ጱዴስ ~ Pudens: ይናፋርማለት ነው። ሮማዊ ክርስቲያ ከክረምት በፊት እንድትመጣ ትጋ። ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።” (2 ጢሞ 4:21)

ጲላጦስ ~ Pilate: ጦረኛ ነፍጠኛ፣ የጦር ልብስ የለበሰማለት ነው። በጌታ ላይ የፈረደ ሮማዊ ገዥ፥ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።” (ማቴ 27:2)

ጲስድያ ~ Pisidia: ሜዳማማለት ነው። በታንሽቱ እስያ የሚገኝ የቦታ ስም፥ እነርሱ ግን ከጴርጌን አልፈው ጲስድያ ወደምትሆን ወደ አንጾኪያ ደረሱ፤ በሰንበትም ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።” (ሐዋ 13:1414:21-24)

ጲርአም ~ Piram: መንጋማለት ነው። ኢያሱ ከነዓንን በያዘ ጊዜ፥ የአሞራውያን ንጉሥ፥ ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ። ወደ እኔ ውጡ፥” (ኢያ 10:3)

ጲርዓቶን ~ Pirathon: ልዑላዊማለት ነው በኤፍሬም አገር የነበረ የቦታ ስም፥ የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፥ በተራራማውም በአማሌቃውያን ምድር በኤፍሬም ባለችው ጲርዓቶን ተቀበረ።” (መሣ 12:15)

ጲጥፋራ ~ Potiphar: የአፍ ወይፈን ማለት ነው። ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው። (ዘፍ 39:1)

ጳስኮር ~ Pashur: የተሻረ፣ የተፈታ፣ ነጻ የሆነማለት ነው።

1. ከካህናት አለቆች አንዱ፥ የመልኪያ ወገን፥ የመልኪያ ልጅ ጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ” (1 ዜና 9:12 24:9 ነህ 11:12)

2. በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ (ኤር 20:1)

ጳርሜና ~ Parmenas: ዘላቂ፣ ቀጣይማለት ነው። በሐዋርያት ከተሾሙ ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ፥ ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።” (ሐዋ 6:5)

ጳትሮስ ~ Pathros: ባተ ራስ፣ ቤተ ራስ፣ የበላይ አባት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ጴጥሮስ]

ከአርባ ዓመት በኋላ እስራኤላውያንን፣ ከተበተኑባቸው እሰበስባለሁብሎ በተናገረው ትንቢት የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ጳትሮስ ከኢትዮጵያ...” (ኢሳ 11:11)

ጳንጦስ ~ Pontus: ባሕርማለት ነው። የታናሽቱ እስያ ክፍለ ግዛት፥ የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም ጳንጦስ በእስያም” (ሐዋ 2:9)

ጳውሎስ ~ Paul: ንኡስ፣ ትንሽማለት ነው። የሳውል ሌላ ስም፥ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ...” (ሐዋ 13:9)

ጳጥራ ~ Patara: ሐዋርያው ጳውሎስ ባደረገው ጉዞ ካለፈባቸው ከተሞች፥ ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤” (ሐዋ 21:12)

ጳጥሮባ ~ Patrobas: አባት አባታዊ... ማለት ነው። ጳውሎስ በሰላምታ ደብዳቤው የጠቀሰው፥ በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ጳጥሮባ ለሄርማንም ... ሰላምታ አቅርቡልኝ” (ሮሜ 16:14)

ጳፉ ~ Paphos: ትኩስ፣ የፈላ፣ የሞቀማለት ነው። ጳውሎስና በርናባስ በጉዟቸው ከጎበኟቸው ቦታዎች፥ የቆጵሮስ ዋና ከተማ፥ ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ በርያሱስ የሚሉትን ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የሆነውን አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ፤” (ሐዋ 13:6)

ጴርጋሞን ~ Pergamos: ምጡቅ፣ ዳገት ማለት ነው። ከሰባቱ አብያተ ክርስቲያን አንዱ የሚገኝባት፥ በታናሽቷ እስያ የምትገኝ ከተማ፥ እንዲሁም። የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞን ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ።” (ራእ 1:11 2:17)

ጴርጌ ~ Phrygia: ደረቅ መሬት የገበረ ማለት ነው። በታናሽቱ እስያ የምትገኝ አገር፥ እነርሱ ግን ጴርጌ አልፈው የጲስድያ ወደምትሆን ወደ አንጾኪያ ደረሱ፤ በሰንበትም ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ። (ሐዋ 13:14)

ጴርጌን ~ Perga: ፈራሽ፣ አላፊ፣ ጠፊ፣ ምድራዊማለት ነው። የጵንፍልያ ከተማ፥ ጳውሎስም ከጓደኞቹ ጋር ከጳፉ ተነሥቶ የጵንፍልያ ወደምትሆን ወደ ጴርጌን መጣ፤ ዮሐንስም ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። (ሐዋ 13:13)

ጴጥሮስ ~ Peter: ቤተ ራስ፣ የአባት ወገን፣ የበላይ አባት... ማለት ነው። (ለት ማለት ነው ተብሎም ይተረጎማል።) [ተዛማጅ ስም- ጳትሮስ]

የስምዖን ስም፥ “...ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ...” (ማቴ 4:18)

ጵልያጦ ~ Amplias: ትልቅ፣ ጉልህ፣ ደምቆ የሚታይ፣ ጎልቶ የሚሰማ... ማለት ነው። በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ጳውሎስ በሰላምታ ደብዳቤው የጠቀሰው፥ በጌታ ለምወደው ጵልያጦ ሰላምታ አቅርቡልኝ። (ሮሜ 16:8)

ጵርስቅላ ~ Prisca, Priscilla: ጥንታዊማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞዎስ በላከው የሰላምታ ደብዳቤ፥ የጠቀሰው፥ ጵርስቅላ ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ። (2 ጢሞ 4:19)

       ጵርስቅላ / Priscilla: የአቂላ ሚስት፥ በወገኑም የጳንጦስ ሰው የሚሆን አቂላ የሚሉትን አንድ አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሚስቱ ጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ መጥቶ ነበር፥ አይሁድ ከሮሜ ይወጡ ዘንድ ቀላውዴዎስ አዞ ነበርና፤ ወደ እነርሱ ቀረበ፥ (ሐዋ 18:2)

ጵሮኮሮስ ~ Prochorus: የመዘምራን አለቃማለት ነው። ከሰባቱ ዲያቆናት ሦስተኛው፥ ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ... የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።” (ሐዋ 6:5)

ጵኒኤል ~ Peniel: ፕኒኤል፣ ፋና ኤል፣ የአምላክ ፊት፣ የጌታ መልክ፣ የእግዚአብሔር ፊት፣ ብርሃናማ፣ አንጸባራቂ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ፋኑኤል]

ያዕቆብ ከአንድ ሰው ጋር እስከ ንጋት ድረስ ይታገል የነበረበት ቦታ፥ ያዕቆብም። እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው (ዘፍ 32:30) ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። (ዘፍ 32:31)

ጵኒኤል ~ Penuel: የአምላክ ፊትማለት ነው። ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር የታገለበት፥ እስራኤል ተብሎ የተጠራበት ሥፍራ፥ ያዕቆብም። እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው” (ዘፍ 32:30)

ጵንፍልያ ~ Pamphylia: የተደባለቀ ሕዝብማለት ነው። ጳውሎስ በሐዋርያዊ ጉዞው ካለፈባቸው ቦታዎች፥ ጳውሎስም ከጓደኞቹ ጋር ከጳፉ ተነሥቶ ጵንፍልያ ወደምትሆን ወደ ጴርጌን መጣ፤ ዮሐንስም ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።” (ሐዋ 13:1314)

ጶጥፌራ ~ Potipherah: የዮሴፍ ሚስት፣ የአስናት አባት፥ የምናሴና ኤፍሬም አያት፥ ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምናሴና ኤፍሬም ተወለዱለት የሄልዮቱ ከተማ ካህን ጶጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው። (ዘፍ 41:45 50 46:20)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ