ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ፈሐት ሞዓብ ~ Pahath-moab: ‘የሞብ ዳኛ፣
ፍትሕ ሰጭ’
ማለት ነው።
ከባቢሎን ምርኮ
ከተመለሱት፥ የኢየሩሳሌምን
ቅጥር በመጠገን
የተባበረ፥ “ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ
ሁለት።”
(ዕዝ 2:6፥ 8:4፥ 10:30)
ፈሉስ ~
Pallu:
‘ታዋቂ’ ማለት ነው። የሮቤል ልጅ፥ የኤልያብ አባት፥ “የእስራኤል በኵር ሮቤል የሮቤል ልጆች ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን
ወገን፥”
(ዘኊ 26:5፣8፤ 1 ዜና 5:3)
ፈሉሶ ~
Phallu:
‘ታዋቂ፣ የተከበረ’ ማለት ነው። የሮቤል ልጅ፥ “የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ።” (ዘፍ 46:9)
ፈሊታውያን ~ Pelethites: ‘ፋራጆች፣ መኳንንት’ ማለት ነው። “የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ።”
(2 ሳሙ 8:18፥ 20:7፣23 ነገ 1:38፣44፤ 1
ዜና 18:17)
ፈላልያ ~ Pelaliah: ‘በሕያው የተዳኘ፣ የሕያው ፍርድ’ ማለት ነው። የአማሲ ልጅ፥
“የቤቱንም ሥራ የሠሩ
ወንድሞቻቸው ስምንት
መቶ ሀያ
ሁለት የመልክያ
ልጅ የፋስኮር
ልጅ የዘካርያስ
ልጅ የአማሲ
ልጅ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ
ዓዳያ”
(ነህ 11:12)
ፈላጥያ ~ Pelatiah: ‘አምላክ የፈታው፥
በሕያው ነጻ የወጣ፣ ሕያው አምላክ ያዳነው’ ማለት ነው።
1. የዘሩባቤል ልጅ፣ የሐናንያ ልጅ፥ “የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች።” (1 ዜና 3:21)
2. የስምዖንም ልጆች አለቃ፥ የይሽዒ ልጅ፥ “የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥410
ነዓርያ፥
ረፋያ፥ ዑዝኤል
ነበሩ።”
(1 ዜና 4:42)
3. ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተመ፥ “ኤዚር፥ ሜሴዜቤል፥
ሳዶቅ፥ ያዱአ፥
ፈላጥያ”
(ነህ 10:22)
4. የበናያስ ልጅ፥ “ትንቢትም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ ...” (ሕዝ 11:5-12)
ፈልጢ ~ Palti: ፍልጥ፣
መፍለጥ፣ መክፈል፣
መለየት፣ ነጻ ማውጣት... ማለት ነው። የራፋ ልጅ፥ ብንያማዊ ሰላይ፥ “ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ ከዛብሎን ነገድ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል” (ዘኁ 13:9)
ፈልጢኤል ~ Paltiel: ‘ያምላክ ነጻነት፣ ምሕረት’
ማለት ነው።
መሬት በማከፋፈል የተባበረ፥ ከይሳኮር ልጆች ነገድ አለቃ፥ “ከይሳኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ
የሖዛ ልጅ
ፈልጢኤል፥”
(ዘኊ 34:26)
ፈስጋ ~ Pisgah: ‘ጫፍ፣ ክፍል’ ማለት
ነው። በኢያሪኮ
አንጻር፥ በዮርዳኖስ
በስተምሥራቅ፥ የሞዓባውያን መስክ
አዋሳኝ የሆነ፥
የቦታ ስም፥
“ከባሞትም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞዓብ በረሀ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ” (ዘኊ
21:20፥ 23:14፥3:27፥ 34:1)
ፈሪ ~ Fear: ፈሪ፣ ፈራ፣ ፍራት፣ ጭንቀት፣ ጥንቃቄ፣ ማስተዋል... ማለት ነው።
Fear-‘ፈሪ’
ከሚለው የመጣ
ቃል ነው።
ከጠቢቡ ሰሎሞን ምክር፥ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ...”
(ምሳ 1፡7) ፣ (ኢዮ 28:28 ፣ መዝ 19:9)
ፈሪሳውያን ~ Pharisees: ፈራሽ፣ አፍራሽ፣ ተገንጣይ፣ መለየትን የሚፈልግ... ማለት ነው።
“በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።” (ማቴ 9:14፥ 23:15፥ ሉቃ 11:39፥ 18:12)
ፈርባር ~
Parbar:
‘ገጠር’
ማለት ነው። “በምዕራብ በኩል በፈርባር መንገድ ላይ አራት፥ በፈርባርም አጠገብ ሁለት ነበሩ” (1 ዜና 26:18)
ፈርዖን ~ Pharaoh: ‘የተበተነ፣ የተከፋፈለ፣ የተስፋፋ’
ማለት ነው።
(‘ግፈኛ፥ ግፍ
ሠሪ ማለት
ነው።’ ተብሎም ይተረጎማል።
ኪወክ /
አ) የግብፅ ነገሥታት
የክብር መጠሪያ፥ “የፈርዖንም አለቆች አዩአት፥ በፈርዖንም ፊት አመሰገኑአት ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት
ወሰዱአት።”
(ዘፍ 12:15)
ፈርዶናጥስ ~ Fortunatus:
‘ዕድለኛ’ ማለት ነው። በኤፌሶን
ጳውሎስን የጎበኘ፥
ቆሮንቶሳዊ ደቀ ምዝሙር፥ “በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም
መምጣት ደስ
ይለኛል፥ እናንተ
ስለሌላችሁ የጎደለኝን
ፈጽመዋልና፤ መንፈሴንና
መንፈሳችሁን አሳርፈዋልና።” (1 ቆሮ 16:17)
ፈታያ ~
Pethahiah:
ፍተ ያሕ፣ አምላክ የፈታው፣ ጌታ የማረው፣ ፍትኅ ያገኘ፣ ይቅር የተባለ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍታህ፣ ያፌት፣ ይፍታሕ፣ ይፍታሕኤል፣ ዮፍታሔ]
‘ፍተ’ እና ‘ያሕ’ (ያሕዌ ፣ ሕያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1. በዳዊት ዘመን፣ ከአልዓዛርና ከኢታምር ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች
የነበረ፥ (1 ዜና 24:16)
2. በዕዝራ ዘመን፣ ከግዞት ከተመለሱ፣ ከካህናቱ ወገን ልጆች እንግዶችን ሴቶች ካገቡ፥
(ዕዝ 10:23)
3. የሜሴዜቤል ልጅ፥ (ነህ 11:24)
ፈዓራይ ~ Paarai:
‘በጌታ የተፈታ’ ማለት ነው። ከዳዊት ኃያላን አንዱ፥ “ቀርሜሎሳዊው
ሐጽሮ፥ ዓርባዊው ፈዓራይ፥” (2 ሳሙ 23:35)
ፈክራት ~
Pochereth:
ፉከራት፣ ፉከራ፣ የቃላት ጦርነት... ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ የፈክራት
ልጆች ይገኙበታል፥
“የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል
ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች” (ዕዝ 2:57፤ ነህ 7:59)
ፈዳያ ~ Pedaiah: የጌታ
ካሳ፣ የአምላክ
ፍዳ፣ የሕያው
መከራ... ማለት ነው።
1.የንጉሥ ኢዮአቄም
የእናቱ አባት፥ “ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም
ዘቢዳ ትባል
ነበር እርስዋም
የሩማ ሰው
የፈዳያ ልጅ
ነበረች።”
(2 ነገ 23:36)
2. የዘሩባቤል ልጅ፥ “ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።የፈዳያ ልጆች
ዘሩባቤልና ሰሜኢ
ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች
ሜሱላም፥ ሐናንያ፥
እኅታቸውም ሰሎሚት።” (1 ዜና 3:17-19)
3. የምናሴ ርስት እኩሌታ ገዥ፥ የኢዩኤል አባት፥ “በኤፍሬም ልጆች ላይ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል” (1 ዜና 27:20)
4. የፋሮስ ልጅ፥ “የኡዛይ ልጅ ፋላል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ። ከእርሱም በኋላ የፋሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።” (ነህ 3:25)
5. ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ
ሲያነብ በቀኙ ከቆሙት፥ “ጸሐፊውም ዕዝራ ስለዚህ ነገር በተሠራ በእንጨት መረባርብ ላይ ቆሞ ነበር። በአጠገቡ መቲትያ፥ ሽማዕ፥ ዓናያ፥ ኦርዮ፥ ኬልቅያስ፥ መዕሤያ በቀኙ በኩል፥ ፈዳያ፥ ሚሳኤል፥ መልክያ፥ ሐሱም፥
ሐሽበዳና፥ ዘካርያስ፥
ሜሱላም በግራው
በኩል ቆመው
ነበር።”
(ነህ 8:4)
6. ከግዞት ከተመለሱት፥ “የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ
ሰሉ።”
(ነህ 11:7)
7. ሌዋውያኑ፥ “በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥
ከሌዋውያኑም ፈዳያን
ሾምሁ ከእነርሱም
ጋር የመታንያ
ልጅ የዘኩር
ልጅ ሐናን
ነበረ እነርሱም
የታመኑ ሆነው
ተገኙ፥ ሥራቸውም
ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል
ነበረ።”
(ነህ 13:13)
ፉራ ~ Phurah: ፈራ፣ አፈራ፣ ፍሬያማ ሆነ ፣ ፍሬ ሰጠ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍራታ፣ ኤፍሬም፣ ኤፍሮን፣ ኦፊር፣ ፍሬ]
‘ፍሬ’
ከሚለው ቃል
የመጣ ስም ነው። የጌዴዎን ሎሌ፥
(ይሁ 7:10
፣ 11)
ፉትኤል ~ Putiel: የአሮን
ልጅ፣ የአልዓላዛር
ሚስት፥ “የአሮንም ልጅ
አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፥ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው” (ዘጸ 6:25)
ፉኖን ~
Punon:
‘ጨለማ’
ማለት ነው። “ከፉኖንም ተጕዘው በኦቦት ሰፈሩ” (ዘኊ 33:42፣43)
ፉጥ ~ Pul: ‘ጌታ’
ማለት ነው።
“በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥
ከእነርሱም የዳኑትን
ዝናዬን ወዳልሰሙ፥
ክብሬንም ወዳላዩ
ወደ አሕዛብ
ወደ ተርሴስ ወደ
ፉጥ ወደ
ሉድ ወደ
ሞሳሕ ወደ
ቶቤል ...” (ኢሳ 66:19)
ፊሀሒሮት ~ Pi-hahiroth: ‘አፍ’
ማለት ነው።
እስራኤላውያን ከግብፅ
ምድር ከወጡ
በኋላ እንዲያርፋ፥
እግዚአብሔር ለሙሴ
ከነገረው ቦታዎች
አንዱ፥ “ተመልሰው በሚግዶልና
በባሕር መካከል፥
በበኣልዛፎንም ፊት
ለፊት ባለው
በፊሀሒሮት ፊት
እንዲሰፍሩ ለእስራኤል
ልጆች ተናገር
...” (ዘጸ 14:2፣9)
ፊሊጦስ ~ Philetus:
‘ቅን፣ ተግባቢ፣ ተወዳጅ’ ማለት
ነው። “ከእነርሱም ሄሜኔዎስና
ፊሊጦስ ናቸው” (2 ጢሞ 2:17፣18)
ፊልሞና ~ Philemon: ‘ተወዳጅ’
ማለት ነው።
የቆለስያ ነዋሪ
የሆነ፥ “የክርስቶስ ኢየሱስ እስር ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ
ለፊልሞና፥”
(ፊል 1:1)
ፊልክስ ~ Felix: ‘ባለጠጋ’ ማለት ነው።
“እርሱም ስለ ጽድቅና
ራስን ስለ
መግዛት ስለሚመጣውም
ኵነኔ ሲነጋገር
ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ፥
አሁንስ ሂድ፥
በተመቸኝም ጊዜ
ልኬ አስጠራሃለሁ
ብሎ መለሰለት።” (ሐዋ
24:25)
ፊልድልፍያ ~ Philadelphia:’ወንድማዊ
ፍቅር’
ማለት ነው። ነቢዩ ዮሐንስ፥ ወደ ቤተክርስቲያን አለቆች እንዲልክ ከታዘዘው አንዱ፥ “በፊልድልፍያም ወዳለው
ወደ ቤተ
ክርስቲያን መልአክ
እንዲህ ብለህ
ጻፍ። ...” (ራእ 3:7-12)
ፊልጶስ ~
Philip, Philippi: ‘ፈረሰኛ፣ የፈረስ ወዳጅ’ ማለት ነው። “በነገው ኢየሱስ ወደ
ገሊላ ሊወጣ
ወደደ፥ ፊልጶስንም
አገኘና። ተከተለኝ
አለው።”
(ዮሐ 1:44)
ፊልጶስ / Philippi: ቂሣርያ አገር ሰው፥
ሐዋርያው፥ “ኢየሱስም ወደ
ፊልጶስ ቂሣርያ
አገር በደረሰ
ጊዜ ደቀ
መዛሙርቱን። ሰዎች
የሰውን ልጅ
ማን እንደ
ሆነ ይሉታል? ብሎ
ጠየቀ።”
(ማቴ 16:13)
ፊሎጎስ ~
Phygellus:
‘ስደተኛ፣ መጻተኛ’ ማለት ነው። ጳውሎስ በሮም ለሁለተኛ ጊዜ
ሲታሰር ትተውት
ከሸሹ አንዱ፥
“በእስያ ያሉቱ ሁሉ
ከእኔ ፈቀቅ
እንዳሉ ታውቃለህ፥ ከእነርሱም ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ናቸው።” (2 ጢሞ 1:15)
ፊስጦስ ~ Festus: ‘ፌስታ፣ ደስታ’ ማለት
ነው። አይሁድ
ጳውሎስን በከሰሱት
ጊዜ፥ አገረ
ገዥውን፣ ፊልክስ
የተካ፥ “ሁለት ዓመትም
ከሞላ በኋላ
ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ
ታሰረ ተወው” (ሐዋ 24:27)
ፊሶን ~ Pison: ‘ፍስ፣ ፈሳሽ፣ የሚፈስ’
ማለት ነው።
“የአንደኛው ወንዝ ስም
ፊሶን ነው። እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው” (ዘፍ 2:11)
ፊቶም ~ Pithom:
‘ፍጹም፣ የፍትሕ ከተማ’ ማለት
ነው። “በብርቱ ሥራም
ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን
ጽኑ ከተሞች
አድርገው ሠሩ።” (ዘጸ 1:11)
ፊንሐስ ~Phinehas: ፈንሐስ፣ አፈ ንሐስ፣ ንግግር አዋቂ፣ መልካም ቃል... ማለት ነው።
‘አፍ’ እና ‘ንሐስ’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
1. የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ፥ ፊንሐስ፥ (ዘጸ 6:25)
2. የዔሊ ልጅ፥ ፊንሐስ፥ (1 ሳሙ 1:3፣ 2:34፣ 4:4፣ 11፣ 17፣ 19፣ 14:3) ፣ “... ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።” (ዕዝ 8:33)
ፊኖን ~ Pinon: ‘ጨለማ’
ማለት ነው።
የኤዶም መስፍን፥
“አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥” (ዘፍ 36:41፤ 1 ዜና 1:52)
ፊኮል ~Phichol: አፈ ቃል፣ አፈ ጉባኤ፣ ንግግር፣ መልእክት፣ ትእዛዝ... ማለት ነው።
‘አፍ’ እና ‘ቃል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
በአብርሃም ዘመን በአቢሜሌክ መንግሥት ውስጥ የነበረ፣ የሠራዊቱ አለቃ፥ (ዘፍ 21:22፣ 32)
ፊደል ~ Alphabet: አልፋ ቤት፣ የመጀመሪያ ክፍል፣ አንደኛ ደረጃ... ማለት ነው።
Alphabet-
‘አልፋ’ እና ‘ቤት’
ከሚሉ ቃላት
የተመሠረተ ስም
ነው። “እግዚአብሔርም፦ ታላቅ ሰሌዳ ወስደህ፤ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ በሰው
ፊደል ጻፍበት” (ኢሳ 8፡1)
ፋሌቅ ~
Peleg, Phalec: ‘ክፍል፣ ክፍፍል’ ማለት ነው። የዔቦር ልጅ፥ የዮቅጣን ወንድም፥
“ለዔቦርም ሁለት ልጆች
ተወለዱለት የአንደኛው
ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ
ተከፍላለችና የወንድሙም
ስም ዮቅጣን
ነው።”
(ዘፍ 10:25፥ 11:16)
ፋሌቅ / Phalec: በጌታ
የዘር ሐረግ
የተጠቀሰ፥ የአቤር
ልጅ፥ (ሉቃ 3:35) “የናኮር ልጅ፥ የሴሮህ ልጅ፥ የራጋው ልጅ፥ የፋሌቅ ልጅ፥ የአቤር ልጅ፥ የሳላ ልጅ፥”
ፋረዳታ ~
Poratha:
ፍሬያት ማለት ነው። ከሐማ ልጆች አንዱ፥ “ፈርሰኔስ፥
ደልፎን፥ ፋስጋ፥
ፋረዳታ፥”
(አስ 9:8)
ፋራ ~ Parah: ‘ጊደር’
ማለት ነው።
ከብንያም ከተሞች
አንዱ፥ “ዓዊም፥ ፋራ፥
ኤፍራታ፥ ክፊርዓሞናይ፥
ዖፍኒ፥ ጋባ
አሥራ ሁለት
...” (ኢያ 18:23)
ፋራን ~ Paran: ‘ውበት’
ማለት ነው።
የሲና ምድረ በዳ ክፍል የሆነ
ቦታ፥ “በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት።” (ዘፍ
21:21)
ፋሬስ~
Peresh, Perez, Pharez, Upharsin: ፈረስ፣ ፈረሰኛ... ማለት ነው። የሚክር ልጅ፥ የኡላምና ራቄም አባት፥ “የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ
ወለደች፥ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ ልጆቹም ኡላም፥
ራቄም ነበሩ” (1 ዜና 7:16)
ፋሬስ / Perez: ፍርስ፣ ፈራሽ፣ ክፍተት... ማለት ነው። “እርሱ ከፋሬስ ልጆች ነበረ ለመጀመሪያው ወር በጭፍራ አለቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር” (1 ዜና 27:3፤ ነህ 11:4፣6)
ፋሬስ / Pharez:
ማፍረስ፣ መጣስ፣ ክፍተት... ማለት ነው። ከይሁዳ መንትያ
ልጆች ትልቁ፥
“እንዲህም ሆነ እጁን
በመለሰ ጊዜ
እነሆ ወንድሙ
ወጣ እርስዋም፦ ለምን
ጥስህ ወጣህ?
አለች ስሙንም
ፋሬስ ብላ
ጠራችው።”
(ዘፍ 38:29)
ፋሬስ /
Upharsin: መፍረስ፣ መከፈል... ማለት ነው። በንጉሡ ብልጣሶር
ቤተመንግሥት ግድግዳ
ላይ የተጻፈ
ምሥጢራዊ ቃል፥
“የተጻፈውም ጽሕፈት። ማኔ
ቴቄል ፋሬስ ይላል።” (ዳን
5:25)
ፋርስ ~
Persia:
‘ምርጥ፣ ንጹህ፣ የፀዳ’ ማለት ነው። “ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ” (2 ዜና 36:20)
ፋርፋ ~
Pharpar:
ፍራፍሬ ማለት ነው። ከደማስቆ ወንዞች ሁለተኛው። “የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ
ውስጥ መታጠብና
መንጻት አይቻለኝም
ኖሮአልን?
...”
(2 ነገ 5:12)
ፋቁሔ ~ Pekah: ‘ፈች፣ ግልጥ፣ ነጻ አውጭ’ ማለት
ነው። የሮሜልዩ
ልጅ፥ “የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፥ ...የገለዓድ ሰዎች ነበሩ ገደለውም፥
በእርሱም ፋንታ
ነገሠ”
(2 ነገ 15:25)
ፋቁድ ~ Pekod: ‘ክቡር፣ ግርማዊ፣ ገዥ’ ማለት ነው። “በምራታይም ምድር
ላይ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ውጣ
ግደላቸው ፈጽመህም
አጥፋቸው፥ ይላል
እግዚአብሔር፥ እንዳዘዝሁህም
ሁሉ አድርግ።” (ኤር
50:21፤ ሕዝ 23:23)
ፋቂስያስ ~ Pekahiah: ‘ሕያው ያዳነው፣ ዓይኑን ያበራለት፣ ጌታ የፈታው’ ማለት
ነው። የምናሔ
ልጅ፥ በአባቱ ፋንታ በእስራኤል ላይ የነገሠ፥ “ምናሔም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ ልጁም ፋቂስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።” (2 ነገ 15:22)
ፋኑኤል ~
Phanuel:
ፋና ኤል፣ የአምላክ ፊት፣ የጌታ መልክ፣ ብርሃናማ፣ አንጸባራቂ... ማለት ነው።
‘ፋና’ እና ‘ኤል’
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። የነቢይቱ
የሐና አባት፥
(ሉቃ 2:36)
ፋዑ ~ Pau: ‘እንጉርጉሮ፣ ለቅሶ፣
እሮሮ’
ማለት ነው።
ሃዳድ የነገሠባት
ከተማ፥ “በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ
ሚስቱም የሜዛሃብ
ልጅ የመጥሬድ
ልጅ መሄጣብኤል
...” (1 ዜና 1:50)
ፋዶን ~ Padon: ‘አዳኝ፣ ነጻ
አውጭ’
ማለት ነው።
ከምርኮ ከተመለሱ፥
የነታኒም ወገን፥ “የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥” (ዕዝ 2:45፤ ነህ7:47)
ፋግኤል ~
Pagiel:
‘አምላክ ያደለው’ ማለት ነው። የኤክራን ልጅ፥ “ከአሴር የኤክራን ልጅ ፋግኤል፥” (ዘኊ 1:13፥ 2:27፥7:72፣ 77፣ 10:26)
ፌልያ ~ Pelaiah: ‘የሕያው ዕውቅ’
ማለት ነው።
1. በይሁዳ የዘር ሐረግ፥ የኤልዮዔና ልጅ፥ “የኤልዮዔናይም
ልጆች ሆዳይዋ፥
ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥
ዓቁብ፥ ዮሐናን፥
ደላያ፥ ዓናኒ
ሰባት ነበሩ።” (1 ዜና 3:24)
2.
ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ሲያነብ፥ ይረዱት ከነበሩ ሌዋውያን አንዱ፥ “ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥
ሰራብያ፥ ያሚን፥
ዓቁብ፥ ሳባታይ፥
ሆዲያ፥ መዕሤያ፥
ቆሊጣስ፥ ዓዛርያስ፥
ዮዛባት፥ ሐናን፥
ፌልያ፥ ሌዋውያኑም
ሕጉን ያስተውሉ
ዘንድ ሕዝቡን
ያስተምሩ ነበር፤
ሕዝቡም በየስፍራቸው
ቆመው ነበር።” (ነህ 8:7) የቃል ኪዳን ደብዳቤውን ሲያትምም ከነህምያ ጋር ነበረ፥ (ነህ
10:10)
ፌስቲ’ቫል ~
Festival: (ፌስቲ’ቫል-
ይህ ቃል
በአማረኛው መጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ
አይገኝም።)
ፌስቲ ቫል፣
ፌሽታ በዓል፣
ግብዣ፣ ድግስ፣
ዓመት ባል፣
የደስታ ቀን፣ ዓውደ ዓመት... ማለት ነው። (ዘሌ 23)
Festival: ‘ፌስታ’ እና ‘በዓል’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
. ለዘወትር መሥዋዕት፥ “...
ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር …” (ዘኁ 28:1-8) ፥ “በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው በቀን በቀን
ዘወትር ሁለት የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ” (ዘጸ 29:38-42) ፥ (ዘሌ 6:8-23) “አንተም መብራቱን ሁልጊዜ ያበሩት ዘንድ …” (ዘጸ 27:20)
. ሰንበት፥ “ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንበታል ምንም ሥራ አትሠሩም በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።” (ዘሌ 23:1-3) ፣ (ዘጸ 19:3-30) ፣ “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው
ዘንድ አስብ” (ዘጸ
20:8-11) ፣ “... እኔ የምቀድሳችሁ
እግዚአብሔር እንደ
ሆንሁ ታውቁ
ዘንድ በእኔና
በእናንተ ዘንድ
ለልጅ ልጃችሁ
ምልክት ነውና
ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ” (ዘጸ 31:12፣13) ፣ (ዘኁ 28:11-15)
. የዕረፍት ሰንበት፥ “በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ።” (ዘጸ 23: 14:110፣ 11) ፣ “በሰባተኛው ዓመት
ግን ለምድሪቱ
የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር
ሰንበት”
(ዘሌ 25:2-7)፣ (ሌዌ 2335-35፣ 25፣ 816-16፣ 27:16-25)
. ድግስ፥ “… ብላ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ” (ዘዳ 27:7) ፣ “...
ሊበሉና ሊጠጡ ዕድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም …” (ነህ 8:9-12)
. በእግዚአብሔር ፊት ይታይ፥ “… ወንድ ሁሉ በእስራኤል አምላክ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት በዓመት ሦስት ጊዜ ይታይ።” (ዘጸ 34:23፣ 24)
. ስለ ኃጢአት ስርየት፥ “ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው
ሁሉ ያስተስርይ
...” (ዘሌ 16:
34፣ 23:26-32) ፣
“ከዚህም ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ …” (ዘኁ 29:7- 11)
. የመቅደስ መታደስ፥ “በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤” (ዮሐ 10:22)
፥ “አይሁድ እነዚህን
ሁለት ቀኖች
እንደ ጽሕፈቱና
እንደ ጊዜው
በየዓመቱ ይጠብቁ
ዘንድ፥ ... በአይሁድ ዘንድ
እንዳይሻሩ፥ ... ሥርዓት አድርገው
ተቀበሉ።”
(አስ 9:24-32)
ፌርዛውያን ~ Perizzites:
“ነዋሪ፣ መንደርተኛ’
ማለት ነው።
ከነናውያን፥ “ፌርዛውያንንም ራፋይምንም
አሞራውያንንም ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም ኢያቡሳውያንንም” (ዘፍ 15:20፤ ዘጸ 3:8፣ 17፥23:23፥ 33:2፥ 34:11)
ፌቤን ~ Phebe: ‘የፀዳች፣ የነጻች’ ማለት
ነው። ጳውሎስ
ለሮም ሰዎች
በጻፈው ደብዳቤ የጠቀሳት፥ በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነች፥ “በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ” (ሮሜ 16:1፣2)
ፌጎር ~ Peor: ‘ጉድጓድ፣ ክፍተት’
ማለት ነው። ባላቅ፥ በለዓም እስራኤልን እንዲረግምለት፥ የወሰደው የተራራ ጫፍ፥ “ባላቅም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፌጎር ላይ በለዓምን ወሰደው።” (ዘኊ 23:28)
ፍሌጎን ~ Philologus: ‘የቃላት ወዳጅ፣ አንባቢ’ ማለት ነው። በሮም የነበረ ክርስቲያን፥ ጳውሎስ በሰላምታ
ደብዳቤው የጠቀሰው፥
“ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ከእነርሱ ጋር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ” (ሮሜ
16:15)
ፍልስጥኤም ~
Philistines: ፍልሰታም፣ ፍልሰታ፣ ፍልሰት፣ የፈለሰ፣ ፈላሻ፣ ከርስቱ ከግዛቱ የተፈናቀለ ማለት ነው።
‘ፍልሰታም’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ሲሆን ምንጩ ደግሞ ‘ፈለሰ’ የሚለው ግስ ነው።
. እስራኤልን ከግብፅ
ምድር እንዳወጣ ሁሉ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር ያወጣ እግዚአብሔር ነው፥ “የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ
ልጆች አይደላችሁምን? ይላል
እግዚአብሔር፦ እስራኤልን
ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?”
(አሞ 9:7)
. በጌራራ ንጉሥ በአቢሜሌክ ሥር ይተዳደር የነበር አገር፥ “በቤርሳቤህም ቃል
ኪዳንን አደረጉ።
አቢሜሌክና የሙሽራው
ወዳጅ አኮዘት
የሠራዊቱ አለቃ
ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።” (ዘፍ 21:32፣ 34፣ 26:1፣
8)
ፍሩዳ ~
Perida, Peruda:
‘ቅንጣት ፍሬ፣ ነጠላ’ ማለት ነው። ከምርኮ ከተመለሱ፥
የፍሩዳ ልጆች
ይገኙበታል፥ “የሰሎሞን ባሪያዎች
ልጆች የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥
የፍሩዳ ልጆች፥” (ነህ 7:57)
ፍሩዳ / Peruda:
ከግዞት ከተመለሱ፥ የፍሩዳ ልጆች ይገኙበታል፥ “የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥”
(ዕዝ 2:55)
ፍሬ ~
Fruit:
ፍሩት፣ ፍሬያት፣ ምርት፣ ልጅ፣ ውጤት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ኤፍራታ፣ ኤፍሬም፣ ኤፍሮን፣ ኦፊር፣ ፉራ]
Fruit- ‘ፍሬያት’ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
[ከሕያው ፍጥረት
ሁሉ የሚገኝ
/ መቅቃ]
. የማርያም ልጅ፥ ጌታ ኢየሱስ በእናቱ ማኅፀን እያለ የተጠራበት፥ “በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም
ፍሬ የተባረከ
ነው:”
(ሉቃ 1፡42)
. የጽድቅ ሥራ፥ “ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል ፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤” (ገላ
5:22 ፣ 23)
. ውጤት፥ “የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤” (ኤፌ 5:9)
በጎ ነገር፥ “ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።” (ያዕቆ
3:17፣ 18)
ፍናና ~ Peninnah: ‘ዕንቁ፣ አበባ’ ማለት ነው። የሕልቃና
ሚስት፥ “ሁለትም ሚስቶች ነበሩት የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፥
ለሐና ግን
ልጅ አልነበራትም።” (1 ሳሙ 1:2)
ፍንቄ ~ Phenice: ‘ቀይ’
ማለት ነው።
የቀርጤስ ወደብ፥
“ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ
ከዚያ እንዲነሡ
መከሩ።”
(ሐዋ 27:12)
ፍዳሱ ~ Pedahzur: ‘የእድሳት ዓለት’
ማለት ነው።
የምናሴ አገረ
ገዥ፥ የገማሊኤል
አባት፥ “ከዛብሎን የኬሎን
ልጅ ኤልያብ፥
ከዮሴፍ ልጆች
ከኤፍሬም የዓሚሁድ
ልጅ ኤሊሳማ፥
ከምናሴ የፍዳሱ ልጅ ገማልኤል፥”
(ዘኊ 1:10፥ 2:20)
ፍጥሞ ~
Patmos: ‘ምድራዊ፣ ጊዜያዊ፣ ሟች፣ ፈራሽ፣ጠፊ’ ማለት ነው። ዮሐንስ ራእዩን ያየበት
፥ የደሴት
ስም፥ “እኔ ወንድማችሁ
የሆንሁ ከእናንተም
ጋር አብሬ
መከራውንና መንግሥቱን
የኢየሱስ ክርስቶስንም
ትዕግሥት የምካፈል
ዮሐንስ ስለ
እግዚአብሔር ቃልና
ስለ ኢየሱስ
ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ” (ራእ
1:9)
ፎሖ ~ Puah: ‘ግሩም፣ ውብ’ ማለት ነው።
1. ከአቤሜሌክ ቀጥሎ በእስራኤል ላይ ፈራጅ የነበረ፥ የይሳኮር ነገድ፥ የቶላ
አባት፥ “ከአቤሜሌክም በኋላ
ከይሳኮር ነገድ
የሆነ የዱዲ
ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ተቀምጦ
ነበር።”
(መሣ 10:1)
2. ፉዋ፥ (1
ዜና 7:1)
3. ፉሐ፥ (ዘጸ 1:15)
No comments:
Post a Comment