ደኅንነት ~ Shalem: ሸላም፣ ሰላም፣ በደና፣ በአማን... ማለት ነው።

Shalem- ሰላም ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ያዕቆብ ከስደት ሲመለስ ያለፈበት፣ የቦታ ስም፥ ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ ደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ።” (ዘፍ 33:18-20)

ደሊላ ~ Delilah: ደላላ፣ መደለል፣ ማባበል፣ ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር... ማለት ነው።

ደለለከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ፍልስጤኤማዊት ሴት፥ ሶምሶን የወደዳት፥ (መሣ 16:4)

ደላያ ~ Dalaiah: ያሕ፣ ድለ ሕያው፥ በአምላክ ያሸነፈ.. ማለት ነው። የኤልዮዔናይም ልጅ፥ የኤልዮዔናይም ልጆች ሆዳይዋ፥ ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያ ዓናኒ ሰባት ነበሩ” (1 ዜና 3:24)

ደልፎን ~ Dalphon: ፈጣን ማለት ነው። ከአሥሩ የሐማ ልጆች ሁለተኛው፥ ፈርሰኔስ፥ ደልፎን ፋስጋ፥ ፋረዳታ፥ (አስ 9:7)

ደማስቆ ~ Damascus: ደም ከረጢት ማለት ነው። ከቀደሙት የምሥራቅ አገር ከተሞች፥ የሶሪያ ዋና ከተማ፥ የሶርያ ራስ ደማስቆ ነው፥ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው ... ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም” (ኢሳ 7:8 17:3) ደማሪስ ~ Damaris: ልጃገረድማለት ነው። በጳውሎስ ስብከት ክርስትናን ከተቀበሉ የአቴን ሰዎች፥ አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ። (ሐዋ 17:34)

ደራል ~ Darda: ዕንቁማለት ነው። ከሰለሞን ጥበብ ጋር ከተነጻጸሩ፥ በጥበበኛነታቸው ከታወቁት አራት ሰዎች፥ ከሰውም ሁሉ ይልቅ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበረ... (1 ነገ 4:31)

ደርቆን ~ Darkon: ትውልድ ማለት ነው። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ የንጉሥ ሰሎሞን አገልጋይ ከነበሩ፥ አባት፥ የየዕላ ልጆች፥ ደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥” (ዕዝ 2:56 ነህ7:58)

ደርቤ ~ Derbe: ደራቢ፣ ደርብ፣ ድርብ፣ የተደረበ፣ የተደገመ... ማለት ነው።

ደረበከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ የሸሹበት አገር፥ (ሥራ 16:1)

ደቅላ ~ Diklah: ዲቃላ፣ ደቃቃ፣ ልጅ፣ ትንሽማለት ነው። የዮቅጣን ልጅ፥ ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥” (ዘፍ 10:27 1 ዜና 1:21)

ደባሼት ~ Dabbasheth: ደብረ ሰጥ፥ ዳገታማ ቦታማለት ነው። የዛብሎን አዋሳኝ ከተማ፥ ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼት ደረሰ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ (ኢያ 19:11)

ደብራይ ~ Dibri: ደብሪ፣ ደብሬ፣ ደብር፣ ተራራ ቦታ፣ ርስት አምባ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ዲቦራ፣ ዳቤር፣ ዳብራት]

ደብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የሰሎሚት አባት፥ (ዘሌ 2411)

ደና ~ Dannah: ዳና፣ ዳኘ፣ ዳኝ፣ ዳኝነት፣ ዳኛ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ዲና፣ ዳን]

የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት፣ የከተማ ስም፥ (ኢያ 1549)

ዱራ ~ Dura: ክብ፥ ዙሪያ ጥምጥም ማለት ነው። ናቡከደነፆር የጣዖቱን ምስል ያስቀመጠበት መስክ፥ ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ በባቢሎንም አውራጃ ዱራ ሜዳ አቆመው።” (ዳን 3:1)

ዱዲ ~ Dodai, Dodo: ውዴ፥ ወዳጄ... ማለት ነው። ከዳዊት አለቆች አንዱ፥ በሁለተኛውም ወር ክፍል ላይ አሆሃዊው ዱዲ ነበረ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።(1 ዜና 27:4)

       ዱዲ ~ Dodo: ውድ፥ ወዳጅ... ማለት ነው።

1. የይሳኮር ወገን፥ ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ ዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ ... ነበር።” (መሣ 10:1)

2. ከሦስቱ የዳዊት ኃያላን አንዱ፥ የኤልያናን (Eleazar) አባት፥ ከእርሱም በኋላ የአሆሃዊው ዱዲ ልጅ ኤልያናን ነበረ ለሰልፍ የተሰበሰቡትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ከሦስቱ ኃያላን አንዱ እርሱ ነበረ የእስራኤልም ሰዎች ተመለሱ። (2 ሳሙ 23:9 1 ዜና 11:12)

3.ከሠላሳዎቹ የዳዊት ኃያላን አንዱ፥ ኤልያናን (Elhanan) አባት፥ የኢዮአብም ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፥ የቤተ ልሔም ሰው ዱዲ ልጅ ኤልያናን” (2 ሳሙ 23:24)

ዲልዓን ~ Dilean: ‘ጠባቂ፣ ጋራጅማለት ነው። በታችኛው ደልዳላ የይሁዳ መሬት ከሚገኙ ከተሞ አንዱ፥ ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ ዲልዓን” (ኢያ 15:38)

ዲሞና ~ Dimonah: በይሁዳ የሚገኝ ከተማ፥ ዲሞና ዓድዓዳ፥ ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን፥” (ኢያ 15:23)

ዲሞን ~ Dimon: ደመኛ፣ ዲመን፣ ደምነ፣ ደማዊ፣ ደም፣ ቀይ... ማለት ነው።

ደምከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

ስለ ሞዓብ በተነገረ ሸክም፣ የነቢዩ የኢሳይያስ ትንቢት፥ ዲሞን ውኃ ደም ተሞልታለች ዲሞን ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ።” (ኢሳ 15:9)

ዲሳን ~ Dishan: አጋዘን ማለት ነው። የሴይር የመጨረሻ ልጅ፥ በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው ሎጣን፥ ሦባል፥ ፅብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን” (ዘፍ 36:202830 1 ዜና 1:3842)

ዲሶን ~ Dishon: አጋዘንማለት ነው። የሴይር አምስተኛ ልጅ፥ በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው ሎጣን፥ ሦባል፥ ፅብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን ኤጽር፥ ዲሳን” (ዘፍ 36:202830 1 ዜና 1:3842)

ዲብያ ~ Zibia: ዘበ ያሕ፣ ዘብ፣ የተጠበቀ፣ ታላቅ፣ የተከበረ... ማለት ነው።

Zibia- ዘብ እና ያሕ (ያሕዌ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የሸሐራይም ልጅ፣ ከአባቶች ቤቶች አለቆች የነበረ፥ ዲብያ (1 ዜና 8:9)

ዲቦራ ~ Deborah: ደቦራህ፣ ደብርህ፣ ደብር፣ ተራራ፣ ርስት አምባ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ደብራይ፣ ዳቤር፣ ዳብራት]

[ትርጉሙ ንብማለት ነው / መቅቃ]

በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች አሉ።

1. የርብቃ ሞግዚት፥ (ዘፍ 358)

2. በእስራኤል ላይ ዳኛ የነበረች፣ ነቢይቱ ዲቦራ፥ (መሣ 4:4)

ዲና ~ Dinah: ዳኛ፣ ዳኘ፣ ፈረደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ደና፣ ዳን]

[ትርጉሙ ፈረደማለት ነው / መቅቃ]

ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ፥ (ዘፍ 3021)

ዲንሃባ ~ Dinhabah: ደነ አባ፣ አባት ደን፣ ትልቅ ዱር፣ ጫካ... ማለት ነው።

ደን እና አባ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሠ፥ ባላቅ የነገሠባት ከተማ፥ በኤዶምም የቢዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት።” (ዘፍ 3632) (1 ዜና 1:43)

ዲያቆናት ~ Deacon: ዲያቆን፣ ድያቆን፣ ድቁና፣ ደቋና፣ ጉዳይ፣ ክንውን፣ አግልግሎት... ማለት ነው።

ደቆነከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

[አገልጋይ ማለት ነው  / መቅቃ]

በጳውሎስ መልክት የተጠቀሰ የቤተ ክርስቲያን ሹመት፥ (ፊሊ 1:1)

ዲዮናስዮስ ~ Dionysius: ፈውስ ያገኘማለት ነው። በጳውሎስ ስብከት ክርስትና ከተቀበሉ የግሪክ ሰዎች፥ አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።” (ሐዋ 17:34)

ዲዮጥራጢስ ~ Diotrephes: በዮሐንስ መልክት የተጠቀሰ ክርስቲያን፥ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።” (3 ዮሐ 1:9)

ዲዲሞስ ~ Didymus: ጥንድ፣ እጥፍማለት ነው። የሐዋርያው ቶማስ የክብር ስም፥ ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ (ዮሐ 11:16 20:24 21:2)

ዳልማኑታ ~ Dalmanutha: ገንዳማለት ነው። በገሊላ በስተምዕራብ የሚገኝ ከተማ፥ አሰናበታቸውም። ወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ። (ማር 8:10)

ዳርዮስ ~ Darius: ደራሽ፣ ንቁማለት ነው።

1. ዳርዮስ በመንግሥቱ ሁሉ ዘንድ እንዲሆኑ መቶ ሀያ መሳፍንት በመንግሥቱ ላይ ይሾም ዘንድ ወደደ። (ዳን 6:1 11:1)

2. በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳርዮስ መዛግብት ባሉበት በባቢሎን ቤተ መጻሕፍት እንዲመረመር አዘዘ።” (ዕዝ 5:1)

3. ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ ካህናቱም በፋርሳዊው ዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።” (ነህ 12:22)

ዳቤር ~ Debir: ደብር፣ ተራራ፣ ቦታ፣ ርስት፣ ጉልት፣ አምባ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ደብራይ፣ ዲቦራ፣ ዳብራት]

ደብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

. የንጉሥ አዶላም አገር፥ (ኢያ 10:3)

. ሶኮ፥ ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና (ኢያ 1549)

ዳብራት ~ Dabareh, Daberath: ደብራ፣ ደብራት፣ ደብሮች፣ ቦታዎች፣ ርስታት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ደብራይ፣ ዲቦራ፣ ዳቤር] ደብርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

       ዳብራት / Dabareh: ለሌዋውያን ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ርስት እንዲሆን የተሰጠ፥ (ኢያ 2128)

      ዳብራት / Daberath: (ኢያ 1912)

ዳታን ~ Dathan: ሕጋዊ ባለመብትማለት ነው። ከሮቦል ነገድ፥ ፈራጅ የነበረ፥ በቆሬ ሙሴን ከተቃዎሙት፥ የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከሮቤልም ልጆች የኤልያብ ልጆች ዳታን አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን በሙሴ ላይ ተነሡ።” (ዘኊ16:1 26:9 11:6 መዝ 106:17)

ዳን ~ Dan: ዳኝ፣ ዳኛ፣ ዳኘ፣ ፈረደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ደና፣ ዲና]

ዳኝ  ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

[ትርጉሙ ዳኛማለት ነው / መቅቃ]

በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።

1. የቦታ ስም፥ ሌሳ ዳን ተባለች፥ አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ ... ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።” (ዘፍ 1414) ከተማይቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው ዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት የከተማይቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ። (መሣ 18:29)

2. የራሔል ባሪያ ባላ ለያቆብ የወለደችለት፥ ራሔልም። እግዚአብሔር ፈረደልኝ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው:” (ዘፍ 306) ዳን በወገኑ ይፈርዳል ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ።” (ዘፍ 49:16)

ዳንኤል ~ Daniel: ዳኝ ኤል፣ አምላክ ዳኘ፣ እግዚአብሔር ፈረደ... ማለት ነው።

ዳኝ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው / መቅቃ] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ የተወለደው፣ የዳዊት ልጅ፥ (1 ዜና 31)

2. የኢታምር ልጅ (ዕዝ 8:2)

3. ነቢዩ ዳንኤል፥ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” (ሕዝ 14:14) (ዳን 1:6) (ዳን 1:3 6)

4. ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳን ደብዳቤ ካተሙት፥ (ነህ 10:6)

ዳኤል ~ Lael: ለኤል፣ ለአምላክ፣ ለጌታ፣ ለእግዚአብሔር... ማለት ነው።

Lael- ኤል ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

የኤሊሳፍ አባት፥ (ዘኁ 3:24)

ዳዊት ~ David: ደውድ፣ ውድ፣ ዘውድ፣ የተወደደ ማለት ነው። የእሴይ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ፥ (ሩት 422) (2 ሳሙ 1725)

ዳጎን ~ Dagon: ማለት ነው። የፍልስጤማውያን አምላክ፥ ጣዖት፥ በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር ዳጎንንም አንሥተው ወደ ... (1 ሳሙ 5:34)

ዴሬት ~ Zereth: ዘራት፣ ዘር፣ ወገናት፣ ዘመዶች... ማለት ነው።

Zereth- ‘ዘርከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የአሽሑር ልጅ፣ ከሔላ የተወለደ፥ (1 ዜና 4:7)

ዴቀር ~ Dekar: ጦረኛ፣ ቀስተኛ...’ ማለት ነው። የዴቀር ልጅ፣ የንጉሥ ሰሎሞን አማካሪና ሹም ነበር፥ በማቃጽና በሸዓልቢም በቤትሳሚስና በኤሎንቤትሐናን ዴቀር ልጅ (1 ነገ 4:9)

ዴቤላይም ~ Diblaim: ደባል፣ ድርብ፣ ድርብርብ...ማለት ነው። የሆሴዕ ሚስት፣ የጎሞር እናት፥ እርሱም ሄዶ ዴቤላይም ልጅ ጎሜርን አገባ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት።” (ሆሴ 1:3)

ዴብላታ ~ Diblath: ደባላማለት ነው። የቦታ ስም፥ እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ እኔም እግዚአብሔር ...” (ሕዝ 6:14)

ዴቦን ~ Dibon: ሊቅነትማለት ነው።

1. የሞዓባውያን ከተማ፥ ገተርናቸው ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው። (ዘኊ 21:30)

2. ከግዞ መልስ፥ የይሁዳ ነገድ መቀመጫ፥ (ነህ 11:25)

ድላያ ~ Delaiah: ያሕ፣ ድለ ሕያው፥ በአምላክ ያሸነፈ... ማለት ነው።

1. በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ ካህን፥ የሀያ ሶሥተኛው የመቅደሱና የእግዚአብሔር ቤት አለቃ፥ ሀያ ተኛው ድላያ ሀያ አራተኛው ለመዓዝያ።” (1 ዜና 24:18)

2. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥ ዳላያ፥ ዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። (ዕዝ 2:60 ነህ 7:62)

3. የመሔጣብኤል ልጅ፥ እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ቤት ገባሁ እርሱም ተዘግቶ ነበርና ... (ነህ 6:10)

4. ነገር ግን ኤልናታንና ድላያ ገማርያም ክርታሱን እንዳያቃጥል ንጉሡን ለመኑት፥ እርሱ ግን አልሰማቸውም።” (ኤር 36:1225)

ድልማጥያ ~ Dalmatia: ድንግዝግዝማለት ነው። ጳውሎስ፥ ቲቶን የላከበት፥ ተራራማ ቦታ፥ ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል” (2 ጢሞ 4:10)

ድሩሲላ ~ Drusilla: በጤዛ የራሰ፥ የረሰረሰ ርጥብማለት ነው። የሄሮድ ሴት ልጅ፥ ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ አይሁዳዊት ከነበረች ድሩሲላ ከሚሉአት ከሚስቱ ጋር መጥቶ ጳውሎስን አስመጣ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ማመን የሚናገረውን ሰማው።” (ሐዋ 24:24)

ድብ ~ Arcturus: ክምችት፣ ጥርቅም፣ ስብስብማለትነው። የኮከብ ስም፥ ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል። (ኢዮ 9:9 38:32)

ድያ ~ Jupiter: ረጅ አባትማለት ነው። የግሪክ የጣዖት ስም፥ በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት።” (ሐዋ 14:12 13)

ድዳናውያ ~ Dedanim: የድዳን ወገኖች፥ ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም። ድዳናውያ ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ። (ኢሳ 21:13)

ድዳን ~ Dedan: ደልዳላ፣ ዝቅተኛ ቦታ... ማለት ነው።

1. የኩሽ ልጅ፥ የራዕማ ልጅ፥ ኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው።” (ዘፍ 10:7 1 ዜና 1:9)

2. (ዘፍ 25:3 1 ዜና 1:32)

ዶሎሕያ ~ Chileab: ቻለ አብ፣ ቃለ አብ፣ ቃለ ሕያው፣ ቃለ እግዚአብሔር... ማለት ነው።

የዳዊት ልጅ፣ የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው፥ (2 ሳሙ 33)

. ዳንኤል- (1 ዜና 3:1)

ዶር ~ Dor: ትውልደ ትውልድማለት ነው። የከነናውያን ጥንታዊ፥ መናገሻ ከተማ፥ በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶር የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ... ነበሩ።” (ኢያ 17:11 1 ነገ 4:11)

ዶርቃ ~ Dorcas: ‘ጮርቃ፣ ለጋ፣ እንቡጥ፣ ቀንበጥማለት ነው። በኢዮጴ፥ ጴጥሮስ ከሞት ያስነሣት ክርስቲያን፥ በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች።” (ሐዋ 9:36-41)

ዶታይ ~ Dothan: ሁለት ጉድጓዶች ማለት ነው። ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ከሄደባቸው ቦታዎች፥ ሰውዮውም። ከዚህ ተነሥተዋል ወደ ዶታይ እንሂድ ሲሉም ሰምቼአቸዋለሁ አለው። ዮሴፍም ወንድሞቹን ተከታትሎ ሄደ፥ በዶታይንም አገኛቸው።” (ዘፍ 37:17)

ዶይቅ ~ Doeg: ደግ፣ ትሑት፣ ለጋስ፣ ርኁሩኅ፣ አምላክን የሚፈራ... ማለት ነው።

Doeg- ደግከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። የሳኦል የእረኞቹ አለቃ የነበረ፥ (1 ሳሙ 217)

ዶዳያ ~ Dodavah: ውደ ያሕ፣ የሕያው ወዳጅ፣ ወደ አምላክ የቀረበ... ማለት ነው። መሪሳ በተባለው የይሁዳ ግዛት የነበረ፥ ኢዮሣፍጥን ከአካዝያስ ጋር በመተባበር የተቃወመ፥ የአልዓዛር አባት፥ የመሪሳም ሰው ዶዳያ ልጅ አልዓዛር። ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራህን አፍርሶታል ብሎ በኢዮሣፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ ...” (2 ዜና 20:37)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ