ ሕዝባዊ፣ የአምላክ ሕዝብ... ማለት ነው።
‘ዘ አብ’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
በዳዊት ጭፍሮች ዘንድ ከነበሩት ኃያላን፣ የነዕራይ አባት፥ (1 ዜና 11፡37)
ኤድራይ ~ Edrei: ‘ብርቱ፣ ጠንካራ’ ማለት ነው።
1.
ከባሳን መንግሥት ዋና ከተሞች አንዱ፥ “ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና
በኤድራይ የተቀመጠው፥
...” (ኢያ 12:4፣5)
2.
የንፍታሌም ከተማ፥
“ቃዴስ፥ ኤድራይ፥ ዓይንሐጾር፥ ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥
ሖሬም፥ ቤትዓናት፥
ቤትሳሚስ አሥራ
ዘጠኝ ከተሞችና
መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 19:37)
ኤዶም ~
Edom:
ኤደም፣ የደም፣ አደም፣ ደማዊ፣ ቀይ... ማለት ነው።
‘ደም’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
የዔሳው ሌላ ስም፥ “ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።” (ዘፍ 25:30)
ኤዶምያስ ~
Idumea:
‘ደሜ፣ ወገኔ’ ማለት ነው። “ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች እነሆ፥ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ ለፍርድ ትወርዳለች።” (ኢሳ 34:5)
ኤዶታምን ~
Jeduthun:
‘ማመስገን’ ማለት ነው። ከሌዊ ወገን፥ የሜራሪ ልጅ፥
“ምህረቱም ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔርን ያመሰግኑ
ዘንድ ኤማንንና
ኤዶታምን፥ በስማቸውም
የተጻፉትን ...” (1 ዜና 16:41፣42፥ 25:1፣3፣6)
ኤግላይም ~ Eglaim: ‘ሁለት ኩሬዎች’ ማለት
ነው። በኢሳይያስ የተጠቀሰ
የቦታ ስም፥
“ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ
ሁሉ ዞረ
ልቅሶዋም ወደ
ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።” (ኢሳ 15:8)
ኤጣም ~ Etam: ‘ጫካ፣ ዱር’ ማለት ነው።
1.
የሲሞን ነገድ
ከተማ፥ “መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥
ቶኬን፥ ዓሻን፥
አምስቱ ከተሞች” (1 ዜና 4:32)
2.
“በይሁዳና በብንያም
ያሉትንም የተመሸጉትን ከተሞች፥ ቤተ ልሔም፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥” (2 ዜና 11:6)
ኤጤሌ~ Apelles: ‘ማጥለል፣ መለየት’ ማለት ነው። በሮም የነበረ፥
ጳውሎስ በሰላምታ
ደብዳቤው የጠቀሰው፥
“በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ
ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ።”
(ሮሜ 16:10)
ኤጳፍራ ~ Epaphras:
‘ተወዳጅ’ ማለት ነው። የሐዋርያው
ጳውሎስ ደቀ
መዝሙርና አገልጋይ የነበረ፥ “ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ
ተማራችሁ፥ ...” (ቆላ 1:7)
ኤጽር ~
Ezer:
እዝር፣ ዘር፣ ወገን፣ ዘመድ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤድር፣ ዔጼር]
‘ዘር’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በዚህ
ስም የሚታወቁ
ሰዎች:-
1.
የሖሪው የሴይር ልጅ፥ (ዘፍ 36፡21 ፣ 27)
2.
የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ፥ ... (1 ዜና 4:4)
3.
የኢያሱ ልጅ፥
... (ነህ 3:19)
4.
በነህምያ ዘመን፥
የኢየሩሳሌምን ቅጥር
በመጠገን የተባበረ
ካህን፥ (ነህ
12:42)
. ዳዊት ከምድረ በዳ ሳለ ፥ ጋሻና ጦር ከሚይዙ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ሰልፈኞች፥
ዔጼር፥ (1 ዜና 12:8)
. የኤፍሬም
ልጅ፥ ኤድር፥
(1 ዜና 7:21)
ኤፌስደሚ ~ Ephes-dammim:
የፈሰሰ ደም፣ የደም ድንበር... ማለት ነው።
በይሁዳ ነገድ፥
ዳዊት ከጎልያድ
ጋር በተዋጋ
ጊዜ፥ ፍልስጤማውያን
የሰፈሩበት ምሽግ፥
“ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን በይሁዳ
ባለው በሰኮት
አከማቹ በሰኮትና
በዓዜቃ መካከል
በኤፌስደሚም ሰፈሩ።” (1 ሳሙ 17:1)
ኤፌሶን ~ Ephesus: ‘የተፈቀደ’
ማለት ነው።
በእስያ የሮማውያን
ዋና ከተማ፥
“የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን
ጸጥ አሰኝቶ
እንዲህ አለ፦
የኤፌሶን ሰዎች
ሆይ፥ የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?” (ሐዋ 19:35)
ኤፍራታ ~
Ephrath:
የፍሬያት፣ ያፍራት፣ ያብዛ፣ ያበርክት... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስሞች-
ኤፍሬም፣ ኤፍሮን፣ ኦፊር፣ ፉራ፣ ፍሬ]
‘ፍሬያት’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
1.
ያዕቆብ ከቤቴል ሲመለስ ያረፈበት ቦታ፥ (ዘፍ 35፡16)
2.
የካሌብ ሚስት፥ “... ካሌብም ኤፍራታን አገባ እርስዋም ሆርን ወለደችለት።”
(1 ዜና 2:50)፣ የቤተ
ልሔም አባት፥
(1 ዜና
4:4)
ኤፍራታ ~ Ophrah: አፈራ፣ ፍሬያት፣
ፍሬያማ... ማለት ነው።
1.
በብያምያን ነገድ
የሚገኝ ከተማ፥ “ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር
ማራኪዎች በሦስት ክፍል ሆነው ወጡ አንዱም ክፍል በዖፍራ መንገድ ወደ ሦጋል ምድር
ሄደ።”
(1 ሳሙ 13:17)
2.
የጌዲዮን የትውልድ ቦታ፥ “የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው
ለኢዮአስ በነበረችው
በአድባሩ ዛፍ
በታች ተቀመጠ
ልጁም ጌዴዎን
ከምድያማውያን ለመሸሸግ
በወይን መጥመቂያው
ውስጥ ስንዴ
ይወቃ ነበር።” (መሣ 6:11)
3.
የመዖኖታይ ልጅ፥ “መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ። ሠራያም የጌሃራሽምን አባት ኢዮአብን ወለደ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ።” (1 ዜና 4:14)
፥ (መሣ 7:20-
25)
ኤፍራጥስ ~ Euphrates: የፍሬያት፣ ፍሬአማ... ማለት ነው፥ “አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ...” (ዘፍ 2:15)
ኤፍሬማዊ ~ Ephrathite:
ኤፍሬያታይት፣ ኤፍራታዊ፣ የኤፍራት አገር ሰዎች ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኤፍራታ፣ ኤፍሬም፣ ኤፍሮን]
ሕልቃና ኤፍሬማዊ ተብሎ ተጠራ፥ (1 ሳሙ 1፡1)
ኤፍሬም ~
Ephraim:
የፍሬያም፣ ፍሬያም፣ ፍሬአማ፣ ዘረ ብዙ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኤፍራታ፣ ኤፍሮን፣ ኦፊር፣ ፉራ፣ ፍሬ]
‘ፍሬያም’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የስሙ ምንጭ ‘ፍሬ’ የሚለው ቃል ነው።
በግብፅ የተወለደው፣ የዮሴፍ ልጅ፥ “የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ።” (ዘፍ 41፡52)
ኤፍሮን ~
Ephron:
አፈሮ፣ አፈር... ማለት ነው።
‘አፈር’ ከሚለው ቃል የመጣ
ስም ነው።
አብርሃም ሣራን ለመቅበር መሬት የገዛው የኬጢ ልጆች ወገን፣ የሰዓር ልጅ፥ (ዘፍ 23፡8-17)
ኤፍታህ ~ Ephphatha: ኢፍታህ፣ ይፍታህ፣ ፍትሕ አግኝ፣ ፈውስ ይስጥህ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ያፌት፣ ይፍታሕ፣ ይፍታሕኤል፣ ዮፍታሔ፣ ፈታያ]
‘ይፍታህ’ ከሚለው ቃል የተገኘ ነው። የቃሉ ምንጭ ደግሞ ‘ፈታ’ የሚለው ነው። ደንቆሮና ኰልታፋ የሆነውን ሰው ጌታ ሲፈውስ የተጠቀመው ቃል፥ “ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና። ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው። ወዲያውም ጆሮቹ
ተከፈቱ የመላሱም
እስራት ተፈታ
አጥርቶም ተናገረ።” (ማር
7፡34) ፣ ሐዋርያው ማርቆስ- (ማር 3:17፣ 5:41 ፣ 7:11፣ 14:36 ፣ 15:34)
እላሳር ~ Ellasar: ኤል
አሳር፣ መከረኛ... ማለት
ነው። የእስያ ግዛት
የሆነ አገር፥
“በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥
በእላሳር ንጉሥ
በአርዮክ፥ በኤላም
ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥
በአሕዛብ ንጉሥ
በቲድዓል ዘመን
እንዲህ ሆነ” (ዘፍ
14:1፣9)
እልዋሪቆን ~ Illyricum: ‘ደስታ’
ማለት ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ
ወንጌልን ከሰበከባቸው
አገሮች፥ የጣልያን
አዋሳኝ አገር
የነበረ፥ “... ስለዚህ
ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ፤ ሰብኬአለሁ።” (ሮሜ 15:19)
እልፍዮስ ~
Alphaeus:
እልፍ ዋስ፣ የሽዎች ዋስ፣ የብዙዎ ች አዳኝ ማለት ነው።
‘እልፍ’
እና ‘ዋስ’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ስም ነው።
ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ የያዕቆብ አባት፥ (ማቴ 10:30)
እሴይ ~
Jesse:
የሽ፣ የሺህ፣ የእልፍ፣ የብዙ፣ ባለጸጋ፣ ብርቱ... ማለት ነው። ከሩት ወገን የሆነ፣ የኢዮቤድ ልጅ፣ የዳዊት አባት፥ (ሩት 4፡17፣22)
እስማኤል ~ Ishmael: ሰማ ኤል፣ አምላክ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ጸሎትን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም-
ይስማኤል፣ ሳሙኤል]
‘ሰማ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። [ትርጉሙ “እግዚአብሔር ይሰማል” ማለት
ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የአብርሃም ልጅ፣ ከአጋር የተወለደው፥ “የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥
እግዚአብሔር መቸገርሽን
ሰምቶአልና።” (ዘፍ
16፡11) ፣ “...አብራምም አጋር
የወለደችለትን የልጁን
ስም እስማኤል ብሎ ጠራው፥”
(ዘፍ 16:3 ፣ 21:5)
2.
የኤሴል ልጅ፥
(1 ዜና 8:38)
3.
የናታንያ ልጅ፥ (ዘፍ 40:8 ፣ 15) ፣ (ኤር 40:8)
. ከይሁዳ ወገን የሆነ፥ የዝባድያ አባት፥ ይስማኤል ፥ (2 ዜና 19:11)
. ከይሁዳ ወገን የሆነ፣ ዮዳሄን ወደ ዙፋን ለማድረስ የተባበረ፣ የይሆሐናንን ልጅ፥
ይስማኤልን፥ (2 ዜና 23:1)
. በዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ ከተደረጉ፣ ካህኑ፥ ይስማኤል
፥ ይስማኤል፥
(ዕዝ 10:22)
እስራኤል ~ Israel: እ’ሥራ ኤል፣ ሥራ ኤል፣ የአምላክ ሥራ፣ ግብረ ኤል... ማለት ነው።
‘ሥራ’ እና ’ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጓሜውም ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፋልም ማለት ነው / መቅቃ] የይስሐቅ
ልጅ፣ የያዕቆብ
ሁለተኛ ስም፥
“አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ
ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ
አይባል ከእግዚአብሔር
ከሰውም ጋር
ታግለህ አሸንፈሃልና”
(ዘፍ 32፡28)
እሥርኤል ~
Ashriel:
እስረ ኤል፣ የጌታ እሥር፣ ግዝት፣ የአምላክ ምርኮኛ... ማለት ነው።
Ashriel- ‘እስር’
እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የምናሴ
ልጅ፥ እሥርኤል፥
(1 ዜና 7:14)
እስክንድሮስ፣ አሌክስንድሮስ ~ Alexander:
እስከ እንደራስ፥ እንደራሴ፣ ክንድ ራስ፣ መመኪያ ማለት ነው።
1.
የሊቀ ካህናቱ የሐና ወገን፥ በጳውሎስ ክስ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ፥ “በነገውም አለቆቻቸውና
ሽማግሌዎች ጻፎችም
ሊቀ ካህናቱ
ሐናም ቀያፋም
ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤” (ሐዋ 4:6)
2.
የጌታን መስቀል የተሸከመ፥ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ልጅ፥ “አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።” (ማር 15:21)
3.
አይሁድ ጳውሎስን
ተቃውመው ሲተባበሩ፥ አቤቱታቸውን እንዲያቀርብላቸው የመረጡት፥ “አይሁድም ሲያቀርቡት፥ እስክንድሮስን ከሕዝቡ መካከል ወደ ፊት ገፉት፤ እስክንድሮስም በእጁ ጠቅሶ ...” (ሐዋ 19:33)
4.
ከሐዋርያው ጳውሎስ
ትምህርት ከራቁ፥ “... ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፥ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።” (1 ጢሞ 1:19፤ 2 ጢሞ 4:14)
እስያ ~ Asia: ‘ገጽታ፣ የሽ ያሕ፣ የሕያው ሕዝብ’
ማለት ነው።
የሮም ግዛት
የሆነ፥ የኤፌሶን
አገር፥ “የጳርቴና የሜድ
የኢላሜጤም ሰዎች፥
በሁለት ወንዝም
መካከል በይሁዳም
በቀጰዶቅያም በጳንጦስም
በእስያም”
(ሐዋ 2:9፥ 6:9፥ 16:6፥ 19:10፣22፣26፣ 27፥2 0:4፣16፣18፥ 21:27፥ 27:2፤ ሮሜ16:5፤1 ቆሮ 16:19፤ 2 ቆሮ 1:8፤
2 ጢሞ 1:15፤ 1 ጴጥ 1:1፤ ራእይ 1:4፣11)
እስጢፋኖስ ~ Stephanas, Stephen: ፋና፣ ፋኖስ፣ ብርሃን... ማለት ነው። ‘ባለ ተክሊል፥ ማለት
ነው’። ተብሎም ይተረጎማል። ከሰባቱ
ዲያቆናት አንዱ፥
የመጀመሪያ ሰማዕት
የሆነ፥ “ይህም ቃል
ሕዝብን ሁሉ
ደስ አሰኛቸው፤
እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም
ጢሞናንም ጳርሜናንም
...” (ሐዋ 6:5)
እስጳንያ ~
Spain:
‘ውድ፣ ብርቅዬ’ ማለት ነው። ጳውሎስ በሐዋርያዊው ጉዞ ሊጎበኛቸው ካሰበ አገሮች አንዱ፥ “ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ ...”
(ሮሜ 15:24፣28)
እንበረም ~ Amram: ‘ታላቅ ሕዝብ’ ማለት ነው።
1.
የሌዊ ወገን፥
የሙሴ አባት፥
“የቀዓትም ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥
ዑዝኤል ናቸው
...” (ዘጸ 6:18፣20)
2.
“የዓና ልጅ ዲሶን፦ የዲሶንም ልጆች ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን”
(1 ዜና 1:41)
3.
በዕዝራ ዘመን
ከግዞት ከተመለሱ፥
እንግዳ ሴቶችን
ካገቡ፥ የባኒ ልጅ፥
“ከባኒ ልጆችም፤
መዕዳይ፥ ዓምራም፥” (ዕዝ 10:34)
እንድርያስ ~
Andrew:
እንድርያስ፣ እንደ ራሴ፣ እንደ ራስ ፥ የራስ የሆነ፣ የሌላ ያልሆነ... ማለት ነው።
‘እንደ’ እና ‘ራስ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ከጌታ ሐዋርያት
አንዱ፥ በመጀመሪያ
ዓሣ በማጥመድ
ይተዳደር ነበር፥
“…ሁለት ወንድማማቾች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ...” (ዮሐ 1:44 ፣ 45) ፣ (ማቴ 4:18 ፣ 10:2)
እንግዳ ~
Barbarian:
በር በሪያ፣ የበሪያ ልጅ፣ አገልጋይ፣ ታዛዥ፣ ነጻ ያልወጣ... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች-
ላልተማሩ፣ አረማውያን]
Barbarian- ‘በር’ እና ‘በረ ያሕ’
ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
. ልዩ
ቋንቋን እንግዳ
ተብሏል፥ “እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው
እንግዳ እሆናለሁ፥
የሚናገረውም ለእኔ
እንግዳ ይሆናል።” (1 ቆሮ
14:11)
. ያልሠለጠነ
ሕዝብ፥ ላልተማሩ- (ሮሜ 1:14)
. ባዕዳን፥ አረማውያን- (ሥራ 28:1 ፣ 2 ፣ 4) ፣ አረማውያን- (ሥራ 28:1፣ 2፣ 4)
እግዚአብሔር ~ Jah, Jehovah, God: ያሕ፣ ይህዌ፣ ህያዊ፣ ሕያው አምላክ፣ የማይሞት፣ የማያልፍ... ማለት ነው።
Jehovah -‘ያሕዌ’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
እግዚአብሔር / God:
. ቀዳማዊነትን እና
ሕያውነትን ይገልጻል፥
“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና
ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1:1)
. በሁሉ ቦታ
መገኘቱን ይገልጻል፥
“ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም
ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ …”
Jah- (መዝ 68:4)
እግዚአብሔር / Jehovah:
ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም የተገለጠበት፥
ስሙን ያሳወቀበት፥
“እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው
አለውም፦ እኔ
እግዚአብሔር ነኝ፤
ለአብርሃምም ለይስሐቅም
ለያዕቆብም ሁሉን
እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።” (ዘጸ 6፡
2፣3)
እግዚአብሔር ሰላም ~
Jehovah-shalom: ሕያው ሰላም፣ ዘላለማዊ ደኅንነት፣ የአምላክ ሰላም... ማለት ነው።
Jehovah- ‘ያሕዌ’ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። Shalom- ‘ሻሎም’ ደግም ሰላም ከሚለው ነው።
ጌዴዎን ለእግዚአብሔር የሠራው መሠዊያ ስም፥ “ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም። እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለአቢዔዝራውያን በምትሆነው በዖፍራ አለ።” (መሣ 6:24)
እግዚአብሔር በዚያአለ ~ Jehovah-shammah: ሕያው ስም፣ የእግዚአብሔር ስም፣ የአምላክ ስም... ማለት ነው።
Jehovah-shammah- ‘ያሕዌ’ እና ‘ስም’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
የሌዋውያን ርስት
የከተማይቱ ይዞታ፥
“ዙሪያዋም አሥራ ስምንት
ሺህ ክንድ
ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም። እግዚአብሔር በዚያ አለ ተብሎ ይጠራል።” (ሕዝ 48፡35)
እግዚአብሔር ጽድቃችን ~ Jehovah-tsidkenu : ያሕዌ ጻድቃኑ፣ ያሕዊ ጻድቅ፣ ሕያው ጻድቅ፣ እውነተኛ አምላክ፣ ዘለአለማዊ ገዥ... ማለት ነው። Jehovah-tsidkenu- ‘ያሕዌ’
እና ‘ጽድቅነ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው።
የሕያው አምላክነት
ባሕርይን ለመግለጽ
የተሰጠ ስም፥
“በዘመኑም ይሁዳ ይድናል
እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ
ነው።”
(ኢያ 23፡6)
ኦሃድ ~
Ohad:
ኦሃድ፣ ውሑድ፣ የተዋሐደ፣ አንድ የሆነ... ማለት ነው።
‘አሐደ’
ከሚለው ግስ
የተገኘ ስም ነው። የስሞዖን ልጅ፥
(ዘፍ 46:10)
ኦሄል ~ Ohel: ‘ድንኳን’
ማለት ነው።
የዘሩባቤል አራተኛ
ልጅ፥ “ሐሹባ፥ ኦሄል፥
በራክያ፥ ሐሳድያ፥
ዮሻብሒሴድ አምስት
ናቸው።”
(1 ዜና 3:20)
ኦሖሊባ ~ Aholibah:
‘ድንኳኔ፣ ማደሪያዬ’
ማለት ነው።
በሕዝቅኤል ትንቢት
ከሁለት ለተከፈለ
ለእስራኤል መንግሥት፥
የአንደኛው መጠሪያ፥
“ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ።
ስማቸውም ኦሖላ
ሰማርያ ናት
ኦሖሊባ ደግሞ
ኢየሩሳሌም ናት።” (ሕዝ
23:4፤11፣22፣36፣44)
ኦሖላ ~ Aholah: ‘ባለ ድንኳን፣ ሴትአዳሪ)’ ማለት
ነው። በሕዝቅኤል
ትንቢት ከሁለት ለተከፈለ ለእስራኤል መንግሥት፥ የአንደኛው መጠሪያ፥ “ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ...” (1 ዜና 23:4፣5፣36፣44)
ኦማር ~
Omar, Omri: ኦማር፣ ማሪ፣ መሐሪ፣ ይቅር ባይ፣ አምላካዊ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አምሪ፣ ዖምሪ]
‘ማረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኦማር / Omar:
የኤልፋዝ ልጅ፥ (ዘፍ 36:11-15)
ኦማር / Omri: “የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥
ጎቶም፥ ቄኔዝ” (1 ነገ 16:15-27)
ኦሬክ ~ Erech: ‘እሩቅ’ ማለት ነው።
የናምሩድ መንግሥት
ከተማ የነበረ፥
“የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።” (ዘፍ
10:10)
ኦርና ~
Araunah:
‘ታቦት’
ማለት ነው። ጋድ በነገረው መሠረት፣ መሬት ለእግዚአብሔር
መሠዊያ ለመሥራት የገዛው ሰው፥ ኢያቡሳዊው፥
“በዚያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ። ውጣ፥ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ አለው” (2 ሳሙ 24:18፣-24፤1 ዜና 21:25)
ኦርና ~ Ornan:
‘ቀልጣፋ’ ማለት ነው። “እግዚአብሔርም ያጠፋት
ዘንድ ወደ
ኢየሩሳሌም መልአክን
ሰደደ ...በኢያቡሳዊው
በኦርና አውድማ
አጠገብ ቆሞ
ነበር”
(1 ዜና 21:15)
ኦርያ ~ Urijah: ኡሪ
ያሕ፣ ሕያው
ብርሃን፣ የአምላክ
ብርሃን... ማለት ነው።
(ኡሪ ማለት ተጓዥ፣ መንገደኛ ማለት ሁኖ ፥ ኦሪያ ፥ ሐዋሪያ ፥ የአምላክ መልእክተኛ ተብሎም
ይተረጎማል።)
[ተዛማጅ ስም-
ኦርዮ]
‘ኡር’ እና ‘ያሕ’ (ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በአካዝ ዘመን የነበረ ካህን፥ (2 ነገ 16:10-16)
ኦርዮ ~
Uriah, Urias, Urijah: ኡሪ ያሕ፣ ሕያው ብርሃን፣ የአምላክ ብርሃን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኦርያ]
‘ኡር’ እና ‘ያሕ’(
ያሕዌ) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። (ኡሪ ማለት ተጓዥ፣
መንገደኛ ማለት
ሁኖ ፥
ኦሪያ ፥
ሐዋሪያ ፥
የአምላክ መልእከተኛ ተብሎም
ይተረጎማል። )
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ኦርዮ / Uriah:
1.
የንጉሥ ዳዊት ወታደር ሆኖ፥ የቤርሳቤህ ባል፥ (2 ሳሙ 11:3)
2.
በአካዝ ዘመን የነበረ ካህን፥ (ኢሳ 8:2) ፣ (2 ነገ 16:10-16)
3.
በነህምያ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ ካህናት፥ (ዕዝ 8:33፣ ነህ 3:4፣ 21)
ኦርዮ / Urias: የንጉሥ ዳዊት ወታደር ሆኖ፥ የቤርሳቤህ ባል፥ “ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤” (ማቴ 1:6)
ኦርዮ / Urijah:
1.
በአካዝ ዘመን
የነበረ ካህን፥
ኦርያ፥ (2 ነገ 16:10-16)
2.
በነህምያ ዘመን ከግዞት ከተመለሱ ካህናት፥ (ነህ 8:4)
3.
የሸማያ ልጅ፥
(ኤር 26:20-23)
ኦባብ ~ Hobab: ‘ሐባብ፣ አበባ፣
ቆንጆ፣ ተወዳጅ’ ማለት
ነው። የሙሴ
አማች፥ “ሙሴም የሚስቱን
አባት የምድያማዊውን
የራጉኤልን ልጅ
ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን እግዚአብሔር ስለ እስራኤል
መልካምን ነገር
ተናግሮአልና አንተ
ከእኛ ጋር
ና፥ መልካምን
እናደርግልሃለን አለው።” (ዘኊ
10:29፤ መሣ 4:11)
ኦቦር ~ Habor: አብር፣ ኅብር፣ አባሪ፣ ረዳት፣ ተባባሪ፣ ማኅበርተኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ዔቦር፣ ሔቤር፣ አቤር፣ ዔብሪ፣ ዔብሮን፣ ዔቤር፣ ዔብሮና፣ ዕብራዊ፣ ኬብሮን]
የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኵሌታ የፈለሱበት፥ (1 ዜና 5፡26)
ኦቦት ~ Oboth: ኦቦት፣
አብ ቤት፣
አባት፣ ወላጅ፣
አሳዳጊ... ማለት ነው።
የእስራኤል ሕዝብ
ከግብፅ ሲወጣ
ያለፈበት፥ “የእስራኤልም ልጆች
ተጓዙ፥ በኦቦትም ሰፈሩ።” (ዘኁ 33:43)
ኦኖ ~ Ono: ‘ጽናት፣ ብርታት’
ማለት ነው። ከብንያም ከተሞች አንዱ፥ “የኤልፍዓልም ... ኦኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ” (1 ዜና 8:12)
ኦዚ ~ Uzzi: ‘ያዚ፣ ብርቱ፣ ጠንካራ’ ማለት ነው።
1.
የቡቂን ልጅ፥ የዘራእያ አባት፥ “አቢሱም ቡቂን ወለደ ቡቂም ኦዚን ወለደ”
(1 ዜና 6:5፣61፤ ዕዝ 7:4)
2.
የቶላ ልጅ፥ “የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሽሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ ...” (1 ዜና 7:2፣3)
3.
የቤላ ልጅ፥ “የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሪሙት፥ ዒሪ፥ አምስት
ነበሩ የአባቶቻቸው
ቤቶች አለቆች፥
ጽኑዓን ኃያላን
ሰዎች ነበሩ። በትውልድ
የተቈጠሩ ሀያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።” (1 ዜና 7:7)
4.
የሚክሪ ልጅ፥ “የይሮሐም ልጅ ብኔያ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ የዪብንያ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም” (1 ዜና 9:8)
5.
ሌዋዊው፥ የባኒ ልጅ፥ “በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ
ነበረ።”
(ነህ 11:22)
6.
ካህን፥ “ከዮያሪብ መትናይ፥
ከዮዳኤ ኦዚ፥” (ነህ 12:19)
7.
የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን ከዕዝራ ጋር ከተባበሩ፥ “ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ ...”
(ነህ 12:42)
ኦፊር ~ Ophir: ኦፍር፣ አፈራ፣ ያፈራ፣ ፍሬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ኤፍራታ፣ ኤፍሬም፣ ኤፍሮን፣ ፉራ፣ ፍሬ]
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውን አንድ ቦታ አሉ።
1.
የዮቅጣን ልጅ፥ (ዘፍ 10:29 ፣ 1
ዜና 1:23)
2.
በወርቅ የታወቀ፥ የቦታ ስም፥ (1 ዜና 29:4 ፣ ዮብ 28:16 ፣ መዝ
45:9
፣ ኢሳ 13:12)
ኦፌር ~
Hepher:
‘ጉድጓድ ቆፋሪ፣ አፈር ገፊ፣ አፈር’
ማለት ነው።
1.
በኢያሱ የተወሰደች፥
የከነናውያን የመናገሻ
ከተማ፥ “የታጱዋ ንጉሥ፥ የኦፌር ንጉሥ፥ የአፌቅ ንጉሥ፥” (ኢያ 12:17)
2.
የገለዓድ ልጅ፥ “ከሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን።” (ዘኊ 26:32፥ 27:1)
3.
ለአሽሑር ልጅ፥ “ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ
የነዕራ ልጆች
ናቸው።”
(1 ዜና 4:6)
4.
በዳዊት ጭፍሮች ዘንድ ከነበሩት ኃያላን አንዱ፥ “የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ ሚኬራታዊው
ኦፌር፥”
(1 ዜና 11:36)
No comments:
Post a Comment