ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሠምላ ~ Samlah:
‘መጎናጸፊያ’
ማለት ነው።
ከኤዶም ነገሥታት
አንዱ፥ ከሃዳድ ቀጥሎ የነገሠ፥ “ሃዳድም ሞተ፥ በስፍራውም የመሥሬቃው ሠምላ ነገሠ።” (ዘፍ 36:36፣37፤1
ዜና 1:47፣48)
ሠራያ ~
Seraiah:
ሠራያሕ፣ የአምላክ ሠራተኛ፣ የጌታ አገልጋይ፣ የአምላክ ሠራዊት... ማለት ነው።
‘ሥራ’ እና ‘ያሕ’(ያሕዌ )
ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች:-
1.
የዮብ አባት፥ የቄኔዝ ልጅ፥ (1 ዜና 4:13፣ 14)
2.
የዮሺብያ ልጅ፥
(1 ዜና 4:35)
3.
የንጉሥ ዳዊት ጸሐፊ የነበረ፥ (2 ሳሙ 8:17)
4.
በሴዴቅያስ ዘመን የነበረ ካህን፥ (2
ነገ 25:18, 23)
5.
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2:2)
6.
በነህምያ ዘመን፣ የቃል ኪዳኑ ደብዳቤ ከፈረሙ ካህናት፥ (ነህ
10:2)
7.
የጸሐፊው የዕዝራ አባት፥ “...በአርጤክስስ መንግሥት ዕዝራ የሠራያ ልጅ፥”
(ዕዝ 7:1)
8.
የቤተ መቅደሱ ሐላፊ፥ የኪልቅያስ ልጅ፥ (ነህ 11:11)
9.
በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቃ፣ ካህን፥ (ነህ 12:1፣ 12)
10.
የኔርያ ልጅ፥ (ኤር 51:59)
ሠርሰኪም ~ Sarsechim: ‘እጩ መኮንን’ ማለት
ነው። ናቡከደነፆር
ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ የነበረ የጦር መሪ፥ “የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል
ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥
ሠርሰኪም፥ ራፌስ
...” (ኤር 39:3)
ሠጉብ ~
Segub: ‘ሰገባ፣ መሸሸጊያ፣ የተመሸገ፣ የተገነባ’ ማለት ነው።
1.
ኢያሪኮን ያደሰው፣
የአኪኤል ትንሹ
ልጅ፥ “በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪኤል ኢያሪኮን ሠራ ... በታናሹ ልጁም በሠጉብ በሮችዋን አቆመ።”
(1 ነገ 16:34)
2.
የኤስሮ ልጅ፥ “ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት፤ ወደ ገለዓድ
አባት ወደ
ማኪር ልጅ
ገባ ሠጉብንም
ወለደችለት። ሠጉብም
ኢያዕርን ወለደ” (1 ዜና 2:21፣28)
ሣሌፍ ~ Sheleph: ሰልፍ ማለት
ነው። የዮቅጣን
ሁለተኛ ልጅ፥
“ሣሌፍን፥ ሐስረሞትን፥
ያራሕን፥ ሀዶራምን፥” (ዘፍ
10:26፤ 1
ዜና 1:20)
ሣሪድ ~ Sarid: ‘አልሞት ባይ፣
ጠንካራ’
ማለት ነው።
በዛብሎን ግዛት
ውስጥ የነበረ
ጉልህ ሥፍራ፥
“ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን
ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ” (ኢያ 19:10፣12)
ሣራ ~ Sarah: ዘር፣ ዘሬ፣ ወገኔ... ማለት
ነው። ‘ልዕልት፣ የብዙኃን እመቤት
ማለት ነው’ ተብሎም ይተረጎማል። የአብርሃም ሚስት፥ የቀድሞ ስሟ ሦራ ነበር፥
“እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ
ሣራ ይሆናል
እንጂ።”
(ዘፍ 17:15)
ሣካር ~ Sacar: ‘ዋጋ፣ ደሞዝ፣ ምርት’ ማለት ነው።
1.
“እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት በኵሩ ሸማያ ... አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥” (1 ዜና 26:4)
2.
የአምና አባት፥
“የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥” (1 ዜና
11:35)
ሣጥን ~
Coffer, Coffin: ከፈን፣ መጠቅለያ፣ መሸፈኛ፣ መቅበሪያ ሳጥን... ማለት ነው።
Coffin
-‘ከፈነ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
ሣጥን / Coffer:
ቀብር፣ ሽፋን... ማለት ነው። የንዋየ ቅድሳት ማስቀመጫ፥“የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ
በሰረገላው ላይ
አኑሩት፤ ስለ በደልም
መሥዋዕት ያቀረባችሁትን
የወርቁን ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት ...” (1 ሳሙ 6፡ 8፣ 11፣ 15)
ሣጥን / Coffin: ዮሴፍ በግብፅ በሞተ ጊዜ በድኑ የተቀመጠበት እቃ፥ “ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ በሽቱም አሹት፥ በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።”
(ዘፍ 50፡26)
ሤራሕ ~
Serah:
ሥራህ፣ ሥራ፣ ድርጊት፣ ክንውን... ማለት ነው። የአሴር ልጅ፥ ሤራሕ ፥ (ዘፍ 46:17፣ 1 ዜና 7:30) ፣ (ዘኁ 26:46)
ሤባ ~
Shebah:
ሰብዓ፣ ሳባ፣ ሰብ፣ ሰው፣ የሰው ልጅ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- ሰበንያ፣ ሰብታ፣ ሰንበት፣ ሳባ፣ ሳባታይ፣ ሳባጥ፣ ሳቤህ፣ ሳቤዔ፣ ጸባዖት]
አንድ ሰውና አንድ ቦታ በዚህ ስም ይታወቃሉ።
. ለስምዖን ልጆች ነገድ እጣ የወጣ የቦታ ስም፥ (ኢያ 19:2)
. የንጉሥ ሰሎሞን ጸሓፊ አባት፥ “ጸሐፊዎቹም የሴባ ልጆች ኤልያፍና ...”
(1 ነገ 4:3)
ሤኩ ~
Sechu:
‘ማማ’ ማለት ነው። በገለዓድና ራማ መካከል የሚገኝ ቦታ፥ “የሳኦልም ቍጣ
ነደደ፥ እርሱም
ደግሞ ወደ
አርማቴም መጣ፥
በሤኩም ወዳለው
ወደ ታላቁ
የውኃ ጕድጓድ
ደረሰ ...” (1 ሳሙ 19:22)
ሥትሪ ~
Zithri:
‘አምላክ ይጠብቅ’ ማለት ነው። የዑዝኤል ልጅ፥ “የዑዝኤል ልጆች ሚሳኤል፥ ኤልዳፋን፥ ሥትሪ ናቸው።” (ዘጸ 6:22)
ሥዖሪም ~ Seorim: ‘ገብስ’
ማለት ነው።
ከሃያ አራቱ
የካህናት ምድብ፥
የአራተኛው ተራ
አለቃ፥ “አራተኛው ለሥዖሪም፥ አምስተኛው …”
(1 ዜና 24:9)
ሦራ ~
Sarai:
‘የኔ እመቤት’ ማለት ነው። የአብርሃም ሚስት፣ የሣራ የቀድሞ ስም፥
“ታራም ልጁን አብራምንና
የልጅ ልጁን
የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም
የአብራምን ሚስት
ምራቱን ሦራን
ወሰደ ከእርሱም
ጋር ወደ
… ካራንም መጡ፥
ከዚያም ተቀመጡ።” (ዘፍ
11:31፥ 17:15)
ሦጋል ~
Shual:
የአሴር ወገን፥ የጾፋ ልጅ፥ “ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ፥ ይትራን፥ ብኤራ ነበሩ።” (1 ዜና 7:36)
No comments:
Post a Comment