ሸሃሪያ ~ Shehariah: ሕያው ህ፣ ያምላክ ብርሃን ማለት ነው። ሸሃሪያ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች። (1 ዜና 8:27)

ሸሚዳ ~ Shemida: ጠቢብማለት ነው የገለዓድ ልጅ፥ ከሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ... (ዘኊ 26:32 ኢያ 17:2)

ሸማዓ ~ Shemaah: ሸማህ፣ ሰማህ፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተረዳ... ማለት ነው። ሰማከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳማያ፣ ሰሜኢ፣ ሸማያ] በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት ከመጡ፥ ጊብዓዊው የይዝኤል አባት፥ ሸማዓ (1 ዜና 12:3)

ሸማያ ~ Shemaiah: ሸማ ያሕ፣ ሰማ አምላክ፣ እግዚአብሔር አዳመጠ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳማያ፣ ሰሜኢ፣ ሸማዓ]

ሰማ እና ያሕ’(ያሕዌ፣ ሕያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት ተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. ከባቢሎን ግዞት ከተመለሱ፣ የሴኬንያ ልጅ፥ ሸማያ (1 ዜና 3:23) (ነህ 3:28 29)

2. የሮቤል ነገድ፥ የኢዮኤል ልጆች ልጁ ሸማያ (1 ዜና 5:4)

3. ከሜራሪ ወገን የሆነ የአሱብ ልጅ፥ ሸማያ (1 ዜና 9:14 ነህ 11:15)

4. የኤሊጻፋ ልጅ ሸማያ (1 ዜና 15:8 11)

5. ከሌዋውያን ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ (1 ዜና 24:6)

6. ዖቤድኤዶ የበኩር ልጅ፥ (1 ዜና 26:4 6 7)

7. የኤዶታም ልጅ ሸማያ (2 ዜና 29:14)

8. ዕዝራ ከላከባቸው የሌዋዊያን አለቆች አንዱ፥ (ዕዝ 8:16)

9. ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን ከተመለሱ፥ ከካሪም ልጆችም መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ ይሒኤል፥ ዖዝያ።” (ዕዝ 10:21)

10. ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን ከተመለሱ፥ ሸማያ ስምዖን፥ ብንያም፥ መሉክ፥ ሰማራያ።” (ዕዝ 10:3231)

11. በነቢዩ ነህምያ ዘመን የነበረ የመሔጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ነቢይ፥ (ነህ 6:10)

12. ቃል ኪዳን አትመው ከላኩት ካህናት አንዱ፥ (ነህ 10:8) (12:6) (ነህ 10:8 12:6 18)

13. ከይሁዳም አለቆች አንዱ፥ (ነህ 12:34)

14. ካህን የነበረ፥ (ነህ 12:42)

15. በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበረ ሐሰተኛ ነቢይ፥ (ኤር 29:24-32)

16. ኢዮሳፍጥ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ከመሳፍንቱ ጋር ከላካቸው፥ (2 ዜና 17:8)

17. በንጉሡ በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ ሌዋዊው፥ (2 ዜና 31:15)

18. የሌዋውያን አለቃ፥ (2 ዜና 35:9)

19. በኢሳያስ ዘመን የነበረ የነቢዩ የኦርዮ አባት፥ (ኤር 36:12)

20. የድላያ አባት፥ (ኤር 26:20)

. ነቢዩ ሳማያ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ” (1 ነገ 12:22-24)

. ከስምዖን ወገን የሆነ ሰሜኢ (1 ዜና 4:27)

ሸማይ ~ Shammai: ሽማይ፣ ስማይ፣ ስም፣ ዝና፣ እውቅና፣ ታሪክ... ማለት ነው።

ስምከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የኦናም ልጅ፥ ሸማይ (1 ዜና 2:28 32)

2. የሬቄም ልጅ፥ (1 ዜና 2:44 45)

3. የዕዝራ ልጅ፣ የዬቴር ልጅ፥ (1 ዜና 4:17)

ሸምሁት ~ Shamhuth: ሺህ ሞት፣ የተጎዳ፣ የፈረሰ... ማለት ነው። በዳዊት የጦር ሠራዊት፥ የአስተኛው ወር ተራ፥ አምስተኛ አለቃ፥ ለአምስተኛው ወር አምስተኛው አለቃ ይዝራዊው ሸምሁት ነበረ በእርሱም ክፍል ሀያ ...” (1 ዜና 27:8)

ሸምሽራይ ~ Shamsherai: ፀሓያዊማለትነው። የብንያንያም፥ ሸምሽራይ፥ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ... ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች።” (1 ዜና 8:26 27)

ሸራይ ~ Sharai: ሼር፣ ሻሪ፣ ቸር፣ ይቅር ባይ፣ ርኁሩኅ... ማለት ነው።

በነቢዩ ዕዝራ ዘመን ከባቢሎን ከተመለሱት፥ ሸራይ (ዕዝ 10:40)

ሸባሪም ~ Shebarim: ስባሪ፥ ክፍተት... ማለት ነው። የቦታ ስም፥ የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያሕል ሰዎችን መቱ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው በቍልቍለቱም መቱአቸው ...” (ኢያ 7:5)

ሸቤር ~ Sheber: ስብር፣ የተሰበረ... ማለት ነው። የካሌብ ልጅ፥ ከማዕካ የወለደው፥ የካሌብም ቁባት ማዕካ ሸቤርንና ቲርሐናን ወለደች።” (1 ዜና 2:48)

ሸንጐ ~ Sanhedrin: ባኤ ችሎት ማለት ነው። በጌታ ዘመን የነበረ የአይሁድ ጉባኤ፥ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጐውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤ (ማቴ 26:59 ማር 15:1)

ሸዓፍ ~ Shaaph: ሰፍ፣ ሰፋ፣ ሰፊ፣ በዛ፣ ተራባ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሳፍ]

ሰፊከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የያሕዳይ ልጅ፥ ሸዓፍ (1 ዜና 2:47)

2. የመድማና አባት፥ ሸዓፍ (1 ዜና 2:49)

ሸዕለቢን ~ Shaalbim: የቀማኛ መንደርማለት ነው። ለነገደ ዳን የተሰጠ ከተማ፥ ሸዕለቢን ኤሎን፥ ይት ... (ኢያ 19:42 መሣ 1:351 ነገ 4:9)

ሹኒ ~ Shuni: እድለኛማለት ነው። የጋድ ልጅ፥ የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ ኤስቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥ አርኤሊ (ዘፍ 46:16 ዘኊ 26:15)

ሺሖር ~ Sihor: ጥቁር፣ አስቸጋሪ ማለት ነው። የአዳይ ወንዝ፥ በግብፅ የሚጠራበት አንዱ ስም፥ አሁንስ ሺሖር ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የኤፍራጥስንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር ...” (ኤር 2:18)

ሺሌም ~ Shallum: ሸሉም፣ ሰላም፣ ስምምነት፣ እርቅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሴሌም]

ሰለመከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:- 1. የንፍታሌም ልጅ፥ ሺሌም (1 ዜና 7:13)

2. የቲቁዋ ልጅ፥ ሺሌም (2 ነገ 22:14 2 ዜና 34:23)

ሺሌም ~ Shillem: ልምማለት ነው። የናፍታሌም ልጅ፥ የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም (ዘፍ 46:24)

ሺልሒ ~ Shilhi: ታጣቂ አንጋች፣ ነፍጠኛማለት ነው። የዓዙባ ልጅ፥ የኢዮሣፍጥ እናት፥ ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ... ነበረ በኢየሩሳሌምም ሀያ አምስት ዓመት ነገሠ። እናቱም ዓዙባ የተባለች ሺልሒ ልጅ ነበረች።” (1 ነገ 22:42 2 ዜና 20:31)

ሺምሪ ~ Shimri: ሺህ መሪ፣ የሺህ አለቃ፣ የሺህ ሰዎች አዛዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሜንር፣ ሽምሪ፣ ሺምሮን፣ ሺምሮን ሚሮን፣ ሾሜር]

ሺህእና መሪከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

1. የሸማያ ልጅ፥ ሺምሪ (1 ዜና 4:37)

2. የኤሊጸፋ ልጅ፥ (2 ዜና 29:13)

. የይድኤል አባት፥ ሽምሪ ልጅ ይድኤል፥ ወንድሙም ይድኤል፥ ወንድሙም ቲዳዊው ዮሐ፥” (1 ዜና 11:45)

ሺምራት~ Shimrath: ሺህ መሪያት፣ መሪ፣ አለቃ፣ ጠባቂ... ማለት ነው። የሰሜኢ ልጅ፥ ...ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት የሰሜኢ ልጆች” (1 ዜና 8:21)

ሺምሮን ~ Shimron: ሺህ መራን፣ የሺህ አለቃ፣ የሕዝብ ጠባቂ፣ የብዙዎች አስተዳዳሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሜንር፣ ሺምሪ፣ ሽምሪ፣ ሺምሮን ሚሮን፣ ሾሜር]

ሺህእና መሪከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው። በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።

1. የያቆብ ልጅ፣ የይሳኮር ልጅ፥ (ዘፍ 46:13)

2. የቦታ ስም፥ “... ወደ ሺምሮንም ንጉሥ...” (ኢያ 11:1 19:15) የአሶር ንጉሥ፥ ሺምሮን ሚሮን ንጉሥ (ኢያ 12:20)

ሺሞን ~ Shimon: ሽማን፣ ስማን፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ተገነዘበ... ማለት ነው። ሰማከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው። [ተዛማጅ ስም- ስምዖን፣ ሲሞን] ሺሞን ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ።...” (1 ዜና 4:20).

ሺሻቅ ~ ShishaK: ኢዮርብዓም ከሰሎሞን ሸሽቶ የሔደበት፥ የግብፅ ንጉሥ፥ ሰሎሞንም ኢዮርብዓምን ሊገድለው ወደደ ... ወደ ግብፅም ንጉሥ ወደ ሺሻቅ መጣ፥ ሰሎሞንም እስኪሞት ድረስ በግብፅ ተቀመጠ” (1 ነገ 11:40)

ሺቦሌት ~ Shibboleth: ት፣ ሰብል፣ እሸት... ማለት ነው። እነርሱ። አሁን ሺቦሌት በል አሉት እርሱም አጥርቶ መናገር አልቻለምና። ሲቦሌት አለ ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገሪያ አረዱት ... ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ (መሣ 12:6)

ሺኦን ~ Shihon: ባድማ፣ ፍርስራሽ፣ ውዳቂማለት ነው። የይሳኮር ከተማ፥ ወደ ከስሎት፥ ... ወደ ሺኦን ወደ አናሐራት፥” (ኢያ 19:19)

ሺዛ ~ Shiza: እጹብ፣ ውብ፣ ግርማዊማለት ነው። የዓድና አባት፥ ሮቤላዊው፥

የሮቤላዊው ሺዛ ልጅ ዓዲና፥ እርሱ የሮቤላውያን አለቃ ነበረ፥ (1 ዜና 11:42)

ሺፊ ~ Shiphi: ሰፊ የተትረፈረፈ... ማለት ነው። የዚዛ አባት፥ ሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ (1 ዜና 4:37)

ሺፍጣን ~ Shiphtan: ሰፈነ፣ ስፍነት፣ መሳፍንት፣ ዳኛነት ማለት ነው።

ሰፈነከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

ከኤፍሬም ልጆች ነገድ፥ የቀሙኤል አባት፥ (ዘኁ 34:24)

ሻሊሻ ~ Shalisha: ሸሊሼ፣ ላሴ፣ ሥላሴ፣ ለሰ፣ ሦስትነት... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስም- በኣልሻሊሻ]

ሠለሰከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።

ሳዖል በአባቱ ትዕዛዝ የጠፉትን አህዮች ለመፈለግ ካአለፈባቸው ቦታዎች አንዱ “...ሻሊሻ አለፉ...” (1 ሳሙ 9:4)

ሻሚድ ~ Shamed: ጠባቂማለት ነው። የኤልፍዓል ልጅ፥ ...ዔቤር፥ ሚሻም፥ ኦኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ (1 ዜና 8:12)

ሻማ ~ Shama: ሽማ፣ ስማ፣ ሰማ፣ አዳመጠ፣ ዛዝ ተቀበለ... ማለት ነው። ሰማ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።[ሻማ፣ መሻማት ተብሎም ይተረጎማል።] የዳዊት ወታደር፣ የኮታ ልጅ፥ ሻማ (1 ዜና 11:44)

ሻሻቅ ~ Shashak: ምኞት ማለት ነው። የበርያ ልጅ፥ ብንያማዊ፥

አሒዮ፥ ሻሻቅ ይሬምት፥” (1 ዜና 8:1425)

ሻዕሊም ~ Shalim: ሻሊም፣ ሰላም፣ ሰላመ፣ ሰላማዊ... ማለት ነው።

ከሚለው ግስ የመጣ የቦታ ስም ነው።

ሳዖል በአባቱ ዛዝ የጠፉትን አህዮች ለመፈለግ ካለፈባቸው ቦታዎች አንዱ፥

“...ሻዕሊም ምድርም አለፉ ...” (1 ሳሙ 9:4)

ሻክያ ~ Shachia: ማስታወቂያ ማለት ነው። ሸሐራይም ከሚስቱ ከሖዴሽ የወለደው፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። (1 ዜና 8:10)

ሻጌ ~ Shage: ሳተ መሳት፣ መሳሳትማለት ነው። ከዳዊት ዘበኞች አንዱ፥ የዮናታን አባት፥ ... የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፥ የሃራራዊው ሻጌ ልጅ ዮናታን፥” (1 ዜና 11:34)

ሻፊር ~ Saphir: ሸፈር፣ ሰፈረ፣ ሰፈር፣ መንደር ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሻፍር]

ሰፈረከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

በነቢዩ ሚክያስ የተጠቀሰ የቦታ ስም፥ (ሚክ 1:11)

ሻፋጥ ~ Shaphat: ሽፍት፣ ስፍነት፣ መስፈን፣ መፍረድ መዳኘት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳፋጥ፣ ሰፈጥ፣ ሻፍጥ]

የሸማያም ልጅ፥ ሻፋጥ (1 ዜና 3:22)

ሻፍር ~ Shapher: ... [Saphir/ ሻፊር - የሚለውን ይመልከቱ።]

‘Shapher’- ሰፈር፣ ሰፈራ፣ ስፍራት ማለት ነው።

እስራኤላውያን በምድረ ባዕዳ የሰፈሩበት የቦታ ስም፥ ከቀሄላታም ተጕዘው ሻፍር ተራራ ሰፈሩ” (ዘኁ 33:23)

ሻፍጥ ~ Shaphat: [ሻፋጥ / Shaphat- የሚለውን ይመልከቱ] [ተዛማጅ ስሞች- ሳፋጥ፣ ሰፈጥ፣ ሻፋጥ]

በዳዊት ከብት እረኞች ዘንድ ሹም የነበረ፥ የዓድላይ ልጅ ሻፍጥ (1 ዜና 27:29)

ሼሻክም ~ Sheshach: ሸክም፣ ጭነት... ማለት ነው። የአገር ስም፥ የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥ የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው ሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።” (ኤር 25:26 51:41)

ሼታር ~ Shethar: ሰጠረ፣ ደበቀ፣ ሰወረ... ማለት ነው። ኮከብ ማለት ነው፥ ተብሎ ይተረጎማል። በመንግሥቱም ቀዳሚዎች ሆነው የሚቀመጡ የንጉሡ ባለምዋሎች ሰባቱ የፋርስና የሜዶን መሳፍንት አርቄስዮስ፥ ሼታር ... (አስ 1:14)

ሼናጻር ~ Shenazar: ዝነኛ መሪ ማለት ነው። የሰላትያል ልጅ፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።” (1 ዜና 3:18)

ሼን ~ Shen: ስን፣ ጥርስ መንጋጋ... ማለት ነው። የቦታ ስም፥ ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና ሼን መካከል አኖረው ስሙንም እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።” (1 ሳሙ 7:12)

ሽሙኤል ~ Shemuel: ስማ ኤል፣ አምላክ ሰማ፣ ጌታ አዳመጠ፣ ልመናን ተቀበለ ሹመ ኤል፣ አምላክ የሾመው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰላሚኤል ሳሙኤል]

ሰማ፥ ሹመ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።

በዳዊት ዘመን የአባታቸው የቶላቤት አለቆች፣ የቶላ ልጅ፥ (1 ዜና 7:2) (ዘኁ 34:20)

ሽማዕ ~ Shema: ሽማ፣ ስማ፣ ሰማ፣ አዳመጠ... ማለት ነው።

ሰማከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ አራት ሰዎች እና አንድ ቦታ አሉ።

1. የኬብሮን ልጅ፥ ሽማዕ (1 ዜና 2:43)

2. የኢዮኤል ልጅ፥ ሽማዕ (1 ዜና 5:8)

3. የብንያም ወገን፥ ሽማዕ (1 ዜና 8:13)

4. ነቢዩ ዕዝራ የሕግ መጽሐፋን ሲያነብ በአጠገቡ ከቆሙት፥ ሽማዕ (ነህ

8:4)

5. የቦታ ስም፥ (ኢያ 15:26)

ሽምሪ ~ Shimri: ሺህ መሪ፣ የሺህ አለቃ፣ የሺህ ሰዎች አዛዥ... ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- ሳሜንር፣ ሺምሪ፣ ሺምሮን ሚሮን፣ ሾሜር] ሺህእና መሪከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

የይድኤል አባት፥ ከዳዊት በረኞች አንዱ፥ ሽምሪ (1 ዜና 11:45)

የሸማያ ልጅ፥ ሺምሪ (1 ዜና 4:37)

የኤሊጸፋን ልጅ፥ ሺምሪ (2 ዜና 29:13)

ሽዓራይም ~ Shaaraim: ሁለት በር ማለት ነው። ለይሁዳ ነገድ የተሰጠ ከተማ፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ ሽዓራይም ዓዲታይም፥ ...” (ኢያ 15:36)

ሽዓርያ ~ Sheariah: ሽረ ያሕ፣ ሕያው የማረው... ማለት ነው። ኤሴል ስድስት ልጆች ነበሩት ስማቸውም ይህ ነበረ ዓዝሪቃም፥ ...” (1 ዜና 8:38 9:41)

ሽክሮን ~ Shicron: ስካርማለት ነው። ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። (ኢያ 15:11)

ሽፋን ~ Shophan: ሽፋን፣ አጥር፣ ሸፈነ፣ መሸፈን፣ መጋረድ፣ መከለል፣ መደበቅ... ማለት ነው።

ሸፈነከሚለው ግስ የተገኘ የቦታ ስም ነው።

ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ፥ የጋድ ልጆች ከሰፈሩባቸው የተመሸጉ ከተሞች፥ ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥” (ዘኁ 32:35)

ሾሃም ~ Shoham: መከልከልማለት ነው። የሜራሪ ልጅ፥ የሜራሪ ልጆች ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም ዘኩር፥ ዔብሪ (1 ዜና 24:27)

ሾሜር ~ Shomer: ሺህ መሪ፣ ሺህ መሪ፣ የሺህ አለቃ፣ ጠባቂ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሳሜንር፣ ሺምሪ፣ ሽምሪ፣ ሺምሮን ሚሮን]

ሺህእና መሪከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-

. የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአስን ከገደሉት ባሪያዎቹ አንዱ፥ የዮዛባት አባት፥ ሾሜር (2 ነገ 12:21)

. ሔቤርም ያፍሌጥን፥ ሳሜንር ኮታምን፥ እኅታቸውንም ሶላን ወለደ።” (1 ዜና 7:32)

ሾፋክ ~ Shophach: ሰፋህ፣ ተስፋፋማለት ነው። የአድርአዛር ሠራዊት አለቃ፥ ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ... ሶርያውያን አስመጡ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ። (1 ዜና 19:1618)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

    ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ