ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ገለዓድ ~ Galeed, Gilead:
‘የምስክር ክምር’
ማለት ነው።
ላባ ይጋር
ሠሀዱታ ብሎ
የጠራት፥ ያዕቆብና
አማቱ ላባ
ቃል ኪዳን
የተገባቡበት ቦታ፥
(ዘፍ 31:47፣48) “ላባም ይጋር ሠሀዱታ ብሎ ጠራት ያዕቆብም ገለዓድ አላት”
ገለዓድ /
Gilead:
1. ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኝ የተራራ ሰንሰለት፥ “እርሱም ያለውን ሁሉ
ይዞ ኮበለለ
ተነሥቶም ወንዙን
ተሻገረ፥ ፊቱንም
ወደ ገለዓድ ተራራ አቀና።”
(ዘፍ 31:21፥ 3:12-17)
2. የማኪር ልጅ፥ “የምናሴ ልጆች ከማኪር የማኪራውያን ወገን ማኪርም ገለዓድን ወለደ
ከገለዓድ የገልዓዳውያን ወገን።” (ዘኊ
26:29፣30)
3. የዮፍታሔን አባት፥ “ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ጽኑዕ ኃያል ሰው የጋለሞታ ሴትም ልጅ ነበረ። ገለዓድም ዮፍታሔን ወለደ” (መሣ 11:1፣2)
ገሊላ ~
Galilee:
የተከለለ፣ የተገለለ፣ የተለየ... ማለት ነው። በጌታ ዘመን፣ ከሦስቱ የፍልስጥኤም ክፍሎች
[ይሁዳ፣ ሰማርያ እና ገሊላ] አንዱ፥ “በንፍታሌም ባለው
በተራራማው አገር
በገሊላ ቃዴስን፥
በኤፍሬምም ባለው
በተራራማው አገር
ሴኬምን፥ በይሁዳም
ባለው በተራራማው
አገር ኬብሮን
የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።” (ኢያ 20:7፤ 1 ነገ 9:11)
ገላትያ ~
Galatia:
‘ነጭ፣ ወተት የመሰለ’ ማለት ነው። የቢታንያ አዋሳኝ የሆን
የሮማ ግዛት
የነበረ፥ “በእስያም ቃሉን
እንዳይናገሩ መንፈስ
ቅዱስ ስለ
ከለከላቸው በፍርግያና
በገላትያ አገር
አለፉ፤”
(ሐዋ 16:6)
ገማሊ ~
Gamalli:
ገማሊ፣ ግመሊ፣ ግመለኛ፣ ግመሎች ያሉት... ማለት ነው።
Gamalli-
‘ግመል’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ከላካቸው፥ ከዳን ነገድ፥ የዓሚኤል
አባት፥ (ዘኁ 13:12)
ገማልኤል ~
Gamaliel:
ገማለ ኤል፣ ግመለ ኤል፣ የአምላክ ግመል፣ የአምላክ አገልጋይ... ማለት ነው።
‘ግመለ’
እና ‘ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። ከምናሴ ነገድ የሆነ የፍዳሱ ልጅ፥ ገማልኤል፥ (ዘኁ 10:23)
ገማርያ ~ Gemariah: ‘ገማረ ያሕ፣
ገረመ ያሕ፣ የሕያው ድንቅ ሥራ፣
አስገራሚ ክንውን’ ማለት
ነው። የኬልቅያስ
ልጅ፥ አይሁድ
በስደት በነበሩበት
ዘመን፥ የኤርሚያስን
ደብዳቤ አድራሽ
ነበር፥ “ኤርምያስ የይሁዳ
ንጉሥ ሴዴቅያስ
ወደ ባቢሎን ንጉሥ
ወደ ናቡከደነፆር
ወደ ባቢሎን
በላካቸው በሳፋን
ልጅ በኤልዓሣና
በኬልቅያስ ልጅ
በገማርያ እጅ
ደብዳቤውን እንዲህ
ሲል ላከው።” (ኤር
29:3)
ገሞራ ~ Gomorrah: ‘መስመጥ፣ መጥለቅ’ ማለት
ነው። ከአምስቱ
የሲዶን ከተሞች አንዱ፥ “የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ... ነው።” (ዘፍ 10:19፥
13:10፥ 19:24፣28)
ገሪዛን ~ Gerizim: ‘ገራዥ፣ ቆራጭ’ ማለት
ነው። “አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።” (ዘዳ 11:29)
ገበታ ~ Gabbatha፣ Bigthan:
ጉብታ፣ ገበታ፣ መድረክ፣ ችሎት፣ አደባባይ... ማለት ነው።
. ማዕድ፣ የምግብ ጠረጴዛ፥ “እነዚህም ሁለት ነገሥታት ክፋትን ያደርጉ ዘንድ
በልባቸው ያስባሉ፥
በአንድ ገበታም
ተቀምጠው ሐሰት ይናገራሉ ...” (ዳን 11:27)
አደባባይ፥ ጲላጦስ በጌታ ላይ ለመፍረድ ችሎት የተቀመጠበት፥ “ጲላጦስም ይህን ነገር ሰምቶ ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፥ በዕብራይስጥም ገበታ በተባለው ጸፍጸፍ በሚሉት ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ።” (ዮሐ 19፡13)
ገበታ / Bigthan: በጌታ፣ የአምላክ ስጦታ... ማለት ነው። የንጉሡ በር ከሚጠብቁት
የንጉሡ ጃንደረቦች
አንዱ፥ “በዚያም ወራት
መርዶክዮስ በንጉሡ
በር ተቀምጦ
ሳለ ደጁን
ከሚጠብቁት ከንጉሡ
ጃንደረቦች ሁለቱ
ገበታና ታራ
ተቈጡ፥ እጃቸውንም
በንጉሡ በአርጤክስስ
ላይ ያነሡ
ዘንድ ፈለጉ።” (አስ
2:21)
ገባቶን ~ Gibbethon:
ግባት፣ ዳገት፣ ኮረብታ... ማለት
ነው። ለነገደ
ዳን የተሰጠ፥
የቦታ ስም፥
“አቃሮን፥ ኢልተቄ፥ ገባቶን፥ ባዕላት፥” (ኢያ19:44)
ገባዖን ~
Geba, Gibeon: ገብ፣ ጉበን፣ በር፣ የከተማ መግቢያ፣ ኬላ፣ ድንበር፣ ገበያ፣ ግባት፣ ዳገታማ ቦታ... ማለት ነው። [ተዛማች ስሞች-
ጊብዓ፣ ጌቤ] ‘ጉበን’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
ገባዖን / Geba:
የብንያም ከተማ፥ (2
ሳሙ 5፡25) ፣ (2 ነገ 23:8፣ ነህ 11:31)
ገባዖን / Gibeon:
(ኢያ 9፡3-15)
ገብርኤል ~ Gabriel:
ገብረ ኤል፣ የጌታ አገልጋይ፣ የእግዚአብሔር ሠራተኛ፣ ገብረ አምላክ፣ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
Gabriel: ‘ገብረ’
እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው።
[“የእግዚአብሔር ሰው” ማለት
ነው / መቅቃ]
. ነቢዩ ዳንኤል፥ ገና በጸሎት ሲናገር አስቀድሞ በራእይ አይቶት የነበረው ሰው፥
(ዳን 8፡16)
፣ (ዳን 9:21)
. የጌታ ኢየሱስ እና
የመጥምቁ ዩሐንስን
መፀነስ ያበሠረ፥ “መልአኩም መልሶ፦
እኔ በእግዚአብሔር
ፊት የምቆመው
ገብርኤል ነኝ፥
እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤” (ሉቃ 1፡9)
ገነት ~
Garden:
ጋርድ ደን፣ በደን የተጋረደ... ማለት ነው። (ተገን፣ ተገነ፣ ገነት ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስም-
ጎናት]
Garden
-‘ጋረደ’
እና ‘ደን’ ከሚሉ ቃላት የመጣ ነው።
የአዳምና ሔዋን መኖሪያ፥ “እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።” (ዘፍ 2፡8፣9)
ገንዘብ ~
Mammon: ‘ሀብት፣ ገንዘብ’ ማለት
ነው። የጣዖት
ስም፥ “ለሁለት ጌቶች
መገዛት የሚቻለው
ማንም የለም፤
ወይም አንዱን
ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” (ማቴ 6:24፤ ሉቃ 16:9)
ገዓል ~ Gaal: ‘ጥላቻ፣ ቅያሜ’ ማለት
ነው። የአቤድም
ልጅ፥ የሴኬም
ሰዎችን አስተባብሮ
በአቢመሌክ ላይ
ለጦርነት የተነሣ፥
ነገር ግን
በውጊያው ተሸንፎ
ወደ መጣበት አገር ሸሸ፥ “የአቤድም ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋር መጥቶ ወደ ሴኬም ገባ
የሴኬምም ሰዎች
ታመኑበት።”
(መሣ 9:1)
ገዓስ ~
Gaash:
‘ውሽንፍር፣ ነጎድጓድ’ ማለት ነው። ተራራማው የኤፍሬም አገር፥ ኢያሱ የተቀበረበት፥
“በተራራማውም በኤፍሬም አገር
በገዓስ ተራራ
በሰሜን ባለችው
በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት።” (ኢያ 24:30፤ መሣ 2:9)
ጉማሬ ~
Behemoth:
‘ትልቅ አውሬ’ ማለት ነው። በሬ የመሰለ፥ ትልቅ አውሬ፥
“ከአንተ ጋር የሠራሁትን
ጉማሬ፥ እስኪ፥
ተመልከት እንደ
በሬ ሣር
ይበላል።”
(ኢዮ 40:15-24)
ጉር ~ Gur: ጎር፣
ጎራ፣ ምሽግ፣
መቀመጫ፣ መኖሪያ... ማለይ
ነው። የይሁዳ
ንጉሥ አካዝያስ የኢዩ አሽከሮች ወግተው የገደሉበት፥ “የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ያንን ባየ ... በጉር ዐቀበት ላይ ወጉት። ወደ መጊዶም ሸሸ፥ በዚያም ሞተ።” (2 ነገ 9:27)
ጉርበኣል ~ Gur-baal: ባለ
ጎራ፣ ባለ
መኖሪያ... ማለት ነው።
በዓረብ አገር
ያለ ቦታ፥
“እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ
ዓረባውያን በምዑናውያንም
ላይ ረዳው።” (2 ዜና 26:7)
ጉኒ ~ Guni: ‘ገን፣ ተገን፣ ግርጃ’ ማለት ነው።
1. የንፍታሌም ልጅ፥ “የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም።” (ዘፍ
46:24፤ 1
ዜና 7:13)
2. የአብዲኤል፥ “የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቃ የጉኒ ልጅ የአብዲኤል ልጅ ወንድም ነበረ።” (1 ዜና 5:15)
ጉዲኤል ~
Gaddiel, Geuel: ጋዲ ኤል፣ ገደ ኤል፣ የጌታ ሀብት፣ አምላክ የረዳው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ጋዲ፣ ጋድ]
‘ገደ’
እና ’ኤል’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
ጉዲኤል / Gaddiel:
ሙሴ አገሩን እንንዲሰልሉ ከላካቸው፣ ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ፥ ጉዲኤል፥ (ዘኁ 13:10)
ጉዲኤል / Geuel: የማኪ ልጅ፥ “ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲኤል” (ዘኁ 13:15)
ጉዲኤል ~
Geuel:
ገደ ኤል፥ የአምላክ ቸርነት፥ ካሳ፥ ይቅርታ... ማለት ነው። የጋዳዊው ሰላይ፥ የሚልኪ ልጅ፥ (ዘኊ 13:15) “ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲኤል”
ጉድጎዳ ~
Gudgodah:
‘ጉድጓድ፣ ጎድጓዳ’ ማለት ነው። “ከዚያም ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ ከጉድጎዳም ወደ ውኃ ፈሳሾች ... ተጓዙ።” (ዘዳ 10:7)
ጊላላይ ~ Gilalai: ገሊላዊ፣
ግልል፣ የተገለለ፣
የተለየ... ማለት ነው።
የእስራኤልን ቅጥር
ካቆሙ ካህናት፥
የአንዱ ልጅ፥
“ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን ... ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።” (ነህ 12:36)
ጊልቦዓ ~ Gilboa: ጋለባ፣
ጋላቢ... ማለት ነው።
የተራራ ስም፥
“ፍልስጥኤማውያንም ተሰብስበው መጡ በሱነምም ሰፈሩ ሳኦልም እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥
በጊልቦዓም ሰፈሩ።” (1 ሳሙ 28:4)
ጊሎ ~ Giloh:
‘ስደተኛ’
ማለት ነው።
በተራራማው የይሁዳ
አገር የሚገኝ
ከተማ፥ “ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥
ዓኒም፥ ጎሶም፥
ሖሎን፥ ጊሎ አሥራ አንድ ከተሞችና
መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 15:51)
ጊምዞ ~ Gimzo: ‘ለም’
ማለት ነው። ፍልስጥኤማውያን በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ከተቆጣጠሯቸው ከተሞች አንዱ፥ “ደግሞም ... ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥
ሦኮንና መንደሮችዋን፥
ተምናንና መንደሮችዋን፥
ጊምዞንና መንደሮችዋን
ወስደው በዚያ
ተቀምጠው ነበር።” (2 ዜና 28:18)
ጊሽጳ ~ Gispa: ጉሰማ፣
መጎሰም፣ መድቃት፣ መምታት...
ማለት ነው።
ከምርኮ ከተመለሱ በናታም
ከተቀመጡ፥ “ናታኒምም በዖፌል
ተቀምጠው ነበር
ሲሐና ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ።” (ነህ 11:21)
ጊብዓ ~
Gibea, Gibeah: ገበያ፣ መገበያያ ቦታ፣ ከፍ ያለ ቦታ፣ ዳገት፣ ኮረብታማ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ገባዖን፣ ጌቤ]
[ጉብታ ወይም ኮረብታ ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሁለት ሰዎች እና ሁለት ቦታዎች አሉ።
ጊብዓ / Gibea:
የሱሳ ልጅ፥ (1
ዜና 2፡49)
ጊብዓ / Gibeah:
1. ኢያሱ የባልጩት መቍረጫ ሠርቶ የእስራኤልን ልጆች የገረዘበት ስፍራ ስም፥ “ኢያሱም የባልጩት
መቍረጫ ሠርቶ
የግርዛት ኮረብታ
በተባለ ስፍራ
የእስራኤልን ልጆች
ገረዘ።”
(ኢያ 5:3)፣ “ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥
ቃይን፥ ጊብዓ፥
ተምና አሥር
ከተሞችና መንደሮቻቸው” (ኢያ 15:57)
2. የካሌብ ልጅ፥ (1 ዜና 2:49)
3. (1 ሳሙ 13፡15)
ጋሊም ~
Gallim:
‘ክምር’ ማለት ነው። ሳኦል ልጁን ሚላካን፥ የዳዊትን ሚስት፣ የሰጠው ሰው አገር፥ “ሳኦል ግን የዳዊትን ሚስት ልጁን ሜልኮልን አገሩ ጋሊም ለነበረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።” (1 ሳሙ 25:44)
ጋላል ~ Galal: ‘ግልል፣ ግልግል፣ ዕረፍት’ ማለት ነው።
1. ሌዋዊው፥ ከአሳፍ ልጆች አንዱ፥ “በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ
የሚካ ልጅ
መታንያ”
(1 ዜና 9:15)
2. “በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ”
(1 ዜና 9:16)
3. የኤዶታም ልጅ፥ “በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ ... የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ።”
(ነህ 11:17)
ጋሌማት ~ Alameth: አለማት ...
[ተዛማጅ ስም-
ዓሌሜት] ‘ዓለማት’- ጋሌማት
በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ሰዎች እና አንድ ቦታ አሉ።
. ለብንያም ነገድ የተሰጠ የቦታ ስም፥ (1 ዜና 6:60)
. የቤኬር ልጅ፥ ዓሌሜት- (1 ዜና 7፡8) ፣ የዕራ ልጅ፥ ዓሌሜት- (1 ዜና
9:42)፣ የይሆዓዳ ልጅ፥ ዓሌሜት- (1 ዜና 8:36)
ጋልዮስ ~
Gallio:
‘ባለወተት፣ በወተት ያደገ’ ማለት ነው። በአካይያ አገረ ገዥ የነበረ፥ “ጋልዮስም በአካይያ አገረ ገዥ በነበረ ጊዜ፥ አይሁድ በአንድ ልብ ሆነው በጳውሎስ ላይ ተነሡ፥ ወደ ፍርድ ወንበርም አምጥተው።” (ሐዋ 18:12)
ጋሙል ~
Gamul:
‘አገልግሎት፣ ካሳ፣ ክፍያ’ ማለት ነው። በቤተ መቅደስ ያገለግሉ ከነበሩ ካህናት፥
የሀያ ሁለተኛው
ምድብ አለቃ፥
“ሀያኛው ለኤዜቄል፥ ሀያ
አንደኛው ለያኪን፥
ሀያ ሁለተኛው
ለጋሙል፥”
(1 ዜና 24:17)
ጋሜር ~ Gomer: ‘ፍጻሜ፣ መጨረሻ’ ማለት ነው።
1. የያፌት ትልቁ ልጅ፥ “የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥
ሞሳሕ፥ ቴራስ
ናቸው።”
(ዘፍ 10:2፣3)
2. የሆሴ ሚስት፥ “እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ እርስዋም ፀነሰች
ወንድ ልጅንም
ወለደችለት።” (ሆሴ1:3)
ጋሴም ~ Gazzam: ‘ማጥፋት፣ ማውደም’ ማለት
ነው። ከግዞት
ከተመለሱ፥ የጋሴም ልጆች ይገኙበታል፥ “የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥” (ዕዝ
2:48፤ ነህ 7:51)
ጋሬብ~ Gareb: ‘ገረባ፣ ሽፋን፣ ጋቢ፣ ኩታ፣ ነጠላ’ ማለት ነው።
1. ከዳዊት ኃያላን አንዱ፥ “ጋሬብ፥ ኬጢያዊው ኦርዮ ሁሉ በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው።” (2 ሳሙ 23:39)
2. በኢየሩሳሌም አቅራቢያ የነበረ ኮረብታ፥ “የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፥ ወደ ጎዓም ይዞራል።” (ኤር 31:39)
ጋቤር ~
Gibbar:
ጊባር፣ ገብር፣ ገባር፣ አገልጋይ፣ ሠራተኛ... ማለት ነው።
[ተዛማጅ ስሞች- ገብርኤል፣ ጋቤር]
የባቢሎን ንጉሥ
ናቡከደነፆር ወደ
ባቢሎን ከማረካቸው
ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2፡ 20)
ጋትሔፍር ~ Gittah-hepher:
‘ቁፋሮ’ ማለት ነው። “ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ።” (ኢያ 19:13)
ጋዛ ~
Gaza, Gazathites: ገዛ፣ ገዥ፣ ተቆጣጣሪ፣ አስተዳደራዊ ቦታ፣ ጠንካራ ምሽግ ማለት ነው። ጋዛይት፣ ጋዛውያን፣ የጋዛ አገር ሰዎች…
‘ገዛ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው።
[ምሽግ ማለት
ነው / መቅቃ]
ጋዛ /Gaza: የከነዓናውያን
ወሰን፥ ከፍልስጤማውያን ከተሞች አንዱ፥ (ገላ 10:19)
ጋዛ / Gazathites:
የጋዛ ነዋሪዎች፥ (ኢያ 13፡3)
ጋዜዝ ~
Gazez:
ዔፋ ለካሌብ የወለደችለት፥ (1 ዜና 2:46) “የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች”
ጋይ ~ Ai, Giah, Ije-abarim, Shaashgaz: ‘የአስከሬን ክምር’ ማለት ነው።
1. በኢየሩሳሌም በስተሰሜን የሚገኝ ከተማ፥ “ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ...” (ኢያ 7:2፤ 8:9)
2. የአሞናውያን ከተማ፥ “ሐሴቦን ሆይ፥ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ... መካከል ተርዋርዋጡ።” (ኤር 49:3)
ጋይ / Giah: ‘ፏፏቴ’ ማለት
ነው። በሳሙኤል
መጽሐፍ የተጠቀሰ
ቦታ፥ “ኢዮአብና አቢሳም አበኔርን አሳደዱ በገባዖንም ምድረ በዳ መንገድ በጋይ ፊት ለፊት እስካለው እስከ አማ ኮረብታ ድረስ ... ፀሐይ ጠለቀች።” (2 ሳሙ 2:24)
ጋይ / Ije-abarim: ‘የአብርሃም
ባድማ’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን በምድረ ባዳ ሲንከራተቱ ካረፉባቸው፥ የሞአባውያን አዋሳኝ፥ “ከኦቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ።” (ዘኊ 33:44)
ጋይ / Shaashgaz:
‘የውበት ተገዥ’ ማለት ነው። የንጉሥ አርጤክስ ጃንደረባ፥
“ማታም ትገባ ነበር፥
ሲነጋም ተመልሳ
ወደ ሁለተኛው
ሴቶች ቤት
ቁባቶችን ወደሚጠብቅ ወደ ንጉሡ ጃንደረባ ወደ ጋይ ትመጣ ነበር ...” (አስ 2:14)
ጋይዮስ ~ Gaius: ‘ባለጠጋ፣ ምድራዊ ጌታ’ ማለት ነው።
1. መቄዶንያዊው፥ ጳውሎስ በጉዞው ዘንድ አገልጋይ የነበረ፥ “ከተማውም በሙሉው
ተደባለቀ፥ የመቄዶንያም
ሰዎች የጳውሎስን
ጓደኞች ጋይዮስንና
አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ... ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ።” (ሐዋ 19:29)
2. ከጳውሎስ ጋር ከቆሮንቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የሔደ፥ የደርቤን ሰው፥ “የሸኙትም የቤርያው ... አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤” (ሐዋ 20:4)
ጋይዳድ ~
Irad:
‘ሯጭ’ ማለት ነው። ከቀደሙ አባቶች አንዱ፥ የሜኤል አባት፥ የቃየን የልጅ ልጅ፥ “ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ ሜኤልም ማቱሣኤልን ወለደ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ።” (ዘፍ 4:18)
ጋዲ ~
Gaddi, Gadi: ጋዲ፣ ገዴ፣ ገደኛ፣ ዕድለኛ፣ እጣ የወጣለት፥ የጋድ ወገን፣ የጋድ አገር ሰው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች-
ጉዲኤል፣ ጋድ]
‘ገድ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:
-
ጋዲ / Gaddi: የሱሲ ልጅ፥ የከነዓን ምድር እንዲሰልሉ ሙሴ ከላካቸው የምናሴ
ወገን፥ (ዘኁ 13፡11)
ጋዲ / Gadi: የምናሔ አባት፣ የእስራኤል ንጉሥ፥ (2 ነገ 15፡14፣17)
ጋዴዮን ~ Gideoni: ገደ
ዓይኔ፥ ዕድለኛ ዓይኖቸ... ማለት ነው።
ብንያማዊው፥ የአቢዳን አባት፥ “ከብንያም የጋዴዮን ልጅ አቢዳን፥ ከዳን የአሚሳዳይ ልጅ
አኪዔዘር፥”
(ዘኊ1:11፥ 7:60፣65፥ 10:24)
ጋድ ~
Gad:
ጋድ፣ ጎድ፣ ጉድ፣ ገድ፣ ዕድል፣ እጣ ፈንታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ጉዲኤል፣ ጋዲ]
‘ገድ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው።
[መልካም ዕድል
ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:
-
1. ልያ ለያቆብ የወለደችለት፥ “ልያም። ጉድ አለች ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው”
(ዘፍ 30፡11-13)
2. በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረ ነቢይ፥ (1 ዜና 29:29) ፣ (2 ዜና 29:25) ፣ (1 ሳሙ 22:5)
ጌልገላ ~ Gilgal: ግልግል፣ ዕረፍት፣ ሸክምን ማቅለል፣ ከባርነት መላቀቅ፣ ነጻነትን ማግኘት... ማለት ነው።
Gilgal- ‘ግልግል’
ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። የቃሉ ምንጭ ደግሞ ‘ገላገለ’የሚለው ግስ ነው።
. ከግብፅ ወጥተው ዮርዳኖስን ፈጽመው ሲሻገሩ የሰፈሩበት ቦታ፥ “እግዚአብሔርም ኢያሱን። ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።” (ኢያ 5፡9)
. (ኢያ 9፡6)
ጌራ ~ Gera:
‘ጎራ፣ ጠበኛ፣ ጠላት’ ማለት ነው።
1. የብንያም ልጅ፣ የቤላ
ልጅ፥ (1 ዜና 8:4፣5፣7)
“ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥
አሖዋ፥ ጌራ…”
2. ብንያማዊው ፈራጅ፣ የናዖድ አባት፥ “የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው
አዳኝ አስነሣላቸው
...” (መሣ 3:15)
3. ዳዊትን የተሳደበ፣ የሳሚ አማት፥ “ንጉሡ ዳዊትም ወደ ብራቂም መጣ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፥ እየሄደም
ይረግመው ነበር።” (2 ሳሙ
16:5፥ 19:16፣18)
ጌራራ ~ Gerar: ‘የመቆያ ቦታ፣
መኖሪያ’
ማለት ነው።
ከጋዛ በስተደቡብ
የነበረ፥ በጣም ጥንታዊ ከተማ፥ “የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣ ድረስ ነው።” (ዘፍ 10:19፥ 20:1፥ 26:17)
ጌርሳም ~ Gershom: ‘እንግዳ፣ መጻተኛ’
ማለት ነው።
1. ሙሴ ከሲፖራ የወለደው፥ “ወንድ ልጅም ወለደች። በሌላ ምድር መጻተኛ ነኝ ሲል ስሙን ጌርሳም ብሎ ጠራው።” (ዘጸ 2:22፥18:3)
ጌርጌሳውያን ~ Girgashite:
‘ከስግደት የተመለሱ’
ማለት ነው። የከነዓን አምስተኛ ልጅ ወገኖች፥ “ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም”
(ዘፍ 10:17)
ጌርጌሴኖ ~ Gadarenes: ‘የገደራ ሰዎች’ ማለት ነው። ‘ገረራ’ ማለት ደግሞ ግድግዳ፣ ግንብ፣ አጥር ማለት ነው። የአገር ስም፥ “ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ።” (ማር 5:1፤ ሉቃ 8:26፣37)
ጌሹር ~ Geshur: ‘መሻገሪያ፣ ድልድይ’ ማለት ነው። በሶርያ በስተሰሜን የምትገኝ፥ ትንሽ ግዛት፥ “እኔ ባሪያሕ በሶርያ ጌሹር ሳለሁ። እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም ቢመልሰኝ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀርባለሁ ...” (2 ሳሙ 15:8)
ጌበር ~ Geber: ገበር፣ ገባር ፥ ሠራተኛ፣ አገልጋይ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች - ገብርኤል፣ ጋቤር]
‘ገበረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው።
የኡሪ ልጅ፣ በገለዓድ አገር ሹም የነበረ፥ (1 ነገ 4፡19)
ጌባል ~ Gebal: ‘ወሰን’ ማለት ነው። የወደብ ከተማ፥ “በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር ...” (ሕዝ 27:9)
ጌቤ ~ Gabbai: ገባይ፣ ገበያ፣ ገቢ የሚያስገኝ፣ አስገባሪ፣ ቀራጭ... ማለት ነ ው። [ተዛማጅ ስሞች- ገባዖን፣ ጊብዓ፣ ጊብዓ]
በነህምያ ዘመን፥ ከግዞት መልስ፥ ከይሁዳና ከብንያም ልጆች በኢየሩሳሌም የተቀመጡ፥
(ነህ 11፡8)
ጌታችንሆይ፥ና ~
Maranatha: ማረን አንተ፣ ምራን አንተ፣ ይቅር በለን፣ ነጻ አውጣን... ማለት ነው።
Maranatha-
‘ምራን’
እና ‘አንተ’
ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተመሠረተ
ቃል ነው።
ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ በጻፈው ሰላምታ መደምደሚያ ላይ የተናገረው ቃል፥ “ጌታን ኢየሱስ
ክርስቶስን የማይወድ
ቢኖር የተረገመ
ይሁን። ጌታችን ሆይ፥
ና”
(1 ቆሮ 16:22)
ጌቴም ~ Gittaim:
‘ጋጣም፣ መንታ የወይን
መጭመቂያ’
ማለትነው። የከተማ
ስም፥ “ብኤሮታውያንም ወደ
ጌቴም ሸሽተው
ነበር፥ እስከ
ዛሬም ድረስ
በዚያ ተጠግተው
ነበር።”
(2 ሳሙ 4:3፤ ሳሙ 11:33)
ጌቴሴማኒ ~ Gethseman: ጌታ ስመኒ፣ የጌታ ስም፣ ስመ አምላክ፣ መልካም ስም፣ ቅዱስ ስም... ማለት ነው። (ዘይት ማለት ነው። ተብሎም ይተረጎማል ኪወክ / አ)
‘ጌታ’ እና ‘ስም’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ጌታ የጸለየበት የቦታ ስም፥ የወይን አትክልት ያለበት፥ (ማር 14፡32)
ጌቴር ~
Gether:
ገጠር ማለት ነው። የአራም በሦስተኛ ተራ ያለ ልጅ፥
“የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።” (ዘፍ 10:23)
ጌት ~
Gath:
ጋት፣ ጋጥ፣ ጓዳ... ማለት ነው። (የወይን መጭመቂያ ተብሎም ይተረጐማል።)
. የእግዚአብሔር ታቦት በፍላስጥኤማውያን ተማርኮ የተወሰደበት ከተማ፥ (1
ሳሙ 5፡8፣9)
. የአቢዳራ አገር፥
(2 ሳሙ 6:11)
. (ኢያ 11:22)
ጌትያውን ~
Gittites:
ጌታይት፣ ጌታውያን፣ የጌት አገር ሰዎች... ማለት ነው።
‘ጌት’
ከሚለው የቦታ ስም የመጣ ስም ነው።
ንጉሥ ዳዊትን
ከተከተሉ ሰዎች
መካከል ጌትያውን
ይገኙበታል፥ (2 ሳሙ 15፡18፣ 19)
ጌንሴሬጥ ~ Gennesaret: ‘ገነተ መሳፍንት’ ማለት ነው። “ተሻግረውም ወደ ጌንሴሬጥ ምድር መጡ።”
(ማቴ 14:34፤ ማር 6:53)
ጌንባት ~ Genubath: ‘ቀማኛ’ ማለት
ነው። የአዳድ
ልጅ፥ እናቱ
የቴቄምናስ እኅት
ናት፥ ያደገው
በፈርዖን ቤተመንግሥት
ነው፥ “የቴቄምናስ እኅት
ጌንባትን ወለደችለት፥ ቴቄምናስም በፈርዖን ቤት አሳደገችው ጌንባትም በፈርዖን ቤት በፈርዖን ልጆች
መካከል ነበረ” (1 ነገ 11:20)
ጌዝር ~ Gazer: ‘ግዝር፣ ግዝረት፣ ከፋፋይ’
ማለት ነው።
በዳዊት ዘመን፥
የፍልስጥኤማውያን የነበረ ቦታ፥ “ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ ከገባዖንም እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ።” (2 ሳሙ 5:25፤ 1 ዜና 14:16)
ጌዝር ~ Gezer: ‘አፋፍ፣ ኮረብታ’ ማለት
ነው። ጥንታዊ፥
የከነናውያን መናገሻ፥
“በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን
ለመርዳት ወጣ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።” (ኢያ 10:33፥ 12:12)
ጌዴል ~
Giddel:
ገድል፣ ትልቅ፣ ከፍተኛ... ማለት ነው።። ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ የጌዴል ልጆች ይገኙበታል፥ “የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥” (ዕዝ
2:47፤ ነህ 7:49)
ጌዴልያ ~
Igdaliah:
ገድለ ያሕ፣ የሕያው ገድል፣ ያምላክ ታላቅ ሥራ... ማለት ነው። የአንድ ነቢይ ስም፥ “ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ
በላይ ባለው
በአለቆች ጓዳ
አጠገብ ወዳለው
ወደ እግዚአብሔር
ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።” (ኤር 35:4)
ጌዴዎን ~ Gideon: ገደ
ዓይን፣ ዕድለኛ ዓይኖች... ማለት ነው።
የአቢዔዝራዊው፥ የኢዮአስ ትንሹ ልጅ፥ “የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው
ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ
በነበረችው በአድባሩ
ዛፍ በታች
ተቀመጠ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን ...” (መሣ 6:15)
ጌድሶን፣ ጌርሳም ~ Gershon: ‘መጻተኛ’ ማለት ነው።
1. ጌድሶን፥ “የሌዊ ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።”
(1 ዜና 6:16፣17፣ 20፣43፣62፣71፥ 15:7)
2. ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ፥
ፊንሐስ ልጅ፥
ጌርሶን፥ “ከፊንሐስ ልጆች ጌርሶን፥ ከኢታምር ልጆች ዳንኤል፥ ከዳዊት ልጆች ሐጡስ፥ ከሴኬንያ ልጆች፥” (ዕዝ
8:2)
ጌድር ~
Geder:
ገደራ፣ ግንብ፣ አጥር፣ ድንበር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ጌዶር]
‘ገደረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም ነው። ኢያሱ ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ የእስራኤል ልጆች ከመቱአቸው ሠላሳ አንድ የምድር ነገሥታት፥ (ኢያ 12፡14)
ጌዶር ~
Geder, Gedor: ገደራ፣ ግንብ፣ አጥር፣ ድንበር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ጌድር]
‘ገደረ’
ከሚለው ግስ
የመጣ ስም
ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ:-
ጌዶር / Geder:
1. በደቡብ በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ካሉት ከይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች፥ (1 ዜና 4:39)
2. የፋኑኤል ልጅ፥ (1 ዜና 4:4)
ጌዶር / Gedor:
(ኢያ 15:58)
ግርግም ~
Manger:
ግርግም የከብቶች
ምግብ የሚቀርብበት
ገበታ፣ በረት፣ ጋጥ፣ ማእድ ቤት፣ አጥር...። በረት
ግርግምን፥ ግርግም
በረትን ይገልጻል።
. ጌታ
እንደተወለደ የተኛበት
ቦታ፥ “የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው” (ሉቃ
2:7 ፣ 12
፣ 16...)
. “ጐሽ ያገለግልህ
ዘንድ ይታዘዛልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን?”
(ኢዮ 39:9)
. ግርግም፥ የቤት እንስሳ ማደሪያ መሆኑንም ከሚከተለው ጥቅስ እንገነዘባለን:- “ጌታም መልሶ፦
እናንተ ግብዞች፥
ከእናንተ እያንዳንዱ
በሰንበት በሬውን
ወይስ አህያውን
ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ
ሊያጠጣው ይወስደው
የለምን?” (ሉቃ
13:15)
ግቤር ~ Gebim: ‘የአንበጣ መንጋ’ ማለት
ነው። በኢየሩሳሌም
በስተምሥራቅ የሚገኝ ከተማ፥ “መደቤና ሸሽታለች በግቤርም የሚኖሩ ቤተ ሰቦቻቸውን
አሽሽተዋል።”
(ኢሳ 10:31)
ግብዣ ~
Feast:
ፌሽታ፣ ፌስታ፣ ደስታ፣ ድግስ፣ ግብዣ፣ በዓል... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስሞች- ማዕድ፣ ሰርግ፣ በዓል]
. አብርሃም ያደረገው ድግስ፥ “...አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ።” (ዘፍ 21:8) ፣ (ሉቃ 15:23)
. ማዕድ-
(ዘፍ 19፡3) ፣ በዓል-
(መሣ 14:10)፣ ሰርግ-
(ዘፍ 29:22)
ግብፅ ~ Egypt:
‘ጨቋኝ፣ የመከራ አገር’ ማለት
ነው። በስሜን
ምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኝ አገር፥ የካም አገር፥ “እስራኤልም ወደ ግብፅ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር
ተቀመጠ።”
(መዝ 105:23፣27)
ግያዝ ~
Gehazi:
ጋዚ፣ ገዛ፣ ገዥ፣ ግዛት፣ አስተዳደር... ማለት ነው።
‘ገዛ’
ከሚለው ቃል
የተገኘ ስም ነው። የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ ሎሌ፥ “ሎሌውንም ግያዝን፦ ይህችን ሱነማዊት ጥራ አለው።” (2 ነገ 4፡31)
ግዮን ~
Gihon: ገዋነ፣ ወደላይ ወጣ... ማለት ነው።
1. ከገነት የሚወጣው ሁለተኛው ወንዝ፥ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው። እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ዘፍ 2:13)
2. “ንጉሡም ... የጌታችሁን ባሪያዎች ይዛችሁ ሂዱ፥ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ
አስቀምጡት፥ ወደ
ግዮንም አውርዱት”
(1 ነገ 1:33፣38፣45)
ግዴሮታይም ~ Gederothaim:
‘ወሰን፣ ድንበር፣ ግድብ፣ ግድግዳ’
ማለት ነው።
በደልዳላው የይሁዳ
ክፍል የሚገኝ
ከተማ፥ “ዓዶላም፥
ሰኰት፥ ዓዜቃ፥
ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥
ግዴራ፥ ግዴሮታይም አሥራ አራት ከተሞችና
መንደሮቻቸው።”
(ኢያ 15:36)
ጎላን ~ Golan: ‘መጻተኛ’
ማለት ነው።
የባሳን ከተማ፥
“ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ
የሆነችውን ጎላንንና
መሰምርያዋን፥ በኤሽትራንና
መሰምርያዋን ሁለቱን
ከተሞች ሰጡአቸው።” (ኢያ 21:27)
ጎልያድ ~
Goliath:
ገላት፣ ገላያት፣ ትልቅ አካል፣ ግዙፍ ሰው፣ ትልቅ ሰውነት... ማለት ነው።
ዳዊት በወንጭፍ የገደለው፣ የጌት ሰው፣ የፍልስጥኤማውያን ጀግና፥ (1 ሳሙ 17፡4)
ጎልጎታ ~ Golgotha: ገለ
ጎታ፣ ገላ
ጎታ፣ የአካል
ክምር ፥
የራስ ቅል
ክምችት... ማለት ነው።
‘ገላ’
እና ‘ጎታ’
ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ነው። ጌታን የሰቀሉበት ስፍራ፥ “ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው
ስፍራ በደረሱ
ጊዜም፥...”
(ማቴ 27፡33)
ጎሶም ~ Goshen: ‘መቅረብ’ ማለት ነው።
1. እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ከሰፈሩባቸው ቦታዎች፥ “ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ።”
(ኢያ 10:41)
2. “ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን
ድረስ መታ።” (ኢያ 10:41)
ጎብ ~
Gob:
‘ጉድጓድ’ ማለት ነው። በሳሙኤል መጽሐፍ የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ “ከዚህም በኋላ
እንደ ገና
በጎብ ላይ
ከፍልስጥኤማውያን ጋር
ሰልፍ ሆነ፥
ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም …
ሳፍን ገደለ።” (2 ሳሙ 21:18፣19)
ጎቶልያ ~ Athaliah:
አታሊ ያሕ፣ አታላይ፣ እግዚአብሔርን የበደለ... ማለት ነው።
1. የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ፥ የንጉሥ አካዝያስ እናት፥ “መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ …
እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች።” (2 ነገ 8:26)
2. ከምርኮ ከተመለሱ፥ የሻያ አባት፥ “ከኤላም ልጆች የጎቶልያ ልጅ የሻያ፥ ከእርሱም
ጋር ሰባ
ወንዶች።”
(ዕዝ 8:7)
3. በትውልዶቻቸው አለቆች ከነበሩ በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ፥ የሶሴቅ ልጅ፥
“ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች።” (1 ዜና 8:26)
ጎቶም ~
Gatam:
‘የተቃጠለ ሸለቆ’ ማለት ነው። የዔሳው ልጅ፣ የኤልፋዝ አራተኛ
ልጅ፥ “የኤልፋዝም ልጆች
እነዚህ ናቸው
ቴማን፥ ኦማር፥
ስፎ፥ ጎቶም፥
ቄኔዝ”
(ዘፍ 36:11፤ 1 ዜና 1:36)
ጎቶንያል ~
Othniel:
‘የአምላክ አንበሳ’ ማለት ነው። የቄኔዝ ልጅ፥ የካሌብ ወንድም፥ “የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት ልጁንም ዓክሳን አጋባው።”
(ኢያ 15:17፤ መሣ 1:13፥ 3:9፤ 1 ዜና 4:13)
ጎናት ~
Ginath:
ገነት፣ ተገን፣ ተጋን፣ በአትክልት የተከለለ... ማለት ነው።
‘ገነት’
ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። [ተዛማጅ ስም- ገነት] የታምኒ
አባት፥ (1 ነገ 16:21 ፣ 22)
ጎዓ ~ Goath: ‘ማግሳት_ (ለበሬ)’ ማለት
ነው። የኢየሩሳሌም
አጎራባች፥ ከጌበር
ኮረብታ ተያይዞ የሚገኝ ቦታ፥ “የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፥ ወደ ጎዓም ይዞራል።” (ኤር 31:39)
ጎዛን ~ Gozan: ‘ግጦሽ፣ ሳር
ሜዳ፥ የከብት
ምግብ’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን በግዞት የተወሰዱበት አገር፥ “…
የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ወሰደ፥ እስራኤልንም
ወደ አሦር
አፈለሰ፥ በአላሔና
በአቦር በጎዛንም ወንዝ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።”
(2 ነገ 17:6፤ 1 ዜና 5:26፤ 2
ነገ 19:12፤ ኢሳ 37:12)
ጎዶልያስ ~ Gedaliah: ገድለ
ዋስ፣ ገድለ
ያሕ፣ የሕያው
ገድል፣ የእግዚአብሔር ገድል፣ የአምላክ ታላቅ ሥራ፣ የአብ ሥራ... ማለት ነው። Gedaliah- ‘ገድል’
እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ፣ ዋስ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ማለት ነው / መቅቃ]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. የኤዶታም ልጅ፥ ጎዶልያስ፥
(1 ዜና 25፡3፣9)
2. የአኪቃም ልጅ፥ ጎዶልያስ፥
(2 ነገ 25:22)
3. የጳስኮርም ልጅ፥ በኤርምያስ
ሴራ ከጠነሰሱ
የአይሁድ ሕግ አዋቂዎች፥ ጎዶልያስ፥ (ኤር 38:1)
4. የአማርያ ልጅ፣ የኵሲ አባት ሁኖ የነቢዩ ሶፎንያስ አያት፥ (ሶፎ 1:1)
ጎግ ~
Gog:
‘ተራራ’ ማለት ነው። (ሠራዊት፣ መንጋ፣ በዝቶ የሚኼድ የሚንጋጋ’ ማለት
ነው፥ ተብሎ
ይተረጎማል ።
ኪወክ / አ)
1. የሸሜያ አባት፥ “ልጁ ጎግ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ሚካ፥” (1 ዜና 5:4)
2. “በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ
የሚያሕል ነው።” (ራእይ 20:8)
ጎፈር ~ Gopher: ጎፈር ማለት ነው። ‘ጎፈረ’ ከሚለው ቃል የተገኘ የእንጨት ስም ነው። [ጥድን የሚመስል ዛፍ /
መቅቃ]
ኖኅ መርከብ
የሠራበት የእንጨት
ስም፣ “ከጎፈር እንጨት
መርከብን ለአንተ
ሥራ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ፥ በውስጥም በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት” (ዘፍ
6፡14)
No comments:
Post a Comment