ፐራሲም ~ Perazim: ክፍተትማለት ነው። የተራራ ስም፥ እግዚአብሔርም ሥራውን ማለት እንግዳ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፥ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ ፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፥ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል። (ኢሳ 28:21)

ፑቲዮሉስ ~ Puteoli: ሐዋርያው ጳውሎስ ካረፈባቸው ቦታዎች፥ ከዚያም እየተዛወርን ወደ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ መጣን። (ሐዋ 28:1314)

ፑፕልዮስ ~ Publius: የጋራማለት ነው። መርከባቸው በተሰባበረች ጊዘ፥ ጳውሎስንና ደቀመዛሙቱን ተቀብሎ ያስተናገደ የመላጥያ ሰው፥ በዚያም ስፍራ አጠገብ ፑፕልዮስ የሚሉት የደሴት አለቃ መሬት ነበረ፥ እርሱም እንግድነት ተቀብሎን ሦስት ቀን በፍቅር አሳደረን።” (ሐዋ 28:7)

ፒላቲ ~ Peulthai: ዋጋዬ ድርሻዬ ማለት ነው። የኦብዲ ኤዶም ስምንተኛ ልጅ፥ ስድስተኛው ዓሚኤል፥ ሰባተኛው ይሳኮር፥ ስምንተኛው ፒላቲ (1 ዜና 26:5)

ፒቶን ~ Pithon: በረታች፣ አንደበተ ርቱዕ ማለት ነው። የሚካም ልጆች ፒቶን ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ (1 ዜና 8:35 9:41)

ፕሮፊሞና ~ Tryphena: አስደሳችማለት ነው። በሮም የነበሩ እኅትማማች ክርስቲያኖች፥ ጳውሎስ በሰላምታ ከጠቀሳቸው አንዷ፥ በጌታ ሆነው ለሚደክሙ ፕሮፊሞና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ እጅግ ለደከመች ለተወደደች ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ” (ሮሜ 16:1)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ